2018 ኦገስት 27, ሰኞ

የምዕራፍ ፭ የ41ኛ ዙር መንፈሳዊ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡አሜን!
`````````````
የምዕራፍ (፭) 41ኛ ዙር

በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ ለተዘጋጀው ጥያቄ እና መልስ መርሐ-ግብር ከአዘጋጁ አካል የማጠቃለያ መልሱ እንደሚከተለው ይቀርባል።
   ✝✝✝


1.የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የትኛው ነው?
ሀ.አብርሃም
ለ.ሔኖክ
ሐ.ሙሴ
መ.ያዕቆብ

✔️ለ

2.ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ዘመን እስራኤላውያን በተለያዪ ቡድኖች ተክፍለው ነበር።እነርሱም፡
ሀ.ሰማርያና ሴኬም
ለ.ሮማዊያን እና እስራኤላውያን
ሐ.ፈሪሳውያን፣ሰዱቃውያን እና ኤሲያውያን
መ.ሰሜን እና ደቡብ እስራኤል

✔️ሐ

3. የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተ-ክርስቲያን የተሠራችው በየትኛዋ ከተማ ነበር?
ሀ.በፊሊጵስዩስ
ለ.በአንጾኪያ
ሐ.በደማስቆ
መ.መልሱ የለም

✔️ሀ

4.የሙሴን ሕግ በጥንቃቄ እንተረጉማለን ሚሉት የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ፈሪሳውያን
ለ.ኤሲያውያን
ሐ.ሰዱቃውያን
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️ሀ

5.ሊቀ-ሐዋርያት ተብሎ ሚታወቀው ማን ነበር?
ሀ.ቅዱስ ቶማስ
ለ.ቅዱስ ዮሐንስ
ሐ.ቅዱስ ታዴዎስ
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️መ

6.ከቅዱሳት አንስት ወገን ያልሆኑት የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ቅድስት ኤልሳቤጥ እና ቅድስት ሀና
ለ.ጤግላና ጲስ
ሐ.ጲላግያና መሪና
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️መ

7.ከምሥጢር ሐዋርያት መካከል ያልሆነ፡
ሀ.ዮሐንስ
ለ.ያዕቆብ-ወልደ ዘብዴዎስ
ሐ.ጴጥሮስ
መ.ያዕቆብ-ወልደ እልፍዮስ

✔️መ

8.«ይሁዳ»ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ.ፍቁረ-እግዚእ
ለ.ዓለት
ሐ.በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው.
መ.ጸጋ የበዛለት ማለት ነው።

✔️ሀ

9.የኒቂያ ጉባኤ ሰብሳቢ ማን ነበር?
ሀ.ቄርሎስ
ለ.እለስክንድሮስ
ሐ.ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ
መ.ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

✔️ለ

10.በቁስጥንጥንያው ጉባኤ ዋነኛው መናፍቅ ማን ነበር?
ሀ.ንስጥሮስ
ለ.መቅዶንዮስ
ሐ.አርዮስ
መ.አውጣቂ

✔️ለ

11.ከሚከተሉት የእስክንድርያ ሊቃነጳጳሳት መካከል«የቤተክርስቲያን ምሰሶ»ሚባለው ማን ነው?
ሀ.ቅዱስ እለስከንድሮስ
ለ.ቅዱስ ቄርሎስ ቀዳማዊ
ሐ.ቅዱስ አትናቴዎስ
መ.ቅዱስ ቄርሎስ 6ኛ

✔️ሐ

12.አቡነ ቄርርሎስ ቀዳማዊ ለእስክንድርያ ቤተ-ክርስቲያን በቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ስንተኛው ፓትርያርክ ነው?
ሀ.12
ለ.23
ሐ.24
መ.32

✔️ሐ

13.በነገረ ሥጋዌ ላይ የ«እውነተኛ ተዋህዶ-Real Unification»ሚልን ቀመር ያዘጋጀ ማን ነበር?
ሀ.ቅዱስ ቄሮሎስ ቀዳማዊ
ለ.ቅዱስ አትናቴዎስ
ሐ.ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️ሀ

14.የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቡነ ባስልዮስ የምንኩስና(የቆብ) ስማቸው ማን ነበር?
ሀ.ንቡረእድ ገብረማርያም
ለ.እጨጌ ገብረጊዮርጊስ
ሐ.ፓትርያርክ ገብረእግዚአብሔር
መ.እጨጌ ተክለሃይማኖት

✔️ለ

15.ምንፍቅና የተጀመረው በማን ነበር?
ሀ.በሳጥናኤል
ለ.በይሁዳ
ሐ.በአርዮስ
መ.በዱዲያኖስ

✔️ሀ

16.በሐዋርያት ጊዜ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ መናፍቃን እነማን ናቸው?
ሀ.ግኖስቲኮች
ለ.አርዮሳውያን
ሐ.ቢጽሐሳውያን
መ.ሁሉም ነበሩ

✔️ሐ

17.ፍልስፍና፣ጥንቆላ እና ምትሐታዊ ሕይወት የነበራቸው የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ግሪኮች
ለ.ቢጽ ሐሳውያን
ሐ.ይሁዳውያን
መ.ግኖስቲኮች

✔️መ

18.የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሲያን ቅጽል መጠሪያዋ ምንድን ነው?
ሀ.ጎርጎርዮሳዊት
ለ.ያዕቆባዊት
ሐ.እስጢፋኖሳዊት
መ.ማርቆሳዊት

✔️ለ

19.የመጀመሪያው የዓለም አብያተ-ክርስቲያናት ኅብረት ጉባኤ የተካሄደው የት ነበር?
ሀ.ኢቫንስተን-አሜሪካ
ለ.ናይሮቢ-ኪንያ
ሐ.ኤፕሳላ-ስዊድን
መ.አምስተርዳም-ሆላንድ

✔️መ

20.የመላው አፍሪካ አብያተ-ክርስቲያናት አንድነት ጽ/ቤቱ የት ይገኛል?
ሀ.አዲስአበባ-ኢትዮጵያ
ለ.ናይሮቢ-ኬንያ
ሐ.ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪካ
መ.አክራ-ጋና

✔️ለ

ማጠቃለያ መልሳችን ላይ ስህተት ካለ እርሙን።
saramareyama.890@gmail.com

2018 ኦገስት 16, ሐሙስ

ቡሔ ማለት ምን ማለት ነው,,??


Watch "እንኳን ለቡሔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!" on YouTube
https://youtu.be/EmL0XMJP-d0
"ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው"??
የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡

በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡

ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህል፣ ፣ ጌሾ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡
የበዓሉ እረዴት በረከት ይደርብን
አሜን
ወስብሀት እግዚአብሔር

2018 ኦገስት 14, ማክሰኞ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የምዕራፍ አራት(፬) የ40 ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር

@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው  ከሚለው   መጽሐፍ የተወሰደ⤵

➡1⃣ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ያለፉባት ከተማ ማን ትባላለች???
ሀ/ አንጾኪያ
ለ/ ሰማርያ
ሐ/ሮም
መ/ መቄዶንያ

✅ሐ

➡2⃣ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ በነበረበት ወቅት ከሰይጣን የቀረበለት ፈተና ምን ነበር??

ሀ/ የትዕቢት
ለ/ የስስት
ሐ/ የፍቅረ ነዋይ
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

➡3⃣ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ በላከው የመጀመርያ መልእክቱ ላይ በመጥፎ ምግባሩ ምክንያት አንድን ሰው ከመካከላቸው እንዲያስወግዱት ነግሮቸው ነበር። ሁለተኛ መልእክቱ ላይ ስለዚህ ሰው ምን አላቸው??

ሀ/ እስካሁ ባለማበረራቸው ተበሳጨ
ለ/ ይቅር እንዲሉት መከራቸው
ሐ/ ማንም ሰው እንዳያናግረው ፈረደበት
መ/ መልስ የለም

✅ለ. 1ኛ.ቆር,5፥4-5

➡4⃣ቅዱስ ጳውሎስ ከነዚህ እቃዎች መካከል ሰዎችን በምን መስሏቸዋል???

ሀ/ በሸክላ እቃ
ለ/ በጠርሙስ
ሐ/ በማንኪያ
መ/ በመጥረቢያ

✅ሀ

➡5⃣ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጴጥሮስን በአንጾኪያ ከተማ ፊት ለፊት የተቀዋወመው ለምን ነበር??

ሀ/ የስህተት ትምህርት በማስተማሩ
ለ/ ራሱን ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመለየቱ
ሐ/አይሁድን ሲያይ ከአሐዛብ ጋር የነበረውን ግንኙነት በማቋረጡ
መ/መልስ የለም

✅ሐ..
➡6⃣ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ መጀመርያ የታየው ለማን ነው??

ሀ/ ለሰሎሜ
ለ/ ለማርያም መግደላዊት
ሐ/ ለቅዱስ ጴጥሮስ
መ/ ለአርማትያሱ ዮሴፍ

✅ለ

➡7⃣በመጀመርያ ለአገልግሎት የተመረጡ ዲያቆናት ብዛት ስንት ነው?

ሀ/ 5
ለ/ 6
ሐ/ 7
መ/ 1

✅ሐ.

➡8⃣መልካም ዕድልን መረጠች ከእርሷም አይወሰድባትም ብሎ ክርስቶስ የተናገረላት ሴት ማን ናት???

ሀ/ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ለ/ ኤልሳቤጥ
ሐ/ ማርያም የአላዛር እኅት
መ/ ማርያም መግደላዊት

✅ሐ.

➡9⃣ስለ ጽድቅ የሚራቡ ብፁዓን ናቸው??

ሀ/መጽናናት ያገኛሉና
ለ/ ምድርን ይወርሳሉና
ሐ/ ይጠግባሉና
መ/ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና

✅ሐ.

➡1⃣0⃣በሌላ ስሙ "የቅዱስ ጴጥሮስ ወንጌል በመባል የሚታወቀው የወንጌል ክፍል የትኛው ነው?

ሀ/ የማቴዎስ ወንጌል
ለ/ የማርቆስ ወንጌል
ሐ/የሉቃስ ወንጌል
መ/ የዮሐንስ ወንጌል

✅ለ

➡1⃣1⃣የሕዝብ መምህር በመባል የሚታወቀው ሐዋርያ ማን ነው?

ሀ/ ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ ቅዱስ ጳውሎስ
ሐ/ ቅዱስ ታዴዎስ
መ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ

✅ለ

➡1⃣2⃣ከዐራቱ ወንጌላዊያን መካከል በንስር የሚመሰለው ማን ነው??

ሀ/ ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ ቅዱስ ሉቃስ
መ/ ቅዱስ ዮሐንስ

✅መ.

➡1⃣3⃣ከሚከተሉት ቋንቋዎች መካከል መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመርያ ያልተፃፈበት የትኛው ነው??

ሀ/ ፅርዕ/ግሪክ/
ለ/ ዕብራይስጥ
ሐ/ዐረብኛ
መ/ አረማይክ

✅ሐ

➡1⃣4⃣ከሚከተሉት ከተሞች መካከል ቅዱስ ጳውሎስ ያልጎበኘው የትኛው ነው??

ሀ/ አንጾኪያ
ለ/ አቴና
ሐ/ እስክንድርያ
መ/ ቤርያ

✅ሐ.

➡1⃣5⃣የጠፋው ልጅ ታሪክ በየትኛው የወንጌል ክፍል ይገኛል??

ሀ/ በማቴዎስ ወንጌል
ለ/በማርቆስ ወንጌል
ሐ/በሉቃስ ወንጌል
መ/ በዮሐንስ ወንጌል

✅ሐ.

➡1⃣6⃣የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የተቀበለው በማን አማካኝነት ነው??

ሀ/ በቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ በቅዱስ ጳውሎስ
ሐ/ በቅዱስ ዮሐንስ
መ/በቅዱስ ጢሞቴዎስ

✅ሀ

➡1⃣7⃣ክርስቶስ ሊሰቀል ባለበት ሰዓት የሚያስጨንቅ ሕልም ያየችውና ባሏ እንዲጠነቀቅ የመከረችው የማን ሚስት ነበረች??

ሀ/ የሊቀ ካህናት ሐና
ለ/የጲላጦስ
ሐ/የሄሮድስ
መ/የአግሪጳ

✅ለ

➡1⃣8⃣እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ዮሴፍና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ከስደት መልስ የኖሩበት ከተማ__ነው??

ሀ/ ናዝሬት
ለ/ ቤተልሄም
ሐ/ቅፍርናሆም
መ/ኢያሪኮ

✅ሀ

➡1⃣9⃣"ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም" ብሎ ጌታችን  ስለነማን ነው የተናገርው??

ሀ/ ቤተ ክርስቲያንና ሰይጣን
ለ/የራሳችን ፍላጎትና የእግዚአብሔር ፍላጎት
ሐ/እግዚአብሔርና ገንዘብ
መ/መልስ የለም

✅ሐ

➡2⃣0⃣የቅዱስ ጴጥሮስ አማት በሽታዋ ምን ነበር??

ሀ/ለምጽ
ለ/ፍርሃት
ሐ/ንዳድ
መ/ደም መፍሰስ

✅ሐ
🌹🌹🌹🌹🌹
ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ከስተታችን አርሙን.?
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜንsaramareyama.890Gmail.com

2018 ኦገስት 9, ሐሙስ

የምዕራፍ (፬)የ39ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝#በስመ #አብ #ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፫
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄና መልሶች⤵
የምዕራፍ አራት(፬)/የ39ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የጹህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር⤵
ምንጭ ማሕበረ ቅዱሳን 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ⤵
➡️ማጠቃለያ መልስ
_1⃣ቅዱስ እስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ ተይዞ በሐሰት ተከሷል ክሱ ምን ነበር ❓_
_ሀ// ዓመጽ አነሳስቷል_
_ለ// ሰንበትን ሽሯል_
_ሐ// ሙሴን እና እግዚአብሔርን ተሳድቧል_
_መ// ፊቱ እንደ መልአክ አብርቷል_
✅ሐ. ሐዋ 6፥11
_2⃣የህግ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው ❓_
_ሀ// ጽድቅ_
_ለ// አስርቱ ትእዛዛት_
_ሐ// መሥዋዕት_
_መ// ፍቅር_
✅.መ. ፍቅር
_3⃣ሐዋርያት በበዓለ ጰንጠቆስጤ የተሰባሰቡባት ቤት የማን ቤት ናት❓_
_ሀ// የማርቆስ እናት_
_ለ// የማርያም ባውፍልያ_
_ሐ// የበርናባስ ወንድም ሚስት_
_መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ_
✅ሀ.የማርቆስ እናት ቤት
_4⃣በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ ለሐዋርያነት ከማትያስ ጋር ሐዋርያት ያቆሙት ማንን ነበር❓_
_ሀ// ኢዮስጦስ_
_ለ// ዮሴፍ_
_ሐ// በርስያን_
_መ// ሁሉም መልስ ይሆናል_
✅መ.ሐዋ.1፥23
_5⃣በሐዋርያት ሥራ <<ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው ፣በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።>> ተብሎ እንደተጻፈው አይሁድ በገረፉአቸው ግዜ ሐዋርያት ምን አደረጉ❓_
_ሀ// ለግዜው ዝም እንበል ብለው ቃሉን ከመስበክ ተከለከሉ_
_ለ// ወደ ሌላ አገር ተበታተኑ_
_ሐ// ወደ ቀድሞ ሥራቸው ተመለሱ_
_መ// እንዲያውም ዕለት ዕለት በመቅደስ እና በቤታቸው ስለ ጌታችን ያስተምሩ እና ይሰብኩ ነበር_
✅መ.
_6⃣ሳኦል ክርስቲያኖችን ያሳድድ ዘንድ ወደ ደማስቆ በቀረበ ግዜ <<ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ>> ሳኦል ከጌታችን ምን ማድረግ እንደሚገባው ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ ያልቻለው ምንድን ነው❓_
_ሀ// መራመድ_
_ለ// ማየት_
_ሐ// መናገር_
_መ// መስማት_
✅ለ.
_7⃣በአይሁድ ሸንጎ ፊት በቀረበ ወቅት መጽሐፍ ቅዱስን ከብሉይ እስከ ሀዲስ ኪዳን ያስተማረው ሰማዕት ማነው❓_
_ሀ// ቅዱስ ጴጥሮስ_
_ለ// ቅዱስ ቶማስ_
_ሐ// ቅዱስ ጳውሎስ_
_መ// ቅዱስ እስጢፋኖስ_
✅መ
_8⃣በግሪክ ቋንቋ "አቡቀለምሲስ"የሚባለው መጽሐፍ የትኛው ነው❓_
_ሀ// ትንቢተ ዳንኤል_
_ለ// ኦሪት ዘዳግም_
_ሐ// መዝሙረ ዳዊት_
_መ// የዮሐንስ ራእይ_
✅መ.
_9⃣ሐሙስ ማታ በጌታችን የመጨረሻዋ ሰዓት ጌቴሴማኒ የተገኙት .......❓_
_ሀ// ቅዱስ እንድርያስ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ_
_ለ// ቅዱስ ጴጥሮስ ፣ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅዱስ ያዕቆብ_
_ሐ// ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅዱስ እንድርያስ _
_መ// ቅዱስ ማቴዎስ ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅዱስ ጳውሎስ_
✅ለ.
_ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሁለት ግዜ መልዕክት የጻፈላቸው የትኞቹ ናቸው❓_
_ሀ// የፊልጵስዩስ ሰዎች_
_ለ// የቆላስይስ ሰዎች_
_ሐ// የተሰሎንቄ ሰዎች_
_መ// የኤፌሶን ሰዎች_
✅ሐ
_1⃣1⃣ከአራቱ ወንጌላውያን በሰው የሚመሰለው ማነው❓_
_ሀ// ቅዱስ ዮሐንስ_
_ለ// ቅዱስ ሉቃስ_
_ሐ// ቅዱስ ማርቆስ_
_መ// ቅዱስ ማቴዎስ_
✅መ.
_1⃣2⃣የቅዱስ ጳውሎስ መምህር የነበረው ማን ነው ❓_
_ሀ// ኒቆዲሞስ_
_ለ// ታዴዎስ_
_ሐ// ፊልክስ_
_መ// ገማልያል_
✅መ
_1⃣3⃣ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እርገት  አስቀድሞ በትንቢት የተናገረው ማን ነው❓_
_ሀ// ቅዱስ ሙሴ_
_ለ// ንጉሥ ዳዊት_
_ሐ// ነብዩ ኢሳያስ_
_መ// ነብዩ ዳንኤል_
✅ለ
_1⃣4⃣ከሚከተሉት መካከል መርዘኛ እባብ ነድፎት ያልተጎዳው ማን ነው ❓_
_ሀ// ቅዱስ በርናባስ_
_ለ// ቅዱስ ጴጥሮስ_
_ሐ// ዮሐንስ መጥመቀ መለኮት_
_መ// ቅዱስ ጳውሎስ_
✅መ.
_1⃣5⃣ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆ ሊገድሉት ከነበሩት አይሁድ አምልጧል ።_
_በምን አይነት ሁኔታ ነበር ያመለጠው❓_
_ሀ// ፊቱን በመሸፋፈንና ሌላ ሰው በመምሰል_
_ለ// በቅርጫት ውስጥ ከከተማው ግንብ በመሻገር_
_ሐ// ተአምር በመስራት_
_መ// እዛው ከተማ ውስጥ በመደበቅ_
_ሠ// መልሱ አልተሰጠም_
✅ለ.
_1⃣6⃣ቅዱስ ጴጥሮስ ከሞት ያስነሳት ጣቢታ የምትባል ደገኛ ሴት ነበረች በግሪክ ቋንቋ የስሟ ትርጓሜ ምን ነበር❓_
_ሀ// ጵርስቅላ_
_ለ// አሌክሳንድራ_
_ሐ// ፌበን_
_መ// ዶርቃ_
✅መ.
1⃣7⃣ከሐዋርያት መካከል ሰማዕትነትን ለመቀበል የመጀመሪያ የሆነው ማን ነው
_ሀ// ቅዱስ እስጢፋኖስ_
_ለ// ቅዱስ ያዕቆብ_
_ሐ// ቅዱስ ቶማስ_
_መ// ቅዱስ ጴጥሮስ_
✅ለ.
_1⃣8⃣ክርስቶስ አልዓዛርን ከሙት ያስነሳበት ታሪክ በየትኛው ወንጌል ላይ ይገኛል❓_
_ሀ// የማቴዎስ ወንጌል_
_ለ// የማርቆስ ወንጌል_
_ሐ// የሉቃስ ወንጌል_
_መ// የዮሐንስ ወንጌል_
✅መ.
_1⃣9⃣ቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ እስኪለያዩ ድረስ ያልተስማሙበት  ሀሳብ ምን ነበር❓_
_ሀ// ቅዱስ በርናባስ ወደ ቆጵሮስ ለመሄድ ስለፈለገ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሮምን ስለመረጠ_
_ለ// ቅዱስ ማርቆስ አብሯቸው እንዲሆን በርናባስ በመፈለጉ ምክንያት_
_ሐ// በነገረ መለኮት ትምህርት ባላመስማማታቸው_
_መ// ቅዱስ በርናባስ_
✅ለ.
_2⃣0⃣ከሚከተሉት ውስጥ በአራቱም ወንጌላውያን ተፅፎ የሚገኘው  የትኛው ነው❓_
ሀ//የዘሩው ምሳሌ
ለ// የጠፋው ልጅ ምሳሌ
ሐ/የክርስቶስ ስቅለት
መ/የበለስ መርገም

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

2018 ኦገስት 4, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬)የ38ኛዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፫

↪የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄና መልስ↩

➡ማጠቃለያ መልስ⤵

የምዕራፍ አራት(፬)/የ38ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር

@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ⤵

➡1⃣ከሚከተሉት ውስጥ ከሐዋርያው  ቅዱስ ጳውሎ ጋር በጉዞ የተሳተፈው ማን ነው??
ሀ/ቲቶ
ለ/ ሉቃስ
ሐ/ጢሞቴዎስ
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

➡2⃣የመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ አንገት እንድትቆረጥ ያደረገው ማን ነው??

ሀ/ጢባርዮስ ቄሳር
ለ/ፊልክስ
ሐ/ ሄሮድስ
መ/ፈርዖን

✅ሐ.

➡3⃣ከመጠራቱ አስቀድሞ ከሰዱቃውያን ወገን የሆነው ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/ ሉቃስ
ለ/ ሰምዖን
ሐ/ቶማስ
መ/ታዴዎስ

✅ሐ

➡4⃣ጴጥሮስ ለስምዖን፣ ማቴዎስ ለሌዌ፣ ቶማስ ፣ ታዴዎስ ለ___ ነው?

ሀ/ሳውል
ለ/ልብድዮስ
ሐ/ናትናኤል
መ/ለዲዲሞስመ/ስምዖን ቀነናዊ

✅ለ.

➡5⃣"ጌታችን የኢያአሮስን ልጅ ከሙታን በአስነሳ ጊዜ አብረውት የነበሩት ደቀ መዛሙት እነማን ነበሩ??

ሀ/ 12ቱ የሐዋርያት
ለ/ጴጥሮስ፣ እንድርያስ
ሐ/ ዮሐንስ፣ያዕቆብና ጴጥሮስ
መ/ያእቆብ፣ፊልጶስ፣እንድርያስ ያዕቆብ

✅ሐ.

➡6⃣"አብን አሳየንና ይበቃናል። ያለው ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/እንድሪያስ
ለ/ዮሐንስ
ሐ/ፊልጶስ
መ/ጴጥሮስ

✅ሐ.

➡7⃣ለአብ መርዓቱ ለወልድ ወላዲቱ፣ ወለመንፈስ ቅዱስ ___

ሀ/ታቦት
ለ/ ጽርሐ ቤቱ
ሐ/እናቱ
መ/ መልስ የለም

✅ለ.

➡8⃣ከዐራቱ ወንጌላውያን መካከል ሐኪምም ሠዓሊም የነበረው ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ቅዱስ ሉቃስ
መ/ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሐ.

➡9⃣ጌታችን ደጋግሞ እኔ ነኝ በማለት ያስተማረው ትምህርት በየትኛው የወንጌል ክፍል ላይ ይገኛል?

ሀ/በማቴዎስ ወንጌል
ለ/ በማርቆስ ወንጌል
ሐ/በሉቃስ ወንጌል
መ/ በዮሐንስ ወንጌል

✅መ.

➡🔟ጌታችን በአዛኙ ሳምራዊ ምሳሌ የመሰለው ምን በመጠየቁ ነው??

ሀ/ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው
ለ/የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ
ሐ/ ባልንጀራዬ ማን ነው?
መ/ለሌሎች እንዴት  መልካም እናድርግ

✅ሐ.

➡1⃣1⃣ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስንት መልእክታትን ጽፏል??

ሀ/12
ለ/14
ሐ/15
መ/7

✅ለ.

➡1⃣2⃣ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ያጠመቀው ማን ነው?

ሀ/ ቅዱስ እስጢፋኖስ
ለ/ ቅዱስ ፊሊጶስ
ሐ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ
መ/ ቅዱስ ቲቶ

✅ለ.

➡1⃣3⃣ክርስቶስ ሊሰቀል ወደ ጎለጎታ በሚሄድበት ወቅት መስቀሉን ይሸከም ዘንድ ግድ ያሉት ሰው ማን ነው?

ሀ/አሌክሳንድሮስ
ለ/ሩፎስ
ሐ/ የአርማትያሱ ዮሴፍ
መ/የቀሬናው ስምዖን

✅መ.

➡1⃣4⃣የቁም ተዝካሩን/ሀብቱን በመጽውቶ/በማውጣት ጌታን የተከተለው ወንጌላዊ ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ቅዱስ ሉቃስ
መ/ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሀ.

➡1⃣5⃣ትንሳዔ ሙታን የለም ይሉ የነበሩት እነማን ነበሩ??

ሀ/ፈሪሳውያን
ለ/ሰዱቃሰዱቃውያን
ሐ/ኤሴያውያን
መ/መለካውያን

✅ለ

➡1⃣6⃣ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር አይደለም?

ሀ/ ጢምቲዎስ
ለ/ቲቶ
ሐ/ሉቃስ
መ/አፍሮዲ
ሠ/ሲላስ
ረ/እስጢፋኖስ

✅ረ

➡1⃣7⃣ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ የአይሁድ ንጉሥ፣ የናዝሪቱ ኢየሱስ የሚለው ጽሑፍ በሦስት ቋንቋዎች ተጽፏል።ከሚከተሉት ውስጥ ያልተፃፈበት ቋንቋ የትኛው ነው??

ሀ/ሮማይስጥ
ለ/ሱርስት
ሐ/ግሪክ
መ/ዕብራይስጥ

✅ለ

➡1⃣8⃣መጽሐፍ ቅዱስ 66 ብቻ ሳይሆን 81 እንደሆነ ለማጠየቅ ከመጽሐፈ ሄኖክ የጠቀሰ ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ያዕቆብ
ለ/ቅዱስ ቶማስ
ሐ/ቅዱስ በርተሎሜዎስ
መ/ቅዱስ ይሁዳ

✅.መ.

➡1⃣9⃣ከሚከተሉት ውስጥ የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት እንደሚያደርግ የተጻፈለት ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ቅዱስ ዮሐንስ
ሐ/ቆርኔሌዎስ
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ.

➡2⃣0⃣ሐናንያና ሰጲራ መሬት ሽጠው ወደ ሐዋርያቱ እግር ሥር አምጥተው ነበር። ነገር ግን ሁለቱም በሞት ተቀስፈዋል፣ በምን ምክንያት.?

ሀ/ የሰው መሬት በመሸጣቸው
ለ/ከመሬቱ ሽያጭ አስቀርተው እኩሌተውን በመስጠታቸው
ሐ/በሐዋርያቱ ላይ በማጉረምረማቸው
መ/መልስ የለም

✅ለ.

🖊ማጠቃለያ መልስ ይህ ይመስላል ስተት ከአለ አርሙን.?

✝ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜንsaramareyama@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...