2017 ዲሴምበር 9, ቅዳሜ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበት ክርስቲያን ቅድስት!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በሰንበተ ክርስቲያን እሁድ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና።

( ውዳሴ ማርያም)
ከሴቶች ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ ከተለዩ የተለየች በውስጧም የኪዳን የህግጽላት ያለባት የምትባይ ሁለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ። ኪዳንም በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ አሥሩ ቃላት ናቸው ። ያለመለወጥ ከአንቺ ሰውየሆነ መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን
መጀመሪያስሙን አስቀድሞ በየውጣ ነገረን ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንጹሃን የሆኑትን ወገኖች አነጻቸው ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሁልጊዜ ንጽሕት የሆንሽ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ሁላችን ስለዚህ እናገንሻለን ሰውን በሚወድ በጌታ ዘንድ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እንለምንሻለን ወደ አንቺም እናንጋጥ
ጣለን። ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ያለመለየትናያለመለወጥሰው የሆነ
የእግዚአብሔርንቃል ይመስልልናል። ይኽውም መለወጥ የሌለበት ንጹሕ መለኮት ነው ከአብ ጋር የተካከለ ነው ።
ለንጽሕት በራሱ አበሰራት።በልዩ ጥበቡ ያለ ወንድ ዘር እንደ እኛ ሆነ።መለኮቱን አዋሕዶ ያለ ርኩሰት በአንቺ ሰው ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።

በእግዚአብሔር ስዕል የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ። ንጽሕት ሆይ ያለመለወጥ ከአንቺ ሰው የሆነው ቃል ኃጢአታችንን የሚያስተሰርይልንና አበሳችንን የሚደመስስልን ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የተሰወረ መና ያለብሽ የንጹሕ ወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መናም ከሰማይ የወረደውና ለዓለም ሁሉ ሕይወ ትን የሚያድለውኅብስት ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ሁልጊዜ ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ። ይኸውም ፋና የዓለም ብርሃን ነው ጥንት ከሌለው ብርሃንም የተገኘ ብርሃን ነው።ከእውነተኛ አምላክየተገኘ
እውነተኛ አምላክ ነው። ያለመለወጥም ከአንቺ ሰው የሆነው ነው።

በመምጣቱምሰው በመሆኑምበጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለምንኖር ለእኛ አበራልን።
በልዩ የጥበቡ ምሥጢር (በሥጋዌ)የልቦናችንን እግር ወደ ሰላም መንገድ አቀናልን።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ።ፍሕም የተባለውም
ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው። ይኸውም ከአንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የእግዚአብሔርን ቃል የወለድሽልን መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ከዕሴይ ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሳይተክሏትና ውሃሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች።ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን እውነተኛ አምላካችንን ክርስቶስንየወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደ እርስዋ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ለአንቺ ይገባሻል። አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ ።በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ።ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኚ ነሽ።ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን። እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምህረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ዛሬም ዘውትርም ለዘለዓለሙ አሜን።saramarèyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...