2017 ዲሴምበር 12, ማክሰኞ

ውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲት አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ረቡዕ

♥የረቡዕ ውዳሴ ማርያም♥
♥♥♥♥♥♥♥♥saramareyama.890@gmail.com

    የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ የሰማይ ሠራዊት (መላእክት) ንዕድ ነሽ ይላሉ። ሙሸራው ንጽሕ የሆነ ንጹሕት የሰርግ ቤት ናት። አብ በሰማይ አይቶ አንድ ልጁን ላከው በአንችም ሰው ሆነ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር(ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ የሆነ ነገርን ተናገሩልሽ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ። ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ ፤ ማርያም ሆይ  ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል። ካንቺ ስለተወልደውም ይሰግዱለታል ያመሰግኑታልም ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የዝናብ ውሃ የታየብሽ የእውነት ደመና አንቺ ነሽ። አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይል ጋረደሽ ፤ ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን የወለድሽልን መጥቶም ከኃጢአት አዳነን። ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው ወደእኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርከን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርካት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ጸጋን አገኘሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይልም ጋረደሽ (ጸለለብሽ) ማርያም ሆይ በእውነት ቅዱስ ወለድሽ ዓለምን ሁሉ የሚያድን መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

አንደበታችን የድንግልን ሥራ ያመስግናል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት አገር ከእርስዋ ስለተወለደ አምላክን የወለደች ማርያምን ዛሬ እናመስግናት አሕዛብ ኑ ማርያን እናመስግናት። እናትና ድንግል ሁለቱንም ሆናለችና። ርኩሰት የሌለንሽና የአብ ቃለ መጥቶ ካንቺ ሰው የሆነ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ ነውር የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለንሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ። ስለቀደመ ሰው አዳም ሁሉተኛ አዳም የሆነ የክርስቶስ ማደሪያው የምትናገሪው  ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ። በክቡር ጌጥ ሁሉ ያጌጠ እርሱ መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንጽሕት የሠርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ የመለኮት እሳት (ባሕርይ) ያላቃጠለሽ ዕፀ ጳጦስ ሆይ ደስ ይበልሽ። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን ሰማያዊ መለኮትን በሥጋ የተሸከምሽ ገረድና እናት ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ።  ስለዚህ ንጹሓን ከሆኑ መላእክት ጋር በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተን እናመስግን በሰማይም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ዕርቅ ይሁን እንበል ክብርና ምስጋና ጌትነት ያለው እርሱ አንችን ወድዋልና ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፣ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማይት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ተሸከመቸው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣልች፣ ከሱራፌልም ትበልጣልች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና።  የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህች ናት። ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው። በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ከድንግል ሰው ሆኗዋልና። ኑ ይህን ድንቅ እዩ። ስለ ተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ። ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና። ቃል ተዋህዷልና። ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግይ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለት እናመስግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እርስዋ መሰከረ ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ ምሥራቅ አየሁ አለ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ኆኅትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት። እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ ቀድሞ በድንግልና ኖራለችና። መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለጅሽ ሆይ የማኅፅንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፥ አንቺ ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ የእውነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖር ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ለአንቺ ይገባል። የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ። ከሰው ጋርም ተመላለሰ። መሓሪ ይቅር ባይ ሰውን ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...