2017 ኦክቶበር 29, እሑድ

ድንግል ሆይ፤ ስደትሽ

https://youtu.be/SwwiaieJtD0

♥አጭር መነባንብ♥
////////////////////////

ድንግል ሆይ፤ ስደትሽ
እመብርሃን ሆይ የአምላክ እናት
ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ወጣሽ ለስደት
ውሃ ጥም ረሀቡ የአሸዋው ግለት
ሳይገባሽ አየሽ ብዙ እንግልት።
ስቃይሽ ብዙ ነው የደረሰብሽ
በግብፅ በረሃ እንባ እያፈሰስሽ
ልጅሽን እንዳይገሉት አዝለሽው ሸሸሽ
በሄድሽበት ሁሉ ፊት እየነሱሽ
የአምላክ እናት ስትሆኝ ሰዎች ግን ጠሉሽ
ልባቸው ደንድኖ ጠላት አውሮት
በአንቺና በልጅሽ አበዙ እንግልት
የተዓምራት ጌታ ሁሉን እየቻለ
ከእናቱ ጋራ ስደት ተካፈለ

////////////////////////
አንች ሶሎሜ ሆይ እስኪ ተናገሪ
እንዴት እንደነበር ስለ ስደቱ አውሪ
////////////////

ሶሎሜ፦
ያኔማ እንዲህ ነበር ታሪኩ ይዘከር
ድንግል ልጇን አዝላ በግብፅ በረሃ
በየሰው ሁሉ ደጃፍ ስትል ተጠማሁኝ ውሃ።
ጠላት ቀድሞ በልባቸው ገብቶ
ያስነቅፋት ነበር አፋቸውን ከፍቶ
እንባዋ ይፈሳል ቆሞ አያውቅም ከቶ።
ልጄን ይገሉታል እያለች በፍርሃት
እንጓዝ ትላለች በረሃ በረሃ ዳገት ቁልቁለት
ተከታትሎ ሄሮድስ ልጇን እንዳይገልባት።
ከዓኗ እንደሰን ውሃ እንባዋ ይፈሳል
ልቧ በጥልቅ ሐዘን እጅጉን ተጨንቋል
የሄሮድስ ጭካኔ የሰዉ ክፋት
ከበረሃው ጋራ ብዙ አንገላታት
ግብፅ በረሃ ላይ ሲፈፀም ትንቢት
ወደምስራቅ ዞሮ ኢትዮጵያን አያት
በአምላክነቱ በእጁ ባረካት
ልጄ ሆይ ምንድናት ይህች ሀገር
ብላ ጠየቀችው ተገርማ ድንግል
እናቴ እኔና አንቺን ስትቀድስ እምትኖር
ቅድስት ሀገር  አለች ኢትዮጵያን  እምትባል
በደመና ተጭና ኢትዮጵያን ባረከች
አስራት አርጎ ሰጣት ድንግል ተደሰተች
ጌታ ሆኖ ሳለ የሰው ስጋ ለብሶ
ብዙ ተንገላታ ስለእኛ ዐብሶ
የነቢያትን ትንቢት ለመፈፀም ወዶ
ከሰማየ ሰማይ ከድንግል ተወልዶ
ለ42 አውርሃ በግብፅ ተሰዶ
ነጻ አወጣን አምላክ የሰውን ልጅ ወዶ።.
////////////
ድንግል ሆይ፤ በስደትሽ ስደታችንን ባሪኪልን አሜን፫

@ተፃፈ በትዝታ አስፋው

2017 ኦክቶበር 28, ቅዳሜ

አምናና ዘንድሮ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም

አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ
እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ
ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ
አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ
ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ
ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር
ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር
ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ
በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ
ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር
ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር
ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል
ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል።

ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ
አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ
እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን
እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ?
አይ እንግዲህ!
ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ
ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ
ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው
በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው
አሁንስ?
እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው
ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው
በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ
በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል
እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል

አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ
አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ
ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል
ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል
ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል
ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል
ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ
በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ
የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ
ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ!

ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ
ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም
ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ
በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ
ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና
የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና
በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ
ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ
እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ
እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ
የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ
በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ

አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ
የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ
ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ
ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም
እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም
የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ
ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ
ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ
ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ
እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ
ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ።

ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ!
 አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ
የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ
የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ
መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ
ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ
በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ
ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ
እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ።

አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት
ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ
ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ
ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ
የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ
በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ
እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ
ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ
ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን
ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት
ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት
ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ
አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን
ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን
አጥር ሁንላት መከታ..
በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ
እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር
የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን
እመን ታሸንፋለህ ሁሉን
የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም
ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም
በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት
ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት
እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት
እና...


ዘንድሮ፦
እናማ...
መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን
ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን
ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን
በእምነት በሃይማኖት በምግባር
ጸንተን በቤቱ እንኑር
የበደለንን ክሰን ታርቀን
ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን
በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን
በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም
@ትዝታ አስፋው

መነባንብ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም

አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ
እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ
ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ
አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ
ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ
ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር
ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር
ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ
በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ
ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር
ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር
ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል
ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል።

ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ
አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ
እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን
እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ?
አይ እንግዲህ!
ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ
ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ
ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው
በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው
አሁንስ?
እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው
ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው
በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ
በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል
እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል

አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ
አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ
ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል
ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል
ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል
ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል
ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ
በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ
የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ
ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ!

ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ
ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም
ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ
በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ
ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና
የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና
በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ
ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ
እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ
እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ
የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ
በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ

አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ
የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ
ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ
ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም
እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም
የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ
ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ
ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ
ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ
እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ
ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ።

ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ!
 አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ
የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ
የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ
መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ
ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ
በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ
ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ
እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ።

አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት
ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ
ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ
ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ
የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ
በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ
እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ
ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ
ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን
ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት
ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት
ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ
አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን
ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን
አጥር ሁንላት መከታ..
በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ
እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር
የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን
እመን ታሸንፋለህ ሁሉን
የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም
ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም
በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት
ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት
እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት
እና...


ዘንድሮ፦
እናማ...
መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን
ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን
ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን
በእምነት በሃይማኖት በምግባር
ጸንተን በቤቱ እንኑር
የበደለንን ክሰን ታርቀን
ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን
በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን
በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም
@ትዝታ አስፋው

አምናና ዘንድሮ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም

አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ
እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ
ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ
አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ
ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ
ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር
ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር
ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ
በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ
ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር
ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር
ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል
ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል።

ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ
አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ
እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን
እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ?
አይ እንግዲህ!
ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ
ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ
ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው
በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው
አሁንስ?
እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው
ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው
በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ
በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል
እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል

አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ
አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ
ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል
ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል
ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል
ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል
ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ
በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ
የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ
ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ!

ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ
ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም
ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ
በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ
ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና
የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና
በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ
ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ
እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ
እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ
የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ
በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ

አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ
የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ
ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ
ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም
እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም
የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ
ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ
ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ
ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ
እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ
ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ።

ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ!
 አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ
የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ
የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ
መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ
ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ
በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ
ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ
እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ።

አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት
ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ
ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ
ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ
የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ
በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ
እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ
ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ
ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን
ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት
ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት
ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ
አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን
ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን
አጥር ሁንላት መከታ..
በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ
እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር
የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን
እመን ታሸንፋለህ ሁሉን
የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም
ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም
በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት
ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት
እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት
እና...


ዘንድሮ፦
እናማ...
መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን
ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን
ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን
በእምነት በሃይማኖት በምግባር
ጸንተን በቤቱ እንኑር
የበደለንን ክሰን ታርቀን
ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን
በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን
በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም
@ትዝታ አስፋው

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል። ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ? አይ እንግዲህ! ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው አሁንስ? እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ! ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ። ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ! አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ። አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን አጥር ሁንላት መከታ.. በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን እመን ታሸንፋለህ ሁሉን የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት እና... ዘንድሮ፦ እናማ... መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን በእምነት በሃይማኖት በምግባር ጸንተን በቤቱ እንኑር የበደለንን ክሰን ታርቀን ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም@ ትዝታ አስፋው


የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...