2018 ሴፕቴምበር 23, እሑድ

የምዕራፍ አምስት(፭) የ42ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫

የምዕራፍ (፭)/የ42ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የጹህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር⤵

@ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ⤵

ማጠቃለያ መልስ🖊
➡1⃣ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዌ በሐዋርያት አጠራር ትርጉሙ "የመጽናናት ልጅ" የሚሆን ስም ተሰጠው። የዚህ ሐዋርያ ስም ማን ነው?

ሀ. ፋሮስ
ለ.እስክንድሮስ
ሐ.አጵሎስ
መ. በርናባስ

✅መ

➡2⃣"ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ ነገር እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎቹ ሰምቻለሁ። በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው።" ተብሎ የተነገረው ስለ ማን ነው?

ሀ. ሐናንያ
ለ.ስምዖን
ሐ.ሳውል
መ.በርስያስን

✅ሐ

➡3⃣የሞት አያት ማን ነው?

ሀ. ኃጢአት
ለ.ተንኮል
ሐ.ምኞት
መ.ቁጣ

✅ለ

➡4⃣አጋቦስ ይባል የነበረው ነቢይ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ በመውረድ ምን ተነበየ?

ሀ. ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚታሰር
ለ. በምድር ላይ ራብ እንደሚመጣ
ሐ. ኢየሩሳሌም በሮማውያን ወታደሮች ፈጽማ እንደምትጠፋ
መ.ክርስትና በዓለም እንደሚሰበክ

✅ለ

➡5⃣አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ በክርስቲያኖች ዘንድ መከራን ያጸናው ንጉሥ ማን ነው?

ሀ. ሄሮድስ አንቲጳስ
ለ. ሄሮድስ ቀዳማዊ አግሪጳ
ሐ.ሄሮድስ ዳግማዊ አግሪጳ
መ.ጲላጦስ

✅ሐ

➡6⃣ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?" ያለው ሐዋርያ ማን ነው?

ሀ.ፊሊጶስ
ለ.ታዴዎስ
ሐ.ቶማስ
መ.ናትናኤል

✅መ

➡7⃣ከሐዋርያት መካከል  አስቀድሞ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የተናገረው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ. ቅዱስ ቶማስ
ሐ.ቅዱስ ናትናኤል
መ. ቅዱስ ፊልጶስ

✅ሀ

➡8⃣በሁለተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ አብሮ የነበረው ማን ነው?

ሀ.አቂላስ
ለ.ሲላስ
ሐ.ጵርስቅላ
መ.በርናባስ

✅ሐ

➡9⃣በሕልሙ የመቄዶንያ ሰው ለእርዳታ ሲጠራው ያየው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጳውሎስ
ለ.ቅዱስ ቲቶ
ሐ.ቅዱስ ሉቃስ
መ.ቅዱስ ጋይዮስ

✅ሀ

➡🔟ቅዱስ ጳውሎስ በአንድ ከተማ በሚመላለስበት ወቅት ሰዎች "ለማይታወቅ አምላክ" ብለው ጽፈው በመመልከቱ በማዘን ትምህርት አስተምሯቸዋል።
ከተማው የትኛው ነበር?

ሀ. ተሰሎንቄ
ለ.ቆሮንቶስ
ሐ.ኤፌሶን
መ.አቴና

✅መ

➡1⃣1⃣ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር አብረው ድንኳን ይሰፉ የነበሩት ማንና ማን ናቸው?

ሀ.ሲላስ እና ጢሞቴዎስ
ለ.አጵሎስ እና በርናባስ
ሐ. አቂላ እና ጵርስቅላ
መ.ማርቆስ እና ሉቃስ

✅ለ

➡1⃣2⃣ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልሞና በጻፈው መልእክቱ ማንን ይቅር እንዲል መክሮታል?

ሀ. አገልጋዩ ግያዝን
ለ.ውሸተኞች ወንድምችን
ሐ. አገልጋዩ አናሲሞስን
መ.መልስ የለም

✅ሐ

➡1⃣3⃣የክፋት ሁሉ ሥር ምንድን ነው?

ሀ. ትዕቢት
ለ.ቁጣ
ሐ.ዝሙት
መ.ገንዘብን መውደድ

✅መ

➡1⃣4⃣የልስጥራን ሰዎች ሁለት ሐዋርያትን ድያ እና ሄርሜን በማለት በአማልክቶቻቸው ስም ሰይመዋቸዋል። ሐዋርያቱ እነማን ነበሩ?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ
ለ.ቅዱስ ጢሞቴዎስ እና ቅዱስ ቲቶ
ሐ. ቅዱስ እንድርያስ እና ቅዱስ ታዴዎስ
መ.ቅዱስ በርናባስ እና ቅዱስ ጳውሎስ

✅መ

➡1⃣5⃣ከሐዋ መካከል በሰማዕትነት ያላለፈው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ.ቅዱስ ያዕቆብ
ሐ. ቅዱስ እንድርያስ
መ.ቅዱስ ዮሐንስ

✅መ

➡1⃣6⃣ቅዱስ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር ጦር ዕቃ ብሎ የሰየመው የትኛውን ነው?

ሀ. የእውነትን ቀበቶ
ለ.ለእግዚአብሔር ቃል
ሐ.የእምነት ጋሻ
መ. ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

➡1⃣7⃣በሐዋርያት ስም ዝርዝር የመጀመሪያውን ቦታ ይዞ የሚገኘው ማን?

ሀ. ቅዱስ እንድርያስ
ለ.ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ. ቅዱስ ጳውሎስ
መ. ቅዱስ ፊልጶስ

✅ለ

➡1⃣8⃣ዐበይት ነቢያት የሚባሉት ማን ማን ናቸው?

✅ኢሳያስ፣ ኤርምያስ፣ሕዝቅኤልና ዳንኤል  ናቸው።

➡1⃣9⃣ የተራራው ሥብከት ዐሥሩ ዐበይት ክፍሎች ማን ማን ናቸው??

✅ክፍል አንድ፦ ስለ አንቀጸ ብፁዓን/ማቴ 5፥3-12/

ክፍል ሁለት፦ስለ አንቀጸ ምግባር/ማቴ 5፥13-16

ክፍል ሦስት፦አጽንኦተ ሕግ/ማቴ 5፥17-48

ክፍል አራት፦ ሦስቱ አናቅጸ ምግባራት/ ማቴ 6፥1-8

ክፍል አምስት፦እግዚአብሔርን ማስቀደም እንዲገባ/ማቴ 6፥19-34

ክፍል ስድስት፦ አትፍረዱ/ማቴ.7፥1-6

ክፍል ሰባት፦ እንድንጸልይ መታዘዛችን/ ማቴ.7፥7-12

ክፍል ስምንት፦ቀጭን መንገድ በጠባቡ በር/ማቴ. 7፥13-14

ክፍል ዘጠኝ፦ መልካም ፍሬ ከመልካም ዛፍ/ ማቴ.7፥15-20

ክፍል አስር፦ ጽድቅ በተአምራት ሳይሆን በሥራ ስለመሆኑ/ማቴ 7፥21-29

➡2⃣0⃣በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ በገና፣ዋሽን፣ጸናጽል፣ከበሮ፣እምቢልታ፣ ነጋሪት፣መለከት፣ መሰንቆ ተጽፎ የምናገኘው በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው?

✅በገና፣መሰንቆ፣ነጋሪት፣ጽናጽል 2ኛ.ሳሙ 6፥5
ዋሽንት፣ክራር ት.ዳ. 3፥5/ ዘፍ.4፥21/ከበሮ፣እንቢልታ/ኢሳ.5፥12/ዘዳ.15፥20/መለከት/1ኛ.ነገስት 1፥40/

ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!saramareyama.890@gmail.com

8 አስተያየቶች:

  1. ፀጋ እግዚአብሔር ያብዛልሽ //ህ በእውነት ቀጥሉበት

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. እግዚአብሔር ይርዳሽ በተረፈ ቀጥሉበት

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. በዕውነቱ መዛኝ አስተማሪ የሚያበረታታ ነው

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  4. በጣም ጠቃሚ እና አሥተማሪ ጥያቄወች ናቸው

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  5. በጣም ጠቃሚ ጥያቆዎች ናቸው፣ቃለ ህይወትን ያሰማልን.

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  6. The 3D titanium white dominus slot machine game
    The apple watch series 6 titanium 3D titanium white dominus slot titanium touring machine game titanium tv is designed using a simple titanium straightener design, the 5.0x5 layout, the maximum payout titanium wood stove is the highest on an

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...