2018 ጃንዋሪ 31, ረቡዕ

#በዮናስ #ስብከት ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት(2) ተመልሶ አረገ(2) በኅዘን በጸሎት (2) ስለሆነ ከልብ የኀዘናቸው ምንጩ ነበር እንደ ራሔል(2)እንባን እየረጩ(2) ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ(2) ጋሻና ጦራቸው(2) ጾም ጸሎት ነበረ (2) እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ(2) በዮናስ ስብከት(2) ጾም ጸሎት ተማሩ(2) #ለሰብአ #ነነዌ ለሰብአ ነነዌ/፪/ አዉጻእኮሙ /እም ማዕከለ እሳት/፬/ ትርጉም:-የነነዌ ሰዎችን ከእሳት መካከል አወጣሃቸው።

https://youtu.be/uc8QTI48fD8



#በዮናስ #ስብከት


ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት(2)
ተመልሶ አረገ(2) በኅዘን በጸሎት (2)
         
ስለሆነ ከልብ የኀዘናቸው ምንጩ
ነበር እንደ ራሔል(2)እንባን እየረጩ(2)

ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ(2)
ጋሻና ጦራቸው(2) ጾም ጸሎት ነበረ (2)

እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ(2)
በዮናስ ስብከት(2) ጾም ጸሎት ተማሩ(2)

#ለሰብአ #ነነዌ

ለሰብአ ነነዌ/፪/
አዉጻእኮሙ /እም ማዕከለ እሳት/፬/

ትርጉም:-የነነዌ ሰዎችን ከእሳት መካከል አወጣሃቸው።saramareyama.890.gmail.com

መንፈሳዊ የግጥም መድብል

እመቤቴ ማርያም የአምላክ እናት
እጅጉን ይደንቃል ያንችስ አሟሟት
በጥር 21 በክብር አርፈሽ
ስለ ኃጥዓን ስትይ ለመሞት ፈቀድሽ
አይሁድ በክፋት በአመጽ ተነስተው
እናቃጥላት አሉ ቅድስናሽን ስተው
ልጅሽ ይህን አይቶ መቼ ዝም አላቸው
መላእክትን ልኮ ተዓምር አሳያቸው
ክብርት ሥጋሽንም ነጠቁ ከእጃቸው
በክብር አኖርላሽ ከገነት አግብተው
የጌታ ቀን ደርሶ ትንሳኤሽን እስኪያዩ
ቅዱስን ሐዋርያትም በፆም ጸሎት ጸኑ
እግዚአብሔር ፈቅዶ እስክልሚደርስ ቀኑ
ያሟሟትሽን ነገር እጹብ እጹብ አሉ
እውነት ነው ይደንቃል የአምላክ እናት
እኛም እንድንድን ከሲዖል እሳት
እመ አምላክ አደራ ምልጃሽ አይለየን
እንደመናፍቃን እንደማያምኑ ሳይሆን
ሞትሽን በጥር ወር ነሐሴ መቃብር
ትንሳኤና እርገትሽን ሁሉን እናምናለን
ሐዋርያት አበውን አብነት አድርገን
እጹብ ድንቅ እያልን እናወድሳለን
እስከ ለዘለዓለም ብጽሒት እንላለን።

@ከ ወለተ ሥላሴ

♥♥♥♥♥♥♥♥

ጌታ ሆይ
አሁን በዚህ ስአት ፊትህ ተደፍቼ እንዲህ ምለምንህ ፣
አንድ ነገርን ነው ዛሬ ምጠይቅህ ፣
እንደ ትላንትናው እንዳለፈው ጊዚያት ፣
ለንዋይ አይደለም መምጣቴ ካንተ ፊት፣
ወይም ህይወት ግራ ሆና እጅግ  ከብዳኛለች ፣
ደስታ'ዬን ነጥቃ ሀዘን ሞልታኛለች ፣
በችግር በርሀብ ወዜ ተሟጠጠብርታቴን ተቀማው ፣
ያ ፀአዳ ፊቴን ማጣት አጠቆረው ፣
በማዲያት ተሞላ እንባዬ አሻከረው ፣
የተትረፈረፈው የሞላው ማጀቴ ፣
ዘይት ሆነ ዱቄት የለኝም ከቤቴ ፣
ሚቀመስ እንጀራ ጠፍቷል ከሌማቴ ፣
ምቀይረው የለም ከለበስኩት በቀር ፣
ማጥብበት እንኳን ጠፍቷል አንዳቺ ነገር ፣
ያው ተራቁቻለው ድህነት አጠቃኝ ፣
ምን ነው ዝም አልክ ታዲያ ምህረትህን ነፈከኝ ፣
ለሌላው ስትቸር ለእኔ ከለከልከኝ ፣
ይሄው የታደሉት እማ ....
4 አምስት ልጅ በቤታቸው ሞልቶደስታቸው ያስቀናል  ፣
የህፃናቱ ድምፅ ለመኖር ያጓጓል ፣
ልብን ተስፋ ሰጥቶ መንፈስን ያድሳል ፣
የእኔስ ወዴት አለ የማህፀኔ ክፋይ ዘሬን ምተካበት ፣
አይኔን በአይኔ አይቼ ምደሰትበት ፣
መውጣቴ መውረዴ ምክንያቴ ምልበት ፣
እኮወዴት አለዘሬን ምተካበት ?
አሁን ይሄን ሁሉ ልጠይቅ አይደለም ዛሬ መገኘቴ ፣
ያሁን ግን ይለያል ሌላ ነው ምኞቴ  ፣
በል ስማኝ ልንገርህ አድምጠኝ አባቴ፣
ስው ናፈቀኝ ብዬ ያነባውት እንባዛሬ ላይ ላልቅሰው ፣
በፀፀት ልታጠብ ሀጥያቴን ላስታውሰው፣
የዘላለም ቤቴ የሰጠኸኝን እርስት ገነትን ልናፍቀው ፣
መሪር እንባን ላውርድ ቃልህ ይመልሰኝ፣
የጴጥሮስን እንባ ለእኔም ዛሬ አድለኝ ፣
በደልሽን እመኚ ዶሮ ጮኃል በለኝ፣
ደግሞም አንዳንድ ጊዜ....
የስጋዬ አምሮት ጌደለብኝ ብዬ ምጉተመተመው ፣
በነጋ በጠባ እሮሮ እማሰማው ፣
እንዲያ ሲለኝ ደግሞ ...
እረሳኸኝ ብዬ ማነባውን እንባ ባክህ ዛሬ ስጠኝ ፣
ለበደሌ ይሁን በሀጥያት መኖር ይብቃኝ ፣
ይሄው.....
ዲያቆኑ በመቅደስ ተንስዑ እያለ ደውል ይደውላል ፣
በፀሎት እንድተጋ ወደ አንተ እንዳንጋጥጥ ቃሉን ይናገራል ፣
ስባኪውም ይላል ..?
ወደ ቤቱ ግቡ በንስሀ ውሀ በፍቅሩ ታጠቡ ፣
ስጋውንም ብሉ ክቡር ደሙን ጠጡ ፣
ከረከሰች ዓለም ቀጠሮ ሳትይዙ ዛሬውኑ ውጡ ፣
ሁሉም በእየፊናው መዳንን ይሰብካል ፣
መንግስትህን እንድወርስ ኑ ቅረቡ ይላል ፣
እባክህ አባቴ ሁሉም ነገር ቀርቶ ይህን አሳካልኝ ፣
የጴጥሮስን እንባ ለእኔ ልጅህ ስጠኝ ፣
አንተን ልፈልግህ አለም አድክሞኛል ፣
የጨበጥኩት ደስታ ወና ሆኖብኛል ፣
አለ ያልኩት ነገር የተማመንኩበት ባንድ ጊዜ ከድቶኛል፣
ደንዳናውን ልቤን በቃልህ ሰብረጀው ፣
ከአለም ምናምንቴ ቀራንዮን ልየው ፣
ጎልጎታን ልመልከት ፍቅርህን ላስበው ፣
አዎ መዳኒቴ

በህይወት ዘመኔ ያለቀስኩት ለቅሶ ፣
ለንስሀ ላንባው ይምጣ ተመልሶ።

@ከ ወለተ ብርሀንsaramareyama.890@gmail.com

እንቆቅልህ/ሽ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

       *እንቆቅልሽ/ህ..?*

1, ጣፋጭ የሆነ እንደማር
የማያስርብ የሚያጠግብ
በስደትም ስንቅ ነው
አምኖ ለሚጠራው
.
//መልስ// የቅድስት ድንግል ማርያም ስም።

2.እግዚአብሔር ቢወደው
ጥፋትን አላሳየው
ሊቀጥፍ ሄዶ በለስን
አንቀላፍቶ ዘመናትን
የዳነ ከምርኮ ማነው?

//መልስ//አቤሜሌክ ነው።

3.ሰንሰለትን ለብሳ የተጋደለች
ለሃይማኖቷ ቆርጣ የታገለች
የሱስንዮስ ክኅደት ፍጹም ያላስፈራት
የእምነት አርበኛ ይህች ቅድስት እናት
በሉ እስኩ ንገሩኝ ማናት?

//መልስ// ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ናት።


4.ሳይገባኝ የማልችለውን ነክቼ
ተጣብቃ ቀረች እጄ ሰለሉ ጣቶቼ
የምሕረትን እናት በክፋት ነክቼ
ኃጢአቴ የበዛ ማነኝ ወገኖቼ?

//መልስ//ታውፋንያ ነው።

5.ለድንግል ማርያም በክብር የሸለማት
በሥጋ ወደሙ ባርኮ ያከበራት
የታቦተ ጽዮን የግዮን መገኛ
የታሪክ የሃይማኖት የእውቀት መመዘኛ
በቅዱስ መጽሐፍ ስሟ ተዘርዝሯል
ስለ ቅድስናዋ በስፋት ተጽፏል
..//መልስ//ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ናት።

6.የጌታን ትእዛዝ ትቶ
በባህር ሲሄድ ሸሽቶ
በአሳአንባሪ ተበልቶ
ከቀናት በኋላ የተፋው አውጥቶ
ማነው እስኪ ካወቃችሁት ንገሩኝ???

//መልስ// ነቢዩ ዮናስ
saramareyama.890@gmail .com

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

2018 ጃንዋሪ 26, ዓርብ

አፊያ ሁሴን ክፍል 12

አፊያ ሁሴን ክፍል #12saramareyame.890@gmail.com

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፲፪)

የጀመርኩት አዲስ ሕይወት ከእርግዝናዬ ጋር ተደማምሮ ነው መሰለኝ የሚፈራረቁብኝ ስሜቶች ቅጥ የለሽ ሆኑብኝ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያለ ምክንያት ቁጭ ብዬ ስነፈርቅ እውላለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ በስልክም ሆነ በአካል ለሚያናግሩኝ ሰዎች ቅን መልስ መስጠት ይቸግረኛል፡፡ ከመሬት ተነስቶ ውስጤ ብስጭትጭት ይልብኛል፡፡ አንዳንዴ ሙሉ ቀን ተኝቼ ሌላ ጊዜ ደግሞ ራሴን በሥራ ጠምጄ እውላለሁ፡፡ በመኝታም ሆነ በሥራ ተወጥሬ የምውለው በውስጤ ከሚጮህብኝ አንዳች ነገር ለማምለጥ የማደርገው እንደሆነ ቆይቶ ነበር የተረዳሁት፡፡ ለእርግዝና ክትትል የሚጎበኘኝን ሀኪም ስለሚሰማኝ ስሜት ነግሬው ነበር፡፡ እርሱ ግን "ከእርግዝና ጋር ተያይዞ በውስጥሽ በሚፈጠር የሆርሞን ለውጥ የስሜት መለዋወጦች ይከሰታሉ፡፡ ነገሩ ተፈጥሮአዊ በመሆኑ መጨነቅ የለብሽም" አለኝ፡፡ በሰርጌ ሰሞንና በአውሮፓ ጉብኝቴ አዕምሮዬ ከመደነቅ የሚተርፍ ሌላ ስሜትን የሚያስተናግድበት ጊዜም ቦታም አልነበረውም፡፡ አሁን ግን የጋብቻው ትኩስነት በመጠኑ መብረድ ሲጀምር፣ ዙሪያዬን የሚያጅበኝ ሰው ሁሉ ወደየመደበኛው ኑሮው ሲመለስ፣ ሁመይድም ሥራ እያለ የተለመደ ውክቢያውን ሲቀጥል የብቸኝነት ስሜት እየከበበኝ መጣ፡፡ በእርግጥ የሚያነጋግረኝ ሰው አላጣም፣ በስልክም ከተለያዩ ሰዎች ጋር ማውራት እችላለሁ፡፡ ችግር የሆነብኝ እርካታ የሚባል ነገር ማጣቴ ነው፡፡ ቤቴ ውስጥ እጅግ ውድ፣ ዘመናዊና ምቹ በሆኑ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች ተከብቤ ነው የምውለው፡፡ ግቢው መሐል ደግሞ እስካሁን ያልተነዱ ሁለት የራሴ የምላቸው መኪኖች አሉ፡፡ ቁስና ምቾትን እንደ ሕይወት ግብ ለሚቆጥሩ ሰዎች የእኔን እርካታ ማጣትን ከቅብጠት እንደሚቆጥሩት አያጠራጥርም፡፡ ማንም ምንም ተሰማው እኔ ግን በውስጣዊ እኔነቴ እርካታ፣ እረፍትና ሰላም አጥቻለሁ፡፡

ሁመይድ ከሀገር እየወጣ አሥራ አምስት ቀንም፣ ሦሥት ሳምንትም አንዳንድ ጊዜ ወር ያህልም እየቆየ ይመጣል፡፡ እርሱ ሀገር ውስጥ በማይኖርበት ጊዜ እህቴ ሰዓዳ ወይም ፋይሰል እየመጡ እኔ ጋር ያድራሉ፡፡ እናቴም ቀን ቀን አዘውትራ ትመጣለች፡፡ አባቴ ግን ከሁለት ቀን በላይ ብቅ አላለም፡፡ እማማ አፀደና ልጃቸው ሄለን፣ አስቻለውና ኤርምያስ የተወሰነ ጊዜ ጎብኝተውኛል፡፡ በተለይ ሄለን አዲሱ ቤት የገባሁ ሰሞን ለሳምንታት ሙሉ ቀን አብራኝ እየዋለች ጓደኝነቷንና አለኝታነቷን አሳይታኛለች፡፡ እርግዝናዬ እየገፋ ሄዶ ሆዴ ማስታወቅ ሲጀምር ቤት የምውልበት ሰዓት እየበዛ መጣ፡፡ ባሌ ሁመይድ ደግሞ ወራቴ እየጨመረ ሲመጣ የእርሱም ወደ ውጭ መመላለስ እየጠነከረ፣ በላይ በላዩም እየሆነ፣ ሄዶ የሚቆይበትም ጊዜ እየሰፋ መጣ፡፡ አንዳንድ ጊዜ "ገና ከማግባቴ ማርገዝ አልነበረብኝም" ስል አስባለሁ፡፡ በእርግጥ "ቸኮልሽ" የሚሉኝም ነበሩ፡፡ ሌሎች ደግሞ "ካገቡ በኋላማ የምን መቆየት ነው? የትዳር ማጥበቂያና የቤት ማድመቂያው ልጅ ነው"  ይላሉ፡፡ ያም ሆኖ እኔ ምኑንም ሳላስብ የልጅ እናት ለመሆን መንገድ ላይ ነኝ፡፡ ከወለድኩ በኋላ ስለሚሆነው ነገር ለማሰብ እሞክርና በፍርሃት "መጀመሪያ እስቲ በሰላም ልገላገል" እልና እተወዋለሁ፡፡ ሃሳቤ ግን እኔ ልተወው ብል እንኳ በዋዛ የሚለቀኝ አልነበረምና በሃሳብ ባህር እዋጣለሁ፡፡ በእርግጥ የሚያሳስቡ በርካታ ነገሮች አሉብኝ፡፡ ትምህርት የመቀጠል ብርቱ ፍላጎትና የከረመ ዕቅድ አለኝ፡፡ አባቴ ዶክሜንቴን ነጥቆ በተንኮልና በማን አለብኝነት እንዳልማር በማድረጉ የትምህርት ፍላጎቴ ይበልጥ ጨምሯል፡፡ ጋብቻዬን ተከትሎ ዶክሜንቶቼን ከመለሰልኝ ሰነባብቷል፡፡ እናም ከወለድኩ በኋላ ስለምማረው ትምህርት አስባለሁ፡፡ ልጄን ማንን እንደሚመስልና እንዴትስ ተንከባክቤ እንደማሳድገውም አሰላስላለሁ፡፡ በሰላም የመገላገሌ ነገርም እንዲሁ ያሳስበኛል፡፡ ከሁሉ ይልቅ የሚያብሰለስለኝ ጉዳይ ግን ሁመይድን ያገባሁበት ዋንኛ ምክንያት የሆነው የህሊና ነፃነቴና እርሱን ተጠቅሜ አደርገዋለሁ ብዬ ያቀድኩት ነገር ነው፡፡

ሁመይድን ለማግባት ስወስን በዋናነት የታየኝ ነገር ከአባቴ መገላገልን ነው፡፡ ሳገባ ይብዛም ይነስም የተሻለ የኢኮኖሚ ነፃነት እንደሚኖረኝ ገምቻለሁ፡፡ ስለዚህም ዋንኛ መደራደሪያ ያደረኩት የህሊና ነፃነትን ነበር፡፡ በዚያ ላይ ያገባች ሴት በዕድሜ የበሰለች፣ ከእርሷ አልፎ ቤተሰቧን የማስተዳደር ሃላፊነት የሚጣልባት ስለሆነች ከወላጆች የሚደርስባት ጫና ይቀንሳል፡፡ የኢኮኖሚ ነፃነቴን በመጠኑም ቢሆን ለማስከበር ሁመይድ የናጠጠ ቱጃር መሆኑና ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው መሆኑ ጠቅሞኛል፡፡ ለእርሱ ቀላል ከመሆኑ በተጨማሪ በእኔና በቤተሰቦቼ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ሲል የምንኖርበትን ቤትም ሆነ የሰጠኝን መኪና በእኔ ስም ነበር የገዛቸው፡፡ እኔ ሙሉ ውክልና የሰጠሁት ወንድሜ ፋይሰል ነው ተዋውሎ የገዛው፡፡ እነዚህን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም በውስጤ ሲብላላ የኖረውን ክርስትና በወግ ልማረውና ልቀበለው አቅጃለሁ፡፡ ጌታ ከፈቀደ ምናልባት ለሁመይድም እተርፍ ይሆናል፡፡ ይህ የእኔ ሃሳብ ይሁን እንጂ እንዲህም ሆኖ ጠንካራ ተግዳሮቶች መኖራቸው አይቀርም፡፡ ከሥጋቶቼ አንዱ ያው አባቴ አንዱ ነው፡፡ እርሱ ካመነበት አስተሳሰብ እንዳልወጣ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለስም፡፡ በዚህ መንገድ አቋሙንም ጭካኔውንም ባለፉት ጊዜያት አሳይቶኛል፡፡ በዚያ ላይ እጀ ረጅምና የተፅዕኖው አድማስ የሰፋ ነው፡፡ ምንም እንኳ እኔም ከመጣብኝ ለምንም ነገር ግንባሬን የማላጥፍ ጽኑ መሆኔ ባይጠፋውም እንቅፋቶች ከመፍጠር ወደ ኋላ እንደማይል ግልፅ ነው፡፡ ሌላው አሳሳቢ ነገር ራሱ ሁመይድ ነው፡፡ እርሱ ገጽታው ሲታይ የዋህ፣ ፎልፏላና ቅን ቢመስልም በደንብ አውቀዋለሁ ማለት ግን አልችልም፡፡ ሌላው ቀርቶ ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ ሄድኩ ሲለኝ አምኜ ከመሸኘት፣ እዚያም ሳለ ሲደውል ከማውራትና ሲመጣ ከመቀበል የዘለለ ዝርዝር ነገር አላውቅም፡፡ በተለያዩ ሀገሮች ልዩ ልዩ ሥራዎች እንዳሉት የታመነ በመሆኑ ለመጠራጠር ዕድል አይሰጥም፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር ለእኔ ያለው ፍቅርን የእውነት የሚያስመስሉ በርካታ ሁኔታዎችም ይታዩበታል፡፡ ይሁን እንጂ ከጋብቻ በፊት ስላወራነው የሕሊናና የእምነት ነፃነት ላለፉት 6 ወራት አንስተን አናውቅም፡፡ ብዙውን ጊዜ ቤት የማሳልፍ ስለሆንኩ ይሁን ያልኩትን ነፃነት እያከበረልኝ ስለ እስላማዊ አለባበስ አንስቶብኝ አያውቅም፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን በማላውቀው ምክንያት መጪውን ጊዜ አስመልክቶ ሁመይድን ጭምር በጥርጣሬ ቀለበት ውስጥ እንዳውለው የሚሰማኝ ስሜት አለ፡፡

ስለዚህ ነገሮችን ከተለያየ ማዕዘን ሳያቸው ከሁሉ በፊት ልጄን መውለድ እንደሚኖርብኝ አመንኩ፡፡ ያን ሁሉ መሥዋዕትነት የከፈልኩበትን ነገር ያላግባብ እንደገፋሁትና እንዳዘገየሁት የሚወቅስ መንፈስ በውስጤ እየተመላለሰ እያወከኝ ቢሆንም በቅድሚያ መውለድ ይኖርብኛል እያልኩ ደጋግሜ ለራሴ ነገርኩት፡፡ እንዲህ ያለው ውሳኔ ፈተና ምናልባትም መከራ ሊከተለው ስለሚችል በጽናት ለመጋፈጥና  በአገባብ ለመጋደል የአካልና የአዕምሮ ጤንነት ላይ መሆን እንደሚያስፈልግ ተሰምቶኛል፡፡ ሆኖም አልፎ አልፎ በራሴ ማስተዋልና ብልሃት ለመመራት እየሞከርኩ እንዳለሁ በማሰብ እጨነቃለሁ፡፡ መልሼ ደግሞ ከየት ያገኘሁት ትምህርት እንደሆነ ባላውቅም "እግዚአብሔር ያለልክ ቸር በመሆኑ በራሱ ጊዜም በእኛ የጊዜ ሰሌዳም ገብቶ ለማዳን የሚሰራ አምላክ ነው" በማለት ራሴን አፅናናዋለሁ፡፡ እንዲህ ባለው የሕሊና ሙግት፣ በዚህ ዓይነት ውጫዊ ሁኔታ ተከብቤ ቀሪዎቹ ወራት ነጎዱና የመውለጃዬ ጊዜ ደረሰ፡፡ ከአሁን አሁን ምጥ ያጣድፈኛል እያልኩ በምጠባበቅበት ሰዓት ሚዜዬና ጓደኛዬ የሆነችው ሄለን ደወለችና "ሁመይድ ተመልሷል እንዴ?" ስትል ጠየቀችኝ፡፡ ግርም አለችኝና "ምን ሆነሻል? በሦሥት ቀኑ ነው እንዴ የሚመጣው? ናዝሬት የሄደ አስመሰልሽው እኮ፡፡ ይልቅ ለምን በፍጥነት አትመጪም?" አልኳት፡፡ በእኔ ቤት የጅል ጥያቄ መጠየቋ አናዶኛል፡፡ ለመውለድ በመቃረቤ እንደ ሚዜነቷና አብሮ አደግነቷ ሰሞኑን ሁሉ አጠገቤ ነበረች፡፡ ዛሬ ግን ብቅ ሳትል ከሰዓቱ ተጋመሰ፡፡ ሄለን አጠገቤ ስትሆን በጣም ደስ ይለኛል፡፡ የሆነ ሁነኛ ሰው ከጎኔ እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ስለዚህም ዛሬ በመዘግየቷ ተነጫነጭኩባት፡፡ እህቴ ሰዓዳ ከእኔ ጋር ብትሆንም እንደ ልጅ ስለማያት ለጨዋታ እንጂ ለጭንቅ የምትሆን አይመስለኝም፡፡ ውስጤ መረጋጋት ሲያቅተው "እንደውም ለምን ብዬ ምጥ እስከሚጀምረኝ እዚህ እቆያለሁ?" አልኩና ክትትል ሳደርግበት የነበረ አንድ ልዩ የማዋለጃ ክሊኒክ ሄድኩ፡፡ እዚያም ምንም እንኳ ምጥ ባይጀምረኝም ጊዜዬ መድረሱን አይተው አልጋ ሰጡኝና ተኛሁ፡፡

እግዚአብሔር ይመስገን የበኩር ልጄን ምጥ ብዙም ሳይጠናብኝ በሰላም ተገላገልሁ፡፡ ዙሪያዬ በበርካታ ሰው ተሞልቶ በማየቴ እጅጉን ደስ አለኝ፡፡ መኝታዬ በአበባና በመልካም ምኞት መግለጫ ተሞልቷል፡፡ የሌለው ሰው ቢኖር የልጄ አባት ሁመይድ ብቻ ነው፡፡ አባቴ ሳይቀር አጠገቤ ነበር፡፡ ከአባቴ የሚወለዱት ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ዘመዶቻችን፣ የሰፈራችን ሰዎች እየተመላለሱ ሲጠይቁኝ የሆነ የኩራት፣ ብቻዬን ያለመሆን ስሜትና ለማህበራዊ መስተጋብር ገዘፍ ያለ ዋጋ የመስጠት ሃሳብ ውስጤን ይሞላዋል፡፡ አንድ ተለቅ ያለ ጉድለት የሚታየው የሁመይድ አለመኖር ነው፡፡ የመጀመሪያ ልጁ ሲወለድ ባለማየቱ፣ አጠገቤ ባለመሆኑ፣ በጠያቂዎች ሊቀርብለት የሚገባን የ"እንኳን ደስ አለህ" ምርቃት አደግድጎ ያለመቀበሉ አሳዘነኝ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ነገሩ ያበሳጨኝ ጀመር፡፡ በተለይ ሰዎች "አባቱ የታለ? እንኳን ደስ አለህ እንበለው" ሲሉ ብሽቀቴ ይጨምራል፡፡ ሆኖም ይህን ነገሬን የተረዱ የቅርብ ሰዎቼ እንዲህ ያለው መገጣጠም የተለመደ እንደሆነና ብዙም ቦታ ልሰጠው እንደማይገባ ደጋግመው ስለወተወቱኝ ነገሩን ቀለል አድርጌ ለማየት ሞከርኩ፡፡ በወለድኩኝ በአራተኛ ቀኔ ሁመይድ ደወለና በተለመደ ጩኸቱና ሳቁ ታጅቦ ደስታውን ገለፀልኝ፡፡ አሁን ዱባይ እንዳለና ከጥቂት ቀን በኋላ በዚያው ወደ እንግሊዝ አቅንቶ እንደሚመለስ ነገረኝ፡፡ አጠገቤ የተኛውንና ከእርሱ የተወለደውን ጨቅላ ሕጻን ዝም ብዬ ሳስተውለው የፈጣሪ ሥራ ይደንቀኛል፡፡ እኔ ለዘጠኝ ወራት ያህል በሆዴ የተሸከምኩትን ይህን ሕጻን እንዲህ አሟልቶና ውብ አድርጎ መሥራት ምን ዓይነት ጥበብ ነው ብዬ እገረማለሁ፡፡ ክንዴ ስር ተወሽቆ በጸጥታ ሲተኛ፣ ጡት ፍለጋ ደረቴ ላይ ሲርመሰመስ፣ ጡቴን በአፉ ጎርሶ በዓይኖቹ ዓይን ዓይኔን ሲመለከት እንዴት አንጀቴን እንደሚያንሰፈስፈው ልነግርሽ አልችልም፡፡ በቃ ተፈጥሮ የራሷ እጅግ የረቀቀ የእናትና ልጅ መስተጋብር አላት፡፡ ወልደው ካላዩት በቀር በፍፁም ለመረዳት ይከብዳል፡፡ በቃ...ገና ከወልድኩ በጥቂት ቀናት ውስጥ "ወይ እናቴ ለካ እንዲህ በስስት ነው ያሳደግሽኝ" እያልኩ መደመም ጀምሬያለሁ፡፡

በአራስነት ጊዜዬ ቤቴ እንደደመቀ ሰነበተ፡፡ እናቴና ሰዓዳ ሙሉ በሙሉ እኔ ጋር ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ሄለንም አዳሯ እኔ ጋር ነው፡፡ ብዙ ጠያቂዎች ስለሚመላለሱ ቀኑ ሳይታወቀኝ ነጎደ፡፡ ሁመይድ እንደተለመደው በሦሥት ትላልቅ ሻንጣዎች ለእኔና ለሕጻኑ የልብስ መዓት አጭቆ መጣ፡፡ ገና ምኑንም ለማያውቀው ጨቅላ በየዓይነቱ አሻንጉሊትና መጫወቻ በመግዛት ቤቱን ሞላው፡፡ የፈጠረው ድባብ የሆነ ዓይነት ደስታ ፈጠረብኝ፡፡ ውጭ ሀገር እንደሚያየው ዓይነት እዚሁ እኛ ጋር የሚኖሩ የሕጻኑን ጤና የምትከታተል ነርስና የምትንከባከብ ሞግዚት ካልቀጠርኩ ብሎ ከእኔ ጋር ሙግት ገጠመ፡፡ እኔ ከአራስ ቤት እስክወጣ እናቴ አጠገቤ መኖሯንና ከዚያም በኋላ ቢሆን ልጄን ራሴ መንከባከብ እንደምፈልግ ለዚህም እንደማላንስ በመናገር ተከራከርኩ፡፡ ይሁን እንጂ ሸምጋዮች ልጁን የምትንከባከብ ሞግዚት እንድትቀጠር የነርሷ አስፈላጊነት ግን ብዙም እንዳልሆነ በማስረዳት ዳኙን፡፡ ለእኔም "ሕጻኑ ከፍ ሲል አንቺም ወጣ ወጣ ማለት ስትጀምሪ የግድ ጠባቂ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ ካሁኑ ቢለምዳት የተሻለ ነው" አሉኝ፡፡ አያይዘውም "አይዞሽ...እናትነቱን እንደው አትቀማሽም፣ በጠረንሽ ነው የሚለይሽ" እያሉም ቀለዱብኝ፡፡ በዚህ የግርግር ወቅት አዲስ አበባ ያልነበረችው ሌላዋ ሚዜዬ ልዕልና ልትጠይቀኝ መጣች፡፡ ስንጫወት ቆይተን አመሻሽ ላይ ሁመይድ መጣ፡፡ ከልዕልና ጋር ረዥም ጊዜ ባለመገናኘታቸው ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ "ኤፊን ለመጠየቅ ትንሽ አርፍጃለሁ፣ አንተም እንኳን ደስ አለህ" ስትለው ትንሽ ራቅ ብዬ ካለሁበት እያስተዋልኳቸው ነበር፡፡ እርሱም "እንኳን አብሮ ደስ አለን..! ለማርፈዱ ግን ችግር የለም፡፡ እኔ ባልየው እንኳን አሁን በቅርብ ነው የመጣሁት" አለ፡፡ "እንዴ..!? ስትወልድም እዚህ አልነበርክም እንዴ?" አለች ልዕልና፡፡ ከሌላኛው ጥግ ያለችው ሄለን ልዕልናን በዓይኗ ስትገስፃት ተመለከትኳት፡፡ "ሄለንና ልዕልና ባሌ ላይ ሙድ እየያዙበት ነው እንዴ?" ስል አሰብኩና ይበልጥ ጆሮዬን እነርሱ ላይ ለማድረግ ሞከርኩ፡፡ ነገር ግን አጠገቤ ያሉት ሰዎች ሲያዋሩኝ ቀሪው የባሌና የጓደኞቼ የቃላት ልውውጥ አመለጠኝ፡፡

ሜሪዬ.. መቼም የልጄን ስም አወጣጥ በተመለከተ የነበረውን ውዝግብ ሳልነግርሽ ባልፍ ደግ አይሆንም፡፡ እኔ የልጄ ስም እስላማዊና አረባዊ ዘይቤ ያለው እንዲሆን አልፈለኩም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስም መስጠትም መሰረታዊው ነገር ሳይነካ በዘርፍ ጉዳዮች ፀብ ማስነሳት መስሎ ታየኝ፡፡ ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ እየተመናመኑ ባሉ ኢትዮጵያዊ ስሞች የሚቆጭ አንድ ጽሑፍ አንብቤ ስለነበር የልጄ ስም ኢትዮጵያዊ ይዘት እንዲኖረው ወስኜ ነበር፡፡ ስለሆነም ለክትባት ክሊኒክ በሄድኩ ጊዜ የልጄን ስም "በረከት" ብዬ አስመዘገብኩ፡፡ ይህን ያልሰሙት ቤተሰቦቼ ስም በመምረጥ ተጠመዱ፡፡ ብዙዎቹ መሐመድ ይሁን አሉ፡፡ የቀሩት ሙስጠፋ፣ ሌሎች ደግሞ ካሊድ እንዲባል ተመኙ፡፡ ነስረዲን፣ ጀማል፣ ሀሰን፣ አብደላህ... መዓት ስም በአማራጭ ቀረበ፡፡ እኔን እንድመርጥ ሲጠይቁኝ ስም እንዳወጣሁለትና ክሊኒክ እንደተመዘገበ፣ የልደት ካርዱንም በአዲሱ ስም እንዲያዘጋጁት እንደላክሁ ነገርኳቸው፡፡ ማን ብዬ እንዳወጣሁለት ሲጠይቁኝ እጄ ላይ ሆኖ የሚቁለጨለጨውን ልጄን በጨዋታ መልክ ወደ ላይ እያነሳሁት "በረከት ብዬዋለሁ...በረከት ሁመይድ" አልኳቸው፡፡ ከተሰበሰቡት ብዙዎቹ ኩምሽሽ ሲሉ ያስታውቅባቸዋል፡፡ አባቴ ግን በእኔና በስም አውጭዎቹ መካከል የማቀራረብ ሥራ ለመስራት እየጣረ "ጥሩ ነው ይሄም ጥሩ ነው..ግን ሙባረክ ቢባል የበለጠ ውብ ይሆናል" አለ ወደ ሰዎቹም ወደ እኔም እያፈራረቀ ተመለከተ፡፡ አባቴን በሰዎች ፊት ለማክበር ስል ገልመጥ አድርጌ አይቼው ዝም አልኩ፡፡ አስተያየቴና ዝምታዬ አንዳች መልዕክት አስተላለፈለት መሰለኝ ጥቂት ግርግር ፈጥሮ ሹልክ አለ፡፡ ከአባቴ የቅርብ ሰዎች አንዱ እንደ ምክርም እንደ ልመናም በሚመስል ቃና "አፊያ ሐጂ ልክ ናቸው፣ ሙባረክ የአንቺንም የሁሉንሜ ፍላጎት ያሟላል" አለኝ፡፡ እኔም "ምነው..በረከት መጥፎ ስም ነው?" ስል ጠየኩት፡፡ "አይ...መጥፎ አይደለም፣ ይበልጥ ውብ ለማድረግ ብዬ ነው፡፡ እስላማዊ ይዘት ቢኖረው ደስ ይላል" አለኝ፡፡ ፈገግ አልኩና "ቀኑን ሙሉ 'ወበረካቱ' ስትሉ አይደል እንዴ የምትውሉት? ምኑ ነው ከእስላማዊ ይዘት የወጣው?" አልኩ፡፡ እርሱ ግን በዋዛ የሚተወኝ አልሆነም፡፡ ቀጠለና "ቁራን በወረደበት፣ ነቢያችን ጥሪ ባደረጉበት ቋንቋ ስም ሲወጣ ጥሩ ነው" አለ፡፡ እኔም "ተው ባክህ አታድክመኝ፣ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በአፍ መፍቻ ቋንቋዬ የተዋበ ትርጉም ያለው ስም አውጥቻለሁ፡፡ ስነ ልቡናዬ በአረቦች ቅኝ ግዛት እንዲገዛ አልፈቅድም" ብዬው ዞሬ ከሌላ ሰው ጋር ማውራት ቀጠልኩ፡፡ በሁመይድ በኩል ጫና ፈጥረው ስሙን ሊያስቀይሩ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀረ፡፡

ልጄ ስድስት ወር ከሞላው በኋላ አንድ ቀን ከሁመይድ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በኃይለኛው ተጨቃጨቅን፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተለመደው እስላማዊ አለባበስ ነው፡፡ አንድ ምሽት ቤታችን ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ ግብዣ ማድረግ እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ እኔም በድግሱ ምንም ቅሬታ እንደሌለኝ ነግሬው የግብዣው ምክንያት ግን ምን እንደሆነ ጠየኩት፡፡ እርሱም "እውነት ለመናገር ምንም የተለየ ምክንያት የለኝም፡፡ ነገር ግን ከሰርጋችን ወዲህ በተለይ ደግሞ ቤታችን ውስጥ ግብዣ አዘጋጅተን አናውቅም፡፡ ዘመዶቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ ሌሎችም እንግዶች የሚገኙበት ፕሮግራም ቢኖረን መልካም ነው፡፡ እንደ አባወራነቴ ቤቴ ውስጥ ወዳጆቼን ብጋብዝና ቆመን ብናስተናግድ በጣም ደስ ይለኛል" አለኝ፡፡ ሃሳቡ እኔንም ደስ አሰኘኝ፡፡ እንደ ቤተሰብ ሃላፊ ማሰቡንም መናገሩንም ወድጄለታለሁ፡፡ ወዲያው ግን የተሰማኝን በጎ ስሜት ሁሉ የገለበጠ ነገር ተከተለ፡፡ እጄን እየያዘና በዓይኑ እየተለማመጠኝ "ኤፊ ቆንጆ የእኔ ውድ..አንድ ነገር ልለምንሽ...እባክሽ እምቢ እንዳትዪኝ?" ብሎ ሁለቱንም እጆቼን በየተራ ይስም ጀመር፡፡ በጥርጣሬ እየተመለከትኩት "ምንድነው..?" አልኩት፡፡ አጥፍቶ በሚቀጣው አባቱ ፊት እንደቆመ ታዳጊ ልጅ መሬት መሬት እያየ ሲቅለሰለስ ቆየና "የዚያን ቀን ማለቴ የግብዣው ቀን በእስላማዊ ልብስ ተውበሽ ብትታዪ በጣም ደስ ይለኝ ነበር" አለኝ፡፡ ጠላትሽ ክው ይበልና ሜሪዬ እንዴት እንዳስደነገጠኝ አትጠይቂኝ፡፡ በድንጋጤ ከደረቅሁበት ሁኔታ ስወጣ ንዴት ከአጥንቴ ሥር እንደ አዲስ ምንጭ ሲፈልቅ ይሰማኝ ነበር፡፡ ነገሩን ሳስበው ድግስ ደግሶ እኔን በሂጃብና አባያ ቁጥጥር ሥር እንዳደረገኝ ለማሳየት የፈለገ መሰለኝ፡፡ ቀድሞውኑ ዋናው ነገር እኔን በእስላማዊ ልብስ ማሳየት እንጂ ድግሱ አልነበረም፡፡ ግብዣው ማጀቢያ ፕሮግራም ብቻ ነበር፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ይህ ሃሳብ ፈፅሞ የእርሱ እንዳልሆነ፣ የአባቴና የግብር አበሮቹ ዕቅድ ሊሆን እንደሚችል ማሰላሰል ያዝኩ፡፡ በውስጤ እንደ እሳት የሚነደውን ብሽቀት አምቄ ልመረምረው ፈለግሁ፡፡

"በጣም ይገርማል...ከመጋባታችን በፊት በዚህ ጉዳይ ተነጋግረን አልነበረ እንዴ? የገባኸውን ቃል ማጠፍህ ነው?" አልኩት የተሰማኝን ንዴት ለመደበቅ እየታገልኩ፡፡ "አይ አይ አይ...እንደዚያ አይደለም ኤፊ፣ እየለመንኩሽ ነው፡፡ ውሳኔው የአንቺ ነው፣ እኔ ልመና ነው ያቀረብኩት" አለ ሁለቱን መዳፎቹን በመዘርጋት የልመና ምልክት ለማሳየት እየሞከረ፡፡ በአንድ በኩል የሌሎች ሰዎች ምክርና ግፊት መሆኑን ሳስብ በሌላ በኩል ደግሞ "በእስላማዊ ልብስ ተውበሽ" የሚለው ንግግሩ እየታወሰኝ 'የራሱ ድብቅ አጀንዳ ይሆን እንዴ?' ስል ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ ይህን ነገር ማውጣጣት አለብኝ ብዬ ምርመራዬን ቀጠልኩ፡፡ "ይህን ሃሳብህን ባልቀበለውስ ድግሱና ግብዣው ይቀራል?" ስል ጠየኩ፡፡ ቀና ብሎ አይቶኝ ዝም አለኝ፡፡ እኔም "መልስልኝ እንጂ እየጠየኩህ እኮ ነው?" ብዬ ኮስተር አልኩ፡፡ እንደማመንታት አረገውና "አይ...ለምን ይቀራል?" አለ፡፡ በጣም እንደተከፋ ያስታውቃል፡፡ ከመጋባታችን በፊትም ሆነ በኋላ እንዲህ ዓይነት ቅሬታ አይቼበት አላውቅም፡፡ "ሁመይድ" ስል ጠራሁት፣ ከአንገቱ ቀና ብሎ አየኝ፡፡ አስተያየቱ "አቤት" ከማለት በላይ ነበር፡፡ "በዚህ ጉዳይ መነጋገር ይኖርብናል፣ እየጠየከኝ ያለኸው ከሕይወት መመሪያዬ ውጪ የሆነ ነገር ነው፡፡ በዚያ ላይ በሕሊና ነፃነቴ ላይ ላትገባ የገባኸው ቃል አለ፡፡ ለምንድነው ታዲያ እንዲህ ቅር የሚልህ?" ስል ጠየኩት፡፡ እርሱም በተለመደ የንግግር ዘዬው "ኤፊ..እኔ እያስገደድኩሽ ወይም እየተጫንኩሽ አይደለም፡፡ ቃሌንም እያጠፍኩ አይደለም፡፡ ልመና ነው ያቀረብኩት፡፡ እኔ ባልሽ ነኝ፣ የልጅሽ አባት ነኝ፡፡ አንቺ ባልሽውና በፈለግሽው መንገድ ነው የተጋባነው፡፡ እስካሁንም አንቺ የፈለግሽው ብቻ ነው እየሆነ ያለው፡፡ አንድ ትንሽ ነገር ብጠይቅሽ ይሄን ያህል..." ብሎ ጭንቅላቱን በትዝብት መልክ ነቀነቀ፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አሳዘነኝ፡፡ ይህ ሰው ባሌ ነው ስል አሰብኩ፣ ከወላጅ አባቴ መሸሻ ይሆነኝ ዘንድ አምኜ የተጠጋሁት ሰው ነው፡፡ እውነት ለመናገር እስካሁንም አስቀይሞኝ አያውቅም፡፡ ምናልባት ግፊት እየተደረገበት ይሆን? በእኔስ ለመኩራት ወይም ለማፈር መንታ መንገድ ላይ እንዲቆም ሥልታዊ በሆነ ዘዴ እየተገደደ ይሆን? ይህን መሳዩን ነገር ሳወጣና ሳወርድ ቆየሁና ብድግ ብዬ እርሱ ያለበት ሶፋ ላይ በጎን እየተቀመጥኩና እጁን እየያዝኩ "እውነቱን ንገረኝ ሁመይድ..ይህ የአንተ ሃሳብ ነው? ንገረኝ፣ እያየኸኝ እውነቱን ንገረኝ?" አልኩት፡፡ ቀና ብሎ አይቶኝና ፈገግ ብሎ "የራሴ ሃሳብ ነው ኤፊ፡፡ ምነው ተልኮ ነው ብለሽ ተጠራጠርሽ እንዴ?" አለኝ፡፡ ለጥቂት ሰከንዶች አስተዋልኩትና "መልካም፡፡ አስቤ ውሳኔዬን አሳውቅሀለው" ብዬ የለቅሶ ድምፁን የሰማሁት ልጄ ጋር ተነስቼ ሄድኩ፡፡

ሁመይድ ባነሳው ሃሳብ ላይ ምን ዓይነት ውሳኔ ላይ እንደምደርስ ችግር ሆነብኝ፡፡ ነገሩን ከሁለቱም አቅጣጫ ለማጤን ሞከርኩ፡፡ ሂጃብና አባያ ላይ በማመፅ ከአባቴ ጋር ብዙ ነገር ተዳርሰናል፡፡ ቤተሰቤን ለበርካታ ጊዜያት ሰላም ነስቻለሁ፡፡ እኔም አባቴም በየፊናችን ለወራት ለከባድ ሕመም ተዳርገናል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ በአቋሜ እንደፀናሁ ዘልቄያለሁ፡፡ ባደረኩት ተጋድሎና ባሳየሁት ጽናት በብዙዎች ዘንድ ሞገስን ሳተርፍ የሚሰድቡኝና የሚረግሙኝም ነበሩ፡፡ ስለዚህም ይህን ጽናቴን መተውና ለሽንገላ መሸነፍ ትልቅ ክህደት መስሎ ታየኝ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ እኔ ያን ሁሉ ፈተና የተቀበልኩት ልቤን ላሳረፈው እምነትና ቃል እንጂ ለሂጃብና አባያ ብቻ አይደለም፡፡ እምነት አጠቃላይ ነገር ነው፣ ልብስ ደግሞ አንድና አነስተኛ መገለጫ ብቻ ነው፡፡ ምነው መካከለኛው ምስራቅ ያሉ ክርስቲያን እህቶች ሂጃብና አባያ ለብሰው ይውሉ የለ፣ የልብ እምነትና የሰውነት ጨርቅ የሚገጥሙበትም የማይገጥሙበትም ጊዜ ይኖራል ስል አሰብኩ፡፡ በዚያ ላይ ምንም ነገር ጠይቆኝ የማያውቀው ሁመይድን ማስቀየም ከባድና ለትዝብት የሚጥል መስሎ ተሰማኝ፡፡ እንዲህ ያለው ፈተና ውስጥ የከተተኝ ለምን እንደሆነ ወደፊት በደንብ ይጠየቃል አልኩና ሃሳቡን ለመቀበል ከጀለኝ፡፡ በሂጃብና አባያ የሚያዩኝ አባቴና አጋሮቹ ምን እንደሚሉ፣ እንዴትስ እንደሚፈነድቁ ታሰበኝ፡፡ በእነርሱ ሁኔታ ከመናደድ ይልቅ ፈገግ አልኩ፡፡ በውስጤ 'ሌላኛውንም መንገድ ማየት ደግ ነው' ብዬ ከመኝታዬ ተነሳሁ፡፡ ከቁርስ በኋላ ለመውጣት የሚዘገጃጀውን ሁመይድ "ሃሳብህን ተቀብያለሁ፣ ለዚያን ቀን በምትፈልገው አለባበስ እታይልሃለው፣ የግብዣውን ቀን በፍጥነት አሳውቀኝ" አልኩት፡፡ ያልጠበቀውን ነገር እንደሰማ የተደነቀው ሁመይድ ጥቂት ከተደናገረ በኋላ "አመሰግናለሁ ኤፊ" ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ወጣ፡፡

                        (ይቀጥላል)

    -------- ማርያማዊት ገብረመድኅን --------

የሰርግ መዝሙሮች

///////////////////////////7

ሰናይ በዜና ሰናይ በዜና/4/
ሰናይ በዜና    ፍፁም ደስታ ነው
ሰናይ በዜና     ከጌታ የሆነ
ሰናይ በዜና     እንዲህ ይሞሸራል
ሰናይ በዜና     ማን አፍሮ ያመነ
ሙሺሬት         አበባ
ስርአቷ            አበባ
ያበራል            አበባ
ህይወቷ          አበባ
ሰናይ በዜና ሰናይ በዜና/2/
ሰናይ በዜና       እንዲ ነው ጋብቻ
ሰናይ በዜና       እንዲ ነው መዳር
ሰናይ በዜና       በቤተ ክርሥቲያን
ሰናይ በዜና       በስራት በክብር
እልልልልልልልልልልልልልልልልsaramareyama.890@gmail.com

2018 ጃንዋሪ 19, ዓርብ

የምዕራፍ ሦስት/የ22ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ?? ሰላማችሁ ይብዛልኝ እያልኩ፦ እነሆ የምዕራፍ ሦስትን/ የ22ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ  ጥያቄና መልስ እንዲህ ተጀመረ።
//////////////////////////

✍ ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣አምስቱ እህት አብያተ ክርስቲያናት/Oriental Churches/ የሚባሉት ማን ማን ናቸው???

//መልስ//፦ ኢትዮጵያ፣ግብፅ፣ ህንድ፣ ሶርያ እና አርመን ናቸው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅2⃣በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የመጀመሪያዋ  ገዳምና ቤተ-ክርስቲያን የትኛዋ ነች??

//መልስ//፦  አክሱም ጽዮን ናት።

✍ ጥ.ተራ.ቁ.✅3⃣ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል አንዱ የሆኑት ባታችን አቡነ አረጋዊ ያረፉበት ገዳም ምን በመባል ይታወቃል?.

//መልስ//፦ትግራይ ውስጥ ደብረ ዳሞ ይባላል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅4⃣ወንጌል ማለት የስሙ ትርጉም ምን ማለት ነው??

//መልስ//፦ ዜና ሠናይ/ መልካም ዜና/ የምስራች ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅5⃣ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው??

//መልስ//ነብይ ማለት፦ኃላፍያን አልፎ የተሰወረውን ሚስጢር ገና ለወደፊት የሚሆነውን የሚያውቁ/ሀብተ ትንቢት  የተሰጣቸው ቅዱሳን አባቶች ቅዱሳት እናቶቻችን  ነብይ ተብለው ይጠራሉ።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅6⃣12ቱ ደቂቀ ነቢያት ከሚባሉት መካከል ቢያንስ 5ቱን ጥቀስ???

//መልስ//፦ደቂቀ ነብያት የሚባሉት
1ኛ ቅዱስ ሆሴዕ
2ኛ አሞፅ
3ኛ ሚክያስ
4ኛ ዮናስ
5ኛ. ናሆም
6ኛ አብድዩ
7ኛ ሶፎንያስ
8ኛ ሐጌ
9ኛ ኢዩኤል
10ኛ ዕንባቆም
11ኛ ዘካርያስ
12ኛ ሚልክያስ እነዚህ ናቸው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅7⃣ጌታችን የተጸነሰበትንና የተወለደበትን ወርና ቀን ጥቀስ??

//መልስ//መጋቢት 29 ተጸነሰ ታህሳስ 29 ተወለደ።


✍ጥ.ተራ.ቁ✅8⃣ አንድ ክርስቲያን ሥጋና ደሙን ከመቀበሉ  አስቀድሞ ስንት ሰዓት መፆም አለበት??

//መልስ//፦ ለ18 ሰዓት መፆም አለበት።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅9⃣ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን በመባል የምትታወቀዋ ድንቅ ቀን የቷ ነች?

//መልስ//መንፈስ ቅዱስ የወረደባት እለት/ቀን ነች። በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣0⃣ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው???

//መልስ//፦ ጥምቀት ማለት በውኃ መነከር መዘፈቅ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣1⃣ጥምቀትን አጥማቂው   ማን ተምማቂውስ ማን ነው???

//መልስ//፦አጥማቂዎች በሁለት የክህነት ደረጃዎች ብቻ ይፈጸማል። ይኸውም፦
በኤጲስ ቆጶስ በሚባለው ጳጳስ" እና በቄስ ብቻ ነው።
ተጠማቄዎች በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ
ዮሐ (8፥36)

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣2⃣ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ ወርዶ {ሄዶ)ለምን ተጠመቀ??

//መልስ//፦አንድም ለትህትና፤ ለፍቅር፤ ስርዓትን፣ ለማስተማር፤ ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢለው ኑሮ የዛሬ ምህመን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ካህናትን ባስቸገሩ
ነበር።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣3⃣ጌታችን ሲጠመቅ ባህር ሸሽች የመሸሹ ምሳሌ ምንድን ነው???

//መልስ// መሸሹ የኃጢአት ምሳሌ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣4⃣በዮርዳኖስ ወንዝ የሥላሴ ሚስጥር እንዴት ተገለጸ???

//መልስ//፦መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ተገለፀ
↪አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው ሲል በቃል ተገለፀ
↪ወልድ ስጋ ለብሶ በዮርዳኖስ መሀል ቁሞ ተገልፀዋል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣5⃣ዮርዳኖስ አንድ ወንዝ ሲሆን ዝቅ ብሎ ለስንት ተከፈለ ጌታችንስ ምኑ ላይ ነው የተጠመቀው???

//መልስ//፦ዮርዳኖስ አንድ ወንዝ መሆኑ አዳም አንድ ሁኖ መፈጠሩ ምሳሌ ነው ዝቅ ብሎ በ2 በዮር" እና በዳኖስ" ተከፍሎል ሁለቱም ዝቅ ብለው ተገናኝተዋል ከመገናኛው ላይም ጌታችን ተጠምቆል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣6⃣ጌታችን ለምን "በዮርዳኖስ" ወንዝ ተጠመቀ???

//መልስ//፦አንድም እዮብና ንእማን በዮርዳኖስ ተጠምቀው ከደዌ ሥጋ ድነዋል።
 ሚስጥሩ ግን አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ ዲያቢሎስ መከራ አፀናባቸው አዳም የዲያቢሎስ ወንድ አገልጋይ ሔዋን የሴት አገልጋይ ነን ብላችሁ ስማችሁን ጽፍችሁ ስጡኝ ብሎ ዲያቢሎስ አታሏቸው ነበርና ይሁንብን ይደረግብን ብለው አዳምና ሔዋን ቃል ሰተው ነበር። ያንን ቃላቸውን/የእዳ ደብዳቤ አድርጎ በ2 እምነ በረድ ቀርፆ አንዱን "በዮርዳኖስ" አንዱን "በሲዖል" ጥሎት ነበርና በዮርዳኖስ ያኖረውን የእዳ ደብዳቤ 'ጌታችን' በጥምቀቱ ጊዜ በዮርዳኖስ የተጣለውን እንደ ሰውነቱ እረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ደምስሶልናል።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣7⃣.በሀገራችን በኢትዮጵያ ጥምቀት ታቦት ወጥቶ መከበር የተጀመረው መቼ ነው???

//መልስ///፦ በ5ኛው ክ/ን በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣8⃣ባህር ሸሽች አንተ ዮርዳኖስስ ወደኋላ የተመለስከው ምን ሁነህ ነው። ይህን ቅዱስ  ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን ምዕራፍና ቁጥሩስ??

//መልስ//፦ መዝ (113፥3-5) ላይ እናገኘዋለን።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣9⃣የእግዚአብሔርን መኖር የምናውቅባቸው መንገዶች /ማስረጃዎቻችን/ የትኞቹ ናቸው??

 ሀ) በሥነ ፍጥረት መኖር

 ለ)የኅሊናችን ምስክርነት

 ሐ) የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት

መ) ሁሉም መልስ ነው

//መልስ//መ/ ሁሉም መልስ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅2⃣0⃣የጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ ምክንያት፡-

  ሀ) ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ

 ለ) የአዳምና የሔዋን የዕዳ ደብዳቤ በዚያ ተቀብሮ ስለነበረ

 ሐ)በብሉይ ኪዳን ለሥጋ ደዌ በዮርዳኖስ ይጠመቁ ስለነበረ ለነፍስ ድኅነት ይሆን ዘንድ።

 መ) ሁሉም መልስ ነው።

//መልስ//መ/ ሁሉም መልስ ነው።

የ22ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ይህን ይመስላል ከስተቴ አርሙኝ 👉ስል በትህትና እጠይቃለሁ።saramareyama.890@gmail.com

2018 ጃንዋሪ 15, ሰኞ

የጠፋው ልጄ ተገኘ መንፈሳዊ መነባንብ

*"*   *የጠፋው*  *ልጄ*   *ተገኘ*  *"*

🙎🏽‍♂ አባቴ ልንገርክ ኧኽ ብለክ ስማኝ
ንብረቴን እሻለሁ ለኔ የሚደርሰኝን አካፍልና ስጠኝ
ከህል ከከብት ከገንዘብም ቢሆን ሁሉን አስረክበኝ
ሆኖም አደራክን ዛሬ ነገ እንዳትል አሁኑኑ ይሰጠኝ
ሽማግሌዎች ጥራ ጉልማዬን ልወቅ ሸንሽነው ያካፍሉኝ
ድርሻዬን ለይተክ እንድታስረክበኝ እፈልጋለሁኝ

👴🏽 *በወላዲትዋ*!
ምንድነው የምትል የሆንከው አለ እንዴ?
እንዲህ ተበሳጭተክ የምታናግረኝ ምን ነክቶክ ነው ውዴ?
ማነው የስቀየመክ ክፉ የተናገረክ ወይስ ምን በደልኩክ
ገንዘብስ ለምንክ ምን ሊጠቅምህ ገና ልጅ አይደለክ?
ችግርም እንዳለ ንገረኝ አትፍራ አንተ በምን አቅምክ ትቋቋመዋለክ
እኔ እስካለሁ ድረስ አደራ እንዳይኖር ከቶ  የሚያስጨንቅክ

🙎🏽‍♂ እንደዚህ ስላልኩክ አይክፋክ አትናደድብኝ
ነገር ግን አሁን ደግሜ ዕልካለሁ ድርሻዬን አካፍለኝ
ያለኝን ስጥና ለኔ የሚደርሰኝ መርቅና ሸኘኝ
ተትረፍርፎ ሳለ አውድማ ጎተራው ለምን አሰሰተክ?
ብታካፍለኝም በእጥፍ ይገባል በወሰድኩት ምትክ
ይልቅ አባዬ ሳታመነታታ አሁኑኑ ስጠኝ ነው ደግሜ ምልክ


👴🏽 እሺ በቃ ልጄ እጅግ ከባሰብክ
እሰጥሀለሁኝ አትናደድ አሁን ውሰድ እሄው ድርሻክ
ሳልል ወደኋላ አስረክቤካለሁ ሁሉም ያልፋልና አትከፋ አይዞክ
ባገር ሽማግሌ ከንብረቴም ሁሉ አካፍዬካለሁ
ሰርተክ ጨምርበት አምላክ ይባርክልክ ብዬ መርቄሀለሁ

🙎🏽‍♂አመሰግናለሁ ደህና ሰንብቱልኝ
እንደዚህ ይሻላል በማያቁት ሀገር ዝና እላለሁኝ
መኖር እንዲህ እንጂ ቀብረር ፀዳ ብሎ
የት ነበርኩ እስካሁን እሄንን ለማየት ያልነቃሁት ቶሎ
በይ ነፍሴ ተደሰች ያሻሽን አድርጊ
ገንዘብ እንደው አለኝ በአንዳች አትስጊ
ብይ ጠጪ በቃ ሀሴት አድርጊ
ለስጋሽ እርካታ ለአይንሽም ደስታ ከቶም አትንፈጊ

💗 ከአባትህ ኮብልለህ ከፈሩ ወተሃል
አክብር የሚለውን ህጌንም ጥሰሃል
የልብህን ምኞት ስትፈፅም ኖረሃል
አላፊ ጠፊውን አለሙን መርጠሃል
መሰረት የሌለው ህወት ገንብተሀል
በዘፈን ጭፈራ በሱስይሁንህ ደንዝዘካል
ለሰራህው ስራ ደመወዝ ልክፈልህ
ተዘጋጅቻለው መማርያ

🙎🏽‍♂  ወይኔ ጉዴ ፈላ  ተራብኩኝ ተጠማው
ገንዘብ አለኝ እያልኩ ያኔ እንዳላቅራራው
 አለቀ ገንዘቤ  እሄው እጄ ባዶ ነው
የአባቴን ንብረት
ተድላን  የለመደው የቀድሞ ሕይውቴ
ጭራሽ ይባስ ብሎ ድንገት ተጎሳቁሎ ጠፋ ማንነቴ
ኪሴ ተራገፈ እጄ ባዶ ቀረ እኔም ሆንኩ ዋተቴ
ደስታ ሰላም ጠፋ  እራቀ  ከፊቴ
እርሀብ ፀናብኝ እጂግ ተንገላታሁ እስኪዝል ጉልበቴቤቴ
ከማር ከወተቱ የበላው  አንጀቴ
ትዝ ይለኝ  ጀመረ ፍቅሩ የአባቴ

ጥፋቴ ከባድ ነሁ አውቃለሁ ጠንቅቄ
ወደ አባቴ ልሂድ ልኑር በግ ጠብቄ
ይቅርታ ልጠይቅ እግሩ ላይ ወድቄ

💗 መመለስ አለብህ መልካም አስበሃል
ስህተት መስራትክ አሁን አስታውሰሃል
አባትክን ይቅርታ መጠየቅ ይገባሃል ስላንተ ያስባል ሁሌም ይወድሀል
ልጁን የሚጠላ አባት የት አይተሀል ?
ከልብህ ሁንና ጠይቀው ይቅርታ
ዳግም ለመበደል ልብህ አያመንታ

👴🏽 ገና ከሩቅ ሳይክ ሀሴት አገኘሁኝ
የጠፋውን ልጄን ጌታ ምልሶልኝ
ለብዙ ጊዜያት ደስታ ከኔ ርቆኝ
ሀዘን ሰፍኖ ቤቴ  ሰላምም  ሳላገኝ
ዛሬ መጣህልኝ ፍሪዳ ጣሉለት ጥሩ ዘመድአዝማድን
እጅግ ደስ ብሎና የጠፋው ልጃችን ስለተገኘልን
ለግሩ ጫማ አምጡ  ለዕጆቹም አንባር
ከጠፋበት ቦታ ስለተመለሰ አምላክ ተመስገን

🙍🏿‍♂ ምንድነው ይህ ሁሉ ትላንት ንቆን አይደል?
ዛሬ ተመልሶ ድርሻውን ሲጨርስ
ዳግም ደሞ መጣ ሌላውን ሊያፈርስ
እንዳሻው ሲቦርቅ ሲፈነጥዝ
ከርሞ የትም ሲልከሰከስ
ሲቸግረው መጣ የኛንም ሊካፈል ሳናስበው ድንገት
እንዴት ለዚህ ብኩን ለሆነብክ ሽፍታ
ንብረቱን አጥፍቶ ለመጣ ከርታታ
እንዴት ተቅበልከው በፍቅር በደስታ
 ለኔም አላሳየህኝ እሄንን ፈገግታ?
አገልጋይህ  ለሆንከህ ጠዋትና ማታ

👴🏽 ልጄ ተው እባክህ የስጋዬ ክፋይ
ላንተም  እንደዛው ነኝ ለያይቼም አላይ
የኔ ያልኩት ሁሉ ነው ግድ የለም ያንተ
ሳትለያዩበኝ አንድላይ ኑሩ እንጂ በፍቅር በሰላም
ወንድምክም አንተ
 ተገኘልን ከሞት ከጥፋት
ዛሬ
 ፀልይለት አንተም
ጥፋቱን እንዳይደግም
እናም እናመስግን ጌታን በዝማሬ


🙎🏽‍♂ ወይ አቤቴ ደጉ የቀዶሞ ስራዬን በደሌን ሳይቆጥር
ይልቁንም አባብሎ እሄው ተቀበለኝ በሰላም በፍቅር
ዕውነት ለውለታው ለታላቅ ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ
ስለቸርነቱ
 ስለዕርሕራሄው በሒወቴ ሁሉ አመሰግናለው
ዳግም ላልባድለው ገፍቼውም ላሌድ ቃል ገባለታለሁ።

   አሜን ወስበሀት ለእግዚአብሔር
ተፃፈ በእህተ ጊዮርጊስ
saramareyama.890gmail.com

2018 ጃንዋሪ 14, እሑድ

የጥምቀት መዝሙሮች

በጥምቀተ ዳግም ልደት ዳግመ ወለደነ (2)
ለቅድስት ቤተክርስቲያን (4)

/////////////////////////

አለው ሞገስ አለው ሞገስ ጥምቀት ሲደርስ /2/

አለው ሞገስ --------እኽ
አለው ሞገስ---------እኽ
ጥምቀት ሲደርስ------እኽ
ነጩን የሰላም ልብስ -----አለው ምገስ
ሁላችን ለብሰነው --------አለው ምገስ
በስሙ ተጠርተን ------- አለው ሞገስ
ልጆቹ ሁነን -------አለው ምገስ
ሳደክም ሳታክት --------አለው ምገስ
እንዘምራለን ------- አለው ምገስ
ታቦቱን ይዘን ------አለው ምገስ
በመንፈስ ተቀኝተን ------አለው ምገስ

♥የሰላሙ መሪ ፍቅር ነው ጌታችን የልጅነት ጸጋ ሰጠን ለሁላችን -------አለው ምገስ
እኽ------- አለው ምገስ
እኽ------- አለው ምገስ
እኽ ---------አለው ምገስ የሚል ደስ ደስ
ሁኝ እድታይለት------አለው ምገስ
ያስተውል ታዛው -------አለው ምገስ
ሰለ ቃል ኪዳኑ -------አለው ምገስ
አብነቱ ቃሉ --------አለው ምገስ
በሰፈር ካለፈ --------አለው ምገስ
ለ እግዚአብሔር ታቦት------አለው ምገስ
የለነም ዝምታ '--------አለው ምገስ
ለእርሱ የሚሰሰት ------አለው ምገስ

+በመንፈስ ተጠምቀን ቁመን በጌታ ፍት ታቦቱን አጅበን አገኝን በርከት-------አለው ምገስ
እኽ--------አለው ምገስ
እኽ-------አለው ምገስ
እኽ ------አለው ምገስ ጥምቀቱ ሲደርስ
///////////////////////////////saramareyama.890@gmail.com
ሖረ ኢየሱስ (2)
እምገሊላ (3) ኀበ ዮሐንስ (2)
ሄደ ኢየሱስ (2)
ከገሊላ (3) ወደ ዮሐንስ (2)

2018 ጃንዋሪ 11, ሐሙስ

የምዕራፍ ሦስት/የ21ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!! ይህ የምዕራፍ ሦስት/የ21ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር ነው።!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

✍ጥ.ተራ ቁ👉1⃣ልደት ማለት ምን ማለት ነው??

//መልስ//✍🏻ልደት ማለት =ግኝት ወደ መኖር መምጣት ማለት ነው ። ኦ.ዘ.ፍ ማለትም ወደ ግኝት መምጣት ማለት እንደሆነ ​አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላቸው ላይ *ገፅ 325​ ላይ ተገልጿል።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉2⃣ዘመነ ብረሀን የሚባለው  ከምን እስከ ማንትወልድ ያለው ነው??

//መልስ//✍🏻ዘመነ ብረሃን የሚባለው ከልደተ ዳዊት እስከ ፍልሰት ባቢሎስን"14"ቱ ትውልድ ነው። ብርሀን የተባለው ጌታችን ኢየሲስ ክርስቶስ ነው ።

✍ጥ.ተራ ቁ..3⃣ዘመነ ሀጋይ ማለት ምን ማለት ነው ??

//መልስ//✍🏻ዘመነ 'ሀጋይ'  ማለት 'ከታህሳስ 26-መጋቢት 25"  ያለው ሲሆን የቃሉ ትርጎሜ ሀጋይ ፡ደርቅ,ጸሀይ፡ሀገር፡በጋ፡፡ሲሆን ከ4ቱ ክፍለ ዘመነ አንዱ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉4⃣ኤፍራታ ማለት ምን ማለት ነው??

//መልስ//✍🏻'ኤፍራታ' ማለት "ፍሬ የምትይዝ/የምትሸከም ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.👉5⃣ሊቁ ቅዱስ ያሬድን የሾሙት አባት ማን ይባላሉ? የትስ ተሾመ?

//መልስ//✍🏻ሊቁን ቅዱስ "ያሬድን" የሾሙት አባት
የአክሱም ጳጰስ አባ 'ዮሐንስ' ይባላሉ የሾሙት።👉🏻በአክሱም "ጽዮን" ተሾመ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
​✍🏻ትክክል ወይም ትክክል አይደለም በማለት መልሱ

✍ጥ.ተራ.ቁ👉6⃣የሰው ልጅ ከእግዝአብሔር ጋር አንድ ይሆን ዘንድ ሰው ሆነ፤ስሙም አማኑኤል ተባለ። ትርጉሙም<እግዚአብሔር ከእኛ ጋር >>ማለትነውና። (ማቴ 1፥23)
.
//መልስ//✍ትክክል ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉7⃣⃣ስለ ጌታችን መወለድ ከተነገሩ ትንቢቶች መካከል አንዱ የሆነው??👉 <<ከያእቆብ ኮከብ ይወጣል፣ -ከእስራኤል በትር ይነሳል>>(ዘኁ.24፣17 የሚለው ነው።

//መልስ//✍ትክክል ነው።

​​✍🏻ምርጫ ጥያቄ​​

✍ጥ.ተራ.ቁ👉8⃣< ሕፃን ተወልዶልናልና፣  ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።  ድንቅ መካር ኃያል አምካክ፣ ወንድልጅምየዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ይህንን ቅዱስ  በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን።

ሀ) ኢሳ. 9፥6 ላይ ቃልእናገኘዋለን

ለ) ዮሐንስ 3፥2 ላይ እናገኘዋለን።

ሐ) ማቴ 5፥10 ላይ እናገኛዋለን።

መ) መልስ የለም።

//መልስ//👉✍ሀ)ኢሳ.9፥6 ላይ እናገኘዋለን።

✍ጥ.ተራ.ቁ.👉9⃣<<ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች>> ይህን  ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን??

ቅዱስሀ) ሚል 4፥2 ላይ እናገኘዋለን።

ለ) ኢሳ. 9፥2 ላይ ይገኛል

ሐ) ማርቆስ 4፥6 ላይ ይገኛል

መ) መልስ የለም።

//መልስ//✍ሀ)ሚል.4፥2 ላይ ይገኛል።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣0⃣ኪዳን ማለት ምን ማለት ነው በቤተክርስቲያናችን ስንስ አይነት ኪዳናት አሉ??

//መልስ//፦"ኪዳን' የሚባለው ቃል «ቃል» ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ «ኪዳን» ቃሉ «ተካየደ» ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡

ኪዳነ አዳም
ኪዳነ ኖህ
ኪዳነ መልከጼዴቅ
ኪዳነ አብርሀም
ኪዳነ ሙሴ
ኪዳነ ዳዊት እና ኪዳነ  ምሕረት ናቸው።

✍ ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣1⃣ለሙሴ የተሰጠው ጽላት የተቀረጸው ከምንድነው?

//መልስ//✍ከዕብነበረድ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣2⃣አንድ ክርስቲያን ከመጠመቁ በፊት ምን ያስፈልገዋል?

ሀ, የክርስትና አባትና ማዕተብ
ለ, ድግስና መኪና
ሐ, ትምህርትና እምነት
መ,ሁሉም

//መልስ//✍ሀ) የክርስትና አባትና ማዕተብ ያስፈልጋል።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣3⃣በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለመስራት ማን መፍቀድ አለበት?

//መልስ//✍የሀገረ-ስብከቱ ኤጶስ ቆጶስ መፍቀድ አለበት።

✍ጥ.ተራ.ቁ 👉1⃣4⃣መስዋዕተ ኦሪት በስንት ይከፈላል ምን ምን ይባላሉ??

//መልስ//✍በሁለት ይከፈላል የሚቃጠልና የእህል።

. ✍.ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣5⃣አንድ ክርስቲያን ሲጠመቅ ከጥምቀቱ ጋር ተከታትለው የሚፈጸሙት ምስጢራት ምን ምን ናቸው????.

//መልስ//✍ሚስጢረ ሜሮንና ሚስጢረ ቁርባን።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣6⃣ኖላዊ ማለት ምን ማለት ነው???

//መልስ//፦ ኖላዊ ማለት እረኛ ማለት ነው። እረኞች ለበጎቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሣር ውሃ ሳያጎድሉ እንደሚጠብቁ ሁሉ እግዚአብሔርም ህዝቡን በነፍስ በሥጋ የሚጠብቅ ቸር እረኛ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣7⃣ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስንት ልደት አለው???

//መልስ//👇
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ #ሁለት ፪ ልደታት አሉት፡፡       
እነዚም=>  ቀዳማዊ ልደትና ደኃራዊ ልደት ሲባሉ፤ ይኸውም ወልድ (ቃል) ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አባት የተወለደው ልደት ነው፡፡   
 “ለእግዚአብሔር ልጅ  ልደታት እንዳሉት ልናምን ይገባናል፡፡ መጀመሪያ ከዘመን ሁሉ በፊት ከእግዚአብሔር አብ ሁለትመወለዱ ነው፡፡ ዳግመኛም በኋላኛው ዘመን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው መወለዱ ነው፡፡” ሲል ሊቁ አስረድቷል፡፡ (ሃይማኖተ አበው ባስልዮስ ዘቂሳርያ)

#ቀዳማዊ_ልደት
የምንለው ዓለም ከመፈጠሩ ዘመን  በፊት እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ የሰው ሕሊና በማይመረምረው ምሥጢር የተወለደው ልደት ነው፡፡ ልደቱም እንደ ከመቈጠሩሰው ልደት ሳይሆን፤ ከአብ ሲወለድ አብን አህሎ፥ አብን መስሎ፥ ማለት አካሉ አካሉን አህሎ፤ ባሕሪው ባሕርይውን መስሎ ባለማነስ ባለመብለጥ፣ ባለመለየት ባለመለወጥ ነው፡፡
ከባሕሪ አባቱ ከአብ ጋር የተለየበት ደቂቃ ሴኮንድ ቅጽበት የለም፡፡ ጊዜ የተፈጠረው ዓለም ከተፈጠረ በኀላ ነው፡፡
፡፡ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” (መዝ. 2 ፥7 ) “ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ” (መዝ. ፻9 ፥3 ) ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ የሚለው ቃል ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ወልድ ከአብ መወለዱን ያስረዳናል፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ሌላ የተወለደ የለምና ለሌላ ሊሰጥ አይችልም፡፡ በተጨማሪም “ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድኩ” (ምሳ. 8 ፥፳5 ) በማለት የወልድን ቀዳማዊ ልደት መጽሐፍ ያስረዳል፡፡
“ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ ከኮረብቶችም በፊት እኔ ተወለድኩ” ያለው ስለራሱ ሳይሆን፤ እግዚአብሔር ወልድ የተናገረው መናገር ነው፡፡ ከዳዊት የተወለደው ዓለም ከተፈጠረ ተራሮች ከተመሠረቱ ከብዙ ሺህ ዓመታት በኋላ ነው፡፡

#ደኃራዊ_ልደት ዓለም ከተፈጠረ 5 ሺህ 5 መቶ ዓመት ሲፈጸም  ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥገጋዋ ሥጋ ከነብሷ ነብስ ነስቶ በተዋህዶ ሰው የሆነበት ነው፡፡
እግዚአብሔርይህ አስቀድሞ በነቢያት የተነገረ ነው።

ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣8⃣ ዶግማ ማለት ምን ማለት ነው?? ቀኖና ማለትስ ምን ማለት ነው??

//መልስ//👉🏻 ዶግማ ማለት፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጉሙም የማይለወጥ፣ የማይቀየር የማይሻሻል፣ የማያረጅ ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ዶግማ ነው፡፡
ምሳሌ፤ አስርቱ ትእዛዛት ፣ስድስቱ ቃላተ ወንጌል፣ አምስቱ አዕማደ ምስጢር፡፡ ዶግማ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ሰው እንደፍላጎቱ እንደምኞቱ ሊጨምርበት፣ ሊቀንስበት ወይም ሲያሸሽለው አይችልም፡፡ 2ኛ ጴጥ 1.20፣ ዕብ 1.1-3 ፣ ማቴ 24.35✅

👉🏻ቀኖና ማለት ፡- እንደ ዶግማ የግሪክ ቃል ነው፡፡ የቃሉ አመጣጥ ‹‹ሸንበቆ›› ከሚለው ነው፡፡ የጥንት አባቶች ሸንበቆን ርዝመት መለኪያ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የክርስቲያኖች ሥርዓታዊ ሕይወት መለኪያ ሆኖ እንዲያገለግል የቤተክርስቲያ አባቶችና ሊቃውንት በጉባዔ ወይም በሲኖዶስ የሚወስኑት ውሳኔ ቀኖና ይባላል፡፡

ቀኖና እንደወቅቱና ጊዜው በሲኖዶስ ሊለወጥ ወይም ሊሻሻል ይችላል፡፡የቀኖና ምሳሌዎች ጾም ዶግማ ሲሆን የጾም ጊዜ ቀኖና ነው፡፡ ቅዳሴ ዶግማ ሲሆን የቅዳሴ ጊዜ ቀኖና ነው፡፡
አብሔር ሁሉን በሥርዓት ያደርጋል፡፡የእጁ ፍጥረታት የሆኑት መላእክትና ሰው በሥርዓት እንዲያመልኩት ሕግና ሥርዓቱን እዲጠብቁ ይፈልጋል፡፡ 1ኛ ቆሮ 11.34፣ 1ኛ ቆሮ 14.40፣ ቆላ 2.5 የሐዋ.ሥራ 16.4፣ 2ኛ ተሰ 3.6፣ 1ኛ ቆሮ 12.2✅

✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣9⃣ የትምህርተ ሃይማኖት አላማና ጥቅም ምንድነው???

//መልስ//👉🏻የትምህርተ ሀይማኖት አላማና ጥቅም ፦
~ምዕመናንን ለመጠበቅ ይጠቅማል ~በተቀደሰ እውነታ ታንፆ ለመኖር የሀይማኖት ትምህርት ይጠቅማል
~ለሰማያዊ ግምጃ ቤት እራስን ለማዘጋጀት ይጠቅማል
~ትምህርተ ሀይማኖትን የተማረ ሰው አስተዋይ ይሆናል ማስተዋሉ ደሞ ከኃጢአያት ይጥብቀዋል።

✍..ጥ.ተራ.ቁ👉2⃣0⃣እኔስ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ ስለ አብ ስለ ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ እናገራለሁ። ያለው አባት ባስልዮስ ዘቂሳርያ ይባላል።

ትክክል ከሆነ ትክክል ካልሆነ ትክክል አይደለም በማለት መልስ/ሽ

//መልስ//፦ ትክክል ነው።

የ21ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ ይህን ይመስላል ከስተቴ አርሙኝ???

ወስብኃት ለእግዚአብሔር.
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን

2018 ጃንዋሪ 9, ማክሰኞ

ልዩ የገና የግጥም መድብልን

ትህትናን አሳየህ
//////////////
ከነገስታት ሁሉ ንግስናህ የላቀ
ከሃያላን በላይ ሃይልህ የረቀቀ
የፍጥረታት ገዢ ሳለህ ታላቅ ጌታ
በግርግም ተወለድክ በተናቀው ቦታ
የምድር ነገሥታት አንተው የሾምካቸው
በወርቅ ያጌጠው ቤተ መንግስታቸው
ላንተ ቢያንስብህም ለክብርህ ባይመጥን
ሁሉ በእጅህ ሆኖ ያንን አላየህም
ከከብቶቹ በረት ራህን ዝቅ አርገህ
የትህትናን ጥግ ለዓለም አሳየህ


♥♥♥♥♥♥♥♥

#በልደትህ #ልወለድ

በልደትህ ልወለድ በመፈስህ አድሰኝ
በመንፈስ ቅዱስ ልመላ ሀጢያት መስራትን ይብቃኝ ከመስቀልህ
ደስታዬን በቤትህ ላክብር በተቀደሰው ዓላማ
በመልካሙ ነገር ልጎልብት  ዜማን ለበእልልታ ላሰማ
በመቅደስህ ልተከል  ሥር አኑረኝ
የሀጢያት ማቄን አስጥለህ ቅዱስ መንፈስን አልብሰኝ
ደካማነቴን ተመልከት በልደትህ ቀን ውለደኝ
የአለምን አሸንክታብ ተመልሼ እንዳላየው
ልቤን  በፍቅርህ አንጸው  በቃልህ መዶሻ አጥብቀው
አመት አመትን ጠብቄ ልደትህን ሳከብር
ተወለደ ብዬ በልልታ በታላቅ ደስታ ስዘምር
የኔን በሀጢያት መሞት ዘንግቼ ተቀምጫለው
አለው እያልኩ በሥጋ በመንገስ ግና ሞቻለው
ቅዱስ ስጋህን ሳልበላ ክቡር ደምህን ሳልጠጣ
አምና ያከበርኩት ልደትህ ይሄው ዛሬ ላይ መጣ
እናም እባክህ አባቴ
የታወረውን ልቤን በምህረትህ አብራልኝ
በቃሽ ተመለሽ ብለህ ከአለም ጎትተህ አውጣኝ
ለንሥሀ አትጋኝና በልደትህ ውለደኝ
♥♥♥♥♥♥

🌹እመጣለሁ 🌹
               .
            ...:...
               :
በአምሳልህ አክብረህ ፈጥረህኝ
ገነትን ያህል እርስት አውርሰህኝ
እንድኖር ፈቅደህልኝ ትዛዝን ጠብቄ
ውዳሴ ከንቱሲጥለኝ በምክረከይሲ ያኔ
ሲገፈፍ ፀጋዬ ስዋረድ ከክብሬ
ባዶ ስሆን ሲሟጠጥ ተስፋዬ
ሞት ተፈርዶብኝ ስኖር በጨለማ
ከውሃና ከመንፈስ ልትወልደኝ ዳግመኛ
በግርግም እንደ ህፃን ተወልደህ ልትሆነኝ አርያ
የፍቅርህን ጥግ ልታሳየኝ ልታደርገኝ የመስቀልክ ምርኮኛ
አንተ አባቴ ሆይ ሆነህ ሳለህ የዚህ አለም ፈጣሪ
በጭቃ አበጃጅተህ የሰውን ልጅ ሰሪ
በባህሪህ ቅዱስ የሆንክ ይቅር ባይ መሃሪ
ምድርን በአበባ ሰማያትን በከዋክብት የሸለምክ
መላእክት ሳይታክቱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሚያመሰግኑህ
አስበህኝ የጨለማውን አበጋዝ ልትሰብር
 ከክብር ዝቅ ብለህ እኔን ልታፈቅር
ሰገነት ልታቆመኝ የተናቀውን ቦታ መርጠህ
ከዘባነ ኪሩብ ከዙፋንህ ወርደህ
ከሲኦል እሳት ልታድነኝ ወደኔ ስትመጣ
ለበደል ለጥፋቴ አንተ ልትሆን ካሳ
የኔን ፅዋ አንተ ልትጠጣ
ልትሰቀል ልትገረፍ በኔ ፈታ
ህይወትን አሳልፈህ ሰተህ ልታለብሰኝ በፍታ
ስትከፍለኝ ይህን ሁሉ ዋጋ
        ፡
        ፡
ታዲያ እኔስ አለም ለምኔ
ይበቃኛል መዋኘቱ በሃፃት ኩነኔ
እናም አባቴ ሆይ እመጣለሁ ከቤትህ ይህን ሁሉ ትቼ
ከነግሳግሷ ቅራቅቦዋን አለምን ወደዚያ ገፍቼ
ስጦታ መባውን ይዜ
ባይሆንልኝ እንኳን እንደ ሰባ ሰገል እጣን ከርቤ
የንስሐ እንባ በጆቼ አቅፌ
እመጣለሁ ከመቅደስህ በልደትህ ልደቴ እንዲታደስ
እግሬ ብቻ  ሳይሆን ልቤ እዲመለስ
     ፡
አዎን እመጣለሁ
♥♥♥♥♥♥

ከጥቂቶች ተርታ

ከተመረጡት ከጥቂቶች ተርታ
ደምረኝ እባክህ እርዳኝ የኔ ጌታ
ድካሜን ሳታይ ሳትንቀኝ በግብሬ
ኃጢአትን አፍርቼ ባዝል መራራ ፍሬ
አንተ የመጣኸው ኃጥኣንን ልትጠራ
ልታወጣቸው ነው ከፍዳ መከራ
እንጅ ጻድቃንማ በስራቸው ጸድቀው
በመንግስትህ ቦታ እርስትን አግኝተው
ይኖሩ የለ እንዴ ጸጋን ተጎናጽፈው
እኔንም ደምረኝ ስለ ቅዱሳንህ
ባለቀው እድሜ ብመጣም ከወይንህ
ማልደው ከመጡት ጋር ክፈለኝ እባክህ
አምላኬ ሆይ እርዳኝ ከደጅ እንዳልጣል
እድል ፈንታ ስጠኝ ከመረጥካቸው ጋር
ስለቸርነትህ ስለቃልኪዳንህ
ምህረትህ ትድረሰኝ ስለቅዱሳንህ
ተጠርቼ እንዳልቀር ከሰርግ ከድግስህ
ከምርጦችህ ተርታ ቆሜ ላመስግንህ

♥♥♥♥♥♥
#የጌታ #ልደቱ

እሰይ ደስ ይበለን በዓሉ መጣልን
የጌታችን ልደት ቀኑ ደረሰልን

ለሀጢአታችን  ሲል ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ማርያም ከሄዋን ተወልዶ
መጣ ሊታደገን ስጋን ተዋህዶ

የኩነኔው ዘመን አልቋልና አመቱ
አድስ ጸሀይ ወጣ ደረሰ ሰዓቱ

ስሙ ተለወጠ በምህረት ተተካ
የጨለማው ዘመን በልደቱ ፈካ

የነቢያት ትንቢት የገብርኤል ብስራት
ይወለዳል ያሉት የአለም መድሃኒት
ተፈጸመ ቃሉ ተወለደ ጌታ በከብቶች በረት
መንገድን እያሳዩ ታዘዙ ከዋክብት

ለሰው ልጆች ብሎ ስጋን ተዋህዶ
ተንከራቶ ሊኖር ደጋ ቆላ ወርዶ
ሳይገባው መጣ እራሱን ዝቅ አርጎ

ፍቅሩ ገደብ አልባ አምሳያ የሌለው
በደልን ደምስሶ አለሙን ወደደው

ገና ሲደርስልን ሲመጣ ባመቱ
በዜማ ይደምቃል ቅኔ ማህሌቱ
ላንተ የተባለው ይቀርባል መስዋዕቱ
ይደምቃል በእኛ ዘንድ የጌታ ልደቱ


♥♥♥♥♥♥♥♥
.
እሷ ማለት ለእኔ

ምንሽ ነች ይሉኛል ምኔ ልበላቸው
የቱን ተናግሬ የቱንስ ልተወው

እሷ ማለት እኮ .....

በድንግዝግዝ ዓለም በጨለማው ቦታ
ብርሀን የወለደች እንዲያ ስንገላታ
ሰው አጣው ባልኩበት በችግሬ ስዓት
አለው የምትለኝ ፈጥኖ ደራሼ ናት

እሷ ማለት ለእኔ ......

ተስፋዬ ተሟጦ ሞቴን ስለምነው
ብቸኝነት ወሮኝ መኖሬን ስጠላው
እንባዬን አንብታ በተስፋ አለምማኝ
የምታነሳኝ ነች ድክመቴን ተረድታኝ
ከአይን ጥቅሻ ፈጥና ዘውትር ትመጣለች
የልቤን ስብራት በእናትነት ፍቅሯ ታክምልኛላች
እሷ ማለት .....በቃ!  ድንግል ማለት ለእኔ
በቃላት ማልገልጣት ልዩ ነች እናቴ
የአምላኬ ስጦታ ድንቅ ሽልማቴ

♥♥♥♥♥♥♥

*የጌታ ልደቱ*

እሰይ ደስ ይበለን በዓሉ መጣልን
የጌታችን ልደት ቀኑ ደረሰልን

ለኃጢአታችን  ሲል ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ማርያም ከሄዋን ተወልዶ
መጣ ሊታደገን ስጋን ተዋህዶ

የኩነኔው ዘመን አልቋልና አመቱ
አድስ ፅሐይ ወጣ ደረሰ ሰዓቱ

ስሙ ተለወጠ በምህረት ተተካ
የጨለማው ዘመን በልደቱ ፈካ

የነቢያት ትንቢት የገብርኤል ብስራት
ይወለዳል ያሉት የአለም መድኃኒት
ተፈጸመ ቃሉ ተወለደ ጌታ በከብቶች በረት
መንገድን እያሳዩ ታዘዙ ከዋክብት

ለሰው ልጆች ብሎ ሥጋን ተዋህዶ
ተንከራቶ ሊኖር ደጋ ቆላ ወርዶ
ሳይገባው መጣ እራሱን ዝቅ አርጎ

ፍቅሩ ገደብ አልባ አምሳያ የሌለው
በደልን ደምስሶ አለሙን ወደደው

ገና ሲደርስልን ሲመጣ በዓመቱ
በዜማ ይደምቃል ቅኔ ማህሌቱ
ላንተ የተባለው ይቀርባል መስዋዕቱ
ይደምቃል በእኛ ዘንድ የጌታ ልደቱ
♥♥♥♥♥♥♥♥
ወስብኃት ለእግዝአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን/saramareyama.890@gmail.com

2018 ጃንዋሪ 7, እሑድ

የመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ ሰብስብ መዝሙሮች

ዮሐንስኒ ሀሎ
♥♥♥♥
/ዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ ቁ.፪/
ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ/፪/ በሄኖን
ያጠምቅ በሄኖን
አዝ…
መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች እያለ
ዮሐንስ ሲያሰተምር ማነው ያስተዋለ
እንደ ተናገረ አዋጅ ነጋሪው
ተራራው ዝቅ ይበል ይሙላ ጎድጓዳው
አዝ…
እድገቱ ምናኔ ትምህርቱ ንስሐ
የጣዝማ ማር በልቶ ኖረ በበረሃ
መጓዝ እንዲያስችለን በሕይወት ጎዳና
ላይ ታቹ ይደልደል ጎባጣውም ይቅና
አዝ…
ሲኖር በምናኔ በሄኖን በረሃ
ያጠምቅ ነበረ ዮሐንስ በውሃ
በማየ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ
ጌታ ተጠመቀ ድኅነትን ሊያውጅ
አዝ…
ጌታውን አጥምቆ ለክብር የሚበቃ
ከእናቱ ማኅፀን ተገኘ ምርጥ ዕቃ
ኤልሳቤጥም ለክብር ሆና የታደለች
መልካም የነፍስ አባት መጥምቁን ወለደች
ዮሐንስኒ ሃሎ ያጠምቅ/፪/ በሄኖን/፫.

////////////////////////////////

♥♥የኤልሳቤጥ ልጅ♥♥
የኤልሳቤጥ ልጅ የዘካርያስ/2/
የእምነት ጀግና ቅዱስ ዮሐንስ /2/
አደገ በበረሃ ለጽድቅ ለይቶት/2/
መንገዱን ጠረገ ሆነ ሰማእት/2/
+~+~+ አዝ +~+~+~+~
ሲመሰክር ስለሚመጣው
ሲያገለግል በኄኖን ማጥመቂያው
ይመልሳል ህዝቡን በንስሀ
መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ፍስሀ
+++~+ አዝ ~+~+~+~+
እየጠጣ የቶራን ወተት
እየበላ የበረሃ ማር
ብትለይም እናቱ በስጋ
አድጓል ጸንቶ አንዳችም ሳይሰጋ
+~+~+~ አዝ +~+~+~+~
ይፈውሳል እምነትህ ጸበልህ
ለሚመጣ አምኖ ከደጅህ
ቃልኪዳኑ ለዘለአለም ነው
ከጌታ ዘንድ አንዴ የተሰጠው
+~+~+~አዝ +~+~+~+
አማላጄ ወዳጄ ብልህ
ድኜ እኮ ነው በቃልኪዳንህ
ፈዋሼ ነህ ዮሐንስ አባቴ
ይመሰክራል ይኸው አንደበቴ

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ


////////////////////////////////

እርሱ ፍፁም ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል
ከእኔ ይልቅ ጌታ እጅግ ይበርታል
እኔ ለንስሃ በውሃ አጠመቅኋችሁ
በእሳት ያጠምቃል ይመጣል ያልኳችሁ
++
ጫማውል ልሽከም ከቶ የማይገባኝ
እኔን አስቀድሞ ለ አገልግሎት ጠራኝ
ከሕዋላየ የመጠው ነበረ ከፊቴ
በስሙ ታምኑ ዘንድ እርሱ ነው ስብከቴ
++
በምድረ በዳ ላይ የጮኹለት ንጉስ
የሃያላን ሃያል ተግልጣል ኢየሱስ
ለሐጥያት ስርየት ይሰዋል ይሄ በግ
ለዐለም ሁሉ መዳን በቀራንዮ ሰርግ
++
ለንሰሃ የሚሆን ፍሬ ዛሬ ኣድርጉ
ለሰርጉ ሊጠራን መጥትዋል እና በጉ
ከሚመጣው ቁጣ በርሱ እንድታመልጡ
የእፉኝት ልጆች ከባቢሎን ውጡ
++
የኣብርሐም ልጆች ነን በማለት ላትድኑ
የመዳኑን ሰኣት ቀኑን ኣታባክኑ
ለ አብርሐም ልጆችን ከድንጋይ ያስነሳል
መንሹም በ እጁ ነው አውድማው ይጠራል
++
ጠማማው ልብ ይቅና ጥርጊያው ይስተካከል
ፍሬ የሌለው ዛፍ በቶን ሳይቃጠል
ምሳር በዛፎቹ ስር ዛሬም ተቀምጣል
ንሰሀ ግቡ ነው የመጨረሻው ቃል
///////////////////////////////
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ /2ጊዜ/

ወበህየ ዮሐንስ /2ጊዜ/ ፍጹመ ተፈሥሐ /2ጊዜ/

ትርጉም፡-

ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው /2×ጊዜ/

በዚህም ዮሐንስ /2×ጊዜ/ በፍጹም ደስ አለው /2×የጊዜን

ሊቀ መዘምራን ቴወድሮስ ዮሴፍ
//////////////////////////////////
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2
                     💟
                     💟
ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /2/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /2/
                 💟💟

በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/ /2/
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /2/
                  💟💟

ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም /2/
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /2/

                  💟💟
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2

                      💟💟
ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉsaramareyama.890@gmail.com

ልዩ የገና መልእክቶቻችሁ መረሀ ግብር

✞ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞

በወንጌሉ ያመናቹ
እንኩዋን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳቹ !

✞♥✞♥✞ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወልደ+ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወል+ቤዛ ኩሉ አለም ዮም ተወል✞♥✞♥✞

✞♥✞እንኩዋን ለጌታችን ለመድሐኒታች ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሳቹ አደረሰን!!! ✞♥✞

«ህፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል»ኢሳ 9፥6 የተባለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሰነና በቤተልሔም ተወለደ።
የወረብ መዝሙር
✞✞✞ሃሌ ሉያ በጎል ሰከበ በአጽርህት ተጠብለለ ውስተ ማህፀነ ድንግል ኃደረ ዬም ተወልደ ✞✞✞
የወረብ መዝሙር
✞✞✞ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም [2] ✞✞✞
✞✞✞በቤተልሔም ዘይሁዳ በቤተልሔም [2] ✞✞✞
«የይሁዳ ምድር አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ ከይሁዳ ገዥዎች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና»ሚክ 5፥2 የሚል ትንቢት ተነግሮ ነበር። እነሆ ይህ ትንቢት እውን ሆነና የነገስታት ንጉሥ፥ የጌቶች ጌታ፥ የአማልክት ሁሉ አምላክ እንደ ቃል ኪዳኑ ተወለደ። ቅዱስ ኤፍሬም የነቢያት አገራቸው ቤተልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ ባንቺ ክርስቶስ ተወልዷልና ያለው ለዚህ ነው።«ህፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል»ኢሳ 9፥6 የተባለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሰነና በቤተልሔም ተወለደ። «የይሁዳ ምድር አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ ከይሁዳ ገዥዎች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና»ሚክ 5፥2 የሚል ትንቢት ተነግሮ ነበር። እነሆ ይህ ትንቢት እውን ሆነና የነገስታት ንጉሥ፥ የጌቶች ጌታ፥ የአማልክት ሁሉ አምላክ እንደ ቃል ኪዳኑ ተወለደ። ቅዱስ ኤፍሬም የነቢያት አገራቸው ቤተልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ ባንቺ ክርስቶስ ተወልዷልና ያለው ለዚህ ነው።

+ይህው ተወለደ ‘ያለም መዳኒት’[3]
+እሰይ ተወለደ ‘ያለም መዳኒት’[3]
አዝ...
ሰባሰገል መጡ ‘ሊሰግዱ በሙሉ’[3]
አምላክ ቀዳማዊ ‘ተወልዶአል እያሉ’[3]
አዝ...
ሰባ ሰገል መጡ ‘እጅ መንሻይዘው’[3]
ወርቅ እጣን ከርቤውን ‘ገበሩለት ሰግደው’[3]
አዝ...
ህፃናት እንሂደ ‘ከመቅደሱ ቤት’[3]
ውሃው ሆኖአልና ‘ማርና ወተት’[3]

ማቴ:2÷1-12
"ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፡- የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤ የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው። እነርሱም፡-አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት። ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥ ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፡- ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው። እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው። ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት። ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።"
የበአሉ እረዴትነና በረከት በሁላችን ይደርብን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር አሜን።ይቆየን

2018 ጃንዋሪ 4, ሐሙስ

አፊያ ሁሴን ክፍል 11

#አፊያ ሁሴን

ክፍል 11

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፲፩)

እንደ መደንገጥ የሚያደርግ ገጽታ ታየበትና "እንዴ.. ልጄ... አፊያ... ከየት መጣሽ? ቁጭ በይ እስቲ.. አረፍ በይ" አለ እየተደናገረው፡፡ እስኪረጋጋ ብዬ ጥቂት ሰከንዶች ፀጥ ብዬ ቆምኩ፡፡ ይዞት የነበረውን ፋይል ከቦታው ላይ መልሶ ሙሉ ለሙሉ ወደ እኔ ዞረና መቀመጫው ላይ ተደላደለ፡፡ ጥቂት በትኩረት አስተዋለኝና "ተቀመጭ እንጂ..?" አለኝ፡፡ "አልቀመጥም እቸኩላለሁ" አልኩት ኮስተር ብዬ፡፡ ለመናገር እየተሰናዳ ሳለ "ሁመይድ የነገረህን ነገር ላረጋግጥልህ ነው የመጣሁት፣ ከእርሱ ጋር መጋባት እፈልጋለሁ" አልኩት ፈርጠም ብዬ፡፡ የተሰማውን ነገር እንጃ ሰክቶት የነበረውንና አውልቆት ጠረጴዛው ላይ ያኖረውን መነጽሩን በእጆቹ እያሽከረከረ ለሰከንዶች ዝም አለ፡፡ የድምፅ አወጣጤ፣ ገጽታዬና ያንን ቃል ተናግሬ ለመውጣት የነበረኝ ጥድፊያ ብዙ ነገር የሚናገር ነበር፡፡ አሁን ከወላጅ አባቴ ይልቅ ፈፅሞ የማላውቀውን ሰው እየመረጥኩ ነው፡፡ አባቴ የነፈገኝን ሰብዐዊ ነፃነት እንኳን ሊዛመደኝ በዜግነትና በሀገር ሰውነት እንኳ ከማይመስለኝ ባዕድ ተሥፋ እያረኩ ነው፡፡ ከወለደኝና ካሳደገኝ ሰው ይልቅ ማንንም ቢሆን እስከምመርጥ ድረስ በአባቴ የተገፋሁ እንደሆንኩ ሁኔታዬ ሁሉ ያሳብቅ ነበር፡፡ ይህን ሁኔታ መቋቋም የተሳነው ይመስል ቀና ብሎ ሊያየኝ ድፍረት ያጣ መሰለ፡፡ በብዙ ጭንቅ ካቀረቀረበት ቀና ሳይል "ደግ...ካንቺው ከመጣ መልካም ነው፡፡ እኔ የምፈልገው ለወግ ማዕረግ እንድትበቂ ነው" አለ፡፡ ይህን ተናግሮ ሲያበቃ የተፈጠረውን የሰከንዶች ፀጥታ ለማጣራት ቀና ሲል ለቅጽበት ዓይኖቻችን ተጋጩ፡፡ ወዲያውም ቃል ሳልተነፈስ በሩን ከፍቼ ወጣሁ፡፡ ከእራሱ ሃሳብና ከገዛ ሕሊናው ሙግት ጋር ትቼው ወጣሁ፡፡ ቁጭ ብዬ ብዙ ባወራው፣ በእርሱ አስተሳሰብ ወደሚፈልገው መስመር ከመጣሁለት በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ነገር ሁሉ የሚያስተሰርይ የአባትና ልጅ ውይይት ብናደርግ ደስ ይለው እንደነበር አያጠያይቅም፡፡ በእኔ ውስጥ ግን እንዲህ ያለው ፍቅርና የመንፈስ ዝምድና ከሞቱ ቆይተዋል፡፡ በሐሰት የተገነባ ሽንገላንም ነፍሴ አጥብቃ ትፀየፋለች፡፡ ስለሆነም ጋብቻን የመሰለ ትልቅና የሚያወያይ አጀንዳ እንደ ልጅ ሳይሆን እንደ ቢሮ ጸሐፊ መረጃ ሰጥቼ ብቻ ውልቅ አልሁ፡፡

ከዚህ በኋላ ነገሮች በፍጥነት መከናወን ቀጠሉ፡፡ እኔም ሁሉን ነገር ዓይኔን ጨፍኜ መጋፈጥ ጀመርኩ፡፡ ሁመይድ በሀገር ወግ መሰረት ሽማግሌ ላከ፡፡ በሽምግልናው ወቅት የእርሱ ሀብትና ብልፅግና፣ መማርና መመራመር፣ የዞረባቸው ሀገሮች ሳይቀር ተደሰኮረ፡፡ መለስተኛ ሰርግ የሚመስል የሁለት ጊዜ የሽምግልና ሥነ ሥርዓትና ድግስ በቤታችን ተካሄደ፡፡ አባቴ በቀድሞውና በአሁኑ የሽምግልና ሥርዓቶች ላይ ጽንፍ የረገጡ ሁኔታዎች አሳየ፡፡ ያኔ በንዴት አሁን በሳቅ ተርገፈገፈ፣ በመጀመሪያው እኔ ላይ በትር እንዳላነሳ አሁን ሽማግሌዎች ያመጡትን ውስኪ በእጁ ይዞ የምርቃት ናዳ አወረደብኝ፡፡ ከዚህ ግርግር ይልቅ የተሻለ እረፍት የሰጠኝ አባቴ ቤት ውስጥ የሚፈጥረውን ሁከት እርግፍ አድርጎ መተዉ ነው፡፡ ሁመይድን እንደማገባ ካሳወቅሁት ጊዜ ጀምሮ አስደናቂ የባህርይ ለውጥ አመጣ፡፡ ከችግሮች አስቀድሞ እንደነበረው ቀኑን እየጠበቀ ቤት ይመጣል፡፡ ከእናቴ ጋር የነበረው የትዳር ሕይወታቸውም እየተሻሻለ ሄደ፡፡ በሆነ ባልሆነ እንደማይጨቀጭቃት አሁን ቀልድና ልፊያም ይከጅላት ጀምሯል፡፡ ከልጆቹና ከግቢው ሰው ሁሉ ጋር ሰላማዊ መስተጋብር ለመመስረት ይጥራል፡፡ እኔና ወንድሜ ፋይሰል ብቻ በቁጥብነታችን ፀናን፡፡ ሁለታችንም እንደ አምባገነን ንጉሥ አጫዋቾች የሰው ፊት እያየን የምንገለፍጥና ፊታችንን የምናጨፈግግ አይደለንም ያልን እንመስል ነበር፡፡ አባቴ ከሽምግልናው ቀደም ብሎ ባለው ሳምንት ጥቂት ዘመዶች፣ ሁለት ሼኪዎች፣ ከጎረቤትም እማማ አፀደና አንድ ሌላ አዛውንት በተገኙበት ተፈጥሮ የነበረው ችግር ሁሉ መቀረፉን የሚገልፅና ቤተሰቡ ይቅርታ የሚጠያየቅበት የቤተሰብ ጉባዔ መሳይ ነገር ጠርቶ ነበር፡፡ እርሱ ፋና ወጊ በመሆን በዋናነት እኔን ቀጥሎም እናቴን ከዚያም ፋይሰልን ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሁላችንም እንዲሁ ይቅርታ ተጠያየቅን፡፡ ነገሩን ሳስተውለው ግን አባቴ ሁኔታውን የተጠቀመበት ባሳየው ፀባይ አጥቶት የነበረውን ሞገስ መልሶ ለማግኘትና ለእማማ አፀደም "በመጨረሻ ያሸነፍኩት እኔ ነኝ" የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ይመስላል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ እንኳ የእኔና የፋይሰል ልብ ያልተፈታው ይህን ሁኔታ በመረዳት ይሆን? እያልኩ አስባለሁ፡፡

የሰርጉ ዝግጅት ላይ ሥልታዊ የሚመስሉ የተንኮል አካሄዶች ይመጡ ጀመር፡፡ ለምሳሌ የጋብቻው ሥርዓት እስላማዊ ለዛ እንዲኖረው አልባሳትና እጀባ ሃይማኖታዊ መልክ እንዲይዝ፣ የጋብቻው ቀን በክርስቲያኖች አቢይ ፆም አጋማሽ ላይ እንዲሆንንና የሚዜ ጥቆማ ሳይቀር በመስጠት የሚፈታተኑኝ ነበሩ፡፡ በአብዛኛው እንዲህ ያለውን ነገር የሚያደርጉት ከአባቴ ሥር ሥር የሚሉ ደርሶ ራሳቸውን የእስልምና ጠበቃ አድርገው የሚሾሙ ምናምንቴዎች ናቸው፡፡ እነርሱም የቤተሰብ ጉዳይ ውስጥ ገብተው ያላግባብ የሚፈተፍቱት የአባቴን ፊት እያዩ ነበር፡፡ ይህ ነገር ሲያበሳጨኝ ቆይቶ ሳለ አንድ ምሽት ስፈልገው የነበረ ጥሩ አጋጣሚ አገኘሁ፡፡ ቤት ውስጥ አባቴ ከሁለት ወጣት ሙስሊሞች ጋር ምግብ እየተመገበ ነበር፡፡ አንድ ጠና ያሉ ሰውም ነበሩ፡፡ እኔና ሄለን የቬሎና የሚዜ ልብስ ካታሎግ ይዛ የምትመጣ አንዲት ሴትን እየጠበቅን ሳለ ሴቲቱ የተለያዩ መጽሔቶች ይዛ ከተፍ አለች፡፡ ብዙም ሳይቆይ ፋይሰልም ከዋለበት መጣና ተቀላቀለን፡፡ የቀረበላቸውን ምግብ ተመግበው እንደጨረሱ አንዱ ሙስሊም ድምፁን ዘለግ አርጎ "አፊያ ጀሚላን ታውቂያታለሽ አይደል?" ሲል ጠየቀኝ፡፡ "አይ አላውቃትም" አልኩት፡፡ የጠራት ልጅ በወጣት ሙስሊም ሴቶች አንዳንድ እንቅስቃሴ ላይ በመሪነት የምትሳተፍ ናት፡፡ እርሱም ይህንኑ በማብራራት ሊያስታውሰኝ ደከመ፡፡ የሚላትን ልጅ ባስታውሳትም "አላወቅኋትም...ምንድነው?" አልኩት፡፡ እርሱም "በቂ ልምድና የማስተባበር ችሎታ ስላላት ሚዜሽ ብታረጊያት መልካም ነው፡፡ አልባሳትና ሌሎች ነገሮች ላይ ታግዝሻለች" አለኝ፡፡ ቀስ ብዬ አጠገቤ ላሉ ሰዎች "እነዚህ ሰዎች ከባል መረጣ ወደ ሚዜ መረጣ ተሸጋገሩ እንዴ?" ስል ሄለንና ሴቲቱ ሳቅ አፍኗቸው ጮኸው እንዳይስቁም ችግር ሆኖባቸው "ቡፍ...ቡፍ..." እያሉ ጎንበስ ጎንበስ አሉ፡፡ ፋይሰልም አንገቱን ቀብሮ የፈገገ ጥርሱን ለመከለል እየጣረ መጽሔቱን ማገላበጥ ያዘ፡፡ እኔም ወደ እርሱ እንኳ ሳልዞር ድምፄን እንዲሰማው አድርጌ "ስለ ሃሳብህ አመሰግናለሁ፣ ሆኖም በቂ ሚዜዎች አሉኝ" አልኩት፡፡ ልጁ ግን ሞዛዛ ቢጤ ኖሮ ይበልጥ ወደ እኛ እየተጠጋ ስለ ልጅቷ ችሎታና ቅልጥፍና፣ በእስልምና ትምህርትና ሥርዓት ስለመታነጿ ሲደሰኩር ብሽቅ አረገኝና "እባክህ ለምን ታሰለቸናለህ? እኛ ብዙ ሥራ አለብን..አታድክመን፡፡ ልጅቷ ይህን ያህል ከገዘፈችብህ ለራስህ ወዳጅ አድርገህ ያዛት" ብዬ ኩም አረኩት፡፡ በንግግሬ የተሸማቀቀው ወጣት "እኔ ላንቺ ብዬ እንጂ.." እያለ በማጉተምተም ወደመጣበት ተመለሰ፡፡ አባቴም ጠጋ ብሎ በልመናም በቁጣም መልክ "አፊያ እንደዚህ ሰው አታስቀይሚ እንጂ፣ ማንም ሰው አስተያየት የሚሰጠው አንቺን ለማገዝ ብሎ እኮ ነው" አለ፡፡ "ለእኔ አስቦ ከሆነ ምን ችክ ያረገዋል? ነገርኩት አይደል እንዴ፣ እዚህ እየመጡ ለምንድነው ያልበላቸውን የሚያኩት? ሰው ቤት ገብቶ መፈትፈት ምንድነው?" ብዬ አባቴ ላይ አፈጠጥኩበት፡፡ ንግግሬ ለአባቴ ብቻ ሳይሆን ራቅ ያለው ሶፋ ላይ ለተቀመጡት ወጣቶችም በመሆኑ ድምፄን ከፍ አድርጌው ነበር፡፡ እንደሰሙኝም እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ አባቴም ልጆቹ እንዲያዩት ራሱን ግራና ቀኝ እየነቀነቀ ወደ እነርሱው ሄደና መሃላቸው ሆኖ በወዳጅነት እጁን ትከሻቸው ላይ በማኖር ይዟቸው ወጣ፡፡ 

አባቴና ወጣቶቹ ከወጡ በኋላ ሄለን ሶፋው ላይ በጎኗ እንደመተኛት እያለች በሳቅ መንከትከት ያዘች፡፡ "ኤፊ ነፍስሽ አይማርም...እንደዚህ ልጁን ዕጢውን ዱብ ታረጊው? ውይ የእኔ ምስኪን...እንዴት እንደደነገጠ" እያለች ታጋንን ጀመር፡፡ ከተወሰነ ሳቅና ቀልድ በኋላ ሁመይድ ጋር ደወልኩና ኮስተር ብዬ "የሰርጉን ሥርዓት በተመለከተ የተነጋገርካቸው ሰዎች አሉ እንዴ?" በማለት ጠየኩት፡፡ "ኧረ ከማንም ጋር አልተነጋገርኩም" አለ እየተርበተበተ፡፡ "ታዲያ ምንድነው እዚህ እየመጡ ምክርና መመሪያ የሚሰጡኝ?" አልኩ አጠገቤ ያለ ይመስል፡፡ በዕለቱ የተፈጠረውን ነገር ነገርኩት፡፡ በእርግጥ ወጣቶቹ አባቴን ተከትለው የመጡ መሆናቸውን ይህም የቆየ ልማድ እንደሆነ ብረዳም ሁኔታውን ግን ሁመይድን ለማስጠንቀቅ ተጠቀምኩበት፡፡ ስለሆነም ሰርጉ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ይዘት እንደማይኖረው፣ የጋብቻው ቀንም የክርስቲያኖች ዋና ፆም ከተፈታ በኋላ በሚያዝያ ወር እንደሚደረግ፣ አልባሳቱም እኔና ሚዜዎቼ በምንመርጠው ቬሎና ከለር እንደሚሆን ረገጥ አድርጌ አሳወቅሁት፡፡ ይህንንም በራሱ መንገድና ተፅዕኖ እንዲያሳምን የቤት ሥራ ሰጠሁት፡፡ "አሊያ ግን ሰርግና ጋብቻ የሚባል ነገር ሕልም ነው... እኔ እንደሆነ ለምንም ነገር ግድ የለኝ" ስል አስፈራራሁ፡፡ እርሱም "አይዞሽ ኤፊ...ይሄ አያሳስብም፣ ሁሉ ነገር አንቺ በፈለግሽውና እኛ በወሰንነው ነው የሚሆነው፡፡ ሙሽራ ክቡር ነው፣ ያለው ሁሉ ይፈፀማል" ሲል ሳቀ፡፡

ሚዜዎቼን አብሮ አደጌ ሄለንን፣ ልዕልና የምትባል አንዲት የሄለን ጓደኛና እንደኔው ሂጃብና አባያ ላይ የምታምፅ ሰሚራ የምትባል የአባቴ ልጅ እህቴን አደረግሁ፡፡ የተጠበቀው ሰርግ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በካፒታል ሆቴል ተደረገ፡፡ አክራሪ ነን የሚሉ ሙስሊሞች ሳይቀሩ መጠጥ ቀማምሰው ይሁን በመድረክ ሞቅታ ተስበው አንዳንዶቹ ሲወዘወዙ ሌሎቹም ጭፈራውን ሲያስነኩት አመሹ፡፡ የእኔ የጋብቻ ሕልም በእንዲህ ያለው አስረሽ ምችው ባይሆንም ተገፍቼ ተገፍቼ እዚህኛው ጽንፍ ላይ ወደቅሁ፡፡ የሚዜዎች ጭፈራ ላይ እህቴ ሰሚራ የሚችላት አልተገኘም፡፡ ብዙ የአባቴ ወገኖች የጎሪጥ እስኪያይዋት ድረስ የውዝዋዜው መሪ ሆነች፡፡ "ይህን ሁሉ የጭፈራ ዓይነት ከየት አገኘችው?" ብለው እስኪደነቁ ድረስ ድብቅ ልምዷን ይፋ አወጣች፡፡ የሰርጉ ዕለትም ሆነ ካለፈ በኋላ ጭፈራዋን ለሚያነሱባት ሁሉ "እህቴ እኮ ነች ያገባችው... ማን መሰለቻችሁ?" እያለች ትመልስ ነበር፡፡ በሰርጉ የታደሙ ብዙዎች "ባሏ ፈረንጅ ነው፣ አፊያን ለመሰለ ቆንጆ የሚመጥን ሰርግ ነው፣ ከተጋቡ በኋላ ውጭ ሀገር ነው የሚኖሩት..." የሚል ግምት ወለድ አስተያየት ይሰነዝሩ ነበር፡፡ አባቴ የሙዚቃው ብዛት እንደረበሸው የሚያስመስል ፊት አልፎ አልፎ ቢያሳይም የክት ልብሱን ለብሶ በድል አድራጊነት ይጎማለላል፡፡ እናቴ የሀበሻ ቀሚሷን አድርጋ እየተፍለቀለቀች ትታያለች፡፡ እታባ ከባሏ ጋር ከፊት ለፊት ተቀምጣ በየደቂቃው የተለያየ የደስታ ምልክት ታሳየኛለች፡፡ ፋይሰል ራሱን በመስተንግዶ ጠምዶ ሲዋከብ እንጂ ተረጋግቶ አይታይም፡፡ ሰዓዳ የአራተኛ ሚዜ የሚመስል ሚና ይዛ ከሦሥቱ ሚዜዎች ቀጥላ መድረክ ላይ ተሰይማለች፡፡ ትንሹ ወንድሜ ሙኒር ሻማ ያዥ ስለሆነ በልዩ ልብስ አጊጦ ከሴት ሚዜዎች ወደ ወንድ ሚዜዎች እየተመላለሰ መድረኩን በልጅነት ሥልጣኑ እንደ ልቡ ተቆጣጥሮታል፡፡

የአባቴ ልጆች የሆኑ ወንድሞቼና እህቶቼ ሌሎች ዘመዶችም በአጃቢነት ወግ በአዳራሹ የፊት መስመር ተገጥግጠዋል፡፡ ከእነርሱ ቀጥሎ እማማ አፀደ፣ ልጃቸው አስቻለው፣ ጓደኛው ኤርምያስና በጉርብትና ስም ከሰፈር የተጠሩ በርካታ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ እማማ አፀደ ከጣራ በላይ የሚጮኸው የሙዚቃ ድምፅና ሁካታው ብዙም እንዳልተመቻቸው ያስታውቃሉ፡፡ ደርበብ ብለው እንደተቀመጡ ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ያደርጋሉ፣ አልፎ አልፎም ከሰዎች ጋር እያወሩ ፈገግ ይላሉ፡፡ ስሜታቸውን ለማጥናት ከትልቁ መድረክ ቁልቁል አሻግሬ ደጋግሜ ወደርሳቸው ባይም ልብ ያሉትም አይመስሉ፡፡ ይልቁኑ ወደርሳቸው ባተኮርኩ ቁጥር በዚያው አንፃር ያሉት ዘመዶች ወደ እነርሱ ያየሁ እየመሰላቸው የተለያየ ምልክት ይሰጡኛል፡፡ አስቻለውና ኤርምያስ በደማቅ ፈገግታ እጃቸውን ሲያውለበልቡልኝ በታመምኩ ጊዜ ያሳዩኝን አለሁ ባይነት አስታውሼ "በመከራና በደስታ የማይለወጥ እንዴት ያለ ወዳጅነት ነው?" ስል ለአፍታ አሰብኩ፡፡ ከመድረክ ሆኜ ወደታች ስመለከት ያለው ትዕይንት የማልረሳው ስዕል በውስጤ ፈጥሮብኝ አልፏል፡፡ በዚያው ድምቀት የኬክ ቆረሳው፣ እርሱን ተከትሎ የሚመጣው ጭፈራና የምሥጋና ካርድ ዕደላው ተካሄደ፡፡ ወደ በኋላ ላይ ከፍተኛ ድካም ስለተሰማኝ የስነ-ሥርዓቱን መጠናቀቅ እስከመመኘት ደረስሁ፡፡ ብመኝም ባልመኝም ተፈጥሯዊው የጊዜ ዑደት በራሱ የማይገሰስ ሕግ መሄዱ ስለማይቀር የሰርጉ ፍፃሜ ሆነ፡፡ አስቀድሞ በተያዘ ፕሮግራም መሰረት በሰርጉ ሳምንት የጫጉላ ሽርሽር ስለምንሄድ መልስና ቅልቅሉ በዚያው ሳምንት ውስጥ ተካሄደ፡፡ የገዛ እልሄ ይሁን የእግዚአብሔር ፈቃድ ባላውቅም ከአባቴ ጥብቅ ቁጥጥርና ተፅዕኖ ወደ ባል ቁጥጥር ተዛወርኩ፡፡ አሁን ያገባሁ ሴት ስለሆንኩ ከልጅነት የተሻለ ሙሉነትና ሃላፊነት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ ሌላኛው የሕይወት ምዕራፌ ምን እንደሚመስል፣ የት እንደሚያደርሰኝና ምን ዓይነት አዳዲስ ተግዳሮቶች እንደሚኖሩት ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡

በሰርጌ ሳምንት እሑድ ምሽት ወደ ለንደን በረርን፡፡ የጫጉላው ሽርሽር የት የት ሀገርን እንዲያካትት እንደምፈልግ ሲጠይኝ የታሪክ ዝንባሌ እንዳለኝ በመጥቀስ ጣልያን፣ ግሪክና ግብፅ ቢካተቱ ደስ እንደሚለኝ ነግሬው ነበር፡፡ ሆኖም እርሱ በሥራ ምክንያት ብዙ ጊዜ እንግሊዝ ስለሚመላለስና እዚያም በርካታ ወዳጆችና የሥራ አጋሮች ስላሉት አስቀድመን ወደዚያው አመራን፡፡ እዚያ ከጠበኩት በላይ ወደ ሃያ ቀን የሚያህል ቆየን፡፡ በጣም ብዙ ሰው ስለሚያውቅ በየቀኑ አነስተኛ ግብዣዎች በየሬስቶራንቱ ሲደረግልን ሰነበተ፡፡ መልካም ምኞት የሚመኙልን፣ ቆንጆ ሚስት አለህ እያሉ የሚያደንቁ በርካቶች ነበሩ፡፡ የአበባና የፖስት ካርድ መዓት ክፍላችንን አጣቦት ነበር፡፡ በስልክ ሲተርክልኝ የነበረውን የእንግሊዝን ከተሞች፣ ዝነኛ ሙዚየሞችና ቤተመጻሕፍት፣ የጥበብ ማዕከላትና የቱሪስት መዳረሻዎች ተዟዙረን ጎበኘን፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ3000-1500 ዓ.ዓ. እንደቆሙ የሚገመቱትን ጥንታዊ የብሪታኒያ የድንጋይ ሐውልቶችን፣ ዝነኛውን የለንደን ታወር፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶችን አቅፎ የያዘውን ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲን፣ የተለያዩ ጥንታዊ ግንቦችን፣ ፓርኮችንና የዱር አራዊት መጠበቂያ ቦታዎችን (zoo) ተዟዙረን ተመለከትን፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ኤደን ፕሮጀክት (Eden Project) ብለው የገነቡት የተለያዩ ዕፅዋት የሚበቅሉበት ሥፍራ ነው፡፡ ከመላው ዓለም የተሰበሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የዕፅዋት ዓይነቶች የሚገኙበት ይህ ሥፍራ ኤደን ገነትን እንዲመስል ብዙ እንደተለፋበት ያስታውቃል፡፡ ቦታው ላይ የእስኪሞዎች የበረዶ ቤቶችን የሚመስሉ ትላልቅ ባለ ክብ ጉልላት መጠለያዎች ታንፀው በውስጣቸው የጸሐይ ቃጠሎ እምብዛም የማይስማማቸው የተክል ዓይነቶችን ይዘዋል፡፡ እኒህ ባለ ክብ ጉልላት ትላልቅ መጠለያዎች ከውጭ ሲያዩዋቸው የማር እንጀራ የሚመስል ቅርፅ አላቸው፡፡ ተክሎቹ የየመጡበትን አካባቢ የአየር ንብረት ለማስመሰል የተደረገው ሥራ የሚደንቅ ነበር፡፡

እንግሊዝ ያለን ቆይታ ሲጠናቀቅ የስዊዘርላንድን አስደናቂ መልክዐ ምድርና የተፈጥሮ ገጽታ እንይ ብሎኝ ወደዚያ ሄድን፡፡ የዕውቀትና የመረጃ ክፍተት ገድቦኝ እንጂ በእርግጥም ተፈጥሮን ለማድነቅ ስዊዘርላንድ ከአውሮፓ እጅግ ተመራጯ ሀገር ነች፡፡ አናታቸውን በበረዶ ብናኝ ሸፍነው ወገባቸውን ብሩህ ደመና ታጥቀው የሚታዩት የዓለት ተራራዎች ከርቀት ሲያዩዋቸው ለአምልኮ የተሰለፉ የሃይማኖት ሰዎች ይመስላሉ፡፡ እጅግ ጥርት ያሉ ሐይቆችና ወንዞች ያሉባት ይህች ሀገር ከአውሮፓ ትልቁና ማራኪው ፏፏቴም የሚገኝባት ናት፡፡ መላዋ ሀገሪቱ አረንጓዴ ሥጋጃ የተነጠፈባት ይመስል ሲበዛ ለምለም ነች፡፡ ይህን መሳዩን የተፈጥሮ ፀጋና ርዕሰ መዲናዋ ዙሪክን ጎብኝተን ወደ ጣሊያን አመራን፡፡ ሁመይድ እንግሊዝን በጥልቀት ስዊዘርላንድን በስሱ የሚያውቃቸው ቢሆንም ጣልያን ዋና ከተማዋ ሮም ሁለት ጊዜ ከመምጣት በቀር እኔ ማየት የፈለኳቸውን ታሪካዊ ሥፍራዎች እርሱም አያውቃቸውም፡፡ ግሪክንማ ጭራሽ ሄዶባት አያውቅም፡፡ ስለሆነም በሁለቱ ሀገሮች ያየናቸው አስደናቂ፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ሥፍራዎች እንዳስገረሙት እየደጋገመ ሲገልጥ ነበር፡፡   ጣልያን ውስጥ ጥንታዊውንና ኃያሉን የሮማን ኢምፓየር የሚዘክሩ ቅርሶች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ ሙዚየሞቿ እጅግ በበዙ ጥንታዊ ቅርሶች የተጣበቡ ናቸው፡፡ ይህቺን ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር አብጠርጥሮ ለመጎብኘት አመት እንኳን የሚበቃ አይመስልም፡፡ እንደ እኛ ላለ ለቀናት ቆይታ ለመጣ ጎብኚ ዝርዝሩን ትቶ ጉልህ ጉልሁን በወፍ በረር ከመቃኘት የዘለለ ዕድል የለውም፡፡ ኮሎዝየም የሚሉት ጥንታዊ የሮማ መኳንንት ቲያትር ቤት ግማሽ ጎኑ ከመፍረስ ተርፎ አሁን ድረስ ተጀንኖ ቆሞ ይታያል፡፡ ለዘመናዊ ስታድየሞችና ግዙፍ ቲያትር ቤቶች ግንባታ ሞዴል መሆን የቻለ አስደናቂ የኪነ ሕንጻ ጥበብ የሚታይበት ይህ ጥንታዊ መዝናኛ ሳይጠቀስ የማይታለፍ ነው፡፡ ፖምፔይ ተብሎ የሚታወቅ ጥንታዊ የመዝናኛ ከተማም በውስጡ ካቀፋቸው የቤቶች፣ የገበያ፣ የመቅደሶች፣ የቲያትር ቤቶችና የመንገዶች ፍርስራሽና ቆመው ከሚታዩ አንዳንድ ግንቦች ጋር ይታያል፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን አልፈው ትርጉም ያለው ታሪካዊ ምስክርነትን የሚሰጡ የሮማ ሸንጎ የሕንጻው ምሶሶዎች (pillars) እና ከፊል መዋቅሮች፣ የጥንታዊ መቅደሶች መሰረቶች፣ የገበያ አዳራሽና የግብር መክፈያ ቤቶች ቅሪተ አካላት እንዲሁ ከሚጎበኙም ከሚደነቁም መካከል ናቸው፡፡ በጣልያን ውስጥ አጅግ በጣም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ ለጉብኝት የሚበቁት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ የሮም ካቶሊክ መንበር የሆነችውን ቫቲካንን፣ ግዙፉን የቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራልና አስደናቂ የግንባታ ጥበብ የሚታይበት የቬነሱ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያንን እዚህ ላይ ሳይጠቅሱ ማለፍ አይቻልም፡፡ ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን እስከ ሦሥተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ በጣኦት አምላኪዎችና በአህዛብ ነገሥታት ሲሳደዱ የነበሩት ክርስቲያኖች ይደበቁበት የነበረው ግበበ ምድር (ካታኮምብ፣ የውስጥ ለውስጥ ዋሻ) ሌላው አስደናቂ ትዕይንት ነው፡፡

በግሪክም እንዲሁ ለአንድ ሳምንት ያህል ስንጎበኝና ስንዘዋወር ቆየን፡፡ የጥንታውያኑ ፈላስፎችና አዋቂዎች የእነ ሆሜር፣ ሄሮዱትስ፣ ሶቅራጥስ፣ አርስጣጣሊስ፣ ሂፖክራተስ፣ ፓይታጎረስ... ሀገር ግሪክ እንዲሁ የበዛና የተወሳሰበ ቅርሶች ባለቤት ናት፡፡ በታዋቂው የአቴንስ ሙዝየም ውስጥ የሆሜር ኤሊያድና ኦዲሴን ጨምሮ የተለያዩ ፈላስፎች መጻሕፍት፣ የግሪክ ሚቶሎጂ የሰፈረባቸው ትርክቶችና ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶች ሞልተዋል፡፡ የአቴንስ ከተማ ምልክት የሆነውና ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደታነፀ የሚነገርለት አክሮፖሊስ (Acropolis) የተባለው ሕንጻ ከበርካታ አምዶቹ ጋር በኩራት ይታያል፡፡  በፓርናሰስ ተራሮች መካከል በጠባብ ሸለቆ ውስጥ ታንፆ የዘመኑ ጣኦት አምላኪዎች አፖሎ ለተባለ አምላካቸው አምልኮ የሚያቀርቡበትና አምላካዊ ምሪት የሚጠይቁበት ዴልፊ (Delphi) የሚባለው ሥፍራም ከጥንታዊነቱ የተነሳ አስጎብኚዎች እንዲጎበኝ የሚመክሩት የቱሪስቶች መዳረሻ ነው፡፡ እንደ ጥንታዊቷ ተሰሎንቄ ከተማና በአርኬኦሎጂ ቁፋሮ የተገኘው የስፓርታ ከተማ ፍርስራሽ በእርጋታ ለሚጎበኛቸው ብዙ የሚሉት ነገር፣ የሚያወሩት ታሪክ አላቸው፡፡

ልክ ጊዜ እንደሚወስድ ሥራና ለተከታታይ ቀናት እንደቀጠለ ድግስ በመጨረሻ ሁለታችንም ድካም ተሰማን፡፡ ስለሆነም የግብፅ ጉብኝታችንን ለሌላ ጊዜ አዛውረን ከአንድ ወር አስራ አምስት ቀን በኋላ በቀጥታ ወደ ሀገር ቤት መጣን፡፡ ለጊዜው የተሟላ ዕቃ ያለው አንድ ገስት ሀውስ ተከራይተን እዚያ ገባን፡፡ እጅግ የናፈቁኝ ቤተሰቦቼ ጋር ስሄድ እንደ ንግስት ተቀበሉኝ፡፡ ለሰርጌ የመጣለኝ ሥጦታ መኝታ ክፍሌን አጨናንቆታል፡፡ የቤት ዕቃው፣ ልብሱ፣ ጌጣጌጡ... ምኑ ቅጡ?! ያን ምሽት ሁመይድ በቤተሰቦቼ ፊት ሁለት ቁልፎች አምጥቶ "ለልዕልቲቱ አፊያ ይህ ቢያንስ እንጂ አይበዛባትም" አለና አስረከበኝ፡፡ አንዱ የአዲስ ያሪስ መኪና ቁልፍ ሲሆን ሌላው ደግሞ ጃክሮስ ኢትዮጵያ የሚባል ሪል ስቴት ካስገነባቸው ቪላዎች ውስጥ የአንዱ ቁልፍ ነበር፡፡ ለካ በጉዞ ሳለን በወንድሜ ፋይሰል አማካኝነት የሁለቱንም ግዢ ፈፅሞ ኖሯል፡፡ አባቴ ደግሞ ከሁመይድ ጋር ፉክክር የያዘ ይመስል ስላለፈው ችግር ኑዛዜ የሚመስል ዲስኩር አሰማና አሁን የተሰማውን ደስታ ገልፆ የቪትዝ መኪና ቁልፍ ሰጠኝ፡፡ መኪና መንዳት የማልችልና መንጃ ፈቃድ የሌለኝ ሴት በአንድ ጊዜ የሁለት መኪና ባለቤት ሆኜ አረፍኩት፡፡ በአንድ ወር  ጊዜ ውስጥ አዲሱ ቤታችን ዕቃ ገብቶበት፣ እንደሚገባ ተደራጅቶና ጥበቃና ሰራተኛ ተቀጥሮ አዲሱን የሕይወት ምዕራፍ "ሀ" ብዬ ጀመርኩት፡፡ ለካ አዲሱ ቤት የገባሁት እንደ ወትሮው ሌጣዬን አልነበረም፡፡ ቤቴ በገባሁ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስሜት አልሰማኝ ሲል ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ የምርመራ ውጤቴም የ2 ወር እርጉዝ እንደሆንኩ አበሰረኝ፡፡

                        (ይቀጥላል)

   ----------- ማርያማዊት ገብረመድኅን -----------sara.mareyama.890@gmail.com

2018 ጃንዋሪ 2, ማክሰኞ

የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት መዝሙሮች

ለተክለሃይማኖት
=============
ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነ ብዝኃ ህማሙ /2/
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ /4/
እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሠተ ሥጋሁ ወአጽሙ /2/
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ /4/
እምነ አድባራት ኵሎን ዘተለአለት በስሙ /2/
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ /4/
ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሰ በደሙ/2/
ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ /4/
ትርጉም- ጻድቁ ተክለሃይማኖት ብዙ ህማም የተቀበለባት ቅዱስ አጽሙ ያረፈባት በስሙ ከታነጹት አድባራት ሁሉ ከፍ ያለች ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የቀደሳት ደብረ ሊባኖስ ታመሰግነዋለች።

/////////////////////////////

ኢትዮጲያዊው ፃድቅ ማነው ብዬ ጠየኩ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈኩ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሸ ፍቅሩን በመቅመሴ

በኢትሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምልክ አለምን ጥለህ
ደብረ ሌባኖስ ህያው ምስክር
ስላንተ ዝና ስላንተ ክብር
ተክለ ሀይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል ባንተ ጓዳ ደጄ

..አ..ዝ....

አክባሪው አምላክ ስላከበረክ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የፃዲቅ ጸሎት ሀይል አላትና
ተክለ ሀይማኖት ፀሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ ከሠማይ

....አ.ዝ......

ወደ ለምለም መስክ ሠብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኸን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርገኅል ትውልዱን ስቦ
ተክለ ሀይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል ባንተ ጎዳ ደጄ

.....አ...ዝ..

ሠላሳ ስልሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አፅሙ ቆመህ ባንድ እግርህ
የመቶሎሜ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊውም ቀና
ተክለ ሀይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል ባንተ ጓዳ ደጄ
...አ...ዝ.....

በኢትሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየክ ለአምላን አላምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስላንት ዝና ስላንተ ክብር
ተክለ ሀይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል ባንተ ጓዳ ደጄ

/////////////////////////////

#ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
አዝ ------------------
ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፈር የታጠቀ
ንጹሕ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ
የጸጋ ዘአብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ
በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ
አዝ ---------------------
ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት
ባላስድስት ክንፉ ጻድቁ የእኔ አባት
እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ
ሌጌዎን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ
አዝ -----------
ከካህናት መካከል ኅሩይ ነው አቡዬ
መጣው ከገዳምህ ልሳለለምህ ብዬ
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት
ወልድ ዋሕድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስካት
አዝ -----------------
የባረከው ውኃ የረገጥከው መሬት
ጥላህ ያረፈበት ሁኗል ጸበል እምነት
ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ
ይሰብካል ተክለአብ ዛሬም እንደጥንቱ
አዝ ------------------ገድሉ


/////////////////////////////
የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ጸበሉ
አናፍርም ትምኪታችን ነው መስቀሉ (2)

የእኛ ነው የእኛ
የሦስት ሽ አመት ታሪክ ያላት

ታቦተ ጽዮን ያለችበት የጸሎት ስፍራ
የኪዳን ሀገር ኢትዮጵያ እናቴ
ሃገር እግዚአብሔር

የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ጸበሉ አናፍርም
ትምክታችን ነው መስቀሉ

የእኛ ነው የእኛ

በአድስ ድንጋይ የተወቀር የላሊበላ
ድንቅ ስራ ነው ጋርው ክፍት ሆኖ
ዝናብ ማይገባው አቡነ ሀሮን
ምንኛ ውብ ነው

የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ጸበሉ አናፍርም
ትምክታችን ነው መስቀሉ

የእኛ ነው የእኛ

ኢትዮጵያ ሃገሬ ልጅሽ ባኮስ
ተጠምቆልሻል በፊሊጶስ
የአምላክ ስው መሆን ምስጥርን አውቆ
በእየሱስ አምኖ መጣ ተጠምቆ

የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ጸበሉ

አናፍርም ትምክታችን ነው መስቀሉ

የእኛ ነው የእኛ.. .

ትምክህታችን ነው የጌታ መስቀል
አምነን ድነናል በእምነት በጸበል

መለያንች ነው አጥማችን
ተዋህዶ ናት እምነታችን

የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ጸበሉ

አናፍርም ትምክህታችን ነው መስቀሉ

የእኛነው የእኛ...

ጻድቃኔ ሂዱ ሽንኮራ ሂዱ

ግሽንም ውጡ አክሱም ውርዱ

ሽባው ተፍቶ እውሩ በርቶ
ጎባጣው ቀንቶ ዴንቆሮው ስምቶ

ፍጹም አምነናል አይናችን አይቶ
ጸንተን ቁመናል ጆሯችን ስምቶ

የእኛ ነው ዋሻው እምነቱ ጸበሉ

አናፍርም ትምክህታችን ነው መስቀሉ

የእኛ ነው የእኛ.. .

//////////////////////////

ገድል_በገድልህ_ቤት_ውስጥ

ገድል በገድልህ ቤት ውስጥ ሲነበብ ሲሰማ
ልቤ ተማረከበት በተክልዬ ግርማ
ደብረ ሊባኖስ ነው ያየሁት እርሱን
ሊባርክ ሲመጣ ሌተ ቀን ገዳሙን

...አ..ዝ..

እየባረከ ይባርከናል እየቀደሰ ይቀድሰናል
ጸጋው በዝቶለት በአምላካችን
በክንፉ ይበራል ሊያማልደን
አቤት የተክለ ሃይማኖት ክብሩ
ሱራፌል ሆነ በሰማይ ሀገሩ
ጽንአ ይዞ እያጠነ ዙፋኑን
ያስታርቀናል ሌሊትና ቀን
ያማልደናል ሌሊት እና ቀን

....አ....ዝ..

እንግዶች ሆነን ዋሻው ስንሄድ
ያሳድረናል ትሁት ነው ውድ
የአምላክ ምስሌ ሆኖልናልና
ልጆቹ ሁሉ ወጡ ምነና
አቤት የተክለሃይማኖት ክብሩ
ሱራፌል ሆነ በሰማይ ሀገሩ
ጸንአ ይዞ እያጠነ ዙፋኑን
ያስታርቀናል ሌሊት እና ቀን… የማልደናል ሌሊትና ቀን

....አ...ዝ..

በንፋስ አውታር ዘውትር ይሄዳል
በወንጌል መረብ ብዙውን ያጠምዳል
የታመመውን እየፈወሰ
ሙታን ያስነሳል እየቀደሰ
አቤት የተክለሃይማኖት ክብሩ
ሱራፌል ሆነ በሰማይ ሀገሩ
ጽንአ ይዞ እያጠነ ዙፋኑን
ያስታርቀናል ሌሊትና ቀን…ያማልደናል ሌሊትና ቀን
....አ..ዝ...

ድካም የለለበት ዘወትር ብርቱ
ግዳጅ ፈጻሚ ስውር ጸሎቱ
ተዘከረኒ በባህር ወየብስ ድረስ
ተክለሃይማኖት ስልህ
.....አ....ዝ...

አቤት የተክለሃይማኖት ክብሩ
ሱራፌል ሆነ በሰማይ ሀገሩ
ጸንአ ይዞ እያጠነ ዙፋኑን
ያስታርቀናል ሌሊት እና ቀን
ያማልደናል ሌሊት እና ቀን
/////////////////////////////

ገና በሦስት ቀንህ ለምስጋና የተጋህ
ከሱራፌል ተርታ ተዋህዳ ፅናህ
የሥላሴን መንበር አብረሃቸው ያጠንህ
አባ ተክለሃይማኖት ምድራዊ መልአክ ነህ
አባ ተክለሃይማኖት ምድራዊ መልአክ ነህ/2/

አዝ===

ገድልና ታምርህ አያልቅም ተነቦ
የተጋደልክባት ትናገር ደብረ አስቦ
ከፀሎትህ ብዛት አንድ እግርህ ቢቆረጥ
ስድስት ክንፍ ተሰጠህ ክብርህን የሚገልጥ

አዝ===

ቀዝቃዛን ውሃ እንኳን በስምህ የሰጠ
ዋጋ ያግኛልና እጅግ የበለጠ
ዝክርህን መዘከር ስምህን መጥራቴ
ምስክር ይሁነኝ በላይኛው ቤቴ

አዝ====.

ከኃጢአት ወጥቼ ጽድቅን እንድሰራ
ልብ እንዲኖረኝ ቃሉም እንድዘራ
ለሕይወት የሚሆን ፍሬም እንዳፈራ
በረዴኤት ጎብኘኝ ገፅህ ለእኔ ይብራ

አዝ===

አባ ተክለሃይማኖት የወንጌል ገበሬ
ኢትዮጵያን የመገብክ የኅይማኖት ፍሬ
በነፍሴ ተርቤ ሕይወት እንዳላጣ
በጸሎትህ ኅይል እርዳኝ ነፃ ልውጣ

አዝ====


//////////////////////////

አለምን የረታ በእምነት ፪
ፃድቁ አባት ነው ተክለሃይማኖት

አክብሮሀል ጌታ፡፡፡፡፡፡አለምን የረታ
ከፍ አድርጎሀል፡፡፡፡፡፡፡አለምን የርታ
ጸሎትህ ተሰምቶ፡፡፡፡፡፡፡፡አለምን የረታ
ኢትዮጵያ ምሯል ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡አለምን የርታ
በክንፎችህ ጥላ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡አለምን የረታ
ከልለን ተክለ አብ።።።።አለምን የርታ
ልጆችህ እንዳንጠፋ።።።።አለምን የረታ
ከቤትህ ኩብልለን።።።።።አለምን የረታ

አለምን የረታ በፀሎት ፪
ፃዱቁ አባት ነው ተክለሃይማኖት

♦እያበሩ ፋና ዘለቁ፪
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡዪ
ፃድቁ
የንሂሳዉ ሕፃን ።።።።እያበሩ ፋና
ዋስ ሆናት ለነፍሴ፡፡፡፡፡፡፡እያበሩ ፋና
በማህፀን ሳለህ፡፡፡፡፡፡፡ እያበሩ ፋና
መረጡህ ስላሴ።።፡፡፡፡እያበሩ ፋና
ቁምልን በፊቱ።።።።።።እያበሩ ፋና
በሀጢአት ወድቀናል፡፡፡፡፡፡እያበሩ ፋና
ለምንልን ለእኛ።።።።።። እያበሩ ፋና
ፀሎትህ ያበርታን።።።።።እያበሩ ፋና

♦ማልጄ መጣሁኝ ደጅህ፪
አቡነ ሀብተማርያም ልጅህ

ፈዋሹ ሉሚህን ።።።።።ማልጀ መጣሁኝ
በእምነት በልቸ።።።።።።ማልጀ መጣሁኝ
እራቀ ደዌየ።።።።።።።።ማልጅ መጣሁኝ
ፀበልክን ጠጥቸ።።።።።።ማልጀ መጣሁኝ
ፅኑ ነው ኪዳኑ።።።።።።።።ማልጀ መጣሁኝ
የማይናወጥ ።።።።።።ማልጀ መጣሁኝ
ከልብ የለመጣሁብህ።።።።።ማልጀ መጣሁኝ
የወጣል ከማጥ።።።።።።።ማልጀ መጣሁኝ

♦የሊዳዉ ኮከብ  ነህ የቤይሩት ፪
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ነዓ በምህረት
በነጭ ፈረሱ።።።።።።። የሊዳዉ ኮከብ ነህ
ቀድሞ ከፊታቸው ።።።።።የሊዳዉ ኮከብ ነህ
ኢትዮጵያውያንን።።።።። የሊዳዉ ኮከብ ነህ
በድል ያቆማቸው ።።።።።።።የሊዳዉ ኮከብ ነህ
ፅኑ ነው ጊዮርጊስ ።።።።።።።የሊዳዉ ኮከብ ነህ
ገድሉ የሚያስደንቅ።።።።።።።የሊዳዉ ኮከብ ነህ
ተፈትኖ ያለፈ።።።።።።።የሊዳዉ ኮከብ ነህ
አንደ ነጠረ ወርቅ ።።።።።የሊዳዉ ኮከብ ነህ

♦የሲሪንቃዋ እናት አርሴማ ፪
ከደጅሽ መጥቸ ፀሎቴ ተሰማ
የስጨንቀኝ ነበር ።።።።።የሲሪንቃዋ እናት
ለብዙ ዘመን ።።።።።።የሲሪንቃዋ እናት
የልቤን ስነግራት።።።።።።የሲሪንቃዋ እናት
ቀለለኝ አሁን ።።።።።።።።የሲሪንቃዋ እናት
ይርዳል አጋንንት ።።።።።።።የሲሪንቃዋ እናት
ሲጠራ ስምሽ።።።።የሲሪንቀዋ እናት 
ገድልሽ ግሩም ነው ።።።።።።።።የሲሪንቃዋ እናት
ዘንባባሽ ፈዋሽ።።።።።።። የሲሪቃዋ እናት

እልልልልልልልልልልልል

ስለ መዝሙሩ የዝማሬው በአለቤት ልዑል አምላካችን የተመሰገነ ይሁን አሜን፫
♥♥♥♥♥
ወስብኃት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል.
ወለ መስቀሉ ክቡርsaramareyama.890@gmail.com

አታልቅስ

የአባታችን የመጨረሻ ቃል
♥♥♥♥♥♥♥
‹‹ልጆቼ! አታልቅሱ፤ ነገር ግን የሽማግሌውን የአባታችሁን ቃል ስሙ፡፡ መጀመሪያ
እምነታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ በዚህ ዓለም እንደተያዙ እንደ ዓለም ሰዎች
ስለ ልብስና ስለ ምግብ አሳብ አታብዙ፡፡ በየጊዜው ሁሉ መጸለይን አታቋርጡ፣ ለቤተ
ክርስቲያን ሌትና ቀን አገልግሉ፡፡ እግዚአብሔር በሚወደው ገንዘብ ንጽሐ ሥጋንና ጾምን
ውደዱ፡፡ ውዳሴ ከንቱም የሚቀረውንም የዚህን ዓለም ክብር አትውደዱት፤ እናንተስ
የቀደሙትን አባቶች በመከራና በድካም ብዛት ከዓለም የወጡትን በመጋደላቸውም
ክፉውን ሀሳብ ድል የነሡትን ምሰሏቸው፡፡ ፍለጋቸውንም ካልተከተላችሁ ልጆቻቸው
አትባሉምና፤ በመከራቸው ካልመሰላችኋቸው በደስታቸው አትመስሏቸውም፤
በድካማቸውም ካልተባበራችሁ ወደ ቤታቸው አትገቡም፡፡ የቀደሙትን ቅዱሳን
አባቶቻቸሁን መስላችሁ ኃጢአተኛ አባታችሁን እኔን ደግሞ ምሰሉ፤ ስለትኅርምቱም
በመብል በመጠጥ ልባችሁ እንዳይከብድ፣ ሥጋ ከመብላትና ጠጅ ከመጠጣት
ተጠበቁ፡፡ ለመመካትም በዓለማዊ ልብስ አታጊጡ፡፡ የመላእክት አስኬማ ከዓለማዊ
ሥራ ጋር አይስማማምና፤ ዓለምንም በዓለም ላይ ያለውን ሁሉ አትውደዱ፡፡ ዓለሙም
ፈቃዱም ሓላፊ ነውና፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፡፡
ልጆቼ ሆይ! ትሩፋትን ሁሉ በችኮላ ሠርታችሁ በጎይቱን ሃይማኖታችሁን አስከትሏት፡፡
ለነፍሳችሁ እንጂ ለሆዳችሁ አትገዙ፡፡ ሁላችሁ ወንድማማች ሁኑ፡፡ እርስ በርሳችሁም
ተፋቀሩ፤ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ፍቅር ኃጢአትን ያጠፋልና፤ የነፍስና የሥጋን ርኲሰት
ያነጻልና፡፡ ይህንንም ብትጠብቁ በእውነት ልጆቼ ናችሁ፡፡ የሕይወትንም ፍሬ የምታፈሩ
ትሆናላችሁ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ፊት በክብር ትደርሳላችሁ…ልጆቼ ሆይ! ሰላም ለእናንተ
ይሁን፡፡››saramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...