2018 ጁላይ 9, ሰኞ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄና መልሶች የምዕራፍ ፬የ35ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ ውድድር

✝የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ✝@Teyakaenamels
@Teyakaenamelsወመንፈስ

በስመ አብ ወወልድ  ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

#የምዕራፍ ፬/የ35 ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃልና የጹህፍ የጥያቄና መልስ ውድድር

የዚህ ጥያቄና መልስ ምንጭ፦ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ ነው👇
===×××===
1⃣ዐማኑኤል ማለት ምን ማለት ነው?
     ሀ.እግዚአብሔር ብርሃን ነው
     ለ.እግዚአብሔር ፍቅር ነው
     ሐ.እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው
     መ.እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው

✅= ሐ

2⃣የነብያት ትንቢት ፍጻሜ የሆነውን ጌታችንን ሳያይ ሞትን እንደማይቀምስ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ የነበረ ሰው ማን ነው?
  ሀ.ቀነናዊው ስምዖን
  ለ.ስምዖን ጴጥሮስ
  ሐ.አረጋዊው ስምዖን
  መ.ሲሞን መሥርይ(መሠርይ)

✅=ሐ

3⃣የሰውነት መብራት የሚባለው የአካል ክፍል የትኛው ነው?
  ሀ.ልብ
  ለ.ልቦና
  ሐ.ዓይን
  መ.አዕምሮ

✅= ሐ

4⃣ከሚከተሉት አባባሎች መካከል በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረው የትኛው ነው?
  ሀ.«ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ»
  ለ.«ስለ እኔና ስለወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል»
  ሐ.«የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና»
  መ.ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅=መ

5⃣«ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው እርሱ ከሙታን ተነሥቷል፡ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል»ያለው ማን ነው?
  ሀ.ፊሊጶስ
  ለ.ጲላጦስ
  ሐ.ሄሮድስ
  መ.አርኬላዎስ

✅=ሐ ማቴ 14፥1

6⃣«የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም»ያለው ማን ነው?
  ሀ.ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
  ለ.ቅዱስ ጴጥሮስ
  ሐ.ልጇ የታመመችባት ከነናዊት ሴት
  መ.ይሁዳ

✅=ሀ

7⃣ልጆቿ በክርስቶስ ቀኝ እና ግራ እንዲቀመጡላት የለመነችው ማን ናት?
  ሀ.የያዕቆብ እና ዮሳዕ እናት
  ለ.የጴጥሮስ እና እንድርያስ እናት
  ሐ.የያዕቆብ እና የዮሐንስ እናት
  መ.የማርታ እና የማርያም እናት

✅=ሐ

8⃣የጌታችን ደቀመዛሙርት ምን በማድረጋቸው ነው ፈሪሳውያኑ ቀርበው«ደቀመዛሙርትህ እንደ ሽማግሎች ወግ ስለምን አይሄዱም»ያሉት?
  ሀ.ስላልጾሙ
  ለ.ሰንበትን ስላላከበሩ
  ሐ.እጆቻቸውን ሳይታጠቡ ስለበሉ
  መ.ብሉይ ኪዳን አያስፈልግም ስላሉ

✅= ሐ

9⃣ወደ ኤማሁስ በሚሄዱበት ጊዜ ሁለት ሐዋርያት ስለምን እየተነጋገሩ ነበር?
  ሀ.ስለ ኢየሰስ ክርስቶስ ማንነት
  ለ.ክርስቶስ በምሳ ስላስተማረው ትምህርት
  ሐ.ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ እየተመካከሩ
  መ.መልስ የለም
✅= መ

🔟በይሁዳ ምትክ ከዐሥራ አንዱ ጋር የተቆጠረው ሐዋርያ ማን ነው?
  ሀ.ማቴዎስ
  ለ.ሉቃስ
  ሐ.ማትያስ
  መ.ቀለዮጳ

✅=ሐ

1⃣1⃣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረታቦር ተራራ አምላክነቱን በገለጠ ጊዜ የነበሩት ሦስት ደቀመዛሙርት እነማን ነበሩ?
  ሀ.ቅዱስ ጴጥሮስ፣ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅዱስ እንድርያስ
  ለ.ቅዱስ ፊሊጶስ፣ቅዱስ በርተሎሚዎስ እና ቅዱስ ታዴዎስ
  ሐ.ቅዱስ ጴጥሮስ፣ቅዱስ ያዕቆብ እና ቅዱስ ዮሐንስ
  መ.ቅዱስ ናትናኤል፣ቅዱስ ስምዖን እና ቅዱስ ማርቆስ

✅=ሐ

1⃣2⃣በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው የሐዲስ ኪዳን ሰማዕት ማን ነው?
  ሀ.ቅዱስ እስጢፋኖስ
  ለ.ቅዱስ ያዕቆብ
  ሐ.ቅዱስ ለንጊኖስ
  መ.ቅዱስ ጴጥሮስ

✅= ሀ

1⃣3⃣ክርስቶስ በተሰቀለበት ዘመን ሊቀ ካህናት የነበረው ማን ነው?
  ሀ.ሐና
  ለ.ቀያፋ
  ሐ.ሰጲራ
  መ.ሐናንያ
✅=ሀ

1⃣4⃣ከሚከተሉት የቅዱስ ጳውሎስ መልዕካታት ውስት ስለ ካህናት አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልፀው የትኛው ነው?
  ሀ.ለቲቶ የተላከው
  ለ.ለጢሞቴዎስ መጀመሪያ የላከው
  ሐ.ወደ ኤፌሶን ሰዎች የላከው
  መ.ወደ ገላቲያ ሰዎች የላከው

✅=ለ

1⃣5⃣ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባት ከተማ ማን ናት?
  ሀ.ገሊላ
  ለ.ቤተልሔም
  ሐ.ናዝሬት
  መ.ቃና

✅=ለ

1⃣6⃣በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው---
  ሀ.መንግስተ-ሰማያት የእነርሱ ናትና
  ለ.መጽናናትን ያገኛሉና
  ሐ.ምድርን ይወርሳሉና
  መ.እግዚአብሔርን ያዩታልና

✅=ሀ

1⃣7⃣ነባቤ መለኮት በመባል ሚታወቀው ወንጌላዊ ማን ነው?
  ሀ.ቅዱስ ማቴዎስ
  ለ.ቅዱስ ማርቆስ
  ሐ.ቅዱስ ሉቃስ
  መ.ቅዱስ ዮሐንስ

✅= መ

1⃣8⃣እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ ------------- መንፈስ አልሰጠንምና
  ሀ.የፍርሃት
  ለ.የግብዝነት
  ሐ.የሐሰት
  መ.የጥላቻ

✅=ሀ

1⃣9⃣አገልጋዩ አናሲሞስን ምሕረት አድርጎ እንዲቀበለው ቅዱስ ጳውሎስ ደብዳቤ የላከለት ሰው ማን ነው?
  ሀ.በርናባስ
  ለ.ጢሞቴዎስ
  ሐ.ፊሊሞና
  መ.ቲቶ
✅=ሐ

2⃣0⃣ከሚከተሉት ውስጥ ምሳሌያዊነት የሌለው ታሪክ የትኛው ነው?
  ሀ.የጠፋው ልጅ
  ለ.የቀራጩና የፈሪሳዊው
 ሐ.የጠፋው በግ
  መ.የሰማርያዊቷ ሴት


✅=መ

✅✅✅
ማጠቃለያመልስ ይህንን ይመስላል ስተት ካለ አርሙን....saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...