2018 ጁን 30, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬) የ34ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

የምዕራፍ አራት(፬) የ34ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር እንዲህ ተጀመረ

@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄ እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

🖊🖊🖊🖊🖊🖊🖊🖊
✅1⃣➡በአቤል ምትክ የተወለደው ልጅ ማን ነበር??
ሀ/ ቃየልን
ለ/ ሴት
ሐ/ አሚናዳብ
መ/ብንያም

✅ሀ

✅2⃣➡ከሦስቱ የኖኅ ልጆች፣መካከል የጌታችን የዘር ሐረግ ከየትኛው ነው??

ሀ/ ሴም
ለ/ ካም
ሐ/ያፌት
መ/ መልስ የለም

✅ሀ

✅3⃣➡በሙሴ ዘመን የነበረው የግብፅ ፈርዖንና ጌታችን በተወለደ ጊዜ የነበረው ሄሮድስ ተመሳሳይነታቸው እንዴት ነበር??

ሀ/ ሁለቱም በስማቸው ፕራሚድ አሠርተው ነበር
ለ/የእስራኤላውያን ሕፃናት ገድለዋል
ሐ/ ሁለቱም ግብፅን አስተዳድረዋል
መ/ ሄሮድስና ፈርፆን አይመሳሰሉም

✅ሀ

✅4⃣ ከሚከተሉት ውስጥ የያዕቆብ ሚስቶች እነማን ናቸው??

ሀ/ ራሔል እና ርብቃ
ለ/ ልያ እና ራሔል
ሐ/ ትዕማር እና ሩት
መ/ ሣራ እና ርብቃ

✅ለ

✅5⃣➡እርሱ አፍ ይሆንሃል አንተም በእግዚአብሔር ፈንታ ትሆንለታለህ ብሎ እግዚአብሔር የነገረው ለማን ነው???
ሀ/ ለሶምሶምን
ለ/ ለሙሴ
ሐ/ ለአሮን
መ/ ለሰሎሞን

✅ለ

✅6⃣➡ሙሴ ዐሠርቱን ትዕዛዛትን የተቀበለው በየትኛው ተራራ ነው,??

ሀ/ በታቦር ተራራ
ለ/ በሲና ተራራ
ሐ/በአራራት ተራራ
መ/ በናባው ምድር

✅ለ

✅7⃣➡ኖኅ ከመርከብ ከመውጣቱ አስቀድሞ ስንት ጊዜ ርግብን ሰድዷል?

ሀ/ አንድ
ለ/ ሁለት
ሐ/ ሦስት
መ/ አራት

✅ሐ

✅8⃣➡እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአብርሃም ድንኳን ለኖህ መርከብ ለያዕቆብ መሰላል ለአዳም ___ናት,?

ሀ/ ሔዋን
ለ/ ቅርበት
ሐ/ ተስፋ
መ/ ገነት

✅ሐ

✅9⃣➡በአባቶቹ በእነ ዳዊት መንገድ ባለመሔዱና እግዚአብሔር በመበደሉ ምክንያት ነቢዩ ኤልያስ ካረገ በኋላ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የላከለት የእሥራኤል ንጉሥ ማን ይባላል??

ሀ/ ኢዮሣፍጥ
ለ/ አክዓብ
ሐ/ ኢዮራም
መ/ አሳ

✅ሐ

✅1⃣0⃣➡ማኔ ቴቁል ፋሬስ ተብሎ የተፃፈበት ንጉሥ ማን ነው??

ሀ/ ናቡከደነጾር
ለ/ ዳርዮስ
ሐ/ ብልጣሶር
መ/ ዳንኤል

✅ሐ

✅1⃣1⃣➡ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና ሕዝብሽን ህዝቤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል ያለች ሞዓባዊት ሴት ማናት??

ሀ/ኑኃሚን
ለ/ ማራ
ሐ/ ሩት
መ/ ራኬብ

✅ሐ

✅1⃣2⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ መንታ ልጆች የነበሩት አባት ማን ነበር??

ሀ/ አብርሃም
ለ/ ይስሐቅ
ሐ/ ያዕቆብ
መ/ ዮሴፍ

✅ለ

✅1⃣3⃣➡ከመዝሙረ ዳዊት ቀጥሎ ብዙ ቃላትን የያዘው  መጽሐፍ የትኛው ነው??

ሀ/ ኦሪት ዘሌዋውያን
ለ/ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀ...ዊ
ሐ/ት.ኤርምያስ
መ/ መጽሐፈ መክብብ

✅ሐ

✅1⃣4⃣➡ያዕቆብ ዲናን የወለዳት ከማን ነው??

ሀ/ ከራሔል
ለ/ ከሩት
ሐ/ ከዘለፋ
መ/ ከልያ

✅መ

✅1⃣5⃣➡ከስደት የተመለሱ አይሁድ ያገቧቸውን አሕዛብ ሴቶች እንዲፈቱ ያዘዘው ማን ነው??

ሀ/ ባሮክ
ለ/ ዕዝራ
ሐ/ዮሴፍ
መ/ ፈርፆን

✅ለ

✅1⃣6⃣➡ስለ ሰባት ወፍራምና ሰባት ቀጫጭን ላሞች ያለመው ሰው ማን ነው??

ሀ/ ዳንኤል
ለ/ ናቡከደነጾር
ሐ/ ዮሴፍ
መ/ፈርፆን

✅መ

✅1⃣7⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ ከዳዊት መዝሙር የማይመደበው ፀሐፊ የትኛው ነው??

ሀ/ ኤታን
ለ/ሙሴ
ሐ/አሳፍ
መ/ መልሱ አልተሰጠም

✅መ

✅1⃣8⃣➡በአዲስ ኪዳን ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ በድንጋይ ተወግሮ የሞተው ሰማዕት ማን ነው??

ሀ/ ቅዱስ እስጢፋኖስ
/ ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ/ቅዱስ ጳውሎስ
መ/ መልስ የለም

✅ሀ


✅1⃣9⃣➡ለእግዚአብሔር እና አባቱ የሚወዱት ወንድሞቹ ግን በቅናት የሚጠሉትና የሸጡት በተሸጠበት ሀገርም እግዚአብሔር ያከበረው ሰው ማን ይባላል??

ሀ/ያዕቆብ
ለ/ ዮሴፍ
ሐ/ ቢኒያም
መ/ መልሱ አልተሰጠም

✅ለ

✅2⃣0⃣➡ብዙ ሰዎች ቸርነታቸውን ያወራሉ፤ የታመነውን ሰው ግን ማን ያገኘዋል? ጻድቅ ያለ ነውር ይሄዳል፥ ልጆቹም ከእርሱ በኋላ ምስጉኖች ናቸው።
 ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ እናገኛዋለን.....???

✅ምሳሌ፦((ም.20፥6-7))

ወስብሐት እግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

2018 ጁን 25, ሰኞ

የምዕራፍ ፬/የ33ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ማኅበርተኞች!:
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁንልን እያልን እነሆ፦ የምዕራፍ አራት(፬) የ33ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር እንዲህ ተጀመረ
@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄ እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

✍1⃣➡እግዚአብሔር በቃየል ላይ ለምን ምልክት አደረገበት??

ሀ/ለመቅጣት
ለ/ ከአቤል ለመለየት
ሐ/ ከሚደርስበት መከራ ለመጠበቅ
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ// ሀ)

✍2⃣➡አብርሃም እግዚአብሔርን ስለ ሰዶም መዳን በማለደ ጊዜ እስከ ስንት ሰው ድረስ ቢገኝ እንዲምርለት ፈጣሪውን ተማጽኖት ነበር??
ሀ/ 5
ለ/ 10
ሐ/ 15
መ/ 50

// መልስ//ለ)

✍3⃣➡ያዕቆብ ይወዳቸው የነበሩት ከራሔል የተወለዱት ሁለት ልጆች ማን ናማን ናቸው??
ሀ/ ዮሴፍና ንፍታሌም
ለ/ ዛብሎንና ጋድ
ሐ/ ሮቤልና ይሁዳ
መ/ ዮሴፍና ብንያም

//መልስ//መ)

✍4⃣➡ከአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የመሬት ርስት ያልተሰጠው የትኛውው ነገድ ነው??

ሀ/ ነገደ ስምዖን
ለ/ ነገደ ዳን
ሐ/ ነገደ ይሳኮር
መ/ ነገደ ሌዊ

//መልስ// መ)

✍5⃣➡ሩት የማን ቅድመ አያት ናት??

ሀ/ የቦኤዝ
ለ/ የዳን
ሐ/የዳዊት
መ/ የሌዊ

//መልስ// ሐ)

✍6⃣➡እግዚአብሔር ለአብርሃም የማለለት ምድር  ተብሎ ይጠራል??

ሀ/ካራን
ለ/ቤቴል
ሐ/ ከነዓን
ምንመ/እስራኤል

//መልስ//ሐ)

✍7⃣➡ከሚከተሉት የአባቷን ጣዖት የደበቀችው ማናት??

ሀ/ ርብቃ
ለ/ ራሔል
ሐ/ሣራ
መ/ ልያ

//መልስ// ለ)

✍8⃣➡አባታችን ኖኅ ስንት ልጆች አሉት??

ሀ/ 2
ለ/ 3
ሐ/4
መ/8

//መልስ// ለ)

✍9⃣➡ደረቅ ሐዲስ ኪዳን በመባል የሚታወቀው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ የትኛው ነው??

ሀ/ ኦሪት ዘፍጥረት
ለ/መጽሐፈ ሩት
ሐ/ ትንቢተ ኢሳይያስ
መ/መጽሐፈ ጦቢት

//መልስ//ሐ)

✍1⃣0⃣➡የአምስቱ ብሔረ ኦሪት ጸሐፊ ማን ነው??

ሀ/ ሄኖክ
ለ/ ሰሎሞን
ሐ/ሙሴ
መ/አሮን

//መልስ// ሐ)

✍1⃣1⃣➡ዳዊት ፍልስጥኤማዊያውንን ጎልያድን የገደለበትን ታረክ በየትኛው መጽሐፍ ላይ ነው??

ሀ/ 1ኛ ነገሥት
ለ/1ኛ ሳሙኤል
ሐ/ 1ኛ ዜና መዋዕል
መ/2ኛ ዜና መዋዕል

//መልስ// ለ)

✍1⃣2⃣➡እኔ ከንፈር ቁልፍ ነኝ በማለት ራሱን ወደ እግዚአብሔር በትህትና ያቀረበው ማነው??

ሀ/ ቅዱስ ጳውሎስ
ለ/ ነቢዩ ዳዊት
ሐ/ሙሴ
መ/ ኤልሳዕ

//መልስ// ሐ)

✍1⃣3⃣➡እንደ በሬ ሣር በመጋጥ ሰባት ዓመት የተቀጣው ንጉስ ማነው??

ሀ/ ዳርዮስ
ለ/ ናቡከደነጾር
ሐ/ብልጣሶር
መ/ ኢዮርብዓም

//መልስ// ለ)

✍1⃣4⃣➡በመጽሐፍ ቅዱስ ርዝመቱ 300 ክንድ፣ ስፋቱ 50 ክንድ እና ከፍታው 30 ክንድ መጠነ ስፍር እንደሌለው የተገለፀው ለየትኛው ነው?

ሀ/ ታቦተ ጽዮን
ለ/ የኖህ መርከብ
ሐ/ ናቡከደነጾር ያቆመው ምስዕል
መ/ የዳዊት ቤተ መቅደስ

//መልስ// ለ)

✍1⃣5⃣➡ከሚከተሉት ሴቶች በመጽሐፈ መሳፍንት ታሪኳ የሠፈረው የእስራኤል ፈራጅ ማናት??
ሀ/ ሩት
ለ/አስቴር
ሐ/ዮዲት
መ/ ዲቦራ

//መልስ// መ)

✍1⃣6⃣➡"ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን የሚለው ሃይለ ቃል ከሚከተሉት ውስጥ በይበልጥ ማነን ይመለከታል??

ሀ/ አብርሃምን
ለ/ይስሐቅን
ሐ/ ያዕቆብ
መ/ ዮሴፍ

//መልስ// መ)

✍1⃣7⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ ክርስቶስን ይመስላል የሚባልለት ማነው??

ሀ/ ሎጥ
ለ/ ኤርምያስ
ሐ/ ሰሎሞን
መ/ ዮሴፍ

//መልስ//መ)

✍1⃣8⃣➡ከሚከተሉት ወንድም አማቾች ያልሆኑት እነማን ናቸው??

ሀ/ ሙሴና አሮን
ለ/ ያዕቆብና ዔሳው
ሐ/ ዳዊትና አቤሴሎም
መ/ አቤልና ቃየል

//መልስ// ሐ)

✍1⃣9⃣➡ዳዊት ንስሐ እንዲገባ በምሳሌ ያስተማረው ነቢይ ማነው??

ሀ/ናታን
ለ/ ነህምያ
ሐ/አሮን
መ/ዳንኤል

//መልስ//ሀ)

✍2⃣0⃣➡ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌሎች ይልቅ የተነበየው ነቢይ ማነው??አመሰግናለሁ

ሀ/ ኤልያስ
ለ/  ናሆም
ሐ/ ዮናስ
መ/ኢሳያስ

//መልስ// መ)


ወስብሀት ለእግዚአብሔር
. @Teyakaenamels
@Teyakaenamels

https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

2018 ጁን 16, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬)/የ32ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን? ሰላማችሁ ይብዛልን እያልን እነሆ፦ የምዕራፍ ፬ የ32ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

@ምንጭ፦ 420 ጥያቄ እስከ መልሶቻቸው ከሚለው በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው መጽሐፍ የተወሰደ።

✍1⃣➡ከዐቢይት ነቢያት የማይመደበው  ነቢይ የትኛው ነው???

ሀ/ሚክያስ
ለ/ ኤርምያስ
ሐ/ኢሳያስ
መ/ዳንኤል

//መለስ//፦ሀ) ሚክያስ

✍2⃣➡ንጉሥ አክዓብ ጣዖት በማምለኩ ምክንያት የገሰጸው ነቢይ ማን ነው??

ሀ/ናታን
ለ/ ኢሳይያስ
ሐ/ ባሮክ
መ/ኤልያስ

//መልስ// ፦መ) ኤልያስ

✍3⃣➡የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ የነበረው ንዕማን ከለምጹ ለመፈወስ ስንት ጊዜ በዮርዳኖስ ወንዝ ብቅ ጥልም አለ፤

ሀ/ 1
ለ/ 3
ሐ/ 5
መ/ 7

//መልስ//፦ መ) 7ት ጊዜ

✍4⃣➡ከሚከተሉት ወንዞች መካከል ከኤደን በመውጣት ገነትን ያጠጣ የነበረው የትኛው ነው??

ሀ/ ዮርዳኖስ
ለ/ኤፌሶን
ሐ/ አባና
መ/ ፋርፋ

//መልስ//፦ለ) ኤፌሶን


✍5⃣➡ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች በባረከ ወቅት ቀኝ እጁን ያደረገው  ማን ራስ ላይ ነበር??።

ሀ/ ኤፍሬም
ለ/ ምናሴ
ሐ/የበኩር ልጁ
መ/መልስ የለም

//መልስ//፦ ለ) ምናሴ

✍6⃣➡ፈርፆን የዮሴፍን ሕልም የመፍታት ጸጋ ስላስደነቀው ለዮሴፍ ምን አደረገለት ??

ሀ/ ከእስር ቤት ፈተው

ለ/ በሀገሩ ላይ ሹም አደረገው
ሐ/ ገንዘብ ሰጠው
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ//፦መ) ሁሉም መልስ ነው።

✍7⃣➡እግዚአብሔር በግብፅ ካደረገው መቅሠፍት የማይመደበው የትኛው ነው??

ሀ/ ሀገሪቱ በበረዶ መመታት
ለ/የዝንብ ወረራ
ሐ/የውኃ ወደ ደም መለወጥ
መ/ የአዞ መንጋ

//መልስ//፦ መ) የአዞ መንጋ

✍8⃣➡በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያውን ሕልም ያለመው ማነው??

ሀ/ ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ ጻዲቁ ዘካርያስ
ሐ/ንጉሥ አቤሜሌክ
መ/አዳም

//መልስ//፦ ሐ) ንጉሥ አቤሜሌክ

✍9⃣➡ያዕቆብ ስለ ራሔል በአጎቱ ቤት ያገለግለው ለስንት ዓመት ነው??

ሀ/7
ለ/ 14
ሐ/ 21
መ/28

//መልስ//፦ለ) 14 ዓመት

✍1⃣0⃣➡በግብፅ ሐገር የወረደው የመጨረሻው መቅሰፍት ምን ነበር??
ሀ/በሰው ሁሉ ላይ ቁስል መውጣት
ለ/ሁሉም የከብት መንጋ ማለቅ
ሐ/ ምድሪቱ በጓጓንቸር መመታት
መ/በኩር የተባለ ሁሉ መሞት

//መልስ//፦መ) በኩር የተባለ ሁሉ መሞት

✍1⃣1⃣➡ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ ብሎ አገልጋዮን ያጽናና ነቢይ ማነው??

ሀ/ ኤልያስ
በማለትለ/ ኢሳይያስ
ሐ/ ዳንኤል
መ/ ኤልሳዕ

//መልስ//፦ መ) ኤልሳዕ

✍1⃣2⃣➡ከሚከተሉት መካከል የብሉይ ኪዳን ነቢይ የነበረ ማን ነው?

ሀ/ አብድዩ
ለ/ሐጌ
ሐ/ናሆም
መ/ሁሉም ናቸው

//መልስ//፦መ) ሁሉም

✍1⃣3⃣➡ ፈርዖን እስራኤላውያን አለቅም ባለ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ በመጀመርያ ያዘዘው መቅሰፍት ምንድን ነበር?

ሀ/ የዝንብ ምድሪቱን መውረር
ለ/ የወንዝ ወደ ደም መለወጥ
ሐ/ የአሮን በትር ወደ እባን መለወጥ
መ/ በሕዝቡ ላይ ቁስል መመታት

//መልስ//፦ ሐ)የአሮን በትር ወደ እባብነት መለወጥ

✍1⃣4⃣➡.የእስራኤላውያንን ከግብፅ የመውጣት የመጀመርያ ታሪክ የሚዘገበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው??
ሀ/ ኦሪት ዘፍጥረት
ለ/ ኦሪት ዘጽአት
ሐ/ ኦሪት ዘሌዋውያን
መ/ ኦሪት ዘኁልቁ

//መልስ//፦ለ)ኦሪት ዘጽአት

✍1⃣5⃣➡ከዳዊት መዝሙት ቀጥሎ ብዙ ምዕራፎች ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው??
ሀ/ ዘፍጥረት
ለ/ ኤርምያስ
ሐ/ ሐጌ
መ/ ኢሳይያስ

//መልስ//፦መ) ኢሳይያስ

✍1⃣6⃣➡ከጥፋት ዘመን በኋላ ኖኅ ከመርከብ መጥቶ በመጀመሪያ ያደረገው ምንድን ነው?

ሀ/የምሥጋና መዝሙር ዘመረ
ለ/እርሻ ማረስ
ሐ/ መስዋት ማቅረብ
መ/ የወይን ጠጅ መጠጥ

//መልስ//፦ ሐ)መሥዋት ማቅረብ

✍1⃣7⃣➡ለአብርሃም ትዕግስትን ለኢዮብ ጽናት፤ ለሰሎሞን ጥበብ፤ ለኤርሚያስ___ዳሽ ነው??
ሀ/ ትንቢት
ለ/ ሀብት
ሐ/ዕንባ
መ/ፈውስ

//መልስ//፦ ሀ) ትንቢት

✍1⃣8⃣➡ከሚከተሉት መካከል ካህኑ መልከ ጼዴቅን የሚገልፀው የትኛው ነው??

ሀ/ ትውልዱ ከአሕዛብ ወገን መሆኑ
ለ/ የሳሌም ንጉሥ መሆኑ
ሐ/ አብርሃም ከጦርነት ሲመለስ ዐሥራት ገብሮለታል
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ//፦ መ/ ሁሉም

✍1⃣9⃣➡እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል ኪዳን ሲገባለት ልጆችህ እንደ___ይበዛሉ አለው.?

ሀ/ እንደ ሰማይ ከዋክብት
ለ/ እንደ ባህር አሸዋ
ሐ/ እንደ ምድር እንስሳት
መ/ መልስ የለም

//መልስ//፦ሀ) ዘፍጥረት 15፥1-21

✍2⃣0⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ በመጀመርያ የተፃፈው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ የትኛው ነው??

ሀ/ ኦሪት ዘፍጥረት
ለ/ መጽሐፈ ሄኖክ
ሐ/ 1ኛ ሳሙኤል
መ/ መጽሐፈ ጦቢት

//መልስ//፦ ለ) መጽሐፈ ሄኖክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyam.890@gmail.com

2018 ጁን 13, ረቡዕ

"ከእኔ አብ ይበልጣል"""

""'ከእኔ አብ ይበልጣል'"" ዮሐ14፥28
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን መናፍቃን ይህንን ጥቅስ በመጥቀስ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባህሪው ከአብ ያንሳል ብለው ይናገራሉ ዳሩ ግን ይህንን አባባል ጠለቅ ብለን ስናጤነው እንደአርዮሳውያን አባባል ወልድ በመለኮቱ ከአብ ያንሳል የሚለውን ትምህርት የሚደግፍ ሆኖ አናገኘውም እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን በመዋሐዱ መከራ የሚቀበልና ስለሰዎች ልጆች ድኀነት ሲልም በፈቃዱ እንደሚሞት ሲገልፅ ነው ሰውን ከወደቀበት የጉስቁልና ህይወት ለማንሳትና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ልዑለ ባህሪ አምላክ እራሱን አዋርዶ ሥጋን ተዋህዶ መከራን ተቀበለ ይህንንም ሲያደርግ ከእግዚአብሔርነቱ አልጎደለም ጳውሎስ በመልእክቱ እንደገለፀው ""ይኸውም የእግዚአብሔር መልኩ ነው ቀምቶ እግዚአብሔር የሆነ አይደለም እራሱን ዝቅ አድርጎ የአዳምን ባህሪ ባህሪ አደረገ እንጂ ሰውንም መሰለ""ፊል2፥6-7 እንግዲህ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ የሰው ፍቅር ስቦትና አስገድዶት ራሱን ዝቅ አድርጎ በሠራው የትህትና ሥራ እንኳን በባህሪ አንድ ከሆነው ከአብ ቀርቶ ከፈጠራቸው መላእክትም አንሶ እንደነበር መፅሀፍ ቅዱስ ይገልፅልናል ""ከመላእክት ይልቅ በጥቂቱ አሳነስከው ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስን...""ዕብ2፥7-9 እንግዲህ ይህንንም ጥቅስ ይዘው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክትም ያንሳል ብለው ሊናገሩ ይችላሉን? ጳውሎስ ጌታችን ስለ እኛ ሲል በተቀበለው መከራና ሞት መላእክትን እንኳን እንዳይሞቱ አድርጎ የፈጠረ እርሱ ስለሰው ልጅ ፍቅር ሲል ግን ሞተ ብሎ እግዚአብሔር ወልድ በለበሰው ሥጋ እንደ ሞተ ግልፅ አድርጎታል ስለዚህ ጌታም ከእኔ አብ ይበልጣል ማለቱ እራሱን ዝቅ አድርጎ ሥጋን ተዋሕዶ በምድር ላይ መንገላታቱን ሞትን በገዛ ፈቃዱ ሊቀበል መምጣቱን ሲገልፅ ሲሆን በትህትና የሚታይበትም ግዜ አጭር መሆኑን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ በልዕልና በክብሩ እንደሚኖር ሲገልፅ ""ወደ አብ በመሔዴ ደስ ይበላችሁ"" ብሏቸዋል በትህትና ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ አንሶ የታየው ጌታ የማዳኑን ሥራ ከፈፀመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሷልና በልዕልና ይታያልና የሐ ሥራ7፥55 ""'ኢየሱስን በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ አየዋለሁ""' ማለት በቀደመ ክብሩ በልዕልናው ሆኖ አየዋለሁ ማለቱ ነውና
ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

አሻጋሪ ዎች

"አሻጋሪዎች"

ሰባኪው በ አንድ ቤተክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር
ያስተምራል። በየ እለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ። ከ እነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ የመሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው።

አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ፡
ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ቢኖራቹ ይህን ተራራ በገፋችሁት ሂድ እልፍ በል ባላችሁት ግዜ በሄደ። " የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ሃይለ ቃል ገልጾ በ እምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳ።
በሚዞረው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ።
ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዜብሔር አምናለው እግዜብሔርም ይህን ለ እኔ ማድረግ አይሳነውም" በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም ይሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ እቤቱ ግባ።
ሚስቱም በመደንገጥ " ቤተክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ" ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው ብላ በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" ብላ ባለቤቷን ተማጸነች።
በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ፡ ትምህርት ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄዶ፥ " ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው፡ እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ፡ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው።
በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን " ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ እናሻግራለን እንጂ አንሻገርም!" ሲል መለሰለት።
እኛስ በእውነቱ የምንናገረውን የምናስተምረውን የምንሰብከውን እየኖርን ነውን? መልሱን ለእናንተ ትቻለው።
(እኔም ያነበብኩትን እንዲህ አካፈልኳችሁ እናንተም ከተመቻችሁ ለሌሎች አድርሱትsaramareyama.890@gmail.com

2018 ጁን 2, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬) የ31ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እያልን እነሆ የምዕራፍ አራት (፬) የ31ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር እንዲህ ይዘን ቀረብን የዚህ ጥያቄ ምንጭ፦ በማኅበረ ቅዱሳን 420 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ።👇
////////////////

✍ጥ.ተራ.ቁ1⃣ በኦሪት ዘዳግም ተዘግቦ እንደምናገኘው በሞዓብ ሸሎቆ የተቀበረው ማነው??

ሀ// ሙሴ
ለ// ኢያሱ
ሐ// አሮን
መ//ፈርፆን

//መልስ// ሀ) ሙሴ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ 2⃣ንጉሥ አቤሜሌክን ከመፍራታቸው የተነሳ ማንነታቸውን በተጠየቁ ጊዜ እኛ ወንድምና እህት ነን ያሉት ባልና ሚስት እነማን ናቸው??

ሀ/አዳምና ሔዋን
ለ/ያዕቆብና ራሔል
ሐ/ አብርሐምና ሳራ
መ/ዳዊትና ቤርሳቤህ

//መልስ// ሐ) አብርሃምና ሳራ

✍ጥ.ተራ ቁ3⃣ የመጀመርያውን የእስራኤል ንጉሥ ሳኦልን የገደለው ማን ነው??

ሀ/ ንጉሥ ዳዊት
ለ/ የዳዊት ልጅ አቤሴሎም
ሐ/ ራሱን በራሱ
መ/ መልስ የለም

//መልስ//መ) መልስ የለም።

✍ጥ.ተራ ቁጥር4⃣ከሚከተሉት ነገሥታት መካከል ሠለስቱ ደቂቅን /ሦስቱ/ ህፃናትን/ ወጣቶችን በእሳት ውስጥ እንዲጣሉ ያደረገው ማን ነው???

ሀ/አክዓብ
ለ/ ናቡከደነጾር
ሐ/ ዳርዮስ
መ/ኢዮሣፍጥ

//መልስ//፦ ለ) ናቡከደነጾር ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ5⃣ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ስንት ልጆች ነበሩት??

ሀ/ 11
ለ/ 12
ሐ/ 13
መ/14

//መልስ// ሐ/ 13 ናቸው።

✍ጥ.ተራ ቁጥር6⃣ ጥበብ ቤቷን ሠራች  ሰባቱንም ምሦሶዎችዋን አቆመች ያለው ማነው???

ሀ/ ንጉሥ ሳፆል
ለ/ ንጉሥ ዳዊት
ሐ/ ንጉሥ ሰሎሞን
መ/ ቅዱስ ጳውሎስ

//መልስ// ሐ) ንጉስ ሰሎሞን ነው።

✍ጥ.ተራ ቁ.7⃣እያሱና ሕዝበ እስራኤል በጩኸት ያፈረሱት የማነን ከተማ ቅጥር ነበር??

ሀ/ባቢሎን
ለ/ እስክንድርያ
ሐ/ ኢያሪኮ
መ/ አንፆኪያ

//መልስ//፦ሐ) ኢያሪኮ

✍ጥ.ተራ ቁጥር8⃣ከእስራኤል መሳፍንት ውስጥ የማይመደበው የትኛው ነው??

ሀ/ዲቦራ
ለ/ ዮፍታሔ
ሐ/ ሕዝቅያስ
መ/ ሶምሶን

//መልስ//፦ሐ) ሕዝቅያስ ነው።

✍ጥ.ተራ ቁጥር9⃣ንጉሥ ዳዊት ኦርዮንን በማስገደድ ሚስቱን እንደ ወሰደበት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይቺ የኦርዮን ሚስት ማን ትባላለች??

ሀ/ሩት
ለ/አስቴር
ሐ/ ቤርሳቤህ
መ/ ሜልኮል

//መልስ//፦ሐ) ቤርሳቤህ

✍ጥ.ተራ.ቁጥር🔟እስራኤል በሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ዘመን ለሁለት ተከፍለው ነበር፤ ስሜኑ እስራኤል የሚል ስም ወሰደ፤ የደቡቡ ስም ማን ይባል ነበር???
.ሀ/ ሰማርያ
ለ/  የሞዓብ ምድር
ሐ/ ከነዓን
መ/ ይሁዳ

//መልስ//፦መ) ይሁዳ

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣1⃣በአባቱ በንጉሥ ዳዊት ላይ ያመፀው ልጅ ማነው??

ሀ/ መቃቢስ
ለ/ ሰሎሞን
ሐ/ ይሁዳ
መ/አቤሴሎም

//መልስ//፦ መ) አቤሴሎም ነው።

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣2⃣ንጉሥ አክዓብ እስራኤልን የምትገለባበጥ አንተ ነህ ብሎ የተናገረው ማንነው??

ሀ/አብድዩ
ለ/ ኤልሳዕ
ሐ/ ኤልያስ
መ/መልስ የለም።

//መልስ//፦ ሐ) ኤልያስ

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣3⃣ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ መለከቱንም የሚነፉ መዘምራንም መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔር እያመሰገኑና እያከበሩ እግዚአብሔር ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ሲሉ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ከደመናው የተነሳ መቆምና ማገልገል አልቻሉም። ተብሎ የተ ፃፈው ለየትኛው በአል ነው??

ሀ/ ፍልስጤማውያን የመሸነፋቸው በዓል
ለ/ ለእግዚአብሔር ታቦት ቤተ መቅደስ ስለተሰራለት
ሐ/ ተማርካ የነበረችው ታቦተ ጽዮን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት በዓል

መ/ ኤልያስ የበኣልን ካህናት የማሸነፉ በዓላት

//መልስ//፦ ለ)

✍ጥ.ተራ.ቁጥር1⃣4⃣በመጽሐፍ ቅዱሳችን ጥራዝ፣ ከ2ኛ ዕዝራ በኋላ የሚመውጣ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማን ነው??

ሀ/ አስቴር
ለ/ ነህምያ
ሐ/ ዕዝራ ሱቱኤል
መ/ ጦቢት

//መልስ//፦ መ) መጽሐፈ ጦቢት

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣5⃣የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግስታት ሁሉ በይሁዳም ባላቸው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራበት ዘንድ አዞኛል፣ ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን። በማለት የተነገረው ማን ነው??

ሀ/ ንጉሥ ናቡከደነጾር
ለ/ ዕዝራ
ሐ/ የፋሪስ ንጉሥ ቄሮስ
መ/ ንጉሥ ኤዶምያስ

//መልስ//፦ ሐ) ዕዝ 1፥2

✍ጥ.ተራ ቁጥር 1⃣6⃣ወደላ ትባል የነበረችው የመርዶክዮስ እኅት ልጅ ማን ናት???

ሀ/ ርብቃ
ለ/ ራሔል
ሐ/ አስቴር
መ/ ሐና

//መልስ//፦ ሐ)አስቴር

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣7⃣ከሚከተሉት ውስጥ የዳዊት ሀብት የሆነው የትኛው ነው??

ሀ/ ፈውስ መስጠት
ለ/ በገና መደርደር
ሐ/ ኃይል
መ/ መ ሁሉ መልስ ነው።

//መልስ//፦ መ) ሁሉም


✍ጥ.ተራ.ቁጥር1⃣8⃣ከሚከተሉት ምሥጉን የሚል ቅጽል የሚያሰጠው ሥራ የትኛው ነው??

ሀ/ በክፉዎች ምክር ያልሄዱ
ለ/ በኃጢአት መንገድ አለመሄድ
ሐ/ በዋዘኞች ወንድበር አለመቀመጡ
መ/ ሁሉም መልስ ነው

//መልስ//፦ መ) መዝ.1፥1-3

✍ጥ.ተራ. ቁጥር2⃣0⃣ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። የሚለውን ሃይለ ቃል የተናገረው ማን ነው??

ሀ/ ነቢዩ ዳንኤል
ለ/ ነቢዩ እንባቆም
ሐ/ነቢዩ ዳዊት
መ/ ነቢዩ ኤርሚያስ

//መልስ// መ/ ነቢዩ ኤርሚያስ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...