2017 ዲሴምበር 31, እሑድ

አስተርአያ ዘገብርኤል

https://youtu.be/zvVnxNe_iaI
*© አስተርአያ ዘገብርኤል*

/ዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ ፩/

አስተርአያ ገብርኤል ግብተ/፪/
ወእንዘ ትፈትል/፬/ ወርቀ ወሜላተ

አዝ…

ከአዳም ልጅ መካከል ከእነዳዊት ዘር
መርጦ ተወለደ ከድንግል በክብር
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
አዳምን ሊያድነው ስላየው ተራቁቶ

አዝ…

ሐር እየፈተለች ቤተ መቅደስ ሆና
ገብርኤል ነገራት ሰማያዊ ዜና
ትፀንሲ እያለ በድንቅ ሰላምታ
በትኅትና ሆኖ ሲታጠቅ ሲፈታ

አዝ…

ከክቡር ዙፋኑ ከመንበሩ ወርዶ
አዳነን ከፍዳ ከማርያም ተወልዶ
የነገሥታት ንጉሥ ቤዛ ኩሉ ዓለም
ሥጋዋን ለበሰ መድኃኔ ዓለም

አዝ…

ንጉሥ መወለዱን ሰብአ ሰገል ሰምተው
አምኃ አቀረቡ ከሩቅ ምሥራቅ መጥተው
የዳዊት ትንቢቱ ተፈጸመለት
የሳባ ነገሥታት ወርቅ አመጡለት/፪/

አዝ…saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 30, ቅዳሜ

አበሰራት ገብርኤል አበሰራት

#አበሰርት #ገብርአኤል
 #አበሰራት #ብርሀነ #መለኮት #ባችያድራል #አላት (፪)

ሐር ከወርቅጋር....  አበሰርት ገብርኤል
አስማምታ ስትፈትል። ።።።።።።
ሰላም ላንች ይሁን። ።።።።።።።
አላት ገብርኤል። ።።።።።፡
ይህ እንዴት  ያለ። ።።።።።
ሰላምታ  ነው አለች። ።።።።።
ንግግሩን ሰምታ። ።።።።።
ድግል ተደነቀች።  ።።።።።
         አዝ
በፍጹም ትህትና። ።።።።።።
በጽድቅ አደበት። ።።።
የሰማዩ ስራ። ።።።።
ሰላምታ ሰጣት።  ።።።
ከጌታ መላኩን።   ።።።።
ሲነግራት ብስራት።   ።።።
ድግልም በመፍራት።  ።።።
ሀሳብም ያዛት።  ።።።።

     አዝ
እንደ ቃልህ ይሁን።  ።።።
ብላ ተቀበለች።  ።።።።
እኔ ለእግዚአብሔር። ።።።።
ባርያው ነኝ እያለች።   ።።።
ይህው ክርስቶስን።።።።።
ለኛ ሰታናለች።።።።።።
ጽዮንን እዳናይ።።።።
ጌታን ወልዳዋለች።።።
      አዝ
ጌታችን ሲወለድ  አበሰራሲ ገብርኤል
በቤተልሔም።።።።።
ለረኞች ተነግሮ።።።።።
አዩት በግርግም።።።።
ሰውና መላእክት።።።።።
ባድነት ዘመሩ።።።።።
ስብኃት ለእግዚአብሔር።።።።
ይድርሰው እያሉ። 
አበሰራት ገብርኤል (፪)

እልልልልልልልልልልልልልልልልልsaramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 29, ዓርብ

የገና ኮሌክሽን መዝሙሮች

በኤፍራታ ምድር
/////////////////
በኤፍራታ ምድር (በቤተልሔም(2×)
ጌታ ተወለደ (ከድንግልኮከብ ማርያም(2×))
ብርሃናዊው  (ከሰማይ ዝቅ አለ(2×)
ፍጥረትም ዘመረ (ሀሌሉያ እያለ(2×)

              መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች
              ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምስራች
              በመላዕክቱ ግርማ ምድር ስታበራ
              የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ
አዝ.....
ድንገት በሰማይ ሰራዊት ተገልጠው
በአንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋቤተልሔም
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሰላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሰው

አዝ.....
                ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሳለሙት
                 ከእናቱ ጋር ሆኖ በግርግም አገኙት
                የመላዕክትን ዜና እረኞች አወሩ
                በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ

አዝ......
ለህዝብ ሁሉ ሚሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈልጉት
እርሱ ነው ለሰዎች የድህነት ምልክት

በኤፍራታ ምድር (በቤተልሔም(2×)
ጌታ ተወለደ (ከድንግል ማርያም(2×))
ብርሃናዊው ኮከብ (ከሰማይ ዝቅ አለ(2×)
ፍጥረትም ዘመረ (ሀሌሉያ እያለ(2×)

//////////////////////////

በጎል በጎል ሰባ ሰገል (2)
     በጎል በጎል ሰባ ሰገል (2)
  በጎል ሰባ ሰገል ሰገዱ ሎቱ (2)

ፀሐይ ፀሐይ ፀሐይ ሰርቀ (2)
ፀሐይ ሰርቀ ክርስቶስ ተጠምቀ (2)
.
አ.ዝ....
አንቺ ዮርዳኖስ ምንኛ ታደልሽ (2)
የእግዚአብሔር መንፍስ ከላይ ውርዶብሽ(2)
የአለም መዳኚት ተጠመቀብሽ (2)

አ....ዝ....

ድንግል ማርያም የሰጠሽው ፍሬ (2)
ህዝቦቹን ለማዳን ተጠመቀ ዛሬ

አ..ዝ....

ድንግል ማርያም ንጽይት ቅድስት
የጌታዬ እናት ምስጋና ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ አንቺን መርጦሻል

አ....ዝ..

እልል እልል ደስ ይበለን (2)
ወንድ ልጅ ተዎልዶ ናጻ አወጣን (2)
ዮሐንስ አጥምቆ ድል አገኛን (2)

እልልልልል
///////////////////////

ተወለደ ጌታ ተወለደልጅ
ተወለደ አምላክ ተወለደ

አ..ዝ...

አንዲት ብላቴና የአሥራ አምስት ዓመት
ጌታን ወለደችው በመላዕክት አዋጅ
በፍጹም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ

አ..ዝ
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋህዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ

አ..ዝ...

ፍጹም ድንግልና ክብር የተሞላች
እንደምን አምላክን በማህጸን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ

አ...ዝ..

አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
ከምድር ተፈልጎ እንደ አንቺ አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንጹህ ስለሆነች
ለአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች

አ..ዝ..

ፍጹም ድንግልና ክብር የተሞላች
እንደምን አምላክን በማህጸን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ

///////////////////////

" በኤፍራታ
በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ------ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ------ሆ
በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ------ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ------ሆ
 
   /////////////////////////

#ተወልደናሆ እም ድንግል/4/
ሲነገር ነበረ በነብያት አፍ    ተወልደናሆ እም ድንግል
ባንዱ በእግዚአብሔር ባንዱ በመንፈስ    ,,,       ,,,
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሀይ እንዲወጣ       ,,,       ,,,
የናፈቅነው ንጉስ ስጋ ለብሶ መጣ            ,,,       ,,,

          #ተወልደናሆ እም ድንግል/2/
አብርሀም ያንን ቀን ለማየት ናፈቀ  ተወልደናሆ እም ድንግል
ዳዊት በኤፍራታ ልደቱን አወቀ               ,,,      ,,,
ኢሣያስ ከድንግል ሲወለድ አየና             ,,,      ,,,
ትንቢት ተናገረ ምልክት አለና                 ,,,      ,,,

        #ተወልደናሆ እም ድንግል/2/
ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል ሲባል   ተወልደናሆ እም ድንግል
ሠማይ ሆነችለት እናቱ ድንግል              ,,,      ,,,
በህዝቡ መካከል ሆኖ የሚያበራ           ,,,      ,,,
በርሱ ፈራረሠ የጨለማውድንግል ስራ             ,,,      ,,,

      #ተወልደናሆ እም ድንግል/2/
ከእረኞች ጋራ ቤተልሔም ግቡ  ተወልደናሆ እም
ከነገስታቱ ጋር አምሀን አቅርቡ             ,,,       ,,,
እንስገድ ለህፃኑ ይገባዋልና                ,,,        ,,,
አለቅነት ስልጣን በጫንቃው ነውና      ,,,        ,,,
         ======✞,,
//////////////////////////
ተወለደ ጌታ ተወለደ ጌታ
ይሁን ደስታ በበረት ተወለደ ጌታ
የአለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ
ሰላም ሰፈነልን በምድር ደስታ
      አ..ዝ..
            እስይ የምስራች ለእግዚአብሔር ክብር
           ለስው በጎ ፍቃድ ሰላም በምድር
           ነብያት የፃፉት ትንቢቱ ሊፍፅም
           ከድንግል ተወልዶ አገኘነው ግርግም
          የሰማይ መላእክት አመሰገኑት
          ስለተወለደ የአለም መዳሀኒት
ላዳም የገባውን ቃል ኪዳን አፀና
ቃሉን አከበረ አብ ልጁን ላከና
ሰማይ እና ምድር ባንድነት ተስማሙ
ሰውና መላእክት ለጌታ ዘመሩ
   
            ሰባት ስግድ መጡ በኮከብ ተመርተው
           ለጌታ ሊስግዱ ከምስራቅ ተነስተው
          ህፃኑን ከናቱ ከማርይም ጋር አዩት
           ወድቀው ስገዱለት ለአለም መድሀኒት

ለክብሩ ያመጡትን ሳጥኑን ከፈቱ
ላምላክ አቀረብ ወርቁን ለመንግስቱ
እጣኑን ለክህነት ከርቤን ሰለሞቱ

          መንጋቸውን ነጥቀው ሲጠብቁ ለሉት
        በዳዊት ከተማ ተውልዳል መኑኒት
        በብርሀን ሰሙና የመላኩን ብስራት
       መጡ ለምስጋና ልደቱን ለማየት
 
ምስጋና ይገባል ለጌታ ልደት
ታርቀዋልና ሰውና መላእክት
ቅዱሳን መላእክት ዘመሩለት
አድረው ቀደሱ ካህናት ለሌት
እኛም ቆመናል በቅዳሴው
የጌታን ልደት ልንዘክረው

      በኢትየጵያ ምድር ይሁን ስባት
      እልልልልልልልልልል እንበል ለጌታ ልደት
      እንበል የጌታ ፍቃድ ይሁን
     ደግም ላመቱ ሰላም ይድርሰን

እልልልልልልልልልልል

///////////////////////

ወስብኃት ለእግዚአብሔር

ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር
አሜን ይቆየን...saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 28, ሐሙስ

የምዕራፍ ሁለት/የ20ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁልኝ??
......ሰላማችሁ ይብዛ እያልኩ እነሆ የምዕራፍ ሁለትን የ20ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ መረሀ ግብር እንዲህ ይቀርባል....
።።።።።።።።።።።።።።።።

✍✅ጥ ተራ ቁ.↪1⃣ ሰብአ ሰገል ማለት ምን ማለት ነው??? ሰባ ሰገል ወርቅ፤ ዕጣን፤ ከርቤ፤ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመገበራቸው ምስጢር ምንድነው??  አንደምታውን በዝርዝር አስረዳ???

//መልስ//👉ሰብአ ሰገል ማለት፦ በአጭሩ የጥበብ ሰዋች ማለት ነው።
👉ሰብአ ሰገል ወርቅ ዕጣን ከርቤ መገበራቸው #ወርቅ ለንግስናው አንድም በፊት ይህንን የምንገብርላቸው ቀድሞ ፍጡራን ኋላም ሀላፊያን ናቸው አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርክ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ አንድም ወርቅ ፅሩይ ነው አንተም ፅሩይ ባህሪ ነህ ሲሉ #ዕጣን ለዘላለማዊ ክህነቱ አንድም በፊት ይህንን  ቀድሞ ፍጡራን ኋላም ሀላፊያን ናቸው አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርክ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ አንድም ዕጣን ምዑዝ ነው የምንገብርላቸውአንተም ምዑዘ ባህሪ ነህ ሲሉ #ከርቤ ለሞቱ አንድም ምንም እንኳን ቀድሞም ያልተፈጠርክ ኋላም የማታልፍ ብትሆን በለበስከው ሥጋ  ሲሉ አንድም ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል የተለያየውን አንድ ያደርጋል አንተም ከመላእክት የተለየውን አዳምን አንድ ትሞታለህታደርጋለህ ሲሉ ገብረውለታል

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪2⃣ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የጌታችን ልደት የተረዳባቸው ምክንያቶች  ምን ምን ናቸው???

//መልስ//👉ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የጌታን ልደት ያወቀበት ወይም የተረዳበት ምልክቶች  (1ኛ)ፍርሀተ ኖሎት ወይም የእረኞች ፍርሀት (2ኛ)የመላእክትን ምስጋና በሰማ ጊዜ (3ኛ)የሰብአ ሰገል መምጣትና መገበር (4ኛ)ደማቅ ኮከብ መታየት (5ኛ)የጌትነቱ ወይም የአምላክነቱ ብርሃን ናቸው።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪3⃣ አስቀድሞ ካህን የነበረ ነገር ግን የሰማዕታትን መከራ በማየት የእምነታቸውን ጥናትና ጌታችንም እነርሱን ሲፈውሳቸው ተመልእክቶ ልቦናውን ወደቀናች እምነት መልሶ በጌታችን ያመነ በኋላም እንደ ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሰማዕትነትን የተቀበለ ቅዱስ አባት ማን ይባላል??

//መልስ//👉ሉኪያኖስ ይባላል።


✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪4⃣ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መላአኩ ስንት  ጊዜ አበሰራት ??

//መልስ//👉3 ጊዜ አበሰራት
👉ውሃ ስትቀዳ፤ ወደ ቤተ መቅደስ ስትገባ እና ወደ ዮሴፍ ቤት ስትገባ

👉አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ( ሉቃ ፩  ÷፳፮ _፴፰

👉 እግዚአብሔር ከአንችቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ( ማቴ ፩÷፲፰ _፳፭) 1÷18-25)

✍✅ጥ.ተራ.ቁ. ↪5⃣ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሥላሴ አንድነት የሚያስረዱን ምዕራፍና  ቁጥሮች ጥቀስ/ሽ??

//መልስ//👉እግዚአብሔር አለ፤ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር (ዘፍ 1፥26)

👉 አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ( ዘፍ 3፥23)

👉 ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚህ እንደባልቀው (ዘፍ 11፥7)

👉ዮሐንስ 10፥30 እኔና አብ አንድነንይልላል ሌሌችንም ጥቅሶች መትቀስ ይላልቻ።

✍✅ ጥ.ተራ.ቁ.↪6⃣አንደበታችን የድንግልን ስራ ያመሰግናል ያለው ቅዱስ አባት ማን ይባላል???

//መልስ//👉ቅዱስ ኤፍሬም ነው።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪7⃣እግዚአብሔር አምላክህን በፍፁም ልብህ በፍፁም ነፍስህ በፍፁም ኃይልህ ውደድ።
 ይህ ኃይለ ቃል በየትኛው  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል  ይገኛል ?  ምዕራፍና ቁጥሩስ??

//መልስ//👉ዘዳግም (6፥4-6)
👉ማር (12፥30)
👉ሉቃስ(10፥27)

✍✅ ጥ.ተራ.ቁ.↪8⃣ገድል ማለት ምን ማለት ነው ?


//መልስ//👉ገድል ማለት፦ ተጋደለ ከሚል የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ተጋደል፣ ተዋጋ ፣ታገለ፣ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ከዓለም ጋር በሥጋ ከዓለማውያን ነገስታት ጋር.. ከዲያብሎስ ጋር  መዋጋት ወዘ..ተ ማለት ነው ።

✍✅ጥ. ተራ.ቁ.↪9⃣የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማስረጃ ጥቀስ/ሽ???
//መልስ//👉ዮሐንስ (2 ፥3)
ሉቃስ (1፥28--1፥48)
መዝሙር (45፥9)
ኢሳያስ (62 ፣2)

ወ.ዘተ..

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣0⃣ እስራኤላውያን ከግብጽ ሲወጡ  በግብፅ ላይ  የተከሰተውን መቅሰፍትን  ዘርዝሩ ???

መልስ 👉ውሃው ወደ ደም ተለወጠ
👉እንቆራሪቶች
👉ቅማል
👉 የእንስሳት እልቂት
👉 በረዶ
👉 የአንበጣ መንጋ
👉 ጨለማ
👉በቁስል መመታት።
👉የግብፃውያ  የበኩር ልጆች እልቂት ወ.ዘተ የመሳሰሉት።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣1⃣በአዲስ ኪዳን ታቦትና ፅላት በማን ይመሰላል???

//መልስ// 👉 ታቦት፦ እመቤታችን ድንግል ማርያም የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማደርያ ሆናለችና  በታቦት እንመስላታለን።
ፅላት፣ በአምላካችን በመድኃኔታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰላል።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣2⃣ በዕለተ ምጽአት ሰዎች ለፍርድ በሚቆሙ ጊዜ ጻድቃን በምን ፣ ኃጥአን ደግሞ በምን ይመሰላሉ? ምዕራፍና ቁጥሩስ?

//መልስ//👉 ጻድቃን በበግ ኃጥአን በፍየል ይመሰላሉ፡፡ ማቲ(.27÷34)


✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣3⃣ በሥርዓተ ቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ ምስባክ ይሰብካል ለመሆኑ ምስባኩ ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው?

//መልስ//፡- ከመዝሙረ  ዳዊት ነው።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣4⃣አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በጸሎት ብዛት እግራቸው ተቆርጦ ሰባት ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው የጸለዩበት ቦታ የት ነው?

//መልስ//፡- ደብረ አስቦ/ ደብረ ሊባኖስ አካባቢ/

✍✅ጥ.ተራ.ቀ.↪1⃣5⃣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት እና የጸለየችበት ቦታ የት ነው??

//መልስ//፡-በጎለጎታ በጌታ መቃብር ላይ ነው፡፡ / የካቲት 16/

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣6⃣በ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መጽሐፈ ሶስናና ተረፈ ዳንኤል ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል  ጋር ቆጠራሉ?

//መልስ//👉ከትንቢተ ዳንኤል ጋር በአንድ ይቆጠራል።


✍✅ጥ.ተራቁ.↪1⃣7⃣ የሰው ልጅ ዕድሜ 70 ቢበዛ 80 ከዚያ ያለፈ ድካምና መከራ ነው ብሎ የተናገረው ማን ነው??

//መልስ//👉ነቢዩ ዳዊት/የሰውመዝሙረ 89፥9-10)


✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣8⃣ እግዚአብሔር ለአዳም ፣ ለአብርሃም ፣ ለኖህ የገባላቸው ቃል ኪዳን ምን ነበር??

//መልስ//፡- 👉ለአዳም፦ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው፡፡
👉ለአብርሃም፡- የሚባርኩህን እባርካለው ……
👉ለኖህ፦ ከአሁን በኋላ በንፍር ውሃ አላጠፋችሁም፡፡

✍✅ጥ.ተራ.ቁ..↪1⃣9⃣ኢየሱስ ፣ አማኑኤል ፣ ክርስቶስ እና መድኃኔዓለም የስማአቸውን ትርጉም አስረዳ/ጂ/.??

//መልስ//👉፦-

#ኢየሱስ፡- ኢየሱስ ማለት አዳኝ  ማለት ነው፡፡ ይህ ስሙ ቅድመ ዓለም በአብ ኅሊና ታስቦ ይኖር እንደነበር
መልክአ ኢየሱስ ይመሰክራል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መድኃኒትእመቤታችንን ሲያበሥራት “ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ”
ብሏታል፡፡ ሉቃ. 1÷"1፡፡ እመቤታችንና ዮሴፍ ጌታ በስምንት ቀኑ ወደ ቤተ ግዝረት ሲገባ በመልአኩ እንደ ተነገራቸው ኢየሱስ ብለው ጠሩት፡፡ ሉቃ. 2÷21፡፡ ከአምልኮ ጸሎት ፈውስና አገልግሎት የሚከናወነው በዚህ በስሙ ነው፡፡ ይህ ስም የባሕታዊያን የተመስጦ ማዕከል የማኅሌታዊያን የዜማቸው ጣዕም የሰባክያን የአትሮንሳቸው ግርማ ሞገስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከዚህ ስም ውጭ ውበት ደምግባት የላትም፡
 #ክርስቶስ፡- ክርስቶስ ማለት የተቀባ መሲህ ማለት ነው፡፡ አይሁድ የጠበቁት መሲህ ነቢያትና ጻድቃን ሊያዩት የናፈቁትጌታ የነፍስ ነጻ አውጪ ስለሆነ ክርስቶስ አሉት፡፡ ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ከእግዚአብሔር ተወልዷል፡፡ 1ዮሐ. 5÷1፡፡
 #አማኑኤል፡- አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ ኢሳ. 7÷14፡፡የተዋረደውን አዳምን ለማክበር ጌታ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጥቷል፡፡እርሱ አምላካችን የእኛን ሥጋና ደም ስለተካፈለ ከእኛ ጋራ ሆነ“አማኑኤል” ተብሏል፡፡ ማቴ. 1÷23፡፡
#መድኃኔአለም፡- መድኃኔዓለም ማለት የዓለም መድኃኒት ማለት ነው፡፡ አብ ልጁን የላከው የዓለም መድኃኒት እንዲሆንነው፡፡ 1ዮሐ. 4÷14፡፡ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን አዳነ፡፡ እኛም እንደ ሰማርያ ሰዎች መድኃኔዓለም አልነው የሁላችንም መድኃኒት ነውና፡፡ ዮሐ. 4÷42፡፡

 #የሰው_ልጅ፡- የሰውን ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች ለማድረግ ሰው ስለሆነ፡፡ ዮሐ. 6÷63፡፡
 #የእግዚአብሔር_ልጅ፡- የአብ የባሕርይ ልጅ ስለሆነ አባቱን በመልክ ስለሚመስልና በክብር ስለሚተካከል በዚህ ስምተጠራ፡፡ 1ዮሐ. 5÷5፡፡



✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪2⃣0⃣ሚከተሉትን የስም ትርጉሞችን አስረዳ/ጂ/?? ዘሩባቤል ፣ ቤቴል ፣ እና መሪባ፡፡??

//መልስ//መልስ፡- 👉ዘሩባቤል ማለት የባቢሎን ዘር ማለት ነው።
 👉ቤቴል ማለት የእግዚአክርክርብሔር ቤት ማለት ነው።
👉መሪባ ማለት፦ ክርክር፣ጥላቻ ማለት ነው፡፡1ኛ.ዜና 3÷16-19 ፣ ዘፍ.28÷19 ፣ ዘጸ.17÷1-7 እናገኘልለን።

የ20ኛው ዙር ጥቄና መልስ ይህን ይመስላል ከስተቴ ታርሙኝ ዘንድም በትህትና እጠይቃለሁ?..

ወስብሐት  ለእግዚአብሔርsaramareyama.890gmail.com

አፊያ ሁሴን ክፍል 10

#አፊያ #ሁሴን ክፍል 10

ፀሀፊ #ማርያማዊት ገብረ መድህን

አንባቢ #ገብረ ሚካኤል

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፲)

ከአንድ ሳምንት በኋላ ሁመይድ ደወለና አንድ ካፌ ውስጥ ቀጠረኝ፡፡ ሰርፕራይዝም አለሽ በማለት አጣደፈኝ፡፡ ብቻዬን እንድመጣም ለመነኝ፡፡ በቦታው ስደርስ ለብቻዬ እንድመጣ የወተወተኝ ብቻችንን ነፃ ሆነን ለማውራት እንዲመቸንና የያዘው ርዕስም ሌላ ሰው ማወቅ እንደማይገባው ስላመነ መሆኑን ሊያስረዳኝ ብዙ ጣረ፡፡ ሰርፕራይዝ ያለውና ሌላ ሰው እንዳይሰማው የፈለገው ነገር ባለፈው "እንድረዳሽ ፍቀጅልኝ" ብሎኝ የተስማማሁትንና አባቴ ቤተሰቤ ላይ እየፈጠረ ስላለው ችግር ነው፡፡ ፊት ለፊቴ ሆኖ አይን አይኔን እያየ "ከሐጂ ጋር በነገርሽኝ ነገር ላይ ተነጋግረን ነበር፡፡ እናም የቡና ላኪ ድርጅቱን ሃላፊነትና ውክልና ለፋይሰል ሊመልሱለት ተስማምተናል" አለኝ፡፡ በጣም ተደንቄ "እውነት...?!" አልኩት መዳፌን እየዘረጋሁለት፡፡ "really" አለ እኔ ባወጣሁት ዜማና መዳፌን በመሐላ መልክ እየመታ፡፡ በሰበቡም እጄን በእጆቹ ይዞ እያፍተለተለ ቆየ፡፡ "ያው ታውቂያለሽ ከሐጂ ጋር ቢዝነስ ፓርትነር ነን፡፡ ስለሆነም ቤት ያልተለመደ ፀባይ ማሳየታቸውንና የፋይሰልንም ሃላፊነት እንደነጠቁት ገልጬ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየኳቸው፡፡ እርሳቸውም መንስኤው አንቺ እንደሆንሽና ቤተሰቡ በጠቅላላ አድማ እንዳረጋችሁባቸው በከፍተኛ ንዴት ገለፁልኝ፡፡ እኔም ችግሮች በውይይት መፈታት እንዳለባቸውና በተለይ ነገሩን ከቢዝነስ አንፃር ስናየው ፋይሰል ብዙ ልምድ ካካበተበት ሥራው ማንሳት ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለው ቆይቶም ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ነገርኳቸው፡፡ ሥራን በእልህና በስሜት ለማስኬድ መሞከር በዘመናዊ የቢዝነስ አመራር ዘዴ ለውድቀት እንደሚዳርግ አስጠንቅቄ አሳሰብኳቸው፡፡ ያንቺንም ችግር በተመለከተ ከፈቀዱልኝ እኔም የመፍትሔው አካል በመሆን ላግዝ እንደምችል ገለፅኩላቸው፡፡ ከዚያ ትክክል እንደተናገርኩ አረጋግጠውልኝ የፋይሰልን ሥራና ሃላፊነት በቅርቡ እንደሚመልሱለት ቃል ገቡልኝ፡፡ አንቺንም የተሻለ ተግባቦት ካላችሁ እስቲ እባክህ ምከርልኝ ሲሉ አደራ ብለውኛል" አለና ፈገግ አለ፡፡

አባቴ እንዲህ በቀላሉና በፍጥነት ሃሳቡን የማለሳለሱ ነገር ከፍተኛ አግራሞት ፈጠረብኝ፡፡ በእርግጥ ለሁመይድ ትልቅ አክብሮት እንዳለው አጠያያቂ አይደለም፡፡ ቢሆንም ይህን ያህል በፍጥነት ውሳኔውን ይቀይራል ብዬ አልጠበኩም ነበር፡፡ ምናልባት የቡናው ንግድ አሳስቦቶ ይሆን? ስል አሰብኩ፡፡ ፋይሰል በዚህ ሥራ ላይ ብዙ ጊዜ በማሳለፉ ከፍተኛ ልምድ አካብቷል፡፡ ከሥራው ጋር የተያያዙና ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ሰዎችንም ያውቃል፡፡ የአባቴ ውሳኔ እልህ የወለደው እንደሆነ ገብቶት ነው ወይስ ሁመይድ ሲያናግረው ይሉኝታ ይዞት...? ለማንኛውም ለእኔ እጅግ በጣም ያሳሰበኝ የፋይሰል ሁኔታ ነበርና ይህንኑ ዜና ልነግረው ቸኩያለሁ፡፡ ይህን መሰሉን ነገር ፀጥ ብዬ እያብሰለሰልኩ እያለሁ ፊቴ የተቀመጠው ሁመይድ "ኤፊ ይህን ነገር ግን ለማንም አትንገሪ... ሐጂ በራሳቸው ተነሳሽነት ነገሩን እንዳስተካከሉት እንዲሰማቸው እፈልጋለሁ" አለኝ፡፡ ሃሳቡ ቢገባኝም እኔ ደግሞ ለፋይሰል የተፈጠረውን ችግር እንደማስተካክለው ቃሌ ገብቼለት ስለነበር ይህንኑ በስሱም ቢሆን ብነግረው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ስለሆነም ለሁመይድ ችግሩ ሁሉ የተፈጠረው በእኔ ምክንያት መሆኑን እየደጋገምኩና እያስረገጥኩ ከተናገርኩ በኋላ አያይዤም "ለፋይሰል ሁኔታዎችን እኔ ራሴ እንደማስተካክለው ቃል ገብቼለታለሁ" አልኩት፡፡ "so..?" አለኝ መቀመጫው ላይ እየተመቻቸ፡፡ "ስለዚህ የአባቴን ሃሳቡን የመቀየር ዜና ልነግረው እፈልግ ነበር...አንተን ቅር ካላለህ" አልኩት አተኩሬ እያየሁት፡፡ "እሺ..." አለ እየተኩመሸመሸ፡፡ ሁኔታውን ሳየው "ይህ ሰው በእርግጥ ከእኔ ፍቅር ይዞታል እንዴ?" ስል በሃሳቤ ራሴን ጠየኩ፡፡ አያይዞም "እሺ ኤፊ ነገሩ ምስጢር ቢሆን እመርጥ ነበር፣ አንቺ ካልሽ ግን ለሌላ ሰው እንዳያወራና ምንም እንዳላወቀ እንዲያስመስል አስጠንቅቀሽው ንገሪው፡፡ ሐጂ ከአንቺ ጋር ተነጋግሬ ጉዳዩን እንዳነሳሁባቸው ባያውቁ የተሻለ ነው" አለ፡፡ እኔም "ትክክል ነህ ሁመይድ... እኔም እንደዚያ ነው የማስበው" አልኩት፡፡

ሁመይድ ጥቂት በሃሳብ እንደመዋጥ ካረገው በኋላ "ኤፊ..እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?" አለ ፊቱ ላይ የሆነ የሥጋት ገፅታ እየታየበት፡፡ "ምን..?" አልኩት ቀልጠፍ ብዬ፡፡ በፍጥነት ፈገግታው ጠፍቶ መልኩ እንደ መወየብ ስላረገው በውስጤ እየገረመኝ ነበር፡፡ እንዳቀረቀረ "ለፋይሰል ችግሩን እንደምታስተካክዪው ቃል የገባሽለት በምን መንገድ ለማስተካከል አስበሽ ነው? ሌላ የማስተካከያ ዘዴ ነበረሽ?" ሲል ጠየቀኝ፡፡ ጥያቄውን እንደሰማሁ ሳቄ ተናነቀኝ፡፡ ምስኪን ሁመይድ የወንድሜንና የቤተሰቤን ችግር ከማይ የአባቴን ፈቃድ ፈፅሜ እርሱ ያመጣልኝን ባል ለማግባት የምስማማ መስሎታል፡፡ ወይም ደግሞ ሌላ የተለየ መንገድ ኖሮኝ የፎከርኩ መስሎት ነው ሥጋት በውስጡ የገባው፡፡ እንደምንም ያፈነኝን ሳቅ ተቆጣጥሬና ኮስተር ብዬ "የለኝም" አልኩት፡፡ ቀና ብሎ በጥርጣሬ ሲመለከተኝ "በእውነት ሌላ መንገድ አልነበረኝም፣ አንተን ተማምኜ ነው" አልኩት፡፡ ፊቱ ከደመና መሐል በምትወጣ ጸሐይ ምክንያት ብሩህነትን በቅጽበት እንደምትላበስ የምድር ገጽ እዚያው በዚያው ሲፈካ ሳየው ሳላስበው ፈገግ አልኩ፡፡ "really..? ትተማመኝብኛለሽ ኤፊ? በእኔ ትተማመኛለሽ?" አለ እንደመቆምም እንደመቀመጥም እያረገው፡፡ ያለ አንዳች ሃፍረት እየተፍለቀለቀ፣ እጄን እየሳመና እየተቁነጠነጠ የሚሆነውን ሲያሳጣው እኔ በሃፍረት ተሸማቅቄ ላልቅ ደረስኩ፡፡ የእርሱ ሁኔታ ካፌው ውስጥ ያሉትን ሰዎች ትኩረት በመሳቡ ወደ ግራ ወደ ቀኝ መዞር እንኳ አፈርኩ፡፡ ከሥንት መቁነጥነጥ በኋላ ተረጋጋና "ይህን ቃል ከአንቺ በመስማቴ የተሰማኝን ደስታ ልደብቅ አልችልም...ለምን ሌላ ቦታ ሄደን በቆንጆ ራት አናከብረውም?" አለኝ፡፡ ወደ ቤት ቶሎ መመለስ እንዳለብኝ ገልጬ የራት ግብዣው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍልኝ ጠየኩ፡፡ እርሱም "በእኔ ላይ ያለሽን እምነት እንድትጨምሪ እለምናለሁ፡፡ ከዚህም ለበለጠ ነገር ለመታመን ዝግጁ ነኝ" አለና ተያይዘን ወጣን፡፡ ወደ ቤት ከመግባቴ በፊት ስላደረገልኝ ነገር ልባዊ ምስጋናዬን አቅርቤ ተሰነባበትን፡፡

ነገሮች በዚህ ሁኔታ እያሉ ጥቂት ቀናት አለፉ፡፡ ለወንድሜ ፋይሰል ለሁመይድ ያለውን ችግር እንደነገርኩትና እርሱም አባቴን በማናገርና በመምከር የእርሱን ሥራና ሃላፊነት እንዲመልስለት እንዳሳመነው ነገርኩት፡፡ ይሁን እንጂ ወንድሜ በጸጥታ ካዳመጠኝ በኋላ ክፉም ደግም ሳይናገር ሄደ፡፡ አተኩረው ሲያዩኝ የነበሩ ዓይኖቹ ውስጥ በውስጡ የሚመላለሰውን ሃሳብ ለማግኘት አዕምሮዬን አስጨነኩት፡፡ ነገር ግን የተጨበጠና ወጥ የሆነ ሃሳብ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ታላቄ እንደመሆኑ መጠን የቤተሰቡን ችግር ለመፍታት ከአቅሜ በላይ የሆነ ሸክም ተሸክሜ መንገላታቴን አይቶ ያዘነልኝ መስሎ ተሰምቶኛል፡፡ በአባቴ በቀለኛ አካሄድ ያለልክ በመበሳጨቱ የነጠቀውን ሥራ መልሶ ቢሰጠውም ባይሰጠውም የማይበርደውም የማይሞቀውም የሚመስል ዓይነ ውሃም አይቼበታለሁ፡፡ በቤተሰብ ጉዳይ የሁመይድ ጣልቃ መግባትና የእርሱ እርዳታ ማስፈለጉም ከክብር አንፃር ምቾት ያልፈጠረለትም ይመስላል፡፡ ምናልባትም ይህን ችግር ለመፍታት ስል እኔ ይዤ የኖርኩትን ክብርና ኩራት እንዳላጣም ሰግቶ ይሆናል፡፡ ብቻ ምንም ይሁን አንዳች ሳይተነፍስ ሄደ፡፡ ዝምታው ትንሽ ቢያስጨንቀኝም እንዲህ ያለው የወንዶች እልህ ተፈጥሯዊ መሆኑን በማሰብ ራሴን አሳመንኩት ወይም ሸነገልኩት፡፡ ከሁመይድ ጋር ካወራን ከአንድ ሳምንት በኋላ አጠር ላለ የሥራ ጉዳይ ነው ብሎ ወደ እንግሊዝ ተጓዘ፡፡ እርሱ በሄደ በአሥረኛው ቀን አካባቢ አባቴ የቡናውን ንግድ ድርጅት ውክልና ሞልቶ መጥቶ እንዲፈርምና ሃላፊነቱንም እንዲረከብ ለፋይሰል ደውሎ ነገረው፡፡ ወንድሜ ክፉኛ አንገራግሮ የነበረ ቢሆንም በእኔና በእናቴ ግፊትና ልመና ጭምር ሄዶ ፈረመ፡፡ ሃላፊነቱንም መልሶ ተረከበ፡፡

ሁመይድ እንግሊዝ ሀገር ሳለ ሌላ ጊዜ አርጎት በማያውቀው ሁኔታ በየቀኑ ይደውልልኛል፡፡ የለንደንንና ሌሎች የእንግሊዝ ከተሞችን በወፍ በረር ያስቃኘኛል፡፡ እዚያ ስለሚገኙ ታሪካዊ ሥፍራዎች፣ ሙዚየሞች፣ አርት ጋለሪዎች፣ ሐውልቶች፣ ቤተ መጻሕፍቶችና ሌሎች መስህቦች ገለፃ ያደርግልኛል፡፡ አያይዞም እኔ ፈቃደኛ ከሆንኩ ምንም ዓይነት ምትክ ውለታ ሳይጠይቅ እንግሊዝንና ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮችን እንደሚያስጎበኘኝ እየደጋገመ ከመሐላ ጋር ይነግረኛል፡፡ በአንፃሩ አባቴ ደግሞ ለፋይሰል ሥራውን ከመለሰለት በኋላ በዚያው ኩርፊያው ቀጥሏል፡፡ ጥቂት የተሻሻለው ከፋይሰል ጋር የነበረው ግንኙነት ብቻ ነው፡፡ የሥራ ጉዳይ የግድ ስለሚያገናኛቸው በጥቂቱም ቢሆን ያወራሉ፡፡ እንደ ወትሮው ቤት የመምጣቱን ነገር ካቋረጠ በኋላ ይህን ነገር ሳያሻሽል መቆየቱ ሁልጊዜ ያሳስበኛል፡፡ በሳምንት አንዴ ብቅ ይልና እየተጎማለለ ግቢው ውስጥ ይዟዟራል፡፡ በትንሽ በትልቁ እናቴ ላይ ይጮሃል፡፡ በገዛ እጁ ከሚፈቀር አባት ወደሚፈራ ንጉሥ ራሱን ስለቀየረ የቤቱ ሰው ሁሉ በተቻለው መጠን ከእርሱ ለመራቅ ይጥራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በድፍረት ላናግረውና በእኔ ምክንያት ቤተሰቡን ሁሉ ማወክ እንደሌለበት ነግሬው ከፈለክ እኔን የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ ልለው አስባለሁ፡፡ ነገር ግን መልሼ ይህ ስሜታዊነት ነው ብዬ እተወዋለሁ፡፡ የጀመርኩትን ስልታዊ አካሄድም ማበላሸት መስሎ ይሰማኛል፡፡ ብቻ በአዕምሮዬ "ይህ ነገር ማብቂያው የት ይሆን?" እያልኩ ፍፃሜው ይናፍቀኛል፡፡ በዚህ ሁሉ የሃሳብ እንግልት ሰንብቼ ለጥቂት ቀናት ብሎ ወደ እንግሊዝ ሄዶ የነበረው ሁመይድ ከ40 ቀናት በኋላ ተመልሶ መጣ፡፡ ከአንድ ሳምንት የእንግሊዝ ቆይታው በኋላ ወደ ዱባይ ጎራ ብሎ በፍጥነት እንደሚመለስ በስልክ የነገረኝ ቢሆንም እዚያ ከወር በላይ መቆየቱ ትንሽ ግርታ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ እርሱ ግን እዚያም በርካታ ሥራዎች ስለቆዩት እንደዘገየ ነገረኝ፡፡ 

ከዚህ ሰው ጋር ያለኝ ግንኙነት ወደሆነ ምዕራፍ እየተሸጋገረ እንደሆነ በውስጤ ይታወቀኛል፡፡ በየቀኑ ማለት በሚቻል መልኩ አብረን ሻይ መጠጣት፣ ምሳ መብላትና አንዳንድ ሥፍራዎች መታየት አዘወተርን፡፡ እኔም የዚህን ሰው ሁኔታ ለማጥናት አስቤ ራሴን በመጠኑ ለቀቅ አደረኩት፡፡ በጣም የሚደንቀው አባቴ ወደ ውጭ ወጣ ወጣ ማለቴ መረጃ እንደሚኖረው የታወቀ ቢሆንም ምንም ያለማለቱ ነው፡፡ ሁመይድ ለአባቴ "ከፈቀዱልኝ የመፍትሄው አካል እሆናለሁ" ሲል እንደነገረው የነገረኝና እርሱም "ከሰማችህ እባክህ ምከርልኝ" ያለውን ተግባራዊ እያደረገው መስሎት ይሆን? ብዬ አሰብኩ፡፡ "ድንቄም ምክር እቴ" ስል ሁኔታው ላይ ለመዘባበት ሞከርኩ፡፡ ያም ሆኖ ከዚህ ክልስ ሰው ጋር የጀመርኩት ወጣ ገባ የት እንደሚያደርሰኝ ለመገመት እየጣርኩ ነበር፡፡ ከእማማ አፀደ ጋር በሁኔታው ልንፀልይበትና ልናስብበት የወሰድነው ጊዜ በራሳችን ግምት የተጠናቀቀ ሲመስል ቁጭ ብለን አውርተናል፡፡ እማማ አፀደም "እንግዲህ ልጄ በምንችለው አቅም ፀልየናል፣ ለእያንዳንዱ ነገር የራዕይ ወይም የሕልም ምሪት መጠበቅ የእምነት መጉደል ምልክት ነው፡፡ ምናልባት ወደ ስህተት የመምራት ዕድልም ይኖረዋል፡፡ በሕሊናሽ የተለየ መላ ካልተከሰተልሽ በያዝሽው መንገድ ወስኖ መቀጠሉ ተመራጭ ነው፡፡ እኔም ቢሆን የመውጫው መንገድ ይኸው ብቻ ነው መስሎ የተሰማኝ፡፡ ደግሞ አይዞሽ...አነሰም በዛም በነገሩ ላይ ፀለይንበት አይደል እንዴ? ጸሎት ማለት ራስንና ነገሮችን ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት ማለት ነው እኮ" ብለውኛል፡፡ ሁመይድ የገባልኝን የነፃነት ቃል በየጊዜው በብዙ እርግጠኝነት የሚደግመው ቢሆንም እንኳ በምስክር ፊት የሚያረጋግጥበትን አንድ የጋራ ሥልት ነደፍን፡፡ የእማማ አፀደ ሴት ልጅና የእኔም አብሮ አደግ የሆነችው ሄለንንም የስትራቴጂያችን አካል አደረግናት፡፡

ከሁመይድ ጋር ጊዜ ባሳለፍን ቁጥር እኔን በእጁ የማድረግ ፍላጎቱ ጣራ ነካ ማለቱ ይቀላል፡፡ የዘወትር ውትወታው እንድንጋባ ነው፡፡ ለሐጂም እኔ እሺ ሳልለው አንዳች ነገር እንደማይተነፍስ እየደጋገመ ይነግረኛል፡፡ ይህ አባባሉ ሁልጊዜ ትርጉም አልባ ቢሆንብኝም እንደ ዋዛ ግን እሰማው ነበር፡፡ ለተደጋጋሚው የጋብቻ ጥያቄው ከዚህ በፊት የነገርኩትን ወገብ የሚቆርጥ መልስ አሁን አልሰጠውም፡፡ ይልቁንም ለበርካታ ቀናት እሺም እምቢም ሳልል አብሬው እታይ ነበር፡፡ ወደ በኋላ ላይ "ወንዶች ስትባሉ ጠብ እርግፋችሁ የምትፈልጉትን በእጃችሁ እስክታስገቡ ድረስ ነው" እለው ጀመር፡፡ እንዲህ ስለው እሺ ለማለት ጫፍ የደረስኩ ነገር ግን በእርሱ ላይ እምነት የማጣቴ ነገር ትልቅ እንቅፋት የሆነ እየመሰለው ከብዙ መሃላ ጋር የቃል ኪዳን መዓት ይገባል፡፡ ከተደራረበብኝ ችግር በተጨማሪ በዋናነት ልቤን በከፊልም ቢሆን እንድከፍት ያደረገኝ እሰጥሻለሁ ያለኝ የሕሊና ነፃነት ነው፡፡ ይህንኑ ነገርም እያስረገጠ ይነግረኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ከእማማ አፀደና ከሄለን ጋር በተነጋገርነው መሰረት ከጓደኛዬ ጋር ላስተዋውቅህ ብዬ አንድ እሑድ ረፋድ ቀጠርኩት፡፡ ይህን ማድረጌ ለእርሱ የድል አጥቢያ እንደሆነ ስለተሰማው ያለልክ ፈነጠዘ፡፡ ብሥራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት በረንዳ ላይ ከሄለን ጋር ጠበቅነው፡፡ እርሱም በሰዓቱ ሲከንፍ መጣና ተቀላቅሎን ቁርስ እየበላን ስንጫወት ቆየን፡፡ ለሄለን እየሳቅሁና ነገሩን ለማዛት እየጣርኩ "ይኸውልሽ ጓደኛዬ ይህ ሰውዬ ካላገባሁሽ እያለ መቆሚያ መቀመጫ ነስቶኛል" አልኳት፡፡ እርሷም እኛ ቤት ሲመላለስና እኔ ጸበል ሳለሁ በተደጋጋሚ እንዳስተዋለችው ነገረችው፡፡ እርሱም ብድግ ብሎ በአክብሮት እጇን ከጨበጠ በኋላ ተቀመጠና ስለ ራሱ አንዳንድ ነገር ማውራት ቀጠለ፡፡ በመሐል ላይ ሄለን ወደ ውጭ ስታይ ቆየችና "እናቴ...እናቴ ያቻትና" ይቅርታ በመጠየቅ ደረጃውን ተንደርድራ ወርዳ ሄደች፡፡ ዓይናችን እርሷን ሲከተል እማማ አፀደ ከሁለት ሴቶች ጋር ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ ነበር፡፡ እኔም ከመቀመጫዬ እየተነሳሁ "እማማ አፀደ ናቸው፣ ታውቃቸዋለህ አይደል?... ያስታመሙኝ ሴቲዮ" አልኩት ለማስታወስ እንዲረዳው፡፡ "እህ...!" አለ አንገቱን በአዎንታ እየነቀነቀ፡፡ ወደርሳቸው መንገድ ስጀምር "ይዘሻቸው ነይ...ቁርስ ይብሉ" አለ፡፡ መንገዱ ዳር እንደቆሙ ተቀላቀልኳቸውና ጥቂት አውርተን እያመነቱና በግድ በሚመስል መልክ ከሰዎቹ ነጥለን ወሰድናቸው፡፡ ሁመይድ ብድግ ብሎ በአክብሮት ተቀበላቸው፡፡ በፍጥነትም ከበረንዳው ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብተን ተቀመጥን፡፡

እማማ አፀደ ከተላበሱት ግርማ ሞገስ በተጨማሪ ጨዋታ አዋቂም ናቸው፡፡ በራሳቸው ለዛና ዘይቤም ስለ እምነታቸው ሲመሰክሩ በጣም ያስገርማሉ፡፡ እርሱ በደንብ እንደሚያውቃቸው ሁሉ ለመስተንግዶ ተሽቆጠቆጠ፡፡ የቀረበላቸውን ቁርስ እንደነገሩ ቀማምሰው ሲያበቁ ስለ እኔ ከልጅነት ጊዜ አንስተው  የነበረኝን ቁጥብነት፣ አሁን በቤታችን የተፈጠረውን ችግር ከወጣነትና ዘመኑ ከፈጠረው ተፅዕኖ ጋር እያያያዙ አወጉ፡፡ እግረ መንገድም ከልጃቸው ከሄለን የማይለዩኝ ልጃቸው እንደሆንኩ አፅንኦት ሰጥተው ተናገሩ፡፡ እኔም በመሐል ለእማማ አፀደ ሁመይድ ካልተጋባን ብሎ ወጥሮ እንደያዘኝ ነገርኳቸው፡፡ እርሳቸው በእኔ ሕይወት ውስጥ ጉልህ ተፅዕኖ ካላቸው ጥቂት ሰዎች አንዷ ናቸው፡፡ በብዙ ነገር የሚተማመኑባቸው፣ ለእያንዳንዱ ችግር የሆነ መላ የማያጡ ዓይነትም ናቸው፡፡ የሁመይድን ጥያቄ ከነገርኳቸው በኋላ "እናንተ ወጣቶቹ እኛ አሮጊቶች ምንም የማናውቅና የማናስተውል ይመስላችኋል እንጂ በጥቂት እይታና በትንሽ መረጃ ወደ እውነታ የሚጠጋ ድምዳሜ ሰጭዎች ነን፡፡ ነገር ግን ይህን ብስለት እኛ ዕድሜ ላይ ሳትደርሱ በፍፁም አታውቁትም" ብለው እንቅስቃሴያችን ወደዚያ እንደሚያመራ ጠርጥረው እንደነበር ነገሩን፡፡ አያይዘውም ፈጣሪ ሃሳባችንን እንዲባርክልን ደጋግመው መረቁን፡፡ ከምርቃታቸው በኋላ በዘዴና በለዘብታ ቃል ጥያቄ አነሱ፡፡ "እሺ...ለቁም ነገር መብቃት ትልቅ ፀጋና ክብር ነው፡፡ ሆኖም በምን መልክ ነው ያሰባችሁት?? ከቤተሰብ ጋርስ ተማክራችኋል? ይቺ ልጅ ያሳለፈችውን መከራና በቤቷ ያለውንም ችግር ታውቃለህ አይደል?? በምን መልኩ ነው ጉዳያችሁን ልትፈፅሙ ያሰባችሁት??" አሉት ሁመይድን በሚመረምር አይኖቻቸው እያስተዋሉት፡፡

ሁመይድ የእማማ አፀደን ጥያቄ ለመመለስ ተርበተበተ፡፡ አይኖቻቸውን ሽሽትም እንደ ዓይናፋር ልጃገረድ አንዴ ወደ ሰማይ አንዴ ወደ ምድር ዓይኖቹን አቅበዘበዘ፡፡ ነገረ ሥራው ብሽቅ አደረገኝና በጠረጴዛው ሥር እግሬን ሰድጄ በጫማዬ ቅልጥሙ ላይ አቀመስኩት፡፡ እንደመባነን አለና ተንተባተበ፡፡ ሄለን ሁኔታው አስገርሟት ሳቋ ሊያመልጣት ሲል በዘዴ ጎንበስ ብላ እግሯን በማሸት ፊቷን ለመደበቅ ሞከረች፡፡ የእርሷን ሁኔታ አይቼ እኔም ሳቅ አፈነኝና ፈገግ እያልኩ "ሁመይድ የእማማ አፀደ ጥያቄ አልገባህም መሰለኝ" አልኩት፡፡ "አይ... አዎ... ምንድነው? መጀመሪያ እኮ እርሷ ገና ፈቃደኛ መሆኗን አልነገረችኝም እማማ" አለ እጁን ወደ እኔ እየጠቆመ፡፡ ሁኔታው ክስ የሚያቀርብ ከመምሰሉም በላይ በጭንቀት ፈገግ ለማለት ሲሞክር የውሸት ፈገግታው ፊቱ ላይ ደስ የማይል ገጽታ ይፈጥራል፡፡ እማማ አፀደ የሁመይድ ጭንቀት ስለገባቸው በዕድሜና በሕይወት ልምድ ያካባቱትን ጥበብ ተጠቅመው የተፈጠረውን ደስ የማይል ድባብ በፍጥነት ቀየሩት፡፡ እሳቸው ወጣት እያሉ የነበረውን የትዳር አመሰራረት፣ የሽምግልና አላላክ፣ የእጮኛ አመራረጥ እየተረኩ፣ የገጠሟቸውን አስቂኝ ገጠመኞች እያወሩ በሳቅ አፈረሱን፡፡ ሁመይድ በሁኔታው ፍፁም ተለወጠና ዘና አለ፡፡ ከዚያ በኋላ ማንም ሳይኮረኩረው እኔ እሺ ብዬ ላግባው እንጂ የሚያደርግልኝን ነገር፣ የሚወስደኝን ቦታ፣ የሚሰጠኝን ሥጦታ፣ የሚጠብቅልኝን የሃይማኖትና የህሊና ነፃነት እየማለና እየተገዘተ በዝርዝር ተናገረ፡፡ እንዲያውም እማማ አፀደን "እርስዎ እናቴ ነዎት፣ ትልቅ ሰውም ነዎት፣ በእርስዎ ፊት ያልኩትን ሁሉ ልፈፅም ቃል እገባለሁ" እስከማለት ደረሰ፡፡ የዚያን ዕለት ፕሮግራም ባቀድነው መልክ ከተጠናቀቀ በኋላ ሁመይድ እየፈነጠዘ በቅርብ ርቀት ወደሚገኘው ሰፈራችን አድርሶን ሄደ፡፡ እማማ አፀደ ቤት ገብተን ከሄለን ጋር በአንዳንድ ሁኔታዎች ስንሳሳቅ ቆየንና በመሐል ላይ ሄለን "ባልሽ ደስ የሚል ሰው ነው፣ በተለይ እንደ ሕጻን ልጅ ሲያፍር ያዝናናል... ከዚሁ ጋር ግን የአይኖቹን መቅበዝበዝ ሲያዩት ሌባ ያስመስለዋል" ብላ ከት ብላ ሳቀች፡፡ እኔም "አንቺ ባሌን እንዴት ነው የምትናገሪው?" ብዬ ለሳቅ ባጎነበሰችበት ጀርባዋን ደለቅኳት፡፡ እርሷ ግን ይባስ በሳቅ መንከትከት ጀመረች፡፡ ንግግሯን የሰሙት እማማ አፀደም "አንቺ ሹል አፍ ምኑን ነው የምትቀባጥሪው?" ብለው ሲጠጓት እየሳቀች ሮጣ አመለጠች፡፡ እማማ አፀደ እያቀፉኝ "ልጄ ሁሉን ፈፃሚው መድኃኔዓለም ነው፡፡ ለምናልባቱም ግን በእኛ ፊት ቃሉን መስጠቱ ደግ ነው" ብለው በብዙ ምርቃት አሰናበቱኝ፡፡

ከዚያ ቀን ጀምሮ ሁመይድ እርሱን ለማግባት እንደተስማማሁና የእሺታ ቃሌን እንደሰጠሁት ቆጠረ፡፡ እውነት ለመናገር እኔም ቀጣዮቹን የአካሄድና የቅደም ተከተል ጉዳዮች ማሰብ ጀምሬያለሁ፡፡ ስለሆነም መጀመሪያ ለፋይሰል ቀጥሎም ለእናቴ ለመንገር ወሰንኩኝ፡፡ ከአሁን በኋላ የነብር ጅራት እንደያዝኩ ዓይነት ራሴን አሳምኜ ቁርጠኛና የውሳኔ ሰው ለመሆን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ፋይሰልን ከቤት ውጭ አንድ ካፌ ቁጭ አድርጌ ያለውን ሁኔታና የደረስኩበትን ውሳኔ ነገርኩት፡፡ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ፀጥ ብሎ ሲሰማኝ ቆየና ምንም ሳይናገር ዝም አለ፡፡ "ወንድሜ አንድ ነገር አትለኝም እንዴ?" ብዬ ጠየኩት፡፡ በመስኮት ማዶ ማዶውን እያየ "ምን ልበልሽ? እኔ ያንቺን ውሳኔ አከብራለሁ፣ ደስተኛ እንድትሆኚ ብቻ ነው የምፈልገው" አለ፡፡ ገጽታው ላይና ዓይኖቹ ውስጥ ግን ግልፅ ቅሬታ ይነበብ ነበር፡፡ የተሸነፍኩ፣ የቤተሰቡን ሰላም ለመጠበቅና ከጥቃት ለመከላከል ስል ከአቋሜ የተንሸራተትኩ አድርጎ በማሰብ ያዘነልኝ ይመስላል፡፡ የወንድሜን አለኝታነትና አሁን ስለ እኔ ሲል ነፍሱን ማስጨነቁን አስቤ ድንገት ኤንባዬ ዝርግፍ አለብኝ፡፡ ማልቀሴን ሲመለከት አጠገቤ መጥቶ ሊያባብለኝ ብዙ ደከመ፡፡ እየደጋገመ "ደስተኛ እንድትሆኚ ብቻ ነው የምፈልገው" ይለኛል፡፡ የሚመለከቱን ሰዎች በአንዳች ነገር ያልተግባባን ፍቅረኛሞች እንጂ ወንድምና እህት አልመሰልናቸውም ነበር፡፡ ይህንኑ ነገር ለእናቴ ስነግራትም ተመሳሳይ ቅሬታ ተመልክቼ መደነቅ ጀመርሁ፡፡ ተስፋ በመቁረጥና አባቴን በማማረር ስሜት "እስቲ እንግዲህ አግቢላቸውና ይረፉት፣ ከዚያ ደግሞ በምን ሰበብ እንደሚነታረኩ እናያለን" አለች፡፡ ከሁሉ ያስገረመኝ ግን የሰዓዳ ነው፡፡ ግዴለሽ ከሚመስል ተፈጥሮዋና ለሁመይድ ካላት ቅርበት የተነሳ ዜናውን በደስታ ትቀበላዋለች ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ እያሳሳቅሁ "ሁመይድን እኮ ላገባው ነው" ስላት ዱብ ዕዳ የወረደባት ይመስል ክው ብላ ቀረች፡፡ ከመፍለቅለቅ ሙዷ ተስፈንጥራ ወጥታና ኮስተር ብላ "ምን..?" ብላ ስትጠይቀኝ በዕድሜዋ ላይ በአንድ ጊዜ 20 ዓመት ጨምራ ታየችኝ፡፡ "አንቺ ክርስቲያን አይደለሽ እንዴ? እንዴት ሙስሊም ታገቢያለሽ?"  አለችኝ፡፡ ረጋ ብዬና ደቂቃዎች ወስጄ ላስረዳት ብሞክር እንኳ በፍፁም ሊገባላት አልቻለም፡፡ "ያ ሁሉ ችግር ለዚሁ ነበር?" ብላ በሚታዘቡ የልጅነት ዓይኖቿ ስትመለከተኝ የምገባበት አሳጣችኝ፡፡ "እንጃ የምትዪው ነገር ምንም አልተዋጠልኝም" ብላ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች፡፡

ክፍሌ ገብቼ መራራ ለቅሶ አለቀስኩ፡፡ ባሳየሁት ጽናትና በፈፀምኩት ተጋድሎ በቤተሰቤ ዘንድ አትርፌው የነበረውን ሞገስ በአንድ ጊዜ ያጣሁት መስሎ ተሰማኝ፡፡ "የእኔ እንባ መቼ ይሆን የሚያቆመው?" እያልኩ ስነፈርቅ አመሸሁ፡፡ የደረስኩበትን ውሳኔ እንደገና ለመመርመር እስክከጅል ድረስ ውስጤ ተነዋወጠ፡፡ ሌሊቱን እንቅልፍ አጥቼ አድሬ ነጋ አልነጋ በማለት በማለዳ እማማ አፀደ ጋር ሄድኩ፡፡ ቤተክርስቲያን መሄዳቸውን ስሰማ ደፍሬ ብሥራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሄድኩ፡፡ እዚያው ስፀልይ ቆይቼ ሲወጡ ተገናኘንና መጠለያ ውስጥ ብዙ ደቂቃ ተቀመጥን፡፡ ከቤተሰቦቼ ያገኘሁትን ምላሽና የፈጠረብኝን አሉታዊ ስሜት እያለቀስኩ ነገርኳቸው፡፡ ውሳኔዬ ልክ መሆኑን መጠራጠር ሁሉ መጀመሬንም አልደበኳቸውም፡፡ እርሳቸው ግን ከእንዲህ ያለ ውሳኔ ጀርባ የተለያዩ ተግዳሮቶች መኖራቸው የተለመደ መሆኑን እየጠቀሱ ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ነገሩኝ፡፡ "በእርግጥ የሰው ልጅ ባህሪ ጀግና ወዳድና አድናቂ ከመሆኑም በላይ ያ ጀግና ጥራቱም ጽናቱም እንዳይቀንስ በብርቱ የሚመኝ ነው፡፡ ነገር ግን የእርሱን ጽዋ ለመቅመስ የሚፈልግ በባትሪም ተፈልጎ አይገኝ፡፡ አሁን አንድ ጊዜ ወስነሽ ከአፍሽ የወጣ ነገር ሆኗል፣ ወደ ኋላ መመለስ ደግ አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ሁነኛ መፍትሄ ሳያመላክቱ ግፊ በርቺ ማለት ብቻውን የአንቺንም ሰብዐዊነት ግምት ውስጥ ያለመክተት ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ሁሉን ነገር ለመድኃኔዓለም ሰጥተናል፡፡ እርሱ እንደሚያበጀው በፍፁም ልብሽ እመኚ፡፡ ከብዙ ለቅሶ በኋላ ነው ሳቅና ደስታ የሚገኘው" ሲሉ መከሩኝ፡፡ እማማ አፀደ ሀኪሜ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ከእርሳቸው ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ እንደገና ሁሉን ነገር ለጌታ ሰጥቼ ወደፊት ብቻ መሄድ እንዳለብኝ ይሰማኝ ጀመር፡፡

ሁመይድ እንደገና ለጥቂት ቀናት ከሀገር ወጥቶ ቆየና ተመልሶ መጣ፡፡ ያን ጊዜ "ኤፊ አሁን ነገሩን ለሐጂ ብነግራቸው ምን ይመስልሻል?" ሲል እየተለማመጠ ጠየቀኝ፡፡ እኔም በአጭሩ "ንገረው" አልኩት፡፡ ያልሰማ ይመስል "እ..." አለኝ፡፡ "ንገረው..ከዚያ የሚልህን ትነግረኛለህ" አልኩት፡፡ የእርካታ ስሜት እየተነበበበት "አመሰግናለሁ ኤፊ" አለኝ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደ ሕጻን ልጅ አኩርፎ መጣና "ሐጂ እርሷ ካላረጋገጠችልኝ አላምንህም...እርሷ እንሆነ እኔን ያለማሳፈር ሥራ የላትም፡፡ ሽማግሌ ተልኮ ሲያበቃ ደግማ ታዋርደኝ እንዴ?" አሉኝ አለና ተከዘ፡፡ "ችግር የለውም...ሄጄ አረጋግጥለታለሁ" አልኩና ብድግ አልኩ፡፡ "የት ልትሄጂ ነው?" አለኝ በተቀመጠበት አሻቅቦ እያየኝ፡፡ "እርሱ ቢሮ እሄዳለሁ" አልኩት፡፡ "ቆይ ላድርስሽ" ሲል "በፍፁም በታክሲ ነው የምሄደው" ብዬ አዋክቤው ወጣንና ኮንትራት ታክሲ ይዤ ሱማሌ ተራ አካባቢ ወደሚገኘው ቢሮው አመራሁ፡፡ በከፍተኛ እልህና ወኔ ተሞልቼ ወደ አንድ ዓይነት ግጥሚያ የምሄድ ዓይነት ስሜት እየ ቢሮው ያሉት ሰራተኞችን ከሞላ ጎደል ያውቁኛል፡፡ ስለሆነም በቀጥታ ቢሮው ገባሁና ፊት ለፊቱ ቆምኩ፡፡ መነጽሩን ሰክቶ ከሚያየው ፋይል ቀና ብሎ ሲያየኝ ዓይኑን ማመን አቃተው መሰል መነጽሩን አውልቆ በግርምት አስተዋለኝ፡፡

                         (ይቀጥላል)

     ---------- ማርያማዊት ገብረመድኅን ----------saramareyama.890@gmail.com

አፊያ ሁሴን ክፍል ፱

#አፊያ ሁሴን ክፍል 9

#ፀሀፊ ማርያማዊት ገብረ መድህን

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፱)
saramareyama.890@gmail.com
ሁመይድ የመላው ቤተሰብ ወዳጅና ቤተኛ ከሆነ ሰንበት ቢልም ከእኔ ጋር ለየት ያለ ቅርበት እንዳለው ሰራተኞቹ ሳይቀር ያስተዋሉ መሆናቸውን ከመልዕክቷ ተረዳን፡፡ ሆኖም መውጣት ስላልፈለኩ ፋይሰልን "ሂድ አጫውተው ራሷን አሟት ተኝታለች በለው" ብዬ ላኩት፡፡ መጀመሪያ ፋይሰል፣ ከዚያ ሰዓዳ ሄዱ፡፡ ከተኛሁ በኋላ ሰዓዳ መጥታ ከአንቺ ጋር ነው የምተኛው ብላ ምኑንም ምኑንም ስትለፈልፍ አመሸች፡፡ እንግዲህ በእርሷ ቤት እየጠበቀችኝ ነው ማለት ነው፡፡ ያን ሳምንት እንዲሁ ሲጠነቀቁኝና ሲፈሩኝ ሰነበቱ፡፡ እናቴ ወደ ሱቅ እንኳን ወጣ ለማለት በተነሳሁ ቁጥር "እባክሽ ልጄ ልጄ..እባክሽ የእኔ እናት.. እዚሁ ቁጭ በዪልኝ፣ የትም ቢሆን ሰራተኞቹን ላኪያቸው" እያለች ትለማመጠኛለች፡፡ እኔም የምችለው እርሷን ነውና "ሰው እኮ ነኝ፣ የቤቱ ውስጥ ዕቃ አረግሽኝ እንዴ? አየር ያስፈልገኛል፣ መንቀሳቀስ ያስፈልገኛል፣ ይሄ የእናንተ ቪላ ለእኔ መኖሪያ ቤቴ ነው ወይስ እስር ቤቴ ነው?" እያልኩ እጮህባታለሁ፡፡ የቱንም ያህል ብናገራት የእናቴን ልመና ረግጬ አልወጣም፡፡ እየተነጫነጭሁ መልሼ ቁጭ እላለሁ፡፡ ለአባቴ "ወይ ጥያችሁ እጠፋለሁ፣ አሊያ ራሴን አጠፋለሁ" ብላ በስንት ልመና በስንት ግልግል ነው የተረጋጋችው ተብሎ ተነግሮታል መሰለኝ ወደ ቤት በመጣ ቁጥር መኖሬን ጠይቆ ያረጋግጣል እንጂ ከእኔ ጋር መገናኘቱን አይፈልገውም ነበር፡፡ እኔም በርቀትም ቢሆን ባየሁትና ድምፁን በሰማሁ ቁጥር "ልጄ መሆኗን እጠራጠራለሁ" ያለው ነገር ትዝ እያለኝ እንደ አዲስ እናደዳለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ያሳየኝ የነበረው የአባትነት ፍቅር ሁሉ ለማስመሰል ያደረገው ሽንገላ እየመሰለኝ በክፉ ሃሳብ እናጣለሁ፡፡ ሽማግሌዎቹ የተቀጠሩበት ቀን እየቀረበ ሲመጣ አባቴ ሃሳቤን ቀይሬ እንደሆነና ረጋ ብለውም ሊያሳምኑኝ እንዲጥሩ እናቴ፣ እህቴና ፋይሰል ላይ ጫና ማድረጉን ተያያዘው፡፡ እነርሱ ደግሞ እኔን ከመናገር እርሱኑ መጋፈጥ የተሻለ እንደሆነ የቆጠሩበት ሳምንት ነበር፡፡ አንድ ቀን እንደውም ከፋይሰል ጋር ኃይለ ቃል እስከመነጋገር ደረሱ፡፡ ወንድሜ አባቴን ከዚህ በላይ ሊያስጨንቀኝ እንደማይገባ ሲነግረው በጄ ስላላለው "አንተ ብዙ ሴት ልጆች ስላሉህ የአንዷ መጨነቅ አልተሰማህ ይሆናል፡፡ እኔ ግን እህቴን እፈልጋታለሁ" ሲል አምርሮ ተናገረው፡፡ በዚህ የተበሳጨው አባቴ ልክ አድማ የተደረገበት ያህል መላ ቤተሰቡን አኮረፈ፡፡

ሽማግሌዎቹ እሑድ ሊመጡ ሐሙስ ከሰዐት ሾልኬ ወጣሁና ቤተክርስቲያን ቆይቼ ማምሻውን እህቴ ቤት ሄድኩኝ፡፡ ትንሽ ሲራበሹ ከቆዩ በኋላ እህቴ ደውላ እርሷ ጋር እንደሆነች ነገረቻቸው፡፡ እስከ እሑድ እዚያው እንደምቆይ ተናግሬ ይህንኑም ለእናቴ በስልክ አስረዳኋት፡፡ እርሷም "እሺ የእኔ ልጅ እንዲያውም እዚያ ብትሆኚ ይሻላል" አለችኝ፡፡ የእሑዱ ሽምግልና ቀዝቀዛ ድባብ እንደወረሰው መጠናቀቁን ሰማሁ፡፡ አባቴም "እነዚህ ሽማግሌዎች ምስክሮቼ ናቸው፣ በዱላም በምክርም በልመናም አልሸነፍም አለች፡፡ እንግዲህ ምን አድርግ ትሉኛላችሁ?...ልጄን አልገላት ነገር" በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሽምግልናው በአሉታ ከተደመደመ በኋላ ሽማግሌ የላከው መምህር "ድሮም ሐጂ ራሳቸው ልጄን ከካፊር ወጥመድ አድንልኝ፣ አግባትና እያስተማርክ ቀስ ብለህ ታቃናታለህ፡፡ እኔ ራሴ ድል አድርጌ ደግሼ እድራችኋለው ብለውኝ እንጂ በሃሳቤም አልነበረች" እያለ ማስወራቱ ተሰማ፡፡ ይህን የሰሙ ቤተሰቦቼ በአባቴ ተግባር አንጀታቸው ቢያርም ደፍሮ የተናገረው ግን አልነበረም፡፡ ለእኔ ግን "ልጄ መሆኗን እጠራጠራለሁ" ካለው ንግግሩ በተጨማሪ ይህን ድርጊቱን ስሰማ ይበልጥ እጠላውና እፈራው ጀመር፡፡ ፍላጎቱን ለመፈፀም አሁንም እንዳልተኛልኝና ማንኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለስ እንደ አዲስ ተገነዘብኩ፡፡

የሽምግልናው ዕለት ሁመይድ ሰዓዳን ይዟት መጣና ምሳ ካልጋበዝኳችሁ ብሎ ተያይዘን ወጣን፡፡ ስለ ሁሉ ነገር በቂ መረጃ የነበረው ሁመይድ "አንቺ ብትደብቂኝም ሁሉን ነገር ሰማሁት" ብሎ ወቀሳ መሳይ ነገር አቀረበ፡፡ "ይህ ምን ተብሎ ይነገራል?" አልኩና "ከየት ሰማህ? ሰዓዳ ናት የነገረችህ?" ብዬ ጠየኩት፡፡ እርሱ ግን "ምን ይሄ የተሰወረ ነገር ነው እንዴ? ሁሉ የሚያወራው አይደል...ዛሬ ራሱ ሽማግሌዎች ስምሽን በእምቢታ ሲያነሱ ብቻሽን ሆነሽ ስቅ ከሚልሽ እኔና ሰዓዳ እናዳብርሽ ብለን ነው የመጣነው" አለና "አይደል እንዴ ሰዓዳ..?" እያለ እርሷን መኮርኮርና አዎንታዋን መፈለግ ጀመረ፡፡ ሰዓዳም በኩርኮራው እየተቁነጠነጠች "አዎ ሃሳቡን እርሱ ነው ያቀረበው፣ እኔ ደግሞ አፀደቅሁት" ብላ መፍለቅለቅ ጀመረች፡፡ ሰዓዳ ባለችበት ቦታ ሁልጊዜም ቁዘማና ድብርት ቦታ አይኖራቸውም፡፡ ተፈጥሮዋ ሆኖ ነው መሰል ተረጋግታ መቀመጥም ሆነ ዝም ማለት አይሆንላትም፡፡ በዚያ ላይ የማታመጣው ወሬና ጨዋታ የለም፡፡ ኃይለኛ የመረጃ ሰውም ናት፡፡ ንግግሯ በፈሊጥ ከመሆኑም በላይ ጊዜውንና ሁኔታውን ያገናዘበ ቀልድ መፍጠር፣ አዋዝታም ማቅረብ ትችልበታለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ መንቀዥቀዧን ብታበዛውም በሰሚም ሆነ በተመልካች ዘንድ አትሰለችም፡፡ በተወሰነ መልኩም ቢሆን አደብ የማሲዛት እኔ ነኝ፡፡ ከአባቴ ጋር በፈጠርኩት ፀብና ቤታችን በገባው ያለመረጋጋት ይቺ ብልህና ተጫዋች እህቴ ቤታችን ውስጥ ባትኖር ኖሮ ሕይወት ለሁላችንም ከባድ በሆነ ነበር፡፡ አሁንም በዚሁ ጨዋታዋ እኔና ሁመይድን በሳቅ ስታፈርሰን ቆየች፡፡ በዚህ መሐል ሁመይድ ቁም ነገር መሳይ ጨዋታ ለማምጣት ደጋግሞ ቢሞክርም መሃላችን ሰዓዳ መኖሯን እየጠቆምኩ በዓይኔ ስገስፀውና ስከላከለው ቆየሁ፡፡ የዕለቱ ውሎአችን ሁመይድ እንዲሁ ከእኔ ጋር ለማውራት እንዳሰፈሰፈ እኔም እንደተከላከልሁ ተጠናቀቀ፡፡ በሁኔታዬ ስለተከፋም በታዛቢ ዓይኖቹ እየሸነቆጠኝ እታባ ቤት ካደረሱኝ በኋላ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡

የአባቴ ኩርፊያ በቶሎ እንደሚበርድ ተገምቶ ነበር፣ እናቴ ራሷ "አሁን ሳምንት ሳይሞላው ይረሱታል" እያለች ለወንድሜም ለእኔም ለቤቱ ሰው ሁሉ ትናገር ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አባቴ ወደ ቤት በመጣ ቁጥር በሆነው ባልሆነው እየተበሰጫጨ ቤተሰቡን ማመሱን ቀጠለበት፡፡ ለእኔ መልካም የሆነው ነገር "እዚህ ስመጣ ፊት ለፊቴ እንዳላያት በዚህ ከዘራ አናቷን ብዬ ነው የምገላግላት" ብሏል በመባሌ ከእርሱ ጋር መፋጠጤ መቅረቱ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ከቤት እንዳልወጣና እንደፈለገኝ እንዳልሆን በእጅ አዙር ጥብቅ ቁጥጥር ያደርግብኛል፡፡ ሽምግልና ሲላክ የአባቴ ስውር እጅ ሊኖርበት ይችላል የሚል ጥርጣሬ ነበረኝ፡፡ እንደገመትኩትም መጨረሻው እንደዚያው ሆኗል፡፡ ይህንኑ ነገር ደግሞ ሽማግሌ ላኪው የራሱን ሞራል ለመገንባት በሚመስል መልኩ ለጀማው በማውራቱ አባቴ ኃፍረትና ንዴት ክፉኛ ተሰምቶታል፡፡ በዚያ ላይ ወንድሜ ፋይሰል ግፊቱን ተቃውሞ በኃይለ ቃል ስለተናገረውና እናቴም በአቅሟ ዘወትር እኔን ስለምትከላከል የብስጭቱ ተጨማሪ ግብዐት ሆኖታል፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር የእኔ እንደ ልቡ አለመሆኔና የአባወራነት ሥልጣኑ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል መላ ማምጣት ያለመቻሉ ሳያብከነክነው አልቀረም፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ ተወዳጁ አባቴን አመል ነሳው፡፡ ለወትሮው ታስቀው የነበረችው ሰዓዳን እንኳን ፊት ነስቷት በቀልዷ መዝናናቱን እርግፍ አድርጎ ትቶታል፡፡ ሲለውም ከአጠገቡ ውሻ አርጎ ያባራታል፡፡ ከፋይሰል ጋር በጣም አስፈላጊ የቢዝነስ ጉዳይ ካልሆነ በቀር መነጋገር አቁመዋል ማለት ይቻላል፡፡ እናቴንማ እንዴት ቁም ስቅሏን እንደሚያሳያት አትጠይቂኝ፡፡ ለተፈጠረው ምስቅልቅል ሁሉ እርሷን ተጠያቂ በማድረግ በነገር ይጠብሳታል፣ ሁላችንም ላይ ይዝታል፡፡ የእናቴ ሥጋት እርሱ እንዲህ ሲበሳጭ ደም ግፊቱ ጨምሮ የባለፈው ዓይነት ወይም ከዚያ የባሰ ጉዳት እንዳይደርስበት ነው፡፡ እርሱ ግን የእርሷን ዝምታ ከንቀት፣ ለልጆቿ የምታሳየውንም ፍቅር ከአድማ በመቁጠር ይብስ ይንጨረጨራል፡፡ ነገሮች በዚህ ሁኔታ እየባሱና ይበልጥ እየተወሳሰቡ ሄዱ፡፡

አባቴ አዲስ ባመጣው ዓመልና ቤተሰቡ ላይ በፈጠረው ጫና እኔ ከፍተኛ የሕሊና ስቃይ አተረፍኩ፡፡ ይህ ሁሉ ነገር በእኔ ምክንያት እንደመጣ በመቁጠር የጥፋተኝነት ስሜት ያንገላታኝ ጀመር፡፡ እኔን በገዛ እጁ ቢሰቅለኝ እንኳ በፀጋ ለመቀበል ብርቱ ነበርኩ፡፡ የእናቴ ሥቃይ፣ የወንድሜ በአባቴ ችላ መባል፣ የቤተሰቡን ሥጋት ግን መቋቋም እየተሳነኝ መጣ፡፡ ጊዜው የአዲሱ ዓመት ሁለተኛ ወር ቢሆንም አባቴ በገባው ቃል መሰረት ትምህርት መጀመሪያዬ ጊዜ ነበር፡፡ ነገር ግን የአባቴ ሁኔታ ዶክሜንቶቼን እንዲሰጠኝና ትምህርት እንድቀጥል መጠየቅ ይቅርና ጭራሽ የሚታሰብም አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ እየተደማመረ ራሴን እንደ ቤተሰቡ እንከን የመቁጠር ሃሳብ በአዕምርዬ እየገባ ያስጨንቀኝ ጀመር፡፡ ይህን ክፉ ሃሳብ ለመጋፈጥ አቅም ባላጣም ይህንን ችግር በሰይጣናዊ መንገድ አንዳርም ውስጤን የሚመክር ክፉ ሃሳብ እየደጋገመ በጭንቅላቴ ያቃጭልብኛል፡፡ ከዚህ በፊት ለማስፈራራትና ጫና ለማሳደር እናገረው የነበረው ራስን የማጥፋት ሃሳብ ሞገዱን ፀጥ የሚያደርግ ሁነኛ መፍትሔ ሆኖ በአዕምሮዬ ይሳልብኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አባቴ ጭራሽ ቤታችን የሚመጣበትን ጊዜ እየቀነሰ መጣ፡፡ ይህ እናቴ ላይ የሚፈፀም ግልፅ መድልኦና ትልቅ በደል ቢሆንም እርሱ ግን "እዚያ ስሄድ የማተርፈው ብስጭት ነው" እያለ ለቀሩት ሚስቶቹና ልጆቹ በማውራት የእኛን ቤተሰብ ማጥላላት ተያያዘው፡፡ በዚሁ ከቀጠለ እናቴን ሊፈታት ሁሉ እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡ እነዚህ ነገሮች የጦርነት አውድማውን ከውጭ ወደ ውስጥ አዞሩብኝ፡፡ ከአባቴና የእርሱን ሃሳብ ደግፈው እኔን ከሚያጠቁ ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ የተሻለ ነበር፡፡ አሁን ግን በገዛ አዕምሮዬ ውስጥ ባለ አውደ ውጊያ ራሴ ከራሴ ጋር መፋለም ጀመርኩ፡፡ በጣም ሲጨንቀኝ ድንገት የዘነጋሁት ሃሳብ መጣልኝና ነጠቅ ብዬ ተነስቼ እማማ አፀደ ቤት ሄድኩ፡፡

የተቀጣጠርን ይመስል እማማ አፀደን ቤት ውስጥ ብቻቸውን ተቀምጠው አገኘኋቸው፡፡ የንባብ መነጽራቸውን ሰክተው የሆነ ደረሰኝ ነገር እየተመለከቱ ነበር፡፡ ሲያዩኝ ገና "ውይ አፊያ..ነይ ግቢ ልጄ" ብለው መነጽራቸው አውልቀው ከደረሰኙ ጋር ጠረጴዛ ላይ አኖሩትና አገላብጠው ሳሙኝ፡፡ አጠገባቸው ውሽቅ ብዬ ስቀመጥ እንደ ሕጻን ልጅ ራሴን ያሻሹኝ ጀመር፡፡ ይህን ሁኔታ መቋቋም የሚያስችል አቅም አልነበረኝምና ተንሰቅስቄ ማልቀሴን ቀጠልኩ፡፡ "እንኳን እናቴ ሞታብኝ እንዲሁም አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል" እንደሚባለው ራሴን በእናትነት ወግ ሲደባብሱኝ ሆድ ባሰኝና መነፍረቄ በዛ፡፡ እማማ አፀደ የቅርብ ጎረቤትና የእናቴ ወዳጅ በመሆናቸው ብዙውን የቤታችንን ነገር ያውቁታል፡፡ ስለሆነም እኔ በውስጤ እየተሰማኝ ያለውን ክፉና አስጨናቂ ሃሳብ ስነግራቸው "ምነው ምነው ልጄ ምኑን አሰብሽው? ጠንካራም አልነበርሽ" ብለው አቅፈውና ራሴን ጭናቸው ላይ አስተኝተው አባበሉኝ፡፡ ለቅሶዬም እስኪወጣልኝ ጠበቁኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙ ነገር ስናወራ ቆየን፡፡ አባቴ በእልህና በጥላቻ ስሜት እኔን ብቻ ሳይሆን እናቴን፣ እህቴንና ወንድሜን በማጥቃት ላይ እንደሆነ፣ ቤት ቶሎ ቶሎ መምጣት እንደተወና ቀጥሎስ ምን እንደሚያደርግ እንደማይታወቅ በሥጋት ነገርኳቸው፡፡ አያይዤም "እኔ ላይ የፈለገውን ቢያደርግ ግድለየኝም፣ ነገር ግን በእኔ ምክንያት የገዛ ሚስቱና ልጆቹ ላይ የሚያደርገውን ነገር መቋቋም አልቻልኩም፡፡ ከፍተኛ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ነው፡፡ ይሄን ከማይ ... ብር ብዬ ብጠፋ እመርጣለሁ" አልኩና ሳጌን ለማቆም ታገልኩ፡፡

እማማ አፀደ ዝም ብለው ሲሰሙኝ ቆዩና ጉሮሮአቸውን አፅድተው ፀጉሬን እያሻሹ እንዲህ አሉኝ፡፡ "ይኸውልሽ ልጄ...ያንቺን ፍላጎት፣ የተጋፈጥሽውንም ፈተና፣ ያሳየሽውንም ተጋድሎ በደንብ ስከታተልና ሳደንቅ፣ በአቅሜም ስፀልይልሽ ቆይቻለሁ፡፡ ደግሞም እናትሽ ነኝ፡፡ እናም እስቲ የእናትነት ምክርና አስተያየት ልስጥሽ" አሉና ዓይኔን ፍለጋ ወደኔ ጎንበስና ዞር አሉ፡፡ እንባ ባቀረረው ዓይኔ እያየኋቸው "እኔም እኮ ሲጨንቀኝ ይህንኑ ፍለጋ ነው የመጣሁት" አልኳቸው፡፡ "አይዞሽ ልጄ" ብለው ይበልጥ ጥብቅ አርገው እያቀፉኝ ቀጠሉ፡፡ "ዝም ብዬ የአንቺን ነገር ሳስተውለው የፈተናሽ ብዛቱና ያንቺም ጽናት ከቅዱሳን አንስትና ከሰማዕታት ጋር ብዙው ነገር ይመሳሰልብኛል፡፡ ከቅድስት አርሴማ፣ ከቅድስት ኢየሉጣ፣ ከወለተ ጴጥሮስ፣ ከሌሎቹም ቅዱሳን ሴቶች ጋር፡፡ እኒህ ቅዱሳን የተጋፈጡት ፈተናና ያሳዩት ጽናት እጅግ ትልቅ ስለሆነ ለእንዲህ ያለው ደረጃና ክብር መመረጥም ያስፈልጋል፡፡ አንቺ ምንም እንኳ እስካሁን ያሳየሽው ተጋድሎ የዚህ ዘመን ሰማዕት ሊያሰኝሽ ቢችልም ቤታችሁ ካለው የገነገነ ችግር የተነሳ እንዳትሰበሪብኝ እሰጋለሁ፡፡ ይሄን ያሳሰበኝ ልጄ ስለሆንሽና ስለምሳሳልሽ ሊሆን ይችላል" አሉና ጥቂት ዝም አሉ፡፡ ቀና ብዬ እያየኋቸውና "ምን ሊሉኝ ነው?" የሚል ጉጉት እየናጠኝ "ታዲያ ምን አድርጊ እያሉኝ ነው?" ስል ጠየኳቸው፡፡ ረጋ ብለው ቀጠሉ "አንዳንድ ጊዜ እንደ ተራራ የገዘፈ ችግር ሲገጥመን ጽናታችን ብቻ፣ መጋፈጣችን ብቻ፣ ቁርጠኛነታችን ብቻ ለውጤት ላያበቃን ይችላል፡፡ በተጨማሪ ብልሃት ያስፈልገናል፡፡ አውሎ ነፋሱን ጎንበስ ብሎ የማሳለፍ ጥበብ፣ እንደ እሳት የሚነድ ቁጣን በለዘብታ ቃል የማብረድ ዘዴ፣ የሰይጣንን እብሪት በትሕትና ድል የመንሳት መላ ያስፈልጋል፡፡ መጽሐፉም "እንደ ርግብ የዋሕ እንደ እባብም ብልህ ሁኑ" ነው የሚለው፡፡ አሉና አሁንም ጥቂት ዝም አሉ፡፡ ዝም ባሉ ቁጥር የእኔን ስሜትና ግብረ መልስ እያጠኑ ነበሩ፡፡

የእምነትና የጽናት ተምሳሌቴ እኚህ ጎምቱ አዛውንት ዛሬ ምን እያሉኝ ነው? ስል አሰብኩና "ታዲያ ይህ የሚሉኝ ጥበብ ምንድነው?" አልኩ እንዳቀረቀርኩ፡፡ "በሆነ መንገድ ከአባትሽ ተፅዕኖ መላቀቅ አለብሽ" ሲሉኝ ክው አልኩ፡፡ "ይሄን ቃል የት ነበር የሰማሁት?" ቃሉን ከማስታወስ የእርሳቸውን ሃሳብ ማስጨረስ የተሻለ እንደሚሆን በቅጽበት አስቤና ወስኜ "እንዴት?" አልኳቸው፡፡ "ስፈልግ የኖርኩት ይህንኑ ነፃነት መሆኑ እንዴት ተሰወረባቸው?" ብዬ በማሰብ እየተደነቅሁ፡፡ እርሳቸው ግን "በሆነው መንገድ" አሉኝ፡፡ "በሆነው መንገድ...በጋብቻ ሊሆን ይችላል፣ የራስሽን ሥራ በመጀመር ሊሆን ይችላል፣ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ሊሆን ይችላል...ብቻ በሆነው መንገድ ይሁን፡፡ የሚፈለገው መንገዱ ሳይሆን ውጤቱ ነው" አሉ፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ያሉትን አማራጮች በውስጤ አውጠነጠንኳቸው፡፡ የራስን ሥራ መጀመር ያሉት በድፍረትና በኃይል ቤቱን ጥዬ መሄድን ተከትሎ የሚመጣ እንጂ በሰላምና በአባቴ ፈቃደኝነት የሚታሰብ አይደለም፡፡ እንኳን ሥራ ቀርቶ ትምህርት እንኳ እንዳልቀጥል በክፋትና በጥበብ ያስቀመጠውን የእንቅፋት ድንጋይ ቤተሰቤ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ ቤቱን ጥዬ ሄጄ ይህን አማራጭ ብሞክር እንኳ የሚገጥሙኝ ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው የቤተሰቤን ሰላም ከድጡ ወደ ማጡ የሚከት ነው፡፡ ወደ ውጭ ሀገር የመሄድን አማራጭም ከዚህ በፊት ለአባቴ አቅርቤለት አምርሮ የተቃወመው ሃሳብ ነው፡፡ ይህን ሃሳብ እርሱ የሚያየው ይበልጥ ካፊር ለመሆን መርቆ እንደ መሸኘት አድርጎ ነው፡፡ የጋብቻን አማራጭ ግን እማማ አፀደ እንዴት ሊያስቡት እንደቻሉ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ "ያዘጋጁልኝ ባል አለ እንዴ?" ስል አሰብኩና በራሴ ሃሳብ ፈገግታዬ አመለጠኝ፡፡ እንደገና መልሼ ደግሞ "ነው የጋብቻ ሽምግልናውን በአሉታ መመለሴን እየተቃወሙ ነው" ብዬ በማሰብ ተገረምኩ፡፡

ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ ወደ ውጭ ለመሄድ ለአባቴ ሃሳብ አቅርቤለት በምን አይነት ምሬት እንደተቃወመውና የራሴን ሥራ መጀመርም የሚፈጥረውን ሁከት በአጭሩ ካብራራሁላቸው በኋላ "ባል ማግባት የሚለውን አማራጭ ለምን እንዳቀረቡት ግን አልገባኝም፣ ክርስቲያን ባል አግቢ ማለቶት ነው ወይስ የአባትሽን ፈቃድ ፈፅሚ እያሉኝ ነው?" ስል በቀጥታ ጠየኳቸው፡፡ እርሳቸው ግን በዚያው እርግት ባለ አነጋገራቸው "ሁለቱንም ማለቴ አይደለም" አሉኝ፡፡ እኔም ወደርሳቸው ዞሬ ግራ ከተጋባ ገጽታዬ ጋር "እና ምን ማለቶት ነው?" በሚል አስተያየት አየኋቸው፡፡ ገልመጥ ብለው ገጽታዬን አዩና በፍጥነት እንደገባቸው ሁሉ "የትኛውንም አማራጭ አወዳድሮ የተሻለ ውጤት የሚያመጣውን መምረጥ ብልህነት ነው፡፡ ቢቻል አባትሽን ጨምሮ ሁሉንም ቤተሰብ የሚያስደስት የአንቺንም ዓላማና ፍላጎት የሚያሟላ፣ ካልሆነም ኪሳራውና የሚከፈለው ዋጋ አነስተኛ ሆኖ የአንቺን ፍላጎት የሚያሳካውን መምረጥ ይኖርብሻል" አሉኝ፡፡ በንግግራቸው ይበልጥ ዞሮብኝ እንደተደናገርኩ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ሆን ብለው ከእነ አዕምሮ ውዝግቤ የተዉኝ የሚያስመስልባቸው የዝምታ ጊዜ ሲያበቃ "እኔ የምልሽ አፊያ" ብለው ፈጠን ባለ እንቅስቃሴ ወደ እኔ ዞር አሉ፡፡ ድምፀታቸውም ከእስካሁኑ እርጋታ በመጠኑ ፈጠን ያለና ኃይል የተሞላ ነበረ፡፡ እኔም ባልረጋና ሥልት በሌለው አኳኋን ከሃሳብ ሃሳብ ሲዘል የነበረውን አዕምርዬን ሰብስቤ "አቤት እማማ አፀደ" አልኩ፡፡ ፊት ለፊቴ በሚመረምር ዓይኖቻቸው አተኩረው እያስተዋሉኝ "ይሄ ቤታችሁ የሚመላለሰው ክልስ ማነው?" ሲሉ ጠየቁኝ፡፡

ሜሪዬ..እንደዚያ ቀን ድንግጥ ያልኩባቸው ጊዜያት ቢቆጠሩ ከአንድ እጅ ጣቶች አያልፉም፡፡ ብቻ ክው ስል እርሳቸውም በደንብ አስተውለውኝ ነበረ፡፡ ከድንጋጤዬ ሌላ የሚያስደንቅ መገረምም በውስጤ ሲመላለስ ይታወቀኛል፡፡ በውስጤ "እኚህ ሴቲዮ የነቢያት ዘር አለባቸው እንዴ?" ስል ራሴን ደጋግሜ ጠየኩ፡፡ ሑመይድ ያቀረብልኝን ሃሳብ ለማንም አልተነፈስኩም፡፡ እርሱም ለሌላ ሰው ያወራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ በእርግጥ ቤታችን መመላለሱን ከቢዝነስ ጉዳዮች ሌላ እኔ ላይ ፍላጎት አሳድሮ በመሆኑ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጎረቤት በቀላሉ መገመት አያዳግተውም፡፡ እኔን በእጅጉ ያስደነቀኝ ሑመይድ ያቀረብልኝ ሃሳብ በእማማ አፀደ እንደ አማራጭ መፍትሄ ከመቅረቡም በላይ ስለ እርሱ ማንነት ጥያቄ ማንሳታቸው ነው፡፡ ከሁሉ ደግሞ  "ቢቻል አባትሽን ጨምሮ ሁሉንም ቤተሰብ የሚያስደስት የአንቺንም ዓላማና ፍላጎት የሚያሟላ.." ሲሉ ያቀረቡት ሃሳብ የሑመይድ ንግግር ኮፒ ፔስት መሆኑ ነው፡፡ ሑመይድ ያንን የጋብቻ ጥያቄ ሊያስገኝልኝ ከሚችለው ጥቅም ጋር አሰናስሎ ሲያቀርበው እጅግ ተጨንቄ እማማ አፀደን ለማማከር ወስኜ ነበር፡፡ ሆኖም በዝንጋታና በተለያዩ ያለመገጣጠሞች ሳላማክራቸው ቆይቼ በእንዲህ ያለ ሁኔታ የእርሱን ገለፃ የሚመስል ንግግር ከእርሳቸው ማድመጤን አጋጣሚ ነው ብሎ ማለፍ ከባድ ነበር፡፡ እኔ የውስጤን አግራሞት ሳዳምጥ እርሳቸው ፊቴ ላይ ያስተዋሉትን ድንጋጤ ታዝበው "ምነው ልጄ ደነገጥሽ? ጥያቄው ያስደነግጣል እንዴ?" አሉኝ አይናቸውን ከዓይኔ ሳይነቅሉ፡፡ ፈገግ እያልኩ "አይ ገርሞኝ ነው" አልኳቸው፡፡ "ምኑ ነው ያስገረመሽ?" አሉኝ ዜማ ባለው አነጋገር፡፡ እኔም ስለ ሑመይድ ማንነት፣ ስለሚከተለው የአኗኗር ዘይቤ፣ ስላቀረበልኝ የጋብቻ ጥያቄ፣ ስለገባልኝ ቃል፣ ያስገኘዋል ብሎ ስለሚያስበው ጥቅምና እኔ ስለሰጠሁት ምላሽ በዝርዝር ነገርኳቸው፡፡ ይህንኑ ነገር ከባለፈው ሽምግልና በፊትና ሑመይድ በነገረኝ ሰሞን ላማክራቸው አስቤ እንደነበርና በዝንጋታና በተለያየ ምክንያት እንደዘገየሁ ጨምሬ አስረዳሁ፡፡

እማማ አፀደ ሲያወጡ ሲያወርዱ ከቆዩ በኋላ "ለምክሩ እንኳን ብዙም አልዘገየሽ፣ ለሌላው ጊዜ ግን ወደ ልብሽ የመጣን ነገር አታሰንብቺው፡፡ ይህ ነገር እስከመቼ እንደዚህ ይቀጥላል? የሚለው ነገር ግን የእኔም የዘወትር ጭንቀት ነው፡፡ እንጃ...እስቲ ጸልዪበት ልጄ፡፡ እኔም ለማያልቅበት ጌታ ለመድኃኔዓለም እነግረዋለሁ" አሉ ሁለት እጃቸውን ዘርግተው በዓይኖቻቸው ሽቅብ እያንጋጠጡ፡፡ ቀጠሉናም "አየሽ...መድኃኔዓለም ያዘጋጀልሽ የዚህ ፈተና መውጫ ቀዳዳ ይሆን እንደሆን ማን ያውቃል? ብቻ አንድን ሃሳብ በቅጡ ሳያስቡበትና ሳይፀልዩበት በጥቁርም በነጭም መነጽር ማየት አይገባም፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ የሚበጀንን አናውቅም፡፡ ለውሳኔ የምንዘገይና የምንፈራ ስለሆንን ብዙ አጋጣሚዎችና መልካም ዕድሎች ያመልጡናል፡፡ በአላስፈላጊ ጥድፊያም ለበርካታ ወጥመዶች እንዳረጋለን፡፡ ስለዚህ ተረጋግቶ ብዙም ሳይዘገዩ፣ ተካልበውም ሳይጣደፉ ማሰብና አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይገባል፡፡ እስከዚያው ግን ይህን ሰው ሳትገፊውም ልብሽን ሳትሰጪውም በወዳጅነት አቆዪው፡፡ ይህ ነው የሚሻለው ልጄ" አሉና በብዙ የእናትነት ምክርና ምርቃት አሰናበቱኝ፡፡ ወደ ቤት ከገባሁ በኋላ አንድ ሰሞን አስጨንቆኝ የነበረው ይህ ሃሳብ አዲስ አጀንዳ ሆኖ አዕምሮዬን ያምሰው ጀመር፡፡ በሁኔታው ጊዜና ሥፍራ ሳልመርጥ እየደጋገምኩ በአጭሩም በረዥሙም እፀልያለሁ፡፡ የእማማ አፀደ ሃሳብ ይሁን፣ የጸሎቴ ውጤት ይሁን፣ ወይም ደግሞ ነፃ የመውጣት ጉጉቴ የፈጠረብኝ ተፅዕኖ ይሁን ባላውቅም የሑመይድ ሃሳብና ጥያቄ አዎንታዊ ጎኑ እየጎላብኝ ሲመጣ ይታወቀኝ ነበር፡፡

ከአራት ቀን በኋላ ታሪከኛው አባቴ በክፋቱ በመቀጠል ቤተሰቡን በሙሉ ያበሸቀ ሌላ ተጨማሪ ነገር አደረገ፡፡ አባቴ ያሉት ንብረቶችና የንግድ ሥራዎች ባልተፃፈ ሕግና በልማድ በሦሥቱ ቤተሰቦቹ ተከፋፍለው የተያዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በእኔ ስም የሚጠራ አንድ ባለ አራት ፎቅ ሕንጻ፣ ወንድሜ ፋይሰል የሚያስተዳድረው የቡና ላኪ ድርጅትና ሌሎች ሁለት ሱቆች በእኛ ቤተሰብ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ የቀሩትም ሁለት ቤተሰቦች እንዲሁ የሚቆጣጠሯቸው በቂ ቢዝነሶች አሏቸው፡፡ ታዲያ ሐጂ ሁሴን ሆዬ ቡና ኤክስፖርት ከሚያደርገው ድርጅቱ ለፋይሰል የሰጠውን ሙሉ ውክልና በማንሳት ሃላፊነቱንም ውክልናውንም ኢብራሒም ለሚባል ከሌላኛው ሚስቱ ለሚወለድ ልጅ ይሰጠዋል፡፡ ይህን የሰማው ወንድሜ እንዴት እንደተቃጠለ አትጠይቂኝ፡፡ በእርግጥም ፋይሰል ይህ ሥራ ብዙ ልምድ ያካበተበትና ትልቅ ደረጃ ያደረሰውም ነበር፡፡ በቂ ልምድና ችሎታ ለሌለው ሰው ሃላፊነቱን ማስተላለፉ የአባቴን በቀለኝነት ያመላከተ ነውረኛ አካሄድ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህን ሁሉም ቤተሰብ የተገነዘበው ሲሆን እኔ ደግሞ ይበልጥ ሃላፊነት በመውሰድ የተበሳጨ ወንድሜን አቅፌ አባበልኩት፡፡ "አይዞህ እኔ ሁሉንም አስተካክለዋለሁ" ስለው ከእቅፌ እየወጣ በመገረም ያየኝ ነበር፡፡ ይህን ጉዳይ ተሰብስበን በምናወራበት ምሽት ቤተኛው ሑመይድ "ጤና ይስጥልኝ...እንዴት አመሻችሁ?" እያለ ገባ፡፡ ከጥቂት የሰላምታ ግርግርና ጨዋታ በኋላ አንድ እያሉ ወጥተው እኔና እርሱ ብቻ ሳሎኑ ውስጥ ቀረን፡፡ "ምንድነው ኤፊ ችግር አለ? ሁላችሁ የሆነ ድብርት ውስጥ ትመስላላችሁ" አለ፡፡ በአጭሩ አባቴ ያደረገውንና ሰሞኑን እየሆነ ያለውን ነገርኩት፡፡ ጥቂት እንደ መተከዝ ብሎ ፈገግ አለና "ኤፊ ቆንጆ የመፍትሄ ሃሳብ አቅርቤልሽ ነበር...አንቺ ግን እምቢ አልሽ" አለ፡፡ ንግግሩ ከፈገግታው ጋር የፈጠረውን ሕብር ሳይ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ብሽቅ አረገኝ፡፡ ለአፍታም ቢሆን አስጠላኝ፡፡ ቀጠለናም "ኤፊ..ያን ጥያቄዬን ባትቀበዪውም እስቲ በሌላም መንገድ ቢሆን ችግርሽን እንድካፈል ፍቀጂልኝ" አለና እጁን ዘረጋልኝ፡፡ በጥርጣሬ ዓይን እያየሁትም ቢሆን እጄን ሰጠሁት፡፡ "አመሰግናለሁ ኤፊ" አለና ብድግ ብሎ እጄን ሳመና ተቀመጠ፡፡

                        (ይቀጥላል)

     --------- ማርያማዊት ገብረመድኅን ---------

2017 ዲሴምበር 24, እሑድ

ልዩ የግጥም መድብል

*አምላክን ሽንገላ*

ጾም የሚሏት ነገር የስጋ ፈተና
አስቸገረች በጣም ካቅም በላይ ሆና
የትሩፋት ስራ መሆኗ ተረስቶ
ሰው ፈጽሞ ጠላት ሸሸ ፊቱን ነስቶ
ወጣቱ አቃለላት ሻራት ቁርሱን በልቶ
ጌታ በቆሮንቶስ መጾሙን ዘንግቶ
"ኑሮ ራሱ ጾም ነው" ይላል አፉን ሞልቶ

ያልታደለ ትውልድ ሚሆነውን ያጣ
መረጠ ለያየው አካፈለው በዕጣ
👉ይሄ የጳጳስ ነው ያኛው🕺 የመነኩሴ
እንደት "ጹም" ይሉኛል ምን ነካወት ቄሴ!?
መጾም ከለከለኝ የጫት የሲጋራ የመጠጡ ሱሴ
እያለ መልሶ የአባን ግሳፄ

የሆነ ያልሆነ ምክንያቱን ደርድሮ
ጾሙን ይሽረዋል አንድ ስበብ ፈጥሮ

ከመልካሙ መንገድ ወተው ከመስመሩ
ያሻቸውን በልተው ካሻቸው ሊዳሩ
ያሻቸውን በልተው ጠጥተው ሊሰክሩ
ሄዱ ተጠራርተው ሊያድሩ ሲጨፍሩ

ወገኔ ተመለስ እባክህ ወድህ ና
ለጽድቅ የሚያበቃህ ምን ስራ አለህና
ደከመኝ ትላለህ ነፍስህ ባዶ ሆና
ጌታ ባለም ሲኖር መቸ ደላውና
"ኑሮ ጾም ነው"ምትል ሳይነካህ ፈተና

ወንድሜ ተመለስ ምልህን ስማ
እንድሆን ከፈለግክ ኑሮህ የተቃና
በገነት እንድትኖር ከቅዱሳን ጋራ
የስጋ ምኞትክን አሸንፈውና
አምላክን መሸንገል ማታለል ተውና
ነፍስህን አድናት ከሲኦል ፈተና
በጾም ጸሎት ትጋ በንጹህ ህሊና
ትዕዛዙን ጠብቅ በልብህ ጻፍና

✍ Written By Z

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

​አትውጡ ከመርከብ​
   ///////         //////

የአማኞች መኖሪያ የነፍሳት መዳኛ፤
ቤተክርስቲያ ናት መርከባችን ለኛ፤
ለሰማያት እየሩሳሌም ምሳሌ የሆነች፤
በክርስቶስ ደም ላይ የተመሰርተች፤
የሐዋርያት ስብከት ቤተክርስቲያን ነች፤
ወጀብ የማይገፋት ባለት የታነፀች፤
ሰባቱ ነፍሳትም ከጥፍት የዳኑት፤
ኖህን ተከትለው መርከቧበመግባት
በውስጥዋ ገብተው ፀንተ በመቆዬት፤
ዛሬም በመርከቧ ተነስቷል ማእበሉ ፤
አድነን እንበለው ፀጥ ይላል በቃሉ፤
መሰርቷ እሱነው ያለው በመቅደሷ ፤
ከመርከብ ሳንወጣ እጠብቅ በተስፋ፤
።።።።።.
ሐዋርያትም ከጌታ ጋር ሁነው በጉዞ ላይ ሳሉ፤
መርከብ ተናወጠች ተነሳ ማእበሉ
ወዳምላክም ጮሁ አድነን እያሉ
ስለመጥፍታችን እደት አይገድህም ብለው ተማጸኑ
ጌታም ተነስቶ ቃል ተናገራቸው
የታል እምነታችሁ ብሎ ገሰጻቸው
ጸተው እድቆሙ በአምልኮታቸው
ለደቀ መዛሙርቱ ትምህርት ሰጣቸው
እነሱም በርቱ ጸተው ተጋደሉ
እስከሞትም ድርስ ለቃሉ ታመኑ
አለምን በመዞር ወንጌል አስተማሩ
ሁሉን ንቀው ትተው እርሱን ተከተሉ
ከመርከብ ሳይወጡ ህዝቡን አስተማሩ
ከላይ ከአርያም ሀይልን ተቀበሉ


     ሙሉአለም // ወለተ ማሪያምsaramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 22, ዓርብ

ብሒለ አበው

ብሒለ አበው

*ጾም በአባቶች አንደበት*
❖ጾም የጤንነት እናት ፥ የፍቅር እኅት ፥ የትሕትና ወዳጅ ናት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

❖መመጽወትና መጾም ለነፍስ ሕይወትን ለሥጋ ጤንነትን ይሰጣል፡፡
አንጋረ ፈላስፋ

❖ያለ ጸሎት መንፈሳዊ ነኝ የሚል ሰው እሳት መካከል ገብቶ የሚጫወትን የእሳት እራትን ይመስላል፡፡
ማር ይስሐቅ

❖ጾም ጸሎት ከሥግደት ጋር ከሆነ የጦር ዕቃ ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

❖በወንድሙ ውድቀት የሚደሰት ሰው ተመሳሳይ ውድቀት ይጠብቀዋል፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም

❖በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ታገኝ ዘንድ ታገስ
ማር ይስሐቅ

❖ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው ፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኮልንም ከመናገር ይከልክል ፤
የሐዋርያት አለቃ የመጀመሪያይቱ የቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት ፫፥፲

❖አሁንስ ይላል እግዚአብሔር ፥ በፍጹም ልባችሁ ፥ በጾምም ፥ በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ፡፡
ነቢዩ ኢዩኤል ፪፥፲፪

❖ልብህ ይጫወት ዘንድ አፍህን ዝም አሰኘው ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ዘንድ ደግሞ ልብህን ዝም አሰኘው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ሳባ

<<<ጾምን ቀድሱ ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ>>> ኢዩ• ፩፥፲፬saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 20, ረቡዕ

አዳምና ሄዋን

☞ #አንብበው ካልጨረሱት አይጀምሩ!!!👈
 ↘መንፈሳዊ ጥያቄ ስለ አዳምና ሄዋን ጥያቄ ከነ መልሱ↙♻♻♻♻♻♻♻♻   /  ♻♻♻♻♻♻♻♻
1● እግዚአብሔር  አዳምን  ከፍጥረታት መጨረሻ
 ለምን ፈጠረው❔
2● እግዚአብሔር  ሌሎች ፍጥረታትን አስጎንብሶ
 ሲፈጥራቸው  አዳምን  አቅንቶ ለምን ፈጠረው❔
3● እግዚአብሔር  አዳምን የሚቆም ፣
የሚተኛ  አድርጎ ለምን ፈጠረው❔
4●  እግዚአብሔር ለአዳም ስንት  ሀብታትን ሰጠው❔
 ምንምን ናቸው❔
5●እግዚአብሔር  ሄዋንን ከአዳም  ከጎኑ አጥንት  ለምን ፈጠራት ❔ከግንባር ወይም ከእግር ለምን
 አልፈጠራትም❔

6● በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ❔
7●አዳምና ሄዋን  የእግዚአብሔርን  ህግ
 በማክበር  በገነት ውስጥ  ምን ያህል ጊዜ ቆዪ❔
8●  አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ
 ያሳታቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል❔

9●አዳምና ሄዋን ስንት ልጆች ነበራቸው ❔

10●አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ  አረፈ❔

↘አዳም ማለት ከመሬት የተፈጠረ  ያማረ
መልከ መልካም ማለት  ሲሆን የተፈጠረው
ከአራት  ባህርያተ  ስጋ ማለትም
👉 ከነፋስ
👉ከእሳት
👉ከውሀ
👉ከመሬት 
እንድሁም ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ማለትም ከልብ ፣ከቃል፣ከእስትፋስ 
የስነ ፍጥረት መካተቻ በሆነች በእለተ አርብ በ3 ስዓተ ከህቱም ምድር  ሚያዝያ  4 ቀን በምድር መካከል በምትገኘው  <ኤልዳ> በተባለች ስፍራ  የ30 አመት ጎልማሳ ሁኖ በእግዚአብሔር  አርአያነት መልክ ተፈጠረ፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት  1፣27   ፣ኩፉሌ 5፣6

   መልስ ፡-   
♻♻♻♻♻
1/አዳም ከፍጥረታት መጨረሻ ለምን ተፈጠረ?
☞መጨረሻ የተፈጠረበት ምክንያት  እግዚአብሔር  አምላካችን  "በጎ አምላክ"  ስለሆነ  በጎ አባት ለልጁ አብሮት  ከብት ያረባለታል  ፣ጥማጅ ያጠምድለታል፣ የኑሮ ጓደኛ ያመጣለታል አስቀድሞ የሚበላው፣የሚጠጣው፣የሚገዛውና  የሚነዳውን ፈጥሮለት በመጨረሻም በሁሉ ላይ ሊያሰለጥነው አዳምን ፈጠረው፡፡

2/ ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ  ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቅንቶ ፈጠረው?
☞ እሱ ገዥ እናተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነወ፣እንድሁም እናተ ፈርሳችሁ  በሰብሳላችሁ ትቀራላችሁ  እሱ ግን" ትንሳኤ  ሙታን " አለው ሲል አቅንቶ ፈጠረው፡፡

3/ አዳምን የሚቆም የሚተኛ አድርጎ ለምን ፈጠረው?
☞ መቆሙ- ሰማያዊ   ፣
☞መቀመጡ- ምድራዊ ነህ ሲለው ነው፣
☞የሚተኛ ፣ የሚነሳ  አድርጎ መፍጠሩ ደግሞ 
☞መተኛቱ- ሞቱን
☞መነሳቱ - ትንሳኤውን ሲነግረው ነው፡፡

4/ እግዚአብሔር  አምላክ ለአዳም  ስንት ሀብታት  ሰጠው? ምን ምን?

☞ሰባት ሀብታትን  የሰጠው ሲሆን እነሱም፡-
➊ሀብተ መንግስት (የማስተዳደር ሀብት
➋ሀብተ ክህነት  ( የመቀደስ፣የመባረክ፣መስዋዕት የማቅረብ
➌ ሀብተ ትንቢት (የመጣውን የመናገር
➍ሀብተ መዋኢ (የማሸነፍ
➎ሀብተ ሀይል  (የጥንካሬ
➏ሀብተ ፈውስ  ( የመዳን ፣የመፈወስ
➐ሀብተ ዝምሬ  (የመዝሙር

5/ ሄዋን ከአዳም ከጎኑ አጥንት  ወስዶ ለምን ተሰራች?ከግንባር ወይም ከእግር ለምን አልሰራትም?
☞ አዳም ለእንሰሳት፣ለሰማይ ወፎች ና ለምድር አራዊቶች   ሁሉ ተባእትና እንስት ሁነው ሲመጡ  ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡ነገር ግን ለአዳም እንደ ራሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር  ፡፡
"እግዚአብሔርም " ሰው ብቻውን  ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት   ልፍጥርለት አለ ፡፡ኦዘፍ 2፣18
ከዚያም  በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበትና ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ  ከጎኑ አጥንት    አንስት አንስቶ  ያችን ስጋ አልብሶ  የ15 አመት ቆንጆ  አድርጎ ፈጠራት ፣ኦዘፍ 2፣18

አዳምም ስሟንም "ሄዋን" አላት   ፣ሄዋን ማለት   "ሀይው" ከሚለው የግዕዝ  ቃል   የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም" የህያዋን ሁሉ እናት "ማለት ነው፡፡

ፈፅሞ ሳይተኛ ፣ፈፅሞ ሳይነቃ  ሄዋንን መፍጠሩ 
☞ፈፅሞ ተኝቶ ቢሆን ኑሮ  ምትሀት መስሎት
  ከየት መጣች ብሎ  ይፈራታል
☞ፈፅሞ ነቅቶ ቢሆን ኑሮ  ከአካሉ አጥንት
ሲነሳለት ያመው ነበርና  ይጠላት ነበር ፡፡

☞ከፍ አድርጎ ከግባር ዝቅ አድርጎ ከእግር   ያልሰራት   ግባርና እግር በልብስ  አይሸፈንም  ጎኑ ግን በልብስ ይሸፈናልና ተሰውራ ወይም ተሸፍና መኖር ይገባታል ሲል ነው፡፡
በሌላ በኩል ግንባር    የባለቤት እግር፣ የቤተሰብ ምሳሌ ነው ፡እሷም ከባለቤቷ በስተታች  ከቤተሰብ በላይ ሁና  ትኑር ሲል ነው ፡፡ 1ኛ ቆሮ  12፣19-22
እንድህ አድርጎ አዳምና ሄዋንን እስከ 40 ቀን ድረስ በተፈጠሩበት በማዕለ ምድር  በቀራንዮ አስናበታቸው
ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ   የሚሰቀልበት ቦታ ነውና  ከዛም  በ40ኛው ቀን አዳምን ብርሃን አልብሰው  ፣ብርሀን አጎናፅፈው፣የብርሀን ዘውድ አቀናጅተው  በብርሃን  ሰረገላ አስቀምጠው  ወደ ገነት አስገቡት፡፡
ሄዋንንም በ80 ቀኗ  እንደ አዳም  ባለ ክብር ወደ ገነት አስገቧት ፡፡ኩፉሌ ፈ  4፣12-15

አዳምና ሄዋን  ከእግዚአብሔር  የባህሪ ደግነት የተነሳ እርሱን ለማመስገንና ክብሩን ለመውረስ  ተፈጠሩ፡፡ ኩፋሌ  4 ፣3-5

እግዚአብሔር  ለአዳም ረዳት የፈጠረለት  ስለ ሶስት ነገሮች ሲል ነው፡፡
➊ዘርን ለማብዛት
➋ ከዝሙት እንድፀዳና
➌ረዳት እንድትሆነው ነው

6/ በገነት  ውስጥ 3 አይነት ዛፎች  ነበሩ
➊ ዕፀ መብል  -እንድበሉት  የተፈቀደላቸው ምግብ ነው

➋ዕፀ በለስ-እንዳይበሉ የታዘዙት ነው

➌ዕፀ ህይወት - እንደ  <እግዚአብሔር > ፈቃድ  የሚመገቡት የዘለዓለም  ህይወት  የሚሰጥ ምግብ ነው፡፡

ህግን ጠብቀው በገነት  ውስጥ 1000 አመት  ከኖሩ ብኀላ እፀ ህይወት  በልተው  ከገነት ወደ ሰማያዊ እየሩሳሌም  (መንግስተ ሰማይ ) እንድገቡ ለበለጠ  ክብርና ፀጋ  ሽልማት እንድሎናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን  ያለ ጊዜው  ሳቱ እንጅ 
'እፀ በለስ  ' እንዳይበሉ የታዘዙበት  ህግ  አዳም  ፈጣሪ   እንዳለው  ፣ለፈጣሪው  ያለውን ፍቅር  የሚገልፅበትና ተገዥነቱን የሚያሳይበት  ነው፡፡

7/ አዳምና ሄዋን  የእግዚአብሔርን ህግ በማክበር በገነት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ቆዩ?
☞አዳምና ሄዋን  ይህን ህግ በማክበር  በገነት ውስጥ ለ7 አመት ከ 2ወር ከ 17 ቀን  ኖሩ፡፡

8/ አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ ያሳታቸው  ሰይጣን ስም ማን ይባላል ?
☞አዳም በሳጥናኤል ተተክቶ መቶኛ ሁኖ  ከመላእክት  ጋር ተቆጥሮ ነበር   ሰይጣንም በእባብ አድሮ  አሳቻቸው  ጽድቃቸውም ተገፈፈ  አዳምና ሄዋንን በእባብ ላይ አድሮ  ያሳታቸው ሰይጣን ስም    ' ጋርድኤል     ይባላል፡፡

በመሆኑም አትብሉ የተባሉትን እፀ በለስ  ህጉን አፈረሱ ከገነት ተባረሩ  ፡ኦዘፍ 3፣1  ኦዘፍ  3 ፣22-24

9/ አዳምና ሄዋን  ስንት ልጆች  ነበሯቸው?
☞ ከገነት ከተባረሩ ብኀላ  በደብረ ቅድስት   ይኖሩ ነበር፡ 
አዳምና ሄዋን በሰሩት ሀጢያት  በመፀፀታቸውና በንሰሀ በመመለሳቸው  "እግዚአብሔር"  መሀሪ ነውና   5 ቀን ተኩል  ወይም 5500 ዘመን  ሲፈፀም  ሰው ሁኖ በመወለድ እንደሚያድናቸው ቃል  ኪዳን ገባላቻው ፡፡ኦዘፍ 3፣15-22

አዳም ግን የራሱን ደም በስንደ ለውሶ ሲሰዋ ጌታችን በአንተ ደም አይደለም  አለም የሚድነው በእኔ  ነው  ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡

አዳምና ሄዋንም በምድር ላይ ዘርን  ተክተዋል  ገብርኤል  ፣ሚካኤል  ፣ሩፋኤል  ወርቅ  ,እጣን,ከርቤ  አምጥተው ለአዳም ሲሰጡት     ወርቁን ማጫ ይሁንሽ ብሎ ሰጣት  ከዛም አዳምና ሄዋን  በ 30 ሩካቤ  60 ልጆችን  ወልደዋል

10/ አዳም በተፈጠረ በስንት አመቱ አረፈ?
☞ አዳም በተፈጠረ  በ930 አመቱ አረፋ   ፡አዳም ለሄዋን የሰጣት ወርቅ ለሴት ሰጠችው ሴትም ለኖህ አስተላለፈው   እጣኑንም  ኖህ  አፅመ አዳም  እያጠነ  ድኖበታል ፡፡
በአዳም ስም  በሀገራችን  የተሰሩ ቤተክርስቲያኖች ብዛታቸው  5 ናቸው
በአዳም ስም የተቀረፀው ታቦት ከሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያመጣው ፃድቅ አባት  'መልከአ እግዚአብሔር ' ይባላል፡፡እንድከበር ያደረገው ቅዱስና ሊቁ ያሬድ ማህሌት ነው፡፡

----------ምንጭ----------
             መጽሐፈ ኩፉሌ
              ኦሪት ዘፍጥረት
              ዜና አዳም
             ገድለ አዳም
             ዜና አበው
             ቅዱሳን ታሪክ
---------------------------------
ለአባ ህርያቆብ ፣ለቅዱስ ኤፍሬም ፣ለቅዱስ ያሬድ፣ለአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ  የተገለፀች እመቤታችን እኛንም በበረከትና በረድኤት  ተጎብኘን  ከልጇ ከወዳጇ ከመድኃኔታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ  ጋር ታማልደን አሜን

⛪ወስብሐት  ለእግዚአብሔር ⛪
⛪ወለ ወላዲቱ ድንግል ⛪
⛪ወለ መስቀሉ ክብር ⛪
           አሜን❤saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 18, ሰኞ

ቀንቷል መንገዴ/2/

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

saramareyama.890@gmail.comቀንቷል መንገዴ።


ቀንቷል መንገዴ (2)
ክርስቶስ አንተን በመዉደዴ.ቀንቷል 
መንገዴ
      ቀንቷል ኑሮዬ  (2)
     አንድዬ አንተን ተከትዬ ቀንቷል ኑሮዬ

አርፍያለሁኝ ዛሬ በቤቴ
ጭንቄ ተጥሎ ባንተ በአባቴ
በልቤ ዙፍን ንጉሴን ሹሜ
ተደላደልኩኝ በዝቶ ሰላሜ

      ቀንቷል መንገዴ (2)
     ክርስቶስ አንተን በመዉደዴ ቀንቷል መንገዴ

ከእንግዲህ አልዘምትም ሳልታጠቅ
ጌታዬን ሳልይዝ የፍቅሩን ስንቅ
እያለቀስኩኝ የዘራሁት
በሳቅ በደስታ ስበስብኩት
       
 

   ቀንቷል ኑሮዬ (2)
     ኢየሱስ አንተን ተከትዬ ቀንቷል ኑሮዬ

እሳቱ ዉሀ ተራራዉ ሜዳ
ለምለም ሆነልኝ ያምድረ በዳ
ከቁጥር በዝቷል ያንተ ስጦታ
እወድሀለዉ ልዩ ነህ ጌታ

      ቀንቷል መንገዴ (2)
     ክርስቶስ አንተን በመዉደዴ ቀንቷል መንገዴ

የለም በስሙ ያላተረፈ
ከእርሱ ጋር ወጥቶ ማን ተሽነፈ
የቅጥሬን ቋሚ ማንም አይነካ
ጌታ ስላለኝ ልቤ ተመካ
       
        ቀንቷል መንገዴ (2)
      ክርስቶስ አንተን በመዉደዴ ቀንቷል መንገዴ

ቀንቷል ኑሮዬ (2)
ኢየሱስ አንተን ተከትዬ ቀንቷል ኑሮዬ
አንድዬ አንተን ተከትዬ ቀንቷል ኑሮዬ
 ።።።።።።፡።።።።።
     
 ። አድርገህልኛልና።

አድርገህልኛልና በቸርነትህ አመሰግንሀለሁ እልል ልልል
ለዓለም ዓለም(2)አማኑኤል እገዛልሀለሁ መድኅኔዓለም
፦፦፦፦፦፦፦፦አዝ ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
የችግር አረንቋ  ፊቴ ተደቅኖ
ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈፅሞ  አራቀልኝ የልቤን ትካዜ
፦፦፦፦፦፦፦፦አዝ ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያየ
ጠላት ማሳረፊያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ
ካለኝ ነገር ሁሉ ባንተ ታምኛለው
፦፦፦፦፦፦፦፦፦አዝ ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ
በቀንም በሌሊት ሁሌ የሚያበራ
ምንከር ለባህሪሀ  እፁብ ያንተ ስራ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦አዝ፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አምላክ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባሃል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል
ድሀ ነኝ አልልም ሐብቴ አንተ ነህና
ማሰሮዬ ሞልቷል ሳይጎል እንደገና
 ።።።።።።፡፡።።።።

ባይኖቼ እፈልግሻለዌ

ባይኖቼ እፈልግሻለው
በሥዕ ሁል ጌዜ እጽናናለው
በልቤ ማርያም እያልኩኝ (2)
ዘመኔን ከመከራዳንኩኝ

..አዝ።።።።።።።

አይሰግድም ጉልበቴ ለሀማ
ስለኔ እመቤቴ ቁማ
አልፈራም እጠፍለው ብዬ
መስቀሉን በጀርባዬ አዝዬ

..አዝ።።።።

ሎዛናት የጎኔ ማረፊያ
አልሰጋም ከደጅዋ ሰተኛ
ማርያም ማርያም እያልኩኝ
በስሟ መች ተርቤ አወኩኝ

..አዝ።።።።

አናብስት ይታዘዙላታል
መላእክት ያገለግሏታል
እኔ ግን ሥዕሏን በደረቴ
ታቅፌው ተባርኳዋል ሕይወቴ

..አዝ።፡።

ልቤ ላይ ተስሏል ያው ፍቅሯ
እኖራለው ሁሌም በምልጃዋ
ሰቶኛል አድርጓት መመኪያ
ዘመኔን አልፋለው ከእርሷጋር
።።።።።።።።።።...

ትህትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም(፪)
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኔዓለም(፪)

ንጽህት ስለሆንሽ እመቤቴ(፪)
እንከን የሌለብሽ “
የፍጥረታት ጌታ “
በአንቺ ያደረብሽ “
የድንግል መመረጥ “
ዜናው አስገረመኝ “
እሳቱን ታቀፈች “
የማይቻለውን “

ምርኩዜ ልበልሽ እመቤቴ
ጥላ ከለላየ “
ጋሻዬ አንቺ ነሽ “
ለእኔ መመክያዬ “
በአለም እንዳልጠፋ “
ህይወቴ ምርሮብኝ “
እንደ ወይን አጣፍጭው “
ማርያም ድረሽልኝ “

የምስራቅ ደጃፍ ነሽ “
የሁላችን ደስታ “
እሙ ለፀሃይ ፅድቅ “
የሁሉ ጠበቃ “
ድንግል የድል አክሊል “
ድንግል የፅድቅ ሥራ “
ድንግል መሰላል ንሽ “
የተዋህዶ ተስፋ ‘’
 ።።።።።።።።።።።።።
ባማረ ቅኔ በተወደደ
ህይወት ለሠጠን እየታረደ
የእግዚአብሔር ልጅ መድኃኒታችን
ጠርቶህ አይጠግብም አደበታችን

አዝ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡//
 የተሰዋው በግ የሚፈሰው ደም
አልሆነምና ድህነት ለአለም
የፍቅር አምላክ ወደኛ መጣ
ፍጥረት በደሙ ከሲኦል የሚሰዋወጣ

አዝ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡//
ከተናገረ ይፈፅመዋል
ሀሰት አያውቅም ሁሉም ያምነዋል
ሞትን በሞቱ ሽሮ አሸነፈ
በልባችን ላይ ፍቅሩ ተፃፈ

አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡//
ያሁሉ እንባ ያሁሉ ለቅሶ
ከሁላችን አይን ፍፁም ታብሶ
ፍፃሜ አግኝቶ መከራችን
የድል ሆነልን ምስጋናችን

አዝ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡//
በአዲሱ ስም አሮጌው አልፏል
በሁለተኛው ስም ህይወት አውጇል
ከፍከፍ ይላል ይሰዋል ገና
ባማረ ቅኔ ባዲስ ምስጋና

ዲ/ን  ወንደሰን በላይ
 ።።።።።።።።።።።።።።።

    ©ዛሬም አለሽ በልቤ
ዛሬም አለሽ በልቤ (3)
ድንግል ሆይ ውለታሽ አይጠፋም ከሃሳቤ
     . አ..ዝ.
እንደ ኃጢአቴ ብዛት እንደበደሌማ
የጥልቁ ሰንሰለት ስያንሰኝ ነው ጨላማ
ግን ያንቺ ሆንኩና ሁሉንም አለፍኩት
ያንን የሞት ባሕር በምልጃሽ ቀዘፍኩት

       ።አ...ዝ።

አርፏል ልቤ ባንቺ ባዛኝቷ ማርያም
ውስጥል እያፈሰሰፍቅር እና ሰላም
ህመሜን ቢያስረሳኝ የውዳሴሽ ቃና
እመቤቴ እላለሁ ዛሬም እንደ ገና
     ።አዝማች።

እናታችን ጽዮን ሰው ሁሉ ይልሻል
ዳዊት በበገና ያመሰግንሻል
የሴቦን ነገስታት ለክብርሽ ዘመሩ
የማትፈርሺ መቅደስ የእግዚአብሔር ሃገሩ

        ።አዝማች።

እጅግ ብዙ ነገር አድርገሽልኛል
ይቅር ባዩ ልጅሽ በፍቅር አይቶኛል
እኔስ እኖራለሁ ድንግል ባንቺ ጥላ
ጨለማን አላይም ከእንግዲህ በኋላ

      ።በዘማሪ ዳ/ን
 ልዑል-ሰግድ ጌታቸው
 ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
    ።ሐዋርያው መነኩሴ።
ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡት ሥላሴ/2/
ዋስ ጠብቃ ሆኗል ትክልዬ ለንፈሴ

 ዳሞት ትናገረው ያንተ ሕዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ፀሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሀይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መላዕክት/2/
            ..አዝ..
ብራናው ሲገልፀ ገደል ትክለሐይማኖት
ከሰው ልጂ ልቦና ይወጣል አጋንት
የቅዳሴው እጣን ሲዎጣ ከዋሻው
ምድረን የባርካል ጸሎተ ምህላው/2/
                 ..አዝ...
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በመስቀል
ጭንጫው ፍራረስ የዘራኸው ወንጌል
ትላንት የዘራኸው ዛሬ ከኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተምረናል/2/
                ..አዝ...
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ሰተመፀን
ቅዱስ ቅዱስ በለህ ስታመስግን
 ቸርነትን ትትናህ ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አደርጎ ሰናይ አደርስን/2/
               ..አዝ..
ዛፉ ሲመነገል አምፀሎትላከ ተከልዬ
ሞቶሎሚም ሲያፈር ቶቅ ሰው ነኝ አለ
ትክልዬ ፀሎቱ በዙ ነው ሚስጥሩ
6ክንፍ አወጣ ቢቆረት አንደ እግሩ/2/

።።።።።።።።።።።።።።
♥ሰብህዎ♥
።።።።።።።።
ስብህዎ ለአምላክነ ሀሌሉያ ለእግዚአብሔር (2)
በሰማይ በምድር (3) 2

አዝ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ሰማይን ያለ ምሰሶ አጥብቋል በቃሉ
መሬትን በውሆች መሐልሁሉ መስርቷል እነሆ
ይታያል ያበራል ጌታ ዛሬም በስራው
ምስጉን ነው ሰራዊት  ያመሰገነው

አዝ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ምህረቱ ይቅርታው ብዙ ከወሰንታላቅ የሰፋ
አባት ነው ብርቱ መጠጊያ የሰው ልጆች ተስፋ
መጋቢ ለፍጥረት ዓለም  ባለ ጸጋ
ያብባል ይለመልማል እሱን የተጠጋ

አዝ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ተመስገን/2/ይላል የተጎበኘ ሰው
ከጥፋት ከጉስቁልና ከሞት የመለሰውየጌታ
ይቀባል ከታች አንስቶ ከእረኝነት ቦታ
ይቅርታ ጸጋው ብዙ ነው ምህረቱ

አዝ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
መላእክት በላይ በሰማይ ይዘምሩለታል
ዳዊትም ከበገናው ጋር ለቅኔ ተነስቷል
በምድርም እኛ ልጆቹ እንበል ንሴብሆ
ይገባል ለአምላከ እስራኤል ውዳሴ አምልኮበመስቀል
።።።።።።።።።
‬: በፍቅር ተስቦ
†††††††††††
በፍቅር ተስቦ ወረደ ለኛ ሲል
የፍቅሩን ፍፃሜ ገለፀ
ለኛ ያላረገዉ ከቶ ምን አለና
አፋችን ዝም አይበል እናቅርብ ምስጋና
- - - አዝ - - -
ደስ ይበለን......... ሰማያትን ቀዶ
ደስ ይበለን......... ታላቁ አባታችን
ደስ ይበለን......... የዘመናት ንጉስ
ደስ ይበለን......... እየሱስ ጌታችን
ደስ ይበለን......... የኤፍራታዉ ህፃን
ደስ ይበለን......... በዳዊት ከተማ
ደስ ይበለን......... ተወልዶ ማደሩን
ደስ ይበለን......... ምስራች ተሰማ
- - - አዝ - - -
እንዳንተ ያለ......... በኃጢአያት ዉስጥ ወድቀን
እንዳንተ ያለ......... ስኖር ተጎሳቁለን
እንዳንተ ያለ......... አምላክ የኔ ጌታ
እንዳንተ ያለ......... ከሞት ዉስጥ አዳንከን
እንዳንተ ያለ......... ዝናዉን አዉረዉ
እንዳንተ ያለ......... ለአህዛብ ሁሉ
እንዳንተ ያለ......... እንደ እግዚአብሔር ያለ
እንዳንተ ያለ......... ማንም የለም በሉ
- - - አዝ - - -
ደስ ይበለን......... ወረደ ወምድር
ደስ ይበለን......... ሰላሙን ሊሰጠን
ደስ ይበለን......... ሰላም ለናንተ ይሁን
ደስ ይበለን......... ብሎ ሰበከልን
ደስ ይበለን......... በመሰስቀል ተሰቅሎ
ደስ ይበለን......... እኛን የተቤዘን
ደስ ይበለን......... ከሲኦል እስራት
ደስ ይበለን......... በፍቅሩ የ ፈታን
- - - አዝ - - -
ሃሌ ሉያ......... ምስጋና በሰማይ
ሃሌ ሉያ......... ምስጋና በምድር
ሃሌ ሉያ......... ሁሉን ቻይ ለሆነዉ
ሃሌ ሉያ......... ለቸሩ እግዚአብሔር
ሃሌ ሉያ......... ሃሌ ሉያ ለእርሱ
ሃሌ ሉያ......... ለነፍሳችን ጌታ
ሃሌ ሉያ......... ዝማሬን አናቅርብ
ሃሌ ሉያ......... ከጠዋት እስከ ማታ

2017 ዲሴምበር 16, ቅዳሜ

ጸሎት ዘዘወትር

ጸሎት ዘዘወትር
           
አአትብ ገጽየ ወኲለንታየ በትእምርተ መስቀል፣
አሜን።

በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ :
በቅድስት ሥላሴ፣እንዘ ኣአምን ወእትመኃጸን፣እክህደከ ሰይጣን፣በቅድመ ዛቲ እምየቅድስት ቤተክርስቲያን፣
እንተይእቲ ስምእየ ማርያም ጽዮን፣ለዓለመ ዓለም፣አሜን።
           

ነአኩተከ እግዚኦ ወንሴብሓከ፣ንባርከከ እግዚኦ ወንትአመነከ ፣ንስእለከ እግዚኦ ወናስተብቁዓከ ፣
ንገኒ ለከ እግዚኦ፣ ወንትቀነይ ለስምከ ቅዱስ።ንሰግድ ለከ፣ ኦ ዘለከ፣ ይሰግድ ኩሉ ብርክ ፣ወለከ ይትቀነይ ኩሉ ልሳን።
አንተ ውእቱ ኣምላከ ኣማልክት፣ወእግዚኣ ኣጋእዝት ፣ወንጉሰ ነገስት፣ኣምላክ አንተ ለኩሉ ዘሥጋ ፣ወለኩላ ዘነፍስ፣
ወንጼውኣከ ንሕነ፣ በከመ መሃረነ ቅዱስ ወልድከ፣
እንዘ ይብል አንትሙሰ ሶበ ትጸልዩ ከመዝ በሉ።
                 

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፣
ትምጻእ መንግሥትከ ፣ወይኩን ፈቃድከ ፣
በከመ በሰማይ ፣ከማሁ በምድር፣
ሲሳየነ፣ዘለለ ዕለትነ፣ሃበነ ዮም።
ኅድግ ለነ፣አበሳነ ወጌጋየነ፣
ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ።
ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፣
ኣላ አድኅነነ ወባልሐነ፣እምኩሉ እኩይ፣
እስመ ዚኣከ፣ይእቲ መንግሥት፣ኃይል ወስብሐት፣
ለዓለመ ዓለም፣አሜን።
                     

በሰላመ፣ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ፣
ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
ድንግል ብኅሊናኪ ፣ወድንግል በሥጋኪ።
እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ።
ቡርክት አንቲ እምአንስት፣ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ።
ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር
ምስሌኪ።
ሰአሊ ወጸልዪ ምሕረት በእንቲኣነ፣
ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ፣
ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
             

ጸሎተ ሃይማኖት

ነአምን በአሐዱአምላክ እግዚአብሔር አብ፣አኃዜ ኩሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ፣ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ወነአምን በአሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ፣
ወልደ አብ ዋሕድ ዘህልው ምስሌሁ ፣እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም።ብርሃን ዘእምብርሃን አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን
ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ።
ዘቦቱ ኩሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ። ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት ተሰብአ ወተሰገወ እምመንፈስ
ቅዱስ ወእም ማርያም እምቅድስት ድንግል ኮነ ብእሴ ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ። ሐመ ወሞተ ወተቀበረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት
በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻህፍት ዓርገ በስብሓት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኮንን ሕያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ።
ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረጸ እም አብ
ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነብያት።
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላእለ ኩሉ ጉባኤ ዘሓዋሪያት። ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየት ሓጢኣት ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም። ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት
ፍጹም ምሉዕ ሰማያት ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
ንሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ ኣቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስከ ቅዱስ ማኅየዊ እስመ መጻእከወአድኃንከነ።
                 
እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐተ ሰግደተ። (ሰልስተ ጊዜ በል) እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት። እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ። እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር።
መስቀል ኃይልነ፡ መስቀል ጽንዕነ፡ መስቀል ቤዛነ፡ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክሕዱ ንሕነሰ ኣመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ።
                   

ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ (ሰለስተ ግዜ በል።) ስብሐት ለእግዘትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፡ ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስቶስ በምሕረቱ ይዘከረነ። አመ ዳግም ምጽአቱ ኢያስተኅፍረነ። ለሰብሖተ ስሙ ያንቅሀነ ወበአምልኮቱ ያጽንአነ እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
አዕርጊ ጸሎተነ፣ ወአስተሥርዪ ኩሎ ኃጢአተነ ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ ለዘአብልዐነ ዘንተ ኅብስተ ወለዘአስተየነዘንተ ጽዋዓ ወለዘሠርዐ ለነ ሲሳየነ ወአራዘነ
ወለዘተዐገሠ ለነ ኵሎ ኃጢአተነ ወለዘወሀበነሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ ወለዘአብጽሐነእስከ ዛቲ ሰዓት። ነሀብ ሎቱ ስብሐተ ወአኰቴተ ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል። ወለመስቀሉ ክቡር ይትአኰት ወይሰባሕ ስሙ ለእግዚአብሔር ወትረ ብኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት።
                 

ሰላምለኪ እንዘ ዝሰግድ ዝብለኪ። ማርያም እምነ ናስተዘቊዐኪ። እምአርዌ ነዓዊ ተማህፀነ ብኪ። በእንተሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ። ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።
                 

ጸሎት እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ ኣምላክ።
ታዐብዮ ነብስየ ለእግዚኣብሔር። ወትትኃሠይ መንፈስየ በኣምላኪየ ወመድኃንየ፤ እስመርእየ ሕማማ ለኣመቱ።
ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትዉልድ። እስመ ገብረ ሊተ ኃይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ። ወሣህሉኒ ለትውልድ ትዉልድ ለእለ ይፈርህዎ። ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፡ ወዘረዎሙ ለእለ የዐብዩ ሕሊና ልቦሙ፡ ወነሠቶሙ ለኃያላን፣ እመናብርቲሆሙ። ኣዕበዮሙ ለትሑታን፡ ወኣጽገቦሙ እምበረከቱ ለርኁባን፡ ወፈነዎሙ ዕራቆሙ ለብዑላን ወተወክፎ ለእስራኤል ቍልዔሁ፡ ወተዘከረ ሣህሎ ዘይቤሎም ለኣበዊነ ለኣብርሃም ወለዘርኡ እስከ ለዓለም።

ሉቃስ ፩፡፵፮-፶፭።

ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፡
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም ኣሜን።saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 15, ዓርብ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት


 ቅዳሜ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምስጋና።

፩. ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ።  ጌታን በመካከል እጅ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ነሽ። ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል።

፪. ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ። ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ ገናንነትሽን እናመሰግናለን እናደንቃለን። እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምስጋና እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን በማህጸንሽ ፍሬ ተገኝቷልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፫. እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና የልዑል ኃይልም ጸልሎሻልና። ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶ ከኃጢያት ያዳነን የአብ ልጅ ቃልን በውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬ ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ የተወለደ ከዓለም በፊት የነበረ አንዱ ቃል ራሱን (ባሕርዩን) ሰወረ። ካንቺም የተገዥን (ሰውን) አርአያ ነሣ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭. አምላክን ያለርኩሰት የወለድሽው ሆይ የምድር ሁለተኛ  ፀሐይ ካንቺ ወጥቶልናልና። እንደነቢያት  ትንቢትም ያለዘርና ያለመለወጥ ወለድሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮. ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ። ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆነ መጥቶ ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘላለም የሚኖር የአብ ልጅ እርሱ መጥቶ ከኃጢአት አድኖናልና።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯. የንጉስ ክርስቶስ እናቱ ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ በሆነ ምሥጢር (ተዋህዶ) አማኑኤልን ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰ እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ። በሁሉ በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት ማህፀንሽ ተሸክመሽዋልና። እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰው በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ ሆንሽን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፱. የተባረክሽ ንጽህት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ እንሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ሁሉ በይቅርታው ብዛት ያድን ዘንድ ካንቺ ወጣ (ተወለደ) ፈጽመን እናመስግነው። ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲. ያለርኩሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። የዓለም ሁሉ ምክበርያ ጽዋ  ነሽ። የማትጠፊ ፋና ነሽ የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ። የቅዱሳን መደገፊያቸው (መጠጊያቸው) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ። ቸር አዳኛችን ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን ፈጽሞ ይቅር ይለን ይምረን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
አ           አ         ን
   ሜ         ሜ       ሜ
        ን          ን        ን
💙💚💖💞💓💙💜💖💞❤️saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 14, ሐሙስ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ዓርብ

«ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክዘይትነበብ በእለተ ዓርብ»

ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማኅፅንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ያለ ርኩሰት አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ እውነተኛ ፀሐይ ከአንቺ ወጣልን /ጌታ ተወለደልን/ በክንፈ ረድኤቱም አቀረበን እርሱ ፈጥሮና ልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ የብርሃን እናት ነሽና አንቺን ብቻሽን በክብር በምስጋና እናገንሻለን የተባረክሽ አንቺ ከመላእክት ትበልጫለሽ ከደቂቀ አዳምም ትበልጫለሽ ከአሳቦች ሁሉ ትበልጫለሽ ገናንነትሽን መናገር የሚቻለው ማነው አንቺን የሚመስል የለምና ማርያም ሆይ መላእክት ያገኑሻል ሱራፌ ልም ያመሰግኑሻል በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማኅጸንሽ አድርዋልና ሰውን የሚወድ ወደ እርሱ አቀረበን ክብር ምስጋና ያለው እርሱ የእኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የደናግል መመኪያቸው አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያምሆይ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ከዓለም በፊት የነበረ እርሱ ሰው ሆኖዋልና ከአንቺ የተወለደ ሥጋችንን ነሣ/ተዋሐደ/ መንፈስ ቅዱስንም ሰጠን በቸርነቱ ብዛት መሳዮቹ አደረገን ጸጋንና ክብርን ከተቀበሉ ብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ አምላክን የወ ለድሽ ማርያም ሆይ ልዑል እግዚአብሔር ያደረብሽ /የከ ተመብሽ/ ረቂቅ ከተማ ነሽ በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ የሚኖረውን ጌታንበመኻል እጅሽ ይዘሺዋልና በቸርነቱ ብዛት ስጋዊ ፍጥረትን ሁሉ የሚመግብ እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ። ይኸውም ሁሉን የሚያድን አምላካችን ነው ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ እርሱ ፈጥሮናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት የማኅፀንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድንዋልና። ከእኛም እርግማንን አጠፋልን። በመካከላችንም ሆኖ በመስቀሉ አስታረቀን በልዩ ትንሳኤውም ሰውን ዳግ መኛ ወደ ገነት መለሰው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለ ደች ናት። ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት። ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ አሰምታ ትናገር ነበርመልአኩ ቅድስት ድንግል ሆይ ሰላምታ ይገባሻል ብሎ አክብሮከነገረኝ ነገር በቀር ምንም ምን ሌላ የማውቀው ነገር እንደሌለኝእግዚአብሔር ያውቃል አለች። የማይቻለውን ቻልሽየማይወሰነውንና ምንም ምን የሚወስነው የሌለውን ወሰንሽ።በክብር ሁሉ ላይ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ምስጋናሽ ይበዛል ክብርሽፍጹም ነው። የአብ ቃል ማደሪያ ሆነሻልና የክርስቲያን ወገኖችምዕመናንን የምትሰበስቢያቸውና ማሕ የዊ የሚያድኑን ለሆኑለሥላሴ ሰጊድን/መስገድን/ የምታስተ ምሪላቸው ሰፊ መጋረጃሙሴ ያየውን የእሳት አምድ የተሸከ ምሽ አንቺ ነሽ ይኸውምመጥቶ በማሕፀንሽ ያደረው የእግዚ አብሄር ልጅ ነው።ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆንሽ። ዘጠኝ ወርበማሕፀንሽ ተሸከምሽው ሰማይና ምድር ለማይወስኑትየታመንሽ አንቺ ነሽ። ከምድር ወደ ሰማይ ለማ ረግ መሰላልሆንሽ። ብርሃንሽ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል።

ቅዱሳን በፍጹምደስታ ያዩት ኮከብ ከአንቺ የተወለደ ምስራቅ አንቺ ነሽ።ይኸውም በጻዕርና በምጥ ትወልድ ዘንድ በሔዋን የፈረደባትነው። አንቺ ማርያም ግን ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽየሚል ቃልን ሰማሽና መጥቶ ያዳነን የፍጥረት ሁሉ ገዥ የሆነንጉሥን ወለድሽልን መሐሪ ነው ሰውንም ወዳጅ ነው።ስለዚህማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነውጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስይበልሽ እያልን መልአኩ ገብርኤል እንዳመሰገነሽእናመሰግንሻለን።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ለዘለዓለሙ አሜን ቅድስት ሆይ ለምኝልን።saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 13, ረቡዕ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሐሙስ

።ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ሐሙስ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።
።።።።።።።።።።።።።።።።።

፩ ርኵሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎኟ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች፥ የአብ ቃል በርሷ ሰዉ ሆኖዋልና እሳተ መለኮት /የመለኮቱ/ ባሕርይ አላቃጠ ላትምና። ከወለደችዉም በኋላ ድንግልናዋ አልተወለወጠምና፥ ሰዉ ቢሆን መለኮቱ አልተወለጠም። በእዉነት አምላክ ነዉና በእዉነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ፥ ሁላችን እናገንሻለን። ይቅርታሽ ለሁላችን ይሆን ዘንድ ነዉና። ሔዋን እንጨት በልታ ባደረገችዉ ዓመፅ በባሕርያችን ያደረ የቀድሞዉ እርግማን በእርሷ የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። ስለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ። ዳግመኛ ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን። ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን። ይኸዉም እኛን ስለ መዉደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ሥጋዉ፣ ክቡር ደሙ ነዉ። ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረዉን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለዉ ምን ልቡና ነዉ) መናገር የሚቻለዉ ምን አንደበት ነዉ) መስማት የሚቻለዉ ምን ጆሮ ነዉ) ሰዉን የሚወድ እግዚአብሔር አንድ ብቻ የሆነ አምላክነቱ ሳይለወጥ ከዓለም በፊት የነበረ የአብ ቃል ከአብ ዘንድ መጥቶ ልዮ ከሆነች እናቱ ሰዉ ሆነ፥ ከወለደችዉ በኋላም ድንግልናዋ አልተለወጠም። ስለዚህም አምላክን የወለደች እንደሆነች ታወቀች። የእግዚአብሔር የጥበቡ ስፋት ምን ይጠልቅ) በሳዕር በምጥ በልብ ጋር ትወልድ ዘንድ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት መገኛ ሆነች፥ ከባሕርያችን እርግማንን የሚያፋልንንም ያለ ወንድ ዘር ወለደችልን። ስለዚህም ሰዉን የምትወድ ሆይ ክብር ላንተ ይገባል፣ ቸርና የሰዉነታችን መድኃኒትም ነህ እያልን እናመስግነዉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።


፫ያለ ወንድ ዘር አምላክን የወለደች ድንግል የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይደንቅ) ለዮሴፍ የታየዉ መልአኩ «ከርሷ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደዉ ያለ መለወጥ ሰዉ የሚሆነዉ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ´ ብሎ መስክሯልና። ማርያም የዚህ ደስታ ዕጽፍ የሆነ እርሱን ወለደችዉ። መልአኩ «ልጅ ትወልጃለሽ፣ ስሙም ዐማኑኤል ይባላል´ አላት። ትርጵሜዉም፣ እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ሆነ ማለት ነዉ። ዳግመኛ ወገኖቹን ከኃጢአታቸዉ የሚያድናቸዉ ኢየሱስ ይባላል። በችሎታዉ /በኃይሉ/ ያድነን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለም ክብር ይግባዉና ሰዉ የሆነ እርሱን አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አዉቀነዋልና። ልዮ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችዉ፥ ልደቱንም ዘር አልቀደመዉም፣ በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠ ዉም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ፣ ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ሰገል ሰገዱለት አምላክ ነዉና ዕጣን አመጡለት፣ ንጉሥም ነዉና ወርቅ አመጡለት ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለዉ መዳኛችን ለሆነ ሞቱም ከርቤ አመጡለት። ቸርና ሰዉን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነዉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬ ከአዳም ገÖን አንዲት ዐፅም መንሣት ምን ይደንቅ) ከርሱ ሴትን ፈጠረ፥ የሰዉ ፍጥረትንም ሁሉ ፈረ። ጌታ የአብ ቃል ተሰጠ ከልዮ ድንግልም ሰዉ ሆነና ዐማኑኤል ተባለ፣ ስለዚህ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን ከተወደደ ልጅዋ ታማልደን ዘንድ። በቅዱሳንና በሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ ዘንድ ቸር ናት ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋለችና፣ ለነቢያትም ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና፥ ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ሰማዕታትና ምእመናንም የተጋደሉለት የጥበቡ ጸጋ ብዛት የማይታወቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዷል የይቅርታዉን ብዛት መርምረን እንወቅ /እንፈልግ/ መጥቶ አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ ብሎ ለዳዊት በእዉነት ማለ አይጸጸትም። ሳድቅ እርሱ /ዳዊት/ ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ፥ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈጸመ። ከዚህም በኋላ «እነሆ በኤፍራታ ሰማነዉ ብሎ በመንፈስ ቅዱስ አሰምቶ ተናገረ´ ይህቺዉም፣ ዐማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወለድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት። ዳግመኛም ከነቢያት አንዱ ሚክያስ አንቺ የኤፍራታ ክፍል የሆንሽ ቤተ ልሔም ከይሁዳ ነገሥታት መሳፍንት አገር አታንሺም፥ ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸዉ ንጉሥ ካንቺ ይወጣልና። ከዛሬ ጅምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከቸር አባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ምሥጋና ስለተገባዉ ስለ ክርስቶስ በአንድ መንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተናገሩ የነዚህ የሚክያስና የዳዊት ነገር ምን ይረቅ) ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮ ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ጠላቶቹ በተነሠሡበት ጊዜ ከቤተ ልሔም ምንጭ ዉኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ። የጭፍሮቹ አለቆች ፈጥነዉ ተነሠሡና በጠ ላቶቹ ከተማ ተዋግተዉ ሊጠጣ የወደደዉን አመጡለት። ሳድቅ ዳዊት ግን ጨክነዉ ሰዉነታቸዉን ስለ እርሱ ለጦርነት ለሞት አሳልፈዉ እንደሰጡ ባየ ጊዜ ያን ዉኃ አፈሰሰ ከእሱም አልጠጣም። ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠ ረለት። ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በዕዉነት ናቁ፣ ደማቸዉንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ። እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።


፯ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዮን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማሕፀን አደረ። ከብቻዋ ከኀጠአት በቀርም እንደኛ ሰዉ ሆነ፣ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩለት በቤተ ልሔም ተወለደ። ፈጽሞ አዳነን ወገኖቹም አደረገን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።saramareyama.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 12, ማክሰኞ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲት አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ረቡዕ

♥የረቡዕ ውዳሴ ማርያም♥
♥♥♥♥♥♥♥♥saramareyama.890@gmail.com

    የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ የሰማይ ሠራዊት (መላእክት) ንዕድ ነሽ ይላሉ። ሙሸራው ንጽሕ የሆነ ንጹሕት የሰርግ ቤት ናት። አብ በሰማይ አይቶ አንድ ልጁን ላከው በአንችም ሰው ሆነ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር(ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ የሆነ ነገርን ተናገሩልሽ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ። ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ ፤ ማርያም ሆይ  ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል። ካንቺ ስለተወልደውም ይሰግዱለታል ያመሰግኑታልም ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የዝናብ ውሃ የታየብሽ የእውነት ደመና አንቺ ነሽ። አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይል ጋረደሽ ፤ ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን የወለድሽልን መጥቶም ከኃጢአት አዳነን። ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው ወደእኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርከን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርካት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ጸጋን አገኘሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይልም ጋረደሽ (ጸለለብሽ) ማርያም ሆይ በእውነት ቅዱስ ወለድሽ ዓለምን ሁሉ የሚያድን መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

አንደበታችን የድንግልን ሥራ ያመስግናል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት አገር ከእርስዋ ስለተወለደ አምላክን የወለደች ማርያምን ዛሬ እናመስግናት አሕዛብ ኑ ማርያን እናመስግናት። እናትና ድንግል ሁለቱንም ሆናለችና። ርኩሰት የሌለንሽና የአብ ቃለ መጥቶ ካንቺ ሰው የሆነ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ ነውር የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለንሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ። ስለቀደመ ሰው አዳም ሁሉተኛ አዳም የሆነ የክርስቶስ ማደሪያው የምትናገሪው  ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ። በክቡር ጌጥ ሁሉ ያጌጠ እርሱ መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንጽሕት የሠርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ የመለኮት እሳት (ባሕርይ) ያላቃጠለሽ ዕፀ ጳጦስ ሆይ ደስ ይበልሽ። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን ሰማያዊ መለኮትን በሥጋ የተሸከምሽ ገረድና እናት ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ።  ስለዚህ ንጹሓን ከሆኑ መላእክት ጋር በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተን እናመስግን በሰማይም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ዕርቅ ይሁን እንበል ክብርና ምስጋና ጌትነት ያለው እርሱ አንችን ወድዋልና ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፣ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማይት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ተሸከመቸው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣልች፣ ከሱራፌልም ትበልጣልች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና።  የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህች ናት። ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው። በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ከድንግል ሰው ሆኗዋልና። ኑ ይህን ድንቅ እዩ። ስለ ተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ። ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና። ቃል ተዋህዷልና። ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግይ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለት እናመስግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እርስዋ መሰከረ ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ ምሥራቅ አየሁ አለ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ኆኅትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት። እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ ቀድሞ በድንግልና ኖራለችና። መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለጅሽ ሆይ የማኅፅንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፥ አንቺ ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ የእውነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖር ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ለአንቺ ይገባል። የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ። ከሰው ጋርም ተመላለሰ። መሓሪ ይቅር ባይ ሰውን ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2017 ዲሴምበር 11, ሰኞ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ዘይትነበብ በዕለተ#ሰሉስ#

የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።saramareyama.890@gmail.com
የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም
መሠረት እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል
በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን ሰው ከሆነ በኋላም
ፍጹም አምላክ ነው
ስለዚህም በድንግልና ወልደችው። ድንቅ የሆነ የመወለድዋ
ችሎታ የማይመረመር ሊነገር የማይችል ነው። ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
በእርሱ ፈቃድ ከአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ መጥቶ አዳነን።
በድንግልና ፍጽምት የሆንሽ ማርያም ሆይ የድንግልናሽ
ምሥጋናና ክብር ታላቅ ነው እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ቢሆን
ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ የእግዚአብሔር መላእክት
ሲወጡባት ሲወርዱናት ያያት መሰላል አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
ሙሴ በነደ እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅ አንቺ ንሽ ይኸውም
መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረው የእግዚአብ
ሔር ልጅ ነው የመለኮቱ እሳትነት ሥጋሽን አላቃጠለውም።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ዘር ያልተዘራባት እርሻ አንቺነሽ የሕይወት ፍሬ ከአንቺ ወጣ።
ዮሴፍ የዋጃትና የከበረ ዕንቁን ያገኘባት ሣጥን አንቺ ነሽ
ይኸውም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በማኅፀንሽ አደረ
በዚህ ዓልምም ወለድሸው ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የመላእክት ደስታቸው የሆነ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ።
የነቢያት ዜናቸው ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር
ከአንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ።
የዓለም የሰው ሁሉ ደስታ የሆነ የመልአኩን ቃል ተቀብለሻልና
ደስ ይበልሽ። ዓለምን ሁሉ የፈጠረ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ
ይበልሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ። የሔዋን
መድኃኒት ሆይ ደስ ይበልሽ። ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግበውን
እሱን ጡትሽን አጥብተሽዋልና ደስ ይበልሽ። የሕያዋን
(የጻድቃን) ሁሉ እናታቸው ህይ ደስ ይበልሽ። ትለምኝልን ዘንድ
ወደ አንቺ እናንጋጥጣለን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን
ድንቅ ምሥጢር (ተዋህዶ) በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን
ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዩ ልዩ መልክ የፈጠረ የርሱን
የገናንነቱን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለምና ዝም እንበል።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ወደ ደብረሲና የወረደ ለሙሴ ሕግን የሰጠ የተራራውን እራስ
በጽጋግ በጢስ በጨለማና በነፋስ የሸፈነ ፈርተው የቆሙትንም
በነጋሪዎሽ ድምጽ የገሠፀ የአብ አካልዊ ቃል ነው። ቅድስት
ሆይ ለምኝልን።
በትሕትና የተጋገርሽ ተራራ ሆይ ይኸውም ወደ አንቺ የወረደው
ነው ሰውን የወደደ እርሱ ያለመለወጥ ባንቺ ሰው ሆነ እንደ እኛ
በሚናገር ሥጋ ፍጹም ሆኖ አምላክ በመንፈስ ቅዱስ በማህፅኗ
አደረና ፍጹም ሰው ሆነ አዳምን ያድነው ዘንድ ኅጢአቱንም
ያስተሠርይለት ዘንድ በሰማያት (በሰማያዊ መዓረግ) ያኖረው
ዘንድ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ወደ ቀድሞው ቦታው
ይመልሰው ዘንድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የድንግልን ገናነቷን ሊናገሩት አይቻልም። ጌታ መርጧታልና
የሚቀርበው በሌል ብርሃን ውስጥ የሚኖር እርሱ መጥቶ
አደረባት ዘጥኝ ወር በማኅፀንቃ አደረ የማይታይና
የማይመረመር (ታይቶ የማይታወቅ) እርሱን በድንግልና
ወለደችው ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ነብዩ ዳንኤል ያየው ያለ እጅ ከረጅም ተራራ የተፈነቀለው ያ
የደጊያ ከአብ ዘንድ የወጣው ቃል ነውና መጥቶ ያለ ወንድ ዘር
ከድንግል አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
እንደ ንጽሕ ጫፍ ሆነሽ የሃይማኖት መገኛ ነሽ የቀናች የቅዱሳን
አባቶቻችን ሃይማኖታቸው ነሽ። አምላክን የወለድሽና
በድንግልና የታተምሽ ንጽሕት ሆይ የአብን ቃል ወለድሽልን
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን መጣ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የከበርሽ ጌታን የወለድሽ ሆይ የማይታይ ቃልን የተሸከምሸው
የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ እሱን ከወለደሽው በኋላ በድንግልና
ኖረሻልና በፍጹም ምስጋና ያገኑሻል ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረውን
ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው ኪሩቤል
ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፋኑ (ማደሪያው) ሆንሽ የተከበርሽ ሆይ
እናመሰግንሻልን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ መልካሟ
እርግብ ሆይ ስምሽን እንጠራለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
እናትና ገረድ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ። የታቀፍሽውን
መላእክት ያመሰግኑታል ኪሩቤልም በፍርሃት ይሰግዱለታልና
ሱራፌልም ያለማቋረጥ ንጉሥ (የክብር ባለቤት) ይህ ነው
በይቅርታው ብዛት የዓለምን ኃጥያት ያሰተሰርይ ዘንድ የመጣው
ይህ ነው ይላሉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2017 ዲሴምበር 10, እሑድ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ : ዘይትነበብ በእለተ ሰኑይ

https://youtu.be/2yT2ggS1zIQ     *_✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

 *_ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ሰኞ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና የመጀመሪያ ክፍል።_*

*(የሰኞ ውዳሴ ማርያም)_*

ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነፃ ያወጣውና ወደ ቀድሞው ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ *ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

ከድንግል ያለወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና አዳነን። ከይሲ (ዲያብሎስ) ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ጻርሽን አበዛዋለው ብሎ ፈረደባት ሰውን ወደደና ነፃ አደረጋት። *ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ክብሩንም ለአባቱ አንደ እንደመሆኑ ክብር አየን። ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ። *ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

ነቢዩ ኢሳያስ በመንፈስ ቅዱስ የአማኤልን ምሥጢር አየ ስለዚህም ሕፃን ተወለደልን ወልድም ተሰጠን ብሎ አሰምቶ ተናገረ። *ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

ሰው ሆይ ፈጽመህ ደስ ይበልህ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን።
*ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

የነበረው የሚኖረው የመጣው ዳግመኛ የሚመጣውም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ያለመለወጥ ፍጹም ሰው ሆነ አንዱ ወልድ በሥራው ሁሉ አልተለየም የእግዚአብሔር ቃል መልኮት አንድ ነው እንጂ ።
*ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

የነቢያት ሀገራቸው ቤተልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ በአንቺ ዘንድ ተወልዷልና ከምድር (ከሲኦል) ወደ ገነት ይመልሰው ዘንድ አዳም ሆይ መሬት ነበርክና ወደ መሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት ፍርድ ያጠፋለት ዘንድ፤ ብዙ ኃጢያት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች።
*ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

የሰው ሁሉ ሰውነት ደስ ይላታል በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰውም እርሱ በሚፈቅደው እያሉ አሰምተው ንጉሥ ክስርቶስን ከመላእክት ጋር ያመስግኑታል። የቀድሞውን እርግማን አጥፍቷልና የጠላትን ምክሩን አፈረሰበት ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸውን ቀደደላቸው በዳዊት ሀገር የተወለደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸው።
*ቅድስት ሆይ ለምኝልን*

በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነትኛ ብርሃን ስለሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣው ፍጥረት ሁሉ በመጣትህ ደስ አለው አዳምን ከስህተት አድረኸዋልና ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና የምንወለድበትን መንፈስ (ረቂቁን ልደት) ሰጠኸን ከመላእክት ጋርም አመስገንህ።
*ቅድስት ሆይ ለምኝልን*saramareyama.890Gmail.com

2017 ዲሴምበር 9, ቅዳሜ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበት ክርስቲያን ቅድስት!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በሰንበተ ክርስቲያን እሁድ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና።

( ውዳሴ ማርያም)
ከሴቶች ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ ከተለዩ የተለየች በውስጧም የኪዳን የህግጽላት ያለባት የምትባይ ሁለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ። ኪዳንም በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ አሥሩ ቃላት ናቸው ። ያለመለወጥ ከአንቺ ሰውየሆነ መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን
መጀመሪያስሙን አስቀድሞ በየውጣ ነገረን ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንጹሃን የሆኑትን ወገኖች አነጻቸው ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሁልጊዜ ንጽሕት የሆንሽ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ሁላችን ስለዚህ እናገንሻለን ሰውን በሚወድ በጌታ ዘንድ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እንለምንሻለን ወደ አንቺም እናንጋጥ
ጣለን። ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ያለመለየትናያለመለወጥሰው የሆነ
የእግዚአብሔርንቃል ይመስልልናል። ይኽውም መለወጥ የሌለበት ንጹሕ መለኮት ነው ከአብ ጋር የተካከለ ነው ።
ለንጽሕት በራሱ አበሰራት።በልዩ ጥበቡ ያለ ወንድ ዘር እንደ እኛ ሆነ።መለኮቱን አዋሕዶ ያለ ርኩሰት በአንቺ ሰው ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።

በእግዚአብሔር ስዕል የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ። ንጽሕት ሆይ ያለመለወጥ ከአንቺ ሰው የሆነው ቃል ኃጢአታችንን የሚያስተሰርይልንና አበሳችንን የሚደመስስልን ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የተሰወረ መና ያለብሽ የንጹሕ ወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መናም ከሰማይ የወረደውና ለዓለም ሁሉ ሕይወ ትን የሚያድለውኅብስት ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ሁልጊዜ ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ። ይኸውም ፋና የዓለም ብርሃን ነው ጥንት ከሌለው ብርሃንም የተገኘ ብርሃን ነው።ከእውነተኛ አምላክየተገኘ
እውነተኛ አምላክ ነው። ያለመለወጥም ከአንቺ ሰው የሆነው ነው።

በመምጣቱምሰው በመሆኑምበጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለምንኖር ለእኛ አበራልን።
በልዩ የጥበቡ ምሥጢር (በሥጋዌ)የልቦናችንን እግር ወደ ሰላም መንገድ አቀናልን።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ።ፍሕም የተባለውም
ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው። ይኸውም ከአንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የእግዚአብሔርን ቃል የወለድሽልን መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ከዕሴይ ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሳይተክሏትና ውሃሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች።ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን እውነተኛ አምላካችንን ክርስቶስንየወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደ እርስዋ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ለአንቺ ይገባሻል። አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ ።በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ።ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኚ ነሽ።ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን። እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምህረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ዛሬም ዘውትርም ለዘለዓለሙ አሜን።saramarèyama.890@gmail.com

የምዕራፍ ሁለት(የ19ኛ)ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

የምዕራፍ ሁለት/የ19ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵⤵⤵⤵⤵

✍ጥ.ተራ ቁ.1⃣✅እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ እና እንደ መጽሐፈ ሄኖክ መጋቤ ብርሃናት በመባል የሚታወቀው መልአክ ማን ነው?

*//መልስ//*- ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ራጉኤል ነው፡፡

✍ጥ.ተራ.ቁ.2⃣✅ የአርማንያ ተወላጅ የሆነችው ፣ገድሏ በወሎ ሲሪንቃ የሚገኘው ታላቋ ሰማዕት ማን ነች?

*//መልስ//*- ቅድስት አርሴማ

✍ጥ.ተራ.ቁ.3⃣✅የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ተጠሪነቱ ለማን ነው?

*//መልስ//*፡- ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

✍ጥ.ተራ.ቁ.4⃣👉 ምስጢር  ማለት ምን ማለት ነው ?? ቃሉስ ከየት የተገኘ ቃል ነው???

*/// መልስ//*👇�
ምስጢር የሚለው ቃል አመሰጠረ፣ሰወረ፣ አረቀቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘጅ ሲሆን ፍቺውም ረቂቅ፣ ስውር፣ ኅቡዕ ማለት ነው።
ምስጢር  መባሉም የሥላሴን ባሕርይ ፍጡር  መርምሮ የማይደርስበት በመሆኑ፣ በፍጡር ባሕርይ መወሰን፣ መጨረሻውን ማወቅ የማይቻልና ከፍጡር እውቀት አቅም በላይ በመሆኑ ነው።

✍ጥ.ተራ.(ቁ) 5⃣✅ዑራኤል  ማለት ምን ማለት ነው???

*///መልስ//*👇�
ዑራኤል የሚለው ስም 'ዑር' እና ኤል ከሚለው ሁለት ቃልት የተመሰረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ " የብርሃን ጌታ;፣  የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.6⃣✅ ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጎድ የተሾመ ነው።
ይህን ቅዱስ ቃል የምንነገኘው በየትኛው  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው?? ምዕራፍና ቁጥሩስ???

*///መልስ//*👇�

መጽሐፈ ሄኖክ 6፥2 ላይ ይገኛ

✍ጥ.ተራ.ቁ.7⃣✅ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው???

*//መልስ*👇�
"ንስሐ ማለት ማዘን መጸጸት መመለስ ክፉ ዐመልን መተው ክፉ ጠባይን መለወጥ ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.8⃣✅• ሱባዔ ማለት ምን ማለት ነው?

*//መልስ//👉�*ሱባዔ በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪዬበቃልም እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡

• ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም  የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
ፈጣሬ ሽለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን
ከመፍጠር ማረፉ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት
 ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡
ዘፍ.2.2፤ መዝ.118.164፡፡ ጊዜከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት
ቀናት ቢጾም «አንድ ሱባዔ ጾመ» ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም «ሁለት ሱባዔ ጾመ» እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

✍ጥ.ተራ.ቁ.9⃣✅• ሱባዔ መቼ ተጀመረ???

*//መልስ//👉�* ሱባዔ የተጀመረው ከውድቀት በኋላ በመጀመሪያው ሰው
በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት መጸለይን
እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡
«መላእክት ለአዳም ጊዜያትን አስተምረውት ነበር፡፡» ቅዳሴ
ማርያም ትርጓሜ፡፡ አዳም ጥፋቱን አምኖ ከባሕር ውስጥ
ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔር በማይታበል ቃሉ
«ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኀለሁ» ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል /መጽሐፈ ቀሌምጦስ አንቀጽ አራት/፡፡


✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣0⃣✅ ቅዱሳን መካከል እመቤታችን ለማን ተገለፃች???

ሀ) ለአባ ሕርያቆስ
ለ) ለቅዱስ ኤፍሬም
ከሚከተሉትሐ) ለቅዱስ ያሬድ
መ) ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ሠ) ሁሉም መልስ ነው / ለሁሉም ተገልፃላቸዋለች።

*// መልስ//👉�*ሠ ለሁሉም ተገልጣላቸዋለች።

✍ጥ.ተራ.ቁ. 1⃣1⃣✅ በመጽሐፍ ቅዱስ የድሜ ባለፀጋ የሆነው ማነው?? ስንት ዓመትስ ኖረ ???

*//መልስ//* ማቱሳላ ነው ኖረየኖረበት ዘመንም 969 አመት ነው።(ዘፍ.5፥27)



✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣2⃣✅እግዚአብሔር ሳያዘው (ስልጣነ ክህነት) ሳይኖረው ታቦተ እግዚአብሔርን በመንካቱ የተቀሰፈው ሰው ማን ይባላል?

*//መልስ//*👉ኦዞ (2ኛ ሳሙኤል 6፥6)

✍ጥ.ተራ.ቁ. 1⃣3⃣✅ፆም ማለት ምን ማለት ነው?

*//መልስ//* ፣መከልከል፣መታቀብ ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣4⃣ ጌታችንና መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፆመው ፆም ምን ይባላል?

*//መልስ//* ዓብይ ፆም ይባላል

✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣5⃣✅የአዋጅ ፆም የሚባሉትን ዘርዝር/ሪ
*//መልስ//*👇
፩, የዐብይ ፆም
፪, ፍልስታ
፫, ፆመ ሐዋርያት
፬, ፆመ ነቢያት
፭,ፆመ ነነዌ
፮,በየሳምንቱ የምንጾመው  እሮብና ዓርብ
፯, ፆመ ጋሀድ  ነው።


✍ጥ.ተራቁ.1⃣6⃣✅ቅዱስ ሉቃስ ወንጌል መፃፍ የጀመረድ ጌታ ባረገ በስንተኛው ዓመት ???

*//መልስ///* ጌታ ባረገ በ22ኛው ዓመት ሲሆን ኸውም በ56 ዓ.ም አካባቢ ማለት ነው።.

✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣7⃣✅ ሙሴ መቶ 20 ዓመት ዕድሜውን በፈፀመለት ጊዜ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማን እንዲሰጥ አዘዘ??

*//መልስ//* ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ነው።(መ.እያሱ 👉 31፥1-3)

✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣8⃣✅ፆም የጤንነት እናት
የፍቅር እኅት
የትሕትና ወዳጅ ናት ያለው ቅዱስ  አባት ማነው??

*//መልስ//*ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው።

.✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣9⃣✅"እናንተ ግን ስትፆሙ እንደ ግብዞች አትሁኑ አትጠውልጉም...
የሚለውን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኘዋለን??

*//መልስ//* በማቴ ፮፥፲ ላይ ይገኛል።
               
✍ጥ.ተራ.ቁ..2⃣0⃣✅.እናንተ አሁን ለፅድቅ ሥራ የምትራቡ/የምትፆሙ ብፁዓን፣ንዑዳን ብሩካንም ናችሁ ትጠግቡማላችሁ..
ይህንን ቅዱስ ቃል በየትኛው  ቅዱስ ክፍል ላይ  እናገኘዋለን።
የመጽሐፍ
*//መልስ//* ሉቃ ፮፥፳፩ ላይ ይገኛል።

ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyam.890@gmail.com

2017 ዲሴምበር 8, ዓርብ

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፰)

#አፊያ #ሁሴን ክፍል 8

#ማርያማዊት ገብረመድኃን

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፰)

ወንድሜ መኪናውን በፀጥታ ሲያሽከረክር እኔ ደግሞ በከፊል ወደ እርሱ ዞሬ አተኩሬ ስመለከተው መሳቅ ጀመረ፡፡ ሳቁን ተከትዬ ስላልሳቅሁ ወይም ምንም ስላልተነፈስኩ ይልቁንም አሁንም ዝም ብዬ እንደማስተውለው ሲረዳ መኪናውን ጥግ ይዞ አቆመና ወደ እኔ እየዞረ "ምንድነው ኤፊ? አስጨነቅሽኝ እኮ" አለ፡፡ "ምንድነው?" አልኩት ኮስተር ብዬ፡፡ "ምኑ?" አለ እንዳልገባው ለመምሰል ጥረት እያደረገ፡፡ "ያልገባህ አትምሰል፣ እነዚህ ተከታትለው የገቡት መኪኖች ምንድናቸው? የአባቴ እንግዶች እንዴት በጠዋት መጡ? ዛሬ ያለ ልማድህ እንዴት በጠዋት ይዘኸኝ ወጣህ? እርሱስ እንዴት በቀላሉ ፈቀደ?" ብዬ በጥያቄ አጣደፍኩት፡፡ ነገሩን እንዳከረርኩት ከድምፄም ከገፄም ተረዳ መሰለኝ መሪውን እንደመደገፍ እያለ ተከዝ አለ፡፡ "ንገረኝ እንጂ ምን ይዘጋሃል?" ብዬ ጮህኩበት፡፡ ከዚያም "በቃ እኔ ወንድምም የለኝም ማለት ነው?" አልኩና ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ በእርግጥም በጣም ተከፍቼ ነበር፡፡ ተደናገጠና አቅፎ ሊያባብለኝ ብዙ ጣረ፡፡ ባባበለኝ ቁጥር ሆድ እየባሰኝ ብዙ ቆየሁበት፡፡ በኋላ "ቆይ እነግርሻለሁ ኤፊ፣ እንባሽን ጥረጊ...አይዞሽ እኔ ወንድምሽ ነኝ" እያለ ተለማምጦ እንደምንም ዝም አሰኘኝ፡፡ ስልኩ ቀደም ብሎ ጀምሮ ደጋግሞ ሲጮህ ነበር፡፡ ስለሆነም "ቀጠሮው በጣም ረፈደብኝ፣ ብዙ አንቆይም፣ አንዳፍታ ሰዎቹን አነጋግሬ ቁርስ እየበላን ቁጭ ብለን እናወራለን" አለና ተነስተን ሄድን፡፡ በእርግጥም አራት ኪሎ የሚገኘው ማለዳ ካፌና ሬስቶራንት መናፈሻው ውስጥ አራት ሰዎች እየጠበቁት ነበር፡፡ ሰዎቹ ሁለቱ ሙስሊሞች መሆናቸው ከንግግራቸውና ከተደጋጋሚ መሃላቸው ያስታውቃል፡፡ ሁለቱ ደግሞ ክርስቲያን መሆናቸውን የአንገታቸው ማተብ ያስረዳል፡፡ በቢዝነስ ጉዳዮች ለ30 ደቂቃ ያህል አወሩ፡፡ እኔም ወሬው ላይ በጥቂቱ ተሳተፍኩ፡፡ ነገሩ ተጠናቆ ሲነሱ አንዱ ክርስቲያን ወንድሜን "ቆንጆ ሚስት አለችህ" ሲለው ጆሮዬ ጥልቅ አለ፡፡ ወንድሜ እየሳቀ "አፊያ..ታናሽ እህቴ ነች" አለው፡፡ የእኔ ከመቀመጫዬ ያለመነሳት እዚያ ቦታ እንድንቆይ መፈለጌን ወንድሜ ተገነዘበና ሰዎቹን ትንሽ እንደምንቆይ ነገሮ ሸኛቸው፡፡

ቁርስ በልተን እንዳጠናቀቅን ወንድሜ በቀጥታ ወደ ጉዳዩ ገባ፡፡ በውስጡ ሲያወጣ ሲያወርድ ቆይቶ ነገሩን ያለ ምንም ማንዛዛት ሊነግረኝ ወስኗል፡፡ ነገሩን ሳስተውለው አባቴ አልፎ አልፎ፣ ቀሪው ቤተሰቤ ደግሞ በብዛት ለእኔ የሚያሳዩት ሀዘኔታና የስስት ልጅ ዓይነት እንክብካቤ የሥጋ መዋለድ ከሚያሳድረው ተፅዕኖ በላይ ይሆንብኛል፡፡ "እንዲህ እንዲሆኑ አንዳች የሚያስገድዳቸው መንፈስ ይኖር ይሆን?" ስል አሰብኩ፡፡ ወዲያውም በዚያው ሃሳቤ "ምን ይሳነዋል የእኔ መድኃኔዓለም" አልኩ፡፡ አባባሌ የእማማ አፀደን አባባል አስታወሰኝና ሳላስበው ፈገግ አልኩ፡፡ ፈገግታዬን የተመለከተው ፋይሰል "ምንድነው የሚያስቀሽ ኤፊ?" አለኝ በፈገግታዬ እየተደሰተ "የልጁ ንግግር ገርሞኝ ነው..ሚስትህ መስዬው ነው?" ብዬ በፍጥነት ነገሩን አዞርኩት፡፡ ወዲያው መልሼ ወደ ቁዘማዬ ገባሁና የሚነግረኝን እንዲነግረኝ ተጠባበኩ፡፡ ወንድሜ እጆቼን በእጆቹ ያዘና "ኤፊ እነዚያ ያየሻቸው ሰዎች አንቺን ለትዳር ሊጠይቁ የመጡ ሽማግሌዎች ናቸው" አለኝ፡፡ ነገሩን ከግምት በላይ አውቄው ስለነበር ብዙም አልተገረምኩ፡፡ ከዚያ ይልቅ የእርሱን አለኝታነት መመርመር ፈለግሁ፡፡ እናም "አንተ መቼ ነው ያወቅኸው?" ስል ጠየኩት፡፡ "ከትናንት ወዲያ የጁምዐ ዕለት መስኪድ ስወስደው ነው የነገረኝ" አለና ቀጠለ "እሑድ እህትህን ለጋብቻ የሚጠይቁ ሽማግሌዎች ይመጣሉ፣ እርሷን በጠዋት ይዘሃት ትወጣለህ፡፡ ጠያቂው ኡመር ይባላል ብታየው ታውቀዋለህ፣ በእስልምናም ትምህርት በቀለሙም ትምህርት የገፋ እንዴት ያለ ልጅ መሰለህ፣ ከወጣት አሰጋጆች መካከል አንዱ ነው፡፡ ልጁስ ለዚህ መላ ለሚያሳጣት ነገር ደህና መድሃኒት ይሆናት ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው ይህች የተረገመች ልጅ በጄ የምትል ይመስልሃል? አለኝ" አለና ቀና ብሎ አየኝ፡፡ "እሺ..." በሚል አስተያየት አየሁት፡፡ እርሱም "እኔም የምትስማማ አይመስለኝም፣ ነገር ግን ጠያቂን ለምን ሽማግሌ ላክህ ማለት አይቻልም፡፡ ጥያቄያቸውን ሰምተህ እርሷን አነጋግሬ መልስ እሰጣለሁ ብለህ መሸኘት ነው" ስለው ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ?" አለ እየሳቀ፡፡ "ምን አለ?" አልኩት በጉጉት፡፡ ድምፁን የአባቴን ድምፅ ለማስመሰል ጎርነን አድርጎ "ጅሎ እርሱ ይጠፋኛል ብለህ ነው? አንተ ደግሞ ወደ ላይ ሽቅብ ልታስተምረኝ ትፈልጋለህ...እኔ የቸገረኝ ከዚያ በኋላ ምን እመልስላቸዋለሁ የሚለው ነው" አለ፡፡

በዚህ መንገድ ወንድሜ በከፊልም ቢሆን ከእኔ ጋር መሆኑን ከተገነዘብኩ በኋላ "አንተና አባትህ ናችኋ ተደራጅታችሁ ሽማግሌ ያስላካችሁብኝ?" ብዬ ቀልድ አዘል ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ እርሱም "ኤፊ ደግሞ ትገርሚኛለሽ...የአባታችንንም ስነ-ልቡና ተረጂ እንጂ፡፡ ለትዳር መጠየቅ ክብር ነው፣ ለምን ልጄን ጠየቃችሁኝ ማለት ይችላል?" ሲል መልሶ እኔኑ ጠየቀኝ፡፡ የእኔ ሥጋት ለእንዲህ ያለው ጥያቄ በምሰጠው አሉታዊ ምላሽ ከአባቴ ጋር የምፈራው ውዝግብ መልሶ እንዳይመጣ ነው፡፡ በእርግጥም ነገሩን በአባቴ በኩል ሆኜ ሳየው የሚቸግር ነገር እንደሆነ አልጠፋኝም፡፡ ከፋይሰል ጋር በእኔ የፀና አቋምና ከአባቴ ጋር ስለሚፈጠረው ችግር፣ አባቴ ሆስፒታል ሳለ ከእኔም ከእርሱም ጋር ስለተጣላው ሱሌይማን፣ ስለ ሁመይድ፣ ስለሌላም ሌላም ነገር ስናወራ ቆየን፡፡ ጊዜውን ለመግደል በሚመስል መልኩ የተለያየ ቦታ ስንዘዋወር በርካታ ሰዓታትን አሳለፍን፡፡ ወደ 8፡00 ሰዓት አካባቢ ከቤት ተደወለና እንግዶቹ ቀጠሮ ተሰጥቷቸውና ምሳ ተበልቶ መመለሳቸውን ለወንድሜ ተነግሮት ወደ ቤት አመራን፡፡ ቤት ስንደርስ የግቢው ውስጥ ድባብ እንግዶቹ ወደመጡበት የተመለሱ አይመስልም፡፡ ሁለት አጎቶቼ፣ ሌሎች ሁለት የአባቴ ጓደኞች፣ ታላቅ እህቴ ከእነ ባሏ፣ የእናቴ እህት የሆነች አንዲት ክርስቲያን አክስቴና አንድ የተከበሩ ሼኽ ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ እንግዲህ እነዚህ ለሽምግልናው ከእኛ ወገን ለመቆም የመጡ ነበሩ፡፡ ግቢው ውስጥ አነስተኛ ግርግር ስለነበር ከሰርቪስ ቤቶች ውስጥ አንዱ ክፍል ገብቼ ተቀመጥሁ፡፡ አንዷን ሰራተኛችንን ሰዓዳን እንድትጠራልኝ ነግሪያት ገና ከመቀመጤ ሳሎን ትፈለጊያለሽ የሚል መልዕክት መጣልኝ፡፡

ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ፍርሃት በሁለመናዬ ተሰራጨ፡፡ መረጃ ከሰዓዳ ሳልጠይቅ በድንገት በመጠራቴ ተደናገጥኩ፡፡ ከመሄዴ በፊት ማን ማን እንዳለ ሰራተኛዋን ጠየኳት፡፡ "አጎቶችሽ አሉ...ሌላ ማንም የለ" ብላ እየተጣደፈች ሄደች፡፡ በጓሮ በወጥ ቤቱ በኩል አድርጌ ሰዓዳን በአይኔ እየቃኘሁ ወደ ዋናው ሳሎን አመራሁ፡፡ ፀጉሬ ላይ ሻርፕ ነገር ጣል አድርጌ በውስጤ "ጌታ ሆይ እርዳኝ...ጌታ ሆይ እርዳኝ" እያልኩ ለመግባት ሳመነታ እናቴ ከሳሎኑ ድንገት ብቅ ብላ "ውይ እቺው መጥታለች..ነይ ግቢ ነይ ግቢ" አለች፡፡ እኔ ኮሪደሩ ላይ ጥቂት እንድታዋራኝ ስፈልግ እርሷ ደግሞ ከተጠራሁ ትንሽ በመዘግየቴ ተጨንቃና የተቀመጡት አዋቂዎች ከብደዋት ልትጠራኝ መውጣቷ ነበር፡፡ ስለሆነም ያለ ድጋሚ ጥሪ በራሴ እንደመጣሁ ለማሳየት ፈልጋ ነበር በር ላይ ሆና "ይኸው መጥታለች..ነይ ግቢ" ስትል ድምጿን ከፍ አርጋ የተናገረችው፡፡ የእናቴን ሁኔታና ጥድፊያ በመቃወም ዓይነት በአይኔ ከገረመምኳት በኋላ ቀስ ብዬ በሩን አልፌ ገባሁና ቆምኩ፡፡ ነገረ ሥራዬ ሁሉ ተከስሼ በችሎት ፊት የቆምኩና በተከበሩ ዳኞች ፊት የምናገረው የጠፋብኝ ምስኪን አስመስሎኛል፡፡ ዝም ብዬ መገተሬን ያየው አባቴ "አጎቶችሽን ሰላም በያቸው እንጂ አፊያ.. እርሷም አክስትሽ ናት፣ ሼኽ ጅብሪልንና ሐጂ ሙሐመድንም ታውቂያቸዋለሽ" አለኝ፡፡ አስቀድሜ ሼኹ ጋር ሄጄ ጉልበታቸውን ሳምኩ፡፡ ሼኹ በዕድሜ ከሁሉ ከፍ ያሉ ከመሆናቸውም በላይ ጥቁር መነጽር የደነቀሩበት ዓይናቸውም እምብዛም አያይላቸውም፡፡ ጉልበታቸውን ስስም እጃቸውን ትከሻዬ ላይ አኑረው የምርቃት ናዳ አወረዱብኝ፡፡ ሁሉንም በየተራ ስስም እግሬ እየተወለካከፈ ስላስቸገረኝ "አይዞሽ..አይዞሽ" የሚሉ የማበረታቻ ድምፆች ከዚህም ከዚያም ይሰሙኝ ነበር፡፡ አክስቴን ስስማት ጥብቅ አርጋ እየያዘችኝ "አይዞሽ የእኔ ቆንጆ..ምንም አትፍሪ" ብላ ሞራል ሰጠችኝ፡፡ እህቴና ባሏን ሰላም ብዬ ስጨርስ ከአባቴና ከሼኹ ፊት ለፊት ባለው ሶፋ ላይ እንድቀመጥ ታዘዝኩ፡፡ ከተቀመጥኩ በኋላ ባለው ጥቂት አፍታ ክፍሉንና በውስጡ ያሉትን በስሱና በፍጥነት ቃኘኋቸው፡፡ ወንድሜ ከአንዱ ጥግ የሶፋ ኩርሲ ላይ ተቀምጦ መሬት መሬት እያየ በያዘው ስንጥር ምንጣፉ ላይ ይጭራል፡፡ እናቴ ለመታዘዝ እንዳደገደገ አገልጋይ መስላ ከሳሎኑ ወደ ኮሪደሩ በሚወስደው በር ላይ ቆማለች፡፡ እህቴ ከባሏ ጎን ተቀምጣ በሀዘኔታ የምታየኝ ትመስላለች፡፡ አክስቴ በዓይኖቿ ቆፍጠን እንድል ትጠቅሰኛለች፡፡ አባቴና ወንዶቹ አዋቂዎች የጀመሩትን ጨዋታ ቆም አረጉና ሼኹ መናገር ጀመሩ፡፡

ሼኹ ወደ አባቴ ጠጋ ብለው የሆነ ነገር ጠየቁት፣ የጠየቁት ስሜን ለመሆኑ ያስታውቅ ነበር፡፡ እናም "አፊያ...እንግዲህ እዚህ የጠራንሽ ሃሳብሽን ልንጠይቅሽ ነው፡፡ ሃሳብሽን ከአንቺ ለመስማት ያህል እንጂ ከእኛም ቃል ከአባትሽም ፈቃድ እንደማትወጪ እናውቃለን፡፡ ቀድሞውኑ አላህ በራሕመቱ የባረከሽ ነሽ፡፡ አሁንም አላህ (ሱባሀነ ወተዐላ) በምድር ዱንያውን በአኺራም ፈርዶውስ ጀነትን ይወፍቅሽ" አሉና ጉሮሮአቸውን አፅድተው ቀጠሉ "እና ልጄ...ዛሬ ለአንቺ ባል መጥቶልሻል" አሉና ስለ ባል ጥቅም፣ ሴት ዕድሜዋ ሲደርስ በፍጥነት ማግባት እንዳለባት፣ ባል አጥተው የተቀመጡ ብዙ ሴቶች እንዳሉና በትዳር ውስጥ ስለሚኖረው መልካም ነገር ሰፋ አርገው አብራሩ፡፡ የሼኹ የዕድሜ ባለፀግነት አይናቸውን ብቻ ሳይሆን ንግግራቸውንም እንደተጫነው ያስታውቃል፡፡ ከተናገሩት ከፊሉ ጭራሽ የማይሰማ ሲሆን የቀረውንም ለማድመጥ ጭንቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዕድሜም በማዕረግም ከፍ ያሉ ስለነበር ንግግራቸውን ለማቋረጥ የደፈረ አልነበረም፡፡ ከእርሳቸው ቀጥሎ ሁሉም በየተራ የሚሰማቸውን ከብዙ ምክርና ምርቃት ጋር ተናገሩ፡፡ አባቴ የጋብቻ ጥያቄ ያቀረበው ሰው በዕድሜ ወጣት በቀለሙም ሆነ በሃይማኖት ትምህርት የበሰለ መሆኑንና ባየው እንደማውቀው የተለያዩ ማስታወሻዎችን እየጠቀሰ ሊያስረዳኝ ደከመ፡፡ በመጨረሻ ከአባቴ ጓደኞች አንዱና ፈገግታ የሚያዘወትሩት አቶ ይመር ዳውድ ሳቅ እያሉ "አፊያ ታዲያ ሃሳብሽ ምንድነው? ከመጣሽ ጀምሮ መሬት መሬት እያየሽ ከመሬቱ ጋር ነው የምትጫወቺው" ብለው ሰዉን ሁሉ አሳቁት፡፡ ቀጠል አርገውም "ለጨዋታው ያህል ይህን አልኩ እንጂ አፈር ማለት፣ ቁጥብ መሆን፣ ቀደም ቀደም ያለማለት የጨዋ ሴት ምልክት ነው፡፡ አንቺም ላይ የምናየው ይህንኑ ነው፡፡ እንዲህ ያለች በሃይማኖትና በመልካም ስነ ምግባር ተኮትኩታ ያደገች ልጅ ደግሞ ለወላጆቿ ኩራት ለባሏም ሽልማት ነች፡፡ ለአንቺ ደግሞ ሽማግሌ ሆኖ መቀመጥ በእውነት ኩራት ነው...ታዲያ ጋብቻ በዋናነት የሚመለከተው አንቺን በመሆኑ እስቲ ሃሳብሽን ንገሪን...አይዞሽ አትፍሪ" አሉና በፊታቸው የተቀመጠውን የታሸገ ውኃ ጎንጨት አደረጉ፡፡ ሌሎቹም "በያ" "አይዞሽ" "ዝምታሽን ከመስማማት እንውሰደው?" እያሉ እንድናገር ገፋፉኝ፡፡

ዝም ብሎ ለሰማቸው ንግግራቸው ያለ ፍላጎት እሺ የሚያስብል ጫናና ኃይል አለው፡፡ በዕድሜና በደረጃ ከፍ ያሉና ለአንቱታ የበቁ እንዲህ ያሉ ሰዎች አንዲት ልጃገረድ ላይ ሲረባረቡ በእርግጥም የማሸነፍና በውድም በግድም የማሳመን ብቃት ይኖራቸዋል፡፡ ብዙ ወጣት ሙስሊም ሴቶች በደህናው ጊዜ ሲፎክሩ ቆይተው በኋላ ተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ የሚገቡት ለካ ወደው አይደለም ስል አሰብኩ፡፡ በዚያው ሃሳቤ "እኔ ግን አፊያ ነኝ" አልኩና ቀና አልኩ፡፡ ለጥቂት ሰከንዶች ሁሉንም በየተራ አየኋቸው፡፡ የእኔን ቀና ማለት የተመለከቱ ሁሉ አተኮሩብኝ፡፡ አባቴ ፊት ላይ ሥጋት መነበብ ሲጀምር ይታየኛል፡፡ ወንድሜ በጉጉት፣ እናቴ በጭንቀት፣ እህቴ በፍርሃት እያስተዋሉኝ ነበር፡፡ አክስቴ ቅንድቦቿን ፈታና ኮስተር እያደረገች የምልክት ማበረታቻዋን እየለገሰችኝ ነው፡፡ እኔ ከአንገቴ ቀና ባልኩ ጊዜ ፍርሃቴን የምመለክተው መሬት ላይ ትቼው ተነስቼ ነበር፡፡ የሆነ የመረጋጋት፣ የድፍረትና የጽናት መንፈስ በውስጤ ሲገባ ይታወቀኛል፡፡ ከመቀመጫዬ ብድግ ስል የሁሉም ትኩረት ጨመረ፡፡ ሆኖም ከዚያም ከዚህም አጣድፈው እንድቀመጥ አስገደዱኝ፡፡ ከዚያም ፈገግ እንዳልኩ "በእኔ ጉዳይ ተጨንቃችሁና ከአባቴም ጎን ለመቆም እዚህ በመገኘታችሁ በእውነት በጣም አመሰግናለሁ፣ ፈጣሪ ብድራችሁን ይክፈላችሁ" በማለት ብድግ ብዬ አመሰገንሁ፡፡ መልሼ ረጋ ብዬ ተቀመጥኩና "ምክራችሁንና ምርቃታችሁን አመስግኜ ተቀብያለሁ፣ ወገንነታችሁንም በልቤ ውስጥ አኖረዋለሁ፡፡ የጋብቻ ጥያቄውን ግን ለመቀበል አልችልም፡፡ ምክንያቱም እኔ አሁን በውስጤ ጋብቻ የመመስረት ፍላጎቱም ሆነ መነሳሳቱ የለኝም፡፡ ዋናው አላማዬ ያቋረጥኩትን ትምህርት ከዳር ማድረስ ነው፡፡ እናም ከትልቅ ይቅርታ ጋር በዚህ ነገር ባታስቸገሩኝ ደስ ይለኛል፡፡ ፈፅሞ የማልቀበለውና የማልደራደርበት ጉዳይ ነው" አልኩኝ፡፡ ለጥቂት ጊዜ ቤቱን አስፈሪ ጸጥታ ዋጠው፡፡ ሰዎቹ ንግግሬ የማያወላዳና አሳሪ መስሎ ሳይሰማቸው አልቀረም፡፡ ከዚያም አቶ ይመር ዳውድ ወደ አባቴ ጠጋ ብለው ዝቅ ባለ ድምፅ "የምን ትምህርት ነው? ያቋረጠችው ትምህርት አላት?" ሲሉ ጠየቁት፡፡ እርሱ ግን ግልፍ ብሎትና እየጮኸ "ምን ትምህርት ትምህርት ትላለች..የትም ስትንዘላዘል ወድቃ የተባረረችውን ትምህርት" አለ፡፡ ያ የተፈራው ፀብና ውዝግብ እንደገና ሊጀምር መሰለ፡፡ ሆኖም ሰዎቹ እየተረዳዱ አባቴን ማረጋጋትና "እንደርሱ እኮ አይደለም ሐጂ.." እያሉ ማረም ጀመሩ፡፡ ከተወሰነ ሁከት በኋላ ነገሮች ሰከን አሉ፡፡

አጎቴ ሰይድ የምንለው የአባቴ ታናሽ ወንድም ልመናም ማግባቢያም የሚመስል ቃና ባለው ንግግር "ልጄ ትምህርቱንም እኮ ቢሆን አግብተሽስ መማር ትቺያለሽ እኮ፣ ደግሞም ልጁ ወጣትና የተማረ ነው የትምህርትን ጥቅም ያውቀዋል፡፡ ሥንቶቹ ይኸው አግብተው አይደለም ወልደው እንኳ ይማሩ የለ እንዴ.. አባትሽንም አታበሳጪው፡፡ ያ ያለፈውን ክፉ ነገር እያወቅሽ" አለ፡፡ ሌላኛው አጎቴም በእርሱ ላይ እየጨመረ "ጋብቻ እኮ ክቡር ነው፣ የፈጣሪ ትዕዛዝ እኮ ነው፡፡ እንዲህ ያለ የተከበረ ሰውስ ለጋብቻ ጠይቆ በአሉታ መመለስ አግባብ ነው እንዴ? ፈፅሞ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ለሴቶች ጋብቻ መጣሁ መጣሁ ሲል እንደሚያስፈራ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ጨክነው ሲገቡበት ነው የባል ፍቅር፣ የልጅ ደስታ፣ ራስን የመቻል ክብር የሚገኘው" አለ፡፡ ሁሉም የመሰለውን እየተናገረ ባለበት ሁኔታ ሼኽ ጅብሪል ሁሉ ዝም እንዲል በእጃቸውም በአፋቸውም ምልክት ከሰጡ በኋላ "ወገኖቼ እዚች ልጅ ልብ ውስጥ የሆነ ጥመት ያለ ይመስለኛል፡፡ አንቺ ከመቼ ወዲህ ነው ልጅ ከአባቷ ፈቃድና ምርጫ መውጣት የጀመረችው?" ሲሉ ተቆጡ፡፡ ከቁጣቸው የተነሳ መቀመጫው አልበቃቸው ያለ ይመስል ተቁነጠነጡ፡፡ "የአባት ክብር እንዲህ ነው እንዴ? አንቺ..! እንዴት ያለ ድፍረት ነው? እዚህ የተሰበሰብነውንስ ከቁም ነገር አልቆጠርሽንም ማለት ነው? በይ አሁን ተነሺና አባትሽንም ሁሉንም ይቅርታ ጠይቂ፡፡ ጥያቄውንም ተቀብያለሁ፣ አጥፍቻለሁ..ማሩኝ...በይ" አሉ፡፡ መመሪያቸው ላይ አንዳች ፊውዳላዊ ቅሪት ያለ ይመስላል፡፡ እኔም እንደ ኳስ ነጥሬ ድንገት ብድግ አልኩኝ፡፡ "ይቅርታ አርጉልኝ ሼኽ ጅብሪል፣ የምወድህ አባቴ፣ አጎቶቼ፣ ቤተሰቦቼ፣ እዚህ ያላችሁ ሁሉ በአይናችሁ ፊትና በእናንተ አስተያየት ጥፋት ሰርቼ አስቀይሜያችሁም ከሆነ ይቅርታ አድርጉልኝ" ብዬ ጎንበስ አልኩ፡፡ ቀጥዬም "የጋብቻውን ጥያቄ በተመለከተ ግን ሃሳብሽን ስጪን ብላችሁ የጠራችሁኝ እኮ እናንተው ናችሁ፡፡ የእኔ ሃሳብ፣ ምርጫና ፈቃድ ካላስፈለገ ለምን ጠራችሁኝ? እዚያው እናንተው መጨረስ ትችሉ አልነበር እንዴ?፡፡ ሃሳብሽን ንገሪን ብላችሁኝ ሃሳቤን ነግሬያችኋለው፡፡ ከዚህ ያለፈው ንግግር ግን እኔን ከማስገመት እናንተንም ከማናደድ የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ በምታምኑት ፈጣሪ የምለምናችሁ ግን ይህን ውሳኔዬን ለአባቴ ካለኝ ውዴታ ጋር አታመዛዝኑት፡፡ ለአባቴ ያለኝን ፍቅር እርሱ ያውቀዋል፣ ቤተሰቦቼ ያውቁታል፣ የሦሥተኛ ወገን ምክርም ግሳፄም አያሻኝም፡፡ ትዳር ሕይወት ነው፣ የምኖረውም እኔ ነኝ፡፡ ለማንም ሰው የዕለት ወይም የሰሞን ብስጭት ብዬ ዕድሜ ልክ የሚያንገበግበኝን ውሳኔ አልወስንም" ብዬ ተቀመጥሁ፡፡

አባቴ ብድግ ብሎ በያዘው ከዘራ አናቴን ሊተረትረው ቃጣ፡፡ ነገር ግን ተረባርበው ያዙትና አስቀመጡት፡፡ ቤቱ በቅጽበት ተተረማመሰ፡፡ አባቴ ውስጡ መናደድ ሲጀምር የአሉታ የሚመስሉ ቃሎችን ብቻ እየመረጠ የሚሰማ ጆሮ ነው ያለው፡፡ እናም "ለእርሷ ክብር የመጡ ሰዎችን ታንጓጥጣለች እንዴ? ይቺ ወፍ ዘራሽ፣ ይቺ ከእኔ ሽንት ለመውጣቷም እጠራጠራለሁ፡፡ አያገባችሁም አትናገሩኝ ስትል እየሰማችኋት" እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል፡፡ እኔ ተስፈንጥሬ ሄጄ ወደ ውስጥ በሚወስደው በር ላይ በእናቴና በአክስቴ ተከልዬ ቆሜያለሁ፡፡ የአብዛኞቹ ትኩረት አባቴ ያለ ልክ ሲናደድ ደም ግፊቱ እንዳይነሳ በመስጋት እርሱን በማረጋጋት ተጠምዷል፡፡ ፋይሰል በውስጥ በኩል መጥቶ "በቃ ወደ ውስጥ ግቢ" እያለ ይጎተጉተኛል፡፡ የአባቴ ጓደኞች እርስ በርስ "እንዴት እንዴት ነው የምትናገረው? ጋዜጠኝነት ነበር እንዴ ታጠና የነበረው?" ይላሉ፡፡ አባቴም "ትምህርት ብላ ባህር ዳር ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ከርማ ነው የመጣችው፡፡ እዚያ ውሎዋም አዳሯም ከክርስቲያኖች ጋር ነበር፡፡ እነርሱ ናቸው እንደዚህ ክፉና ምላጭ አድርገው የላኳት" ይላል፡፡ ከብዙ ሽብርና ግርግር በኋላ ሼኽ ጅብሪል ተነስተው በሁኔታው እንዳዘኑ፣ እንዲህ ያለም ሽምግልና ገጥሟቸው እንደማያውቅ፣ እኔንም የወጣትነት ትዕቢትና ጠማማ የካፊር ሃሳብ ወደ ጥመት እየመራኝ እንደሆነ ገለፃ ሲያደርጉ ቆዩ፡፡ እኔን አክስቴ፣ እህቴና ፋይሰል እየገፋፉ ወደ መኝታ ክፍሌ ይዘውኝ ገቡ፡፡ ሼኽ ጅብሪል "እንግዲህ ልጅቷ በጄ አልልም ብላለች፣ ሌላ የምታሸንፉበት መንገድ ካላችሁ እናንተ ምከሩ፣ ቀስ ብሎ በእናቲቱ፣ በእህቶቿ በኩል ሃሳቧን ትለውጥ እንደው ሞክሩ፡፡ ካልሆነ የቀጠሮው ቀን ተገኝተን እንዳልተሳካ ለሽማግሎቹ መንገር ነው" አሉ እጃቸውን "መላም የለው" በሚል አኳኋን እያወናጨፉ፡፡ የዕለቱ ሽምግልናም በዚሁ ተጠናቀቀና ሁሉም ወደየመጡበት ተመለሱ፡፡

እኔ ግን መኝታ ክፍሌ ገብቼ እየጮህኩ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ በእርግጥም እጅግ በጣም ተከፍቼ ነበር፡፡ አባቴ እኔ ከእርሱ ለመወለዴ እንደሚጠራጠር በአደባባይና ሰው በተሰበሰበበት ተናግሯል፡፡ ሁልጊዜም ለቤቱ መታወክና ለእርሱ ጤንነት መቃወስ ተጠያቂ የመሆኔ ነገር አንገሽግሾኛል፡፡ ማንም ሰው የገዛ ክብሩና የአባቴ ጤንነት እንጂ የእኔ ሕይወትና ዕጣ ፈንታ እንደማያሳስበው ተሰምቶኛል፡፡ ስለዚህም ከዚያ ቤትና ቤተሰብ የቀረኝ ነገር የለም፣ የዝምድና ገመዴም ተቆርጧል እያልኩ በማሰብ መንሰቅሰቄን አበዛሁ፡፡ ቤቱን ጥዬ እንደምሄድ አሊያም ራሴን እንደማጠፋ እየዛትኩ በመናገር ከፍተኛ ግርግር አስነሳሁ፡፡ እናቴ እኔን ተከትላ ማልቀስ ጀመረች፣ ታላቅ እህቴ፣ አክስቴ፣ ሰዎቹን ሸኝቶ የተመለሰው ፋይሰል፣ ቤቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ እኔን ለማባበል መከራቸውን ሲያዩ ቆዩ፡፡ አክስቴ እንዲህ አይነት ሽምግልና አይታ እንደማታውቅና ከልጅቷ ፍላጎት ውጪ በወላጅ ፈቃድ ካልተዳረች ማለት ያረጀና ያፈጀ ሥርዓት እንደሆነ እየተማረረች ትናገር ነበር፡፡ ታናሽ እህቴ ሰዓዳና ትንሹ ወንድሜ ሙኒር ከአንዲት ዘመዳችን ጋር ማምሻውን ሲመጡ እኔ እዬዬውን እያስነካሁት ነበር፡፡ ሰዓዳ የደረሳት መረጃ እኔ ከአባቴ ጋር ተጣልቼ ቤቱን ለቅቄ ካልሄድኩ እያልኩ በማስቸገር ላይ እንደሆንኩ ነበር፡፡ ስትበር እንደመጣች ከእኔ ብሳ እዬዬዋን ታቀልጠው ጀመር፡፡ ወገቤን ይዛ "እህቴ አትሂጂብኝ፣ እኔም አብሬሽ እሄዳለሁ" እያለች ለግልግል አስቸገረች፡፡ ሁኔታውን አልፎ ሳስበው እንደ መሳቅም ይቃጣኛል፡፡ አባቴ ከእንግዶቹ ጋር እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ እንጂ ምሽቱ ምን እንደሚመስል ለመገመት ይከብድ ነበር፡፡ ብቻ ቆራጥ ውሳኔዬ፣ በሽማግሌዎች ፊት ያደረግሁት ንግግርና የለቅሶዬ ብዛት በቀሩት ዘንድ ተጨማሪ ሞገስ ያተረፈልኝ መሰለ፡፡ በአባቴ ላይ ግን ከፍተኛ ቂም ያዝኩበት፡፡ ልጅነቴን እስከ መካድ ያደረሰው ነገር ፈፅሞ ከሆዴ ሊወጣልኝ አልቻለም፡፡ በዚህ ሁኔታ ሳለ አንዷ ሰራተኛችን ብቅ ብላ "አፊያ ሁመይድ መጥቷል ሳሎን ነው" አለችን፡፡

                        (ይቀጥላል)

     ------- ማርያማዊት ገብረመድኅን -------

saramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...