2017 ዲሴምበር 13, ረቡዕ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሐሙስ

።ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ሐሙስ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።
።።።።።።።።።።።።።።።።።

፩ ርኵሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎኟ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች፥ የአብ ቃል በርሷ ሰዉ ሆኖዋልና እሳተ መለኮት /የመለኮቱ/ ባሕርይ አላቃጠ ላትምና። ከወለደችዉም በኋላ ድንግልናዋ አልተወለወጠምና፥ ሰዉ ቢሆን መለኮቱ አልተወለጠም። በእዉነት አምላክ ነዉና በእዉነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ፥ ሁላችን እናገንሻለን። ይቅርታሽ ለሁላችን ይሆን ዘንድ ነዉና። ሔዋን እንጨት በልታ ባደረገችዉ ዓመፅ በባሕርያችን ያደረ የቀድሞዉ እርግማን በእርሷ የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። ስለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ። ዳግመኛ ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን። ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን። ይኸዉም እኛን ስለ መዉደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ሥጋዉ፣ ክቡር ደሙ ነዉ። ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረዉን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለዉ ምን ልቡና ነዉ) መናገር የሚቻለዉ ምን አንደበት ነዉ) መስማት የሚቻለዉ ምን ጆሮ ነዉ) ሰዉን የሚወድ እግዚአብሔር አንድ ብቻ የሆነ አምላክነቱ ሳይለወጥ ከዓለም በፊት የነበረ የአብ ቃል ከአብ ዘንድ መጥቶ ልዮ ከሆነች እናቱ ሰዉ ሆነ፥ ከወለደችዉ በኋላም ድንግልናዋ አልተለወጠም። ስለዚህም አምላክን የወለደች እንደሆነች ታወቀች። የእግዚአብሔር የጥበቡ ስፋት ምን ይጠልቅ) በሳዕር በምጥ በልብ ጋር ትወልድ ዘንድ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት መገኛ ሆነች፥ ከባሕርያችን እርግማንን የሚያፋልንንም ያለ ወንድ ዘር ወለደችልን። ስለዚህም ሰዉን የምትወድ ሆይ ክብር ላንተ ይገባል፣ ቸርና የሰዉነታችን መድኃኒትም ነህ እያልን እናመስግነዉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።


፫ያለ ወንድ ዘር አምላክን የወለደች ድንግል የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይደንቅ) ለዮሴፍ የታየዉ መልአኩ «ከርሷ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደዉ ያለ መለወጥ ሰዉ የሚሆነዉ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ´ ብሎ መስክሯልና። ማርያም የዚህ ደስታ ዕጽፍ የሆነ እርሱን ወለደችዉ። መልአኩ «ልጅ ትወልጃለሽ፣ ስሙም ዐማኑኤል ይባላል´ አላት። ትርጵሜዉም፣ እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ሆነ ማለት ነዉ። ዳግመኛ ወገኖቹን ከኃጢአታቸዉ የሚያድናቸዉ ኢየሱስ ይባላል። በችሎታዉ /በኃይሉ/ ያድነን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለም ክብር ይግባዉና ሰዉ የሆነ እርሱን አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አዉቀነዋልና። ልዮ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችዉ፥ ልደቱንም ዘር አልቀደመዉም፣ በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠ ዉም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ፣ ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ሰገል ሰገዱለት አምላክ ነዉና ዕጣን አመጡለት፣ ንጉሥም ነዉና ወርቅ አመጡለት ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለዉ መዳኛችን ለሆነ ሞቱም ከርቤ አመጡለት። ቸርና ሰዉን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነዉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬ ከአዳም ገÖን አንዲት ዐፅም መንሣት ምን ይደንቅ) ከርሱ ሴትን ፈጠረ፥ የሰዉ ፍጥረትንም ሁሉ ፈረ። ጌታ የአብ ቃል ተሰጠ ከልዮ ድንግልም ሰዉ ሆነና ዐማኑኤል ተባለ፣ ስለዚህ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን ከተወደደ ልጅዋ ታማልደን ዘንድ። በቅዱሳንና በሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ ዘንድ ቸር ናት ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋለችና፣ ለነቢያትም ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና፥ ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ሰማዕታትና ምእመናንም የተጋደሉለት የጥበቡ ጸጋ ብዛት የማይታወቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዷል የይቅርታዉን ብዛት መርምረን እንወቅ /እንፈልግ/ መጥቶ አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ ብሎ ለዳዊት በእዉነት ማለ አይጸጸትም። ሳድቅ እርሱ /ዳዊት/ ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ፥ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈጸመ። ከዚህም በኋላ «እነሆ በኤፍራታ ሰማነዉ ብሎ በመንፈስ ቅዱስ አሰምቶ ተናገረ´ ይህቺዉም፣ ዐማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወለድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት። ዳግመኛም ከነቢያት አንዱ ሚክያስ አንቺ የኤፍራታ ክፍል የሆንሽ ቤተ ልሔም ከይሁዳ ነገሥታት መሳፍንት አገር አታንሺም፥ ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸዉ ንጉሥ ካንቺ ይወጣልና። ከዛሬ ጅምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከቸር አባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ምሥጋና ስለተገባዉ ስለ ክርስቶስ በአንድ መንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተናገሩ የነዚህ የሚክያስና የዳዊት ነገር ምን ይረቅ) ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮ ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ጠላቶቹ በተነሠሡበት ጊዜ ከቤተ ልሔም ምንጭ ዉኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ። የጭፍሮቹ አለቆች ፈጥነዉ ተነሠሡና በጠ ላቶቹ ከተማ ተዋግተዉ ሊጠጣ የወደደዉን አመጡለት። ሳድቅ ዳዊት ግን ጨክነዉ ሰዉነታቸዉን ስለ እርሱ ለጦርነት ለሞት አሳልፈዉ እንደሰጡ ባየ ጊዜ ያን ዉኃ አፈሰሰ ከእሱም አልጠጣም። ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠ ረለት። ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በዕዉነት ናቁ፣ ደማቸዉንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ። እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።


፯ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዮን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማሕፀን አደረ። ከብቻዋ ከኀጠአት በቀርም እንደኛ ሰዉ ሆነ፣ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩለት በቤተ ልሔም ተወለደ። ፈጽሞ አዳነን ወገኖቹም አደረገን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...