2018 ሜይ 13, እሑድ

መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ✍🖊
1 ቄሱ፡- ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ ማለት ምን ማለት ነው?
ሰማያዊ
ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ ማለት በልቡናችሁ  ቤታችሁን የምትወርሱበትን ሥራ አስቡ፤ አሳባችሁንም በሥራ ተርጉሙት ማለት ነው፡፡ ሕዝቡም ሰማያዊ ምስጢርን ካሰብን በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ ሲል ስለ ልቡናችህን ሀሳብ ርስተ መንግስተ ሰማያትን ማሰብ እንዳለብን ለመግለጽና አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡


ጥያቄ 2 ዲያቆኑ፡- የተቀመጣችሁ ተነሱ/ሁለተኛ ትርጓሜውን ስጥ?
የተቀመጣችሁ ተነሱ ሲል በቅዳሴ ጊዜ ከበሽተኛና ከአረጋውያን/ከሽማግሌዎች/ በቀር የሚቀመጥ ኖሮ አይደለም፡፡ ይህን ሲለን ከመዘንጋት አልጋ በንቃት፤ ከክፋት መኝታ አልጋ በቅንነትና በተመስጦ ከአምላካችሁ ጋር በጸሎት ተገኛኙ ማለቱ ነው፡፡ አንድም ክብሩንና የአምልኮቱ ዜና ሲነገር መቀመጥ አይቻልም ማለቱ ነው፡፡


ጥያቄ 3 ዱያቆኑ፡- ወደ ምስራቅ ተመልከቱ- ለምን?
ሀ. ምስራቅ ማህደረ እግዚአብሔር ፤ ምዕራብ ማህደረ ዲያቢሎስ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፤
ለ. ወንጌል የመጣችሁ በምስራቅ በኩል መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፤
ሐ. ምስራቃዊያን ሰባ ሰገል ባመኑበት ወንጌል እመኑ ሲል ነው፤
መ. የጌታን ነገረ ምፅዓቱን አስቡ ማለቱ ነው፤
ሠ. ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው፤ ምክንያቱም ጸሐይ በምስራቅ በኩል እንደሚወጣ ጸሐየ ጽድቅ     ኢየሱስ ክርስቶስም ከእመቤታችን መወለዱን ሲያስረዳ ነው፡፡ ማስረጃ ሚሊኪያስ 4÷2
ረ. ምስራቅ የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፡፡ ሕዝቄል 43÷2
ሰ. የክርስቶስ ዳግም ምጽዓቱም በምስራቅ በኩል መሆኑን ሲያስረዳ ነው፡፡ ማስረጃ ዘካሪያስ 14÷14


ጥያቄ 4 ዲያቆኑ እናስተውል /ምንን/?
-ያለንበትንና የቆምንበትን ሥፍራ የት እንደሆነ እንለይ /እናረጋግጥ/ ሲል ነው፤
-ከእግዚአብሔር ጋር ነን ወይስ ከስጋዊ ሃሳባችን ጋር ነን ሲለን ነው፤
-ከስጋውያን ዘመዶቻችን ጋር ነን ወይስ ከድንግል ማርያም፤ ከቅዱሳን መላዕክት ጋር፤ ከጻድቃን ሰማዕታት ጋር ነን ወይ ሲለን ነው፡፡


ጥየቄ 5 ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር ማለት ምን ማለት ነው?
- ልቡናችሁ ሰማያዊ ነገርን በማሰብ በአንክሮ በተዘክሮ ጸንቶ ይኑር ማለቱ ነው፤
- የምድራዊ ኑሮአችን የኮንትራት ውላችንን እስክናበቃ ድረስ ብቻ መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፤
- ምድራዊያን ስንሆን ሰማያውያን መሆናችንን ልብ እንበል ማለቱ ነው፡፡
- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለፊሊጲዮስ ሰዎች በምዕራብ 3÷20 ሀገራችን በሰማይ ነው በማለት ሰማያውያን መሆናችንን መስክሯል፡፡
- ሕዝቡም እውነት ነው ልቡናችን ሰማያዊ ነገርን ያስብ ይበሉ ማለት ነው፡፡

ጥያቄ 6 አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ለምን እንላለን? ለምን ከአስራ ሁለት አልበለጠም? ከአስራ ሁለትስ ለምን አላነሰም? በጣትስ ለምን እንቆጥራለን?
አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ የምንለው የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ስም ፊደላት ሲቆጠሩ 12 መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ ሌላው በ12 ሐዋሪያት ምልጃ አድነን ይቅርም በለን ማለት ነው፡፡ ከ12 ያልበለጠበትና ያላነሰበት ምክንያት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም ፊደላት ከ12 አይበልጥም አያንስምም፡፡ ሌላው የሐዋርያት ቁጥር ብዛታቸው 12 መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው በራሱ ጥፋት በወጣበት በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ ሐዋሪያው ማትያስ በዕጣ መመረጡን ሐዋ.ሥ1÷23-26 ያስረዳል፡፡ ለዚህም ነው ከ12 ያልበለጠው ወይም ያላነሰው፡፡ ወደ ላይ ዕረገቱን ወደታች መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡
                                                     አዘጋጅ፡- መ/ስ/ቆ/አባ መዝሙር ሐዋዝ
.https://t.me/Teyakaenamels
https://t.me/Teyakaenamels
https://t.me/Teyakaenamels

2018 ሜይ 7, ሰኞ

የክለሳ 30 መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እነሆ የክለሳ መንፈሳዊ 30 ጥያቄ በድንግል ማርያም የአስርአት ልጆች ማኅበር እንዲህ ተዘጋጅቶ ቀረበ⤵

1⃣✍ _ጌታ ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ዳርቻ ለወንጌል አገልግሎት ሲልካቸው ስንት ስንት አድርጎ ነው❓_

_ሀ// ሁለት ሁለት_
 _ለ // አንድ አንድ (ለየብቻቸው)     ሐ// ሦስት ሦስት_
_መ//መልሱ የለም_

//መልስ// ሀ

_2⃣✍ከሐዋርያት መካከል በመጀመሪያ የሰማዕትነትን አክሊል የተቀናጀ እና በሐዲስ ኪዳን መፅሐፍት የተፃፈለት ብቸኛ ሐዋርያ ማን ነው❓_

_ሀ// ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎት_
_ለ// ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ (ወልደ ዘብዲዮስ )_
_ሐ // ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ (ወልደ ዘብዲዮስ )_
_መ// መልሱ የለም_

//መልስ//ሐ


_3⃣✍የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለው ማን ነው❓_
_ሀ//ወንጌላዊው  ዮሐንስ_
_ለ//ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ_
_ሐ//ዮሐንስ አፈወርቅ_
_መ// መልስ የለም_

//መልስ// ሀ
4⃣✍ቅዱስ _ሉቃስ ጌታን_ _ከመከተሉ በፊት ስራው ምን_ _ነበር❓_

_ሀ// አሳ አጥማጅ_
 _ለ//ቁርበት ፋቂ_
_ሐ//  ነጋዴ_
_መ//ሃኪም (ዶክተር )_.

//መልስ// መ

_5⃣✍ለመናብርት አለቃ ሆኖ የተሰየመው መልአክ ማን ነው ❓_

_ሀ//ቅዱስ ሚካኤል_
_ለ//ቅዱስ ራጉኤል_
_ሐ//ቅዱስ ገብርኤል_መሆኑን
_መ//ቅዱስ ሩፋኤል_

//መልስ// መ

_6⃣✍የእመቤታችን የስደት_ _ጊዜ 3 ዓመት ከ6 ወር  የተገለፀበት የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው❓_

_ሀ//ማቴ 2፥13_
_ለ//ት.ኢሳያስ 8፥14_
_ሐ//ራዕይ ዮሐንስ 12፥14_
_መ//ሉቃስ 1፥18_ከፈረሰ

//መልስ//ሀ

_7⃣✍ሰለሞን ያሰራው ቤተ መቅደስ በባቢሎናዊያን  ከፈረሰ በኋላ ከእንደገና እንዲሰራ ያደረገው ሰው ማን ይባላል❓_

_ሀ//ዘሩባቤል_
_ለ//ሄሮድስ_
_ሐ//መልስ የለም_
_መ//ሀ&ለ መልስ ናቸው_

//መልስ//ሀ

_8⃣✍ከሰው ወገን ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን ምስጋና ያቀረበ ማን ነው❓_

_ሀ// ቅዱስ እያቄም_
_ለ// ቅድስት ኤልሳቤጥ_
_ሐ// ቅዱስ ዮሴፍ_
_መ// ቅድስት ሐና_

//መልስ// ለ
_9⃣✍ለመጀመርያ ግዜ እግዚአብሔር ይፍታ ያሉት አባት ማን ይባላሉ❓_

_ሀ// አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሀን_
_ለ// አባ ጳውሊ_
_ሐ//አባ በርናባስ_
_መ// አባ ጴጥሮስ_

//መልስ///መ
_🔟✍የቤተክርስቲያናችን ሊቅ የዜማው ደራሲ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያ ዜማው ምን በመባል ይጠራል ❓_

 _ሀ// በግዕዝ_
_ለ// እዝል_
_ሐ// አራራይ_
_መ//ሁሉም መልስ ናቸው_

//መልስ// ሐ

_1⃣1⃣✍ከገነት ፈሳሽ ወንዞች መካከል ኢትዮጵያን የከበበው ወንዝ ማን ይባላል ❓_

_ሀ// ኤፍራጠስ_
_ለ//ጊዮን_
_ሐ//ጤግሮስ_
መ// ሶፍን

//መልስ// ለ

_1⃣2⃣✍"እህቴ ሙሽራ የተቆለፈ ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመም የውኃ ፈሳሽ ናት" መኃ 4፥10 የሚለው ጥቅስ ምንን ያመለክታል❓_

_ሀ// የእመቤታችን ፍፁም ድንግልናን_
_ለ// እመቤታችን ጌታን መውለዷን_
_ሐ// ለእመቤታችን የተሰጠውን ቃል ኪዳን_
_መ// የእመቤታችንን ስደት_

//መልስ// ሀ

_1⃣3⃣ጠረፍን  የሚያቀዘቅው ወንዝ ማን ይባላል❓_

_ሀ// ሐኖስ_
_ለ// ጤግሮስ_
_ሐ// ሀ&ለ_
_መ// መልስ የለም_

//መልስ//ሀ

_1⃣4⃣✍ ከሚከተሉት ውስጥ የራዕይ መፅሐፍ የሆነው የትኛው ነው❓_

_ሀ// ፍካሬ ኢየሱስ_
_ለ// ራእይ ሲኖዳ_
_ሐ// መፅሐፈ ሳቤላ_
_መ//ሁሉም_

//መልስ// መ

_1⃣5⃣✍በቅደም ተከተል ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን ቤተ መቅደስን የሰሩ 3 ነገስታት እነማን ናቸው❓_

_ሀ// ንጉስ ሄሮድስ ፣ ዘረባቤል፣ንጉስ ሰለሞን_
_ለ// ዘሩባቤል ፣ንጉስ ሰለሞን ፣ንጉስ ሄሮድስ_
_ሐ// ንጉስ ሰለሞን ፣ዘሩባቤል ፣ ንጉስ ሄሮድስ_
_መ// መልስ የለም_

//መልስ// ✍ሐ

1⃣6⃣✍ቅዱሳን ሐዋርያት እስከ መጨረሻ በመጽናት ለክርስቶስ ምስክር ለመሆናቸው ምክንያት ምንድን ነው?

ሀ// በዓይናቸው ስላዩት

ለ// በእጃቸው ስለዳሰሱት

ሐ// ትምህርቱን በጆሮአቸው ስለሰሙት

መ// በእርሱ ስለተላኩ

ሠ// ከትንሳኤው በኋላ ስለአዩት

ረ// ሀ&ንሐ

ቀ// ሁሉም መልስ ነው

//መልስ// ቀ


1⃣7⃣✍የቅዱስ ጳውሎስን የሕይወት ታሪክ መዝግቦ የያዘው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው??

ሀ// የሐዋርያት ሥራ
ለ// የማቴዎስ ወንጌል
ሐ// የማርቆስ ወንጌል
መ// የዮሐንስ ወንጌል

//መልስ//ሀ

1⃣8⃣✍ጌታ ሲወለድ የነበሩት የእስራኤልና የኢትዮጵያ ነገሥታት እነማን ነበሩ??በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልስ ይገኛል??

ሀ// ንጉስ ሰሎሞንና ዳግማዊ ሚኒሊክ (ማር 1፥2)

ለ//ሄሮድስና ንጉሥ ባዚን (ማቴ 2፥1)

ሐ// ንጉሥ ባዚንና ዘሩባቤል( ሉቃ...3፥4)

መ// መልሱ የለም

//መልስ// ለ

 1⃣9⃣✍ነቢዩ ዳዊት ጎልያድን ለመምታት ያነሳው ጠጠር ብዛት ስንት ነው???ታሪኩስ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል??

ሀ//ያነሳው፦ 7ት ጠጠር ሲሆን.(በ2ኛ ሳሙ..ም 1፥10) ላይ ይገኛል።

ለ// ያነሳው፦10 ጠጠር ሲሆን፦(በ1ኛ ነገስት.ም 2፥5) ላይ ይገኛል

ሐ// ያነሳው፦ 5ት ድብልብል። ድንጋይ ሲሆን (1ኛ ሳሙ. 17፥40) ላይ ታሪኩ ይገኛል

መ//ሀ&ለ መልስ ነው።

//መልስ// ሐ

2⃣0⃣✍ለአዲስ ኪዳን የመጀመርያው ሐዋርያ ለብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነቢይ በመባል የሚታወቀው ማነው???

ሀ// ነቢዩ ኤልዕሳ

ለ// ነቢዩ ኢሳያስ

ሐ// ነቢዩ ኤልያስ

መ// መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

//መልስ// መ

2⃣1⃣✍ እስራኤልላውያን ባህረ ኤርትራን እንደ ተሻገሩ   ንሴብሖ/፪/ ለእግዚአብሔር ብላ ለመጀመርያ ጊዜ የምስጋና መዝሙር የዘመረችው ማናት??

ሀ// የሙሴ እህት ማርያም

ለ// እመ ሳሙኤል

ሐ// ዲቦራ
መ// መልስ የለም

//መልስ// ሀ

2⃣2⃣✍ሐዋርያት ለመጀመርያ ጊዜ ክርስቲያን የተባሉት በየት ነው???

ሀ// በደማስቆ

ለ//በአንፆኪያ

 ሐ// በገሊላ አውራጃ

መ// መልስ የለም

//መልስ// ለ

2⃣3⃣✍አምስቱ(፭)አርዕስተ አበው ከሚባሉት መካከል የሆነው የትኛው ነው??

ሀ// አዳም

ለ// ሄኖክ

ሐ// ኖህ

መ// ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ//መ

2⃣4⃣✍የማሕሌት ሰባት(፯) ደረጃዊች ከምንላቸው መካከል የሆነው የቱ ነው???

ሀ// ቁም ዜማ

ለ// ዝማሜ

ሐ// ቁም ጸናጽል

መ//መሁሉም መልስ

//መልስ// መ

2⃣5⃣✍በስርዓተ ቅዳሴ ጊዜ/ ወንጌል ሲነበብ ሻማ/ጧፍ ለምን ይበራል??

ሀ// ጌታችን እኔ የዓለም ብርሀን ነኝ ስላለ

ለ// ሐዋርያት ፃድቃን ሰማዕታት ለወንጌል የከፈሉትን ዋጋ ስለምናስብበት

ሐ// ትርጉም የለውም

መ// ሀ&ለ መልስ ናቸው።

//መልስ// መ


https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

 እንቆቅልሽ/ህ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

2⃣6⃣✍ የወግ የማእረግ ጎጆዬን ጥዬ
 ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በበረሃ ተቃጥዬ
እግሬ እስኪተላ ጣና ሀይቅ  ላይ ጠልዬ
የለመንኩኝ ሳጥናኤልን ማረው ብዬ
እኔ ማነኝ??

ሀ// ቅድስት አርሴማ

ለ// ቅድስት እየሉጣ

ሐ// ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ

መ// መልስ የለም

//መልስ// ሐ

 ↪2⃣7⃣✅አታድርጊ ሲሉኝ አድርጌ የጨው ሀዉልት ሆኘ ቀረሁ ከተራራው ግርጌ እኔ ማነኝ??

ሀ// የሎጥ ሚስት

ለ//አጋር

ሐ//ሶስና

መ// መልስ የለም


//መልስ// ሀ

↪2⃣8⃣✍ወንዝ የፈሰስኩት ደም እየተጣራ ስቅበዘበዝ ኖርኩኝ በሰራሁት ስራ እኔ ማነኝ??

ሀ// ይሁዳ

ለ// ቃየል

ሐ// ሄሮድስ

መ// ሁሉም

//መልስ// ለ

 ↪2⃣9⃣ሊቀብረኝ ጉድጎድ እንዳልቆፈረ ደግሞ እንደወዳጂ ስሞኝ ነበር
ይህ ከዳተኛ ሰው ስሙ ምን ነበረ??

ሀ//ዴማስ

ለ// ሳኦል

ሐ// ይሁዳ

መ// መልሱ አልተሰጠም

//መልስ// ሐ

3⃣0⃣ስታመንላት ከልቤ ሚስጥሬን ሁሉ ባዋያት ግራ ጎኔ ጨክና አስረከበችኝ ለጥላት ይች ከዳተኛ እንስት ስሞ ማን ??
.
ሀ// ደሊላ

ነበረችለ// አስቴር

ሐ// ሩት

መ// መልስ የለም።

//መልስ//ሀ

ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ከአለ አርሙኝ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://www.facebook.com/saramariyama/

https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsara mareyama.890@gmail.com

2018 ሜይ 4, ዓርብ

የምዕራፍ ሦስት መጨርሻል የ30ኛ ዙር ጥያቄና መልስ ውድድር

#✝በስመ #አብ #ወወልድ #ወመንፈስ #ቅዱስ #አሃዱ #አምላክ #አሜን

#↪የምዕራፍ #ሦስት #መጨረሻ #የ30 #ዙር #የጠቅላላ #እውቀት ^የቃል #መንፈሳዊ #ጥያቄና #መልስ #ውድድር

↪ጥ.ተራ ቁ.✍1⃣ትንሳኤ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በየመልኩ በየአይነቱ ሲተረጎም 5ክፍሎች አሉት ምን ምን ናቸው??

#መልስ#

1)አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው ፡፡ይህም ማለት ተዘክሮተእግዚአብሔርነው፡፡
2)
ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና
ነው ፡፡የዚህም ምስጢሩ ቃለእግዘብሔርንመስማትና በንስሐእየታደሱበሕይወት መኖር ነው፡፡
3)
ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው
የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል ፡፡ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
4)
አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ
በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን
አድርጎ መነሣት ነው፡ ፡

5) ዐምስተኛውና የመጨረሻው«
የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ
ድልአምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ»
መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ »
ነው፡፡ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላሰውሁሉ እንደየሥራው ለክብርናለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔበአንድነት የሚነሣው የዘለዓለምትንሣኤ ይሆናል፡፡
ዘጉባኤወደተነሣንበት ዐላማ ስንመለስየትንሣኤበዓል በቃሉም ምስጢርበይዘቱምስለሚመሳሰሉ ጥላውምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎይጠራል፡፡

↪ጥ.ተራ.ቁ✍2⃣ ጴራቅሊጦስ ማለት የግሪክ(የጽርህ ቃል) ሲሆን 5ትርጉሞች አሉት ምን ምን ናቸው??


#መልስ 1.ናዛዚ=የሚያረጋጋ መንፈስ ማለት ነው
2.ከሳቲ=ገላጭ/ምስጢር ገላጭ/ማለት ነው
3.መንቅሂ=የሚያነቃቃ//መንፈስ ማለት ነው
4.መጽንኢ=የሚያጸና /የሚያጠነክር/መንፈስ ማለት ነው
5.መስተስፍሂ=ደስ የሚያነሳሳየሚያሰኝ መንፈስ ማለት ነው።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍3⃣ስንት አይነት ሞት አለ??

#መልስ#
➡አራት አይነት ሞት አለ እነሱም ሞተ  ሥጋ(
 ሞት) እርደተ መቃብር ነው ሥጋ ወደ መሬት ነፍስ ወደ ሰማይ መ መክ 12÷7
➡ሞተ ነፍስ (የነፍስ ሞት) እሱን የማትሰማ ነፍስ የሥጋትሞታለች
ዘዳ 18÷15
ሀዋ 3÷23
➡ሞተ ሀጢአት(የሀጢአ ያት ሞት)የሀጢያት ደመወዝ ሞት ነውና ሮሜ 6÷23 ቆላ 1÷22
➡ሞተ ህሊና (የህሊና ሞት) ናቸው።

↪ ጥ.ተራ ቁ.✍4⃣የእናታችን የድንግል ማርያምን ስም ያስተዋወቀ ማን ነው??

#መልስ# ✍ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ነው።

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍5⃣ መንፈሳዊ ውበት ከሚባሉት ውስጥ ቢያንስ 5 ጥቀስ???

#መልስ#↪
➡እግዚአብሔርን መፍራት በፈሪሀ እግዚአብሔር መገዛት
➡ትህትና ትሁት መሆን ነው
➡ቅንነት
➡ንፁህ ልብ ነው
➡ለፅድቅ መጨከን የእግዚአብሔርን ቃል ላለማፍረስ መጠንከር ውበት ነው
➡ይቅርታ
➡ማስታረቅ.ወ.ዘተ


↪ ጥ.ተራ.ቁ.✍ ህገ ወንጌል ማለት ከማን እስከ ማን ያለው  ዘመን ነው?

#መልስ#✍
➡ክርስቶስ በሥጋ ከተገለጠበት እስከ እለተ ምጽዓት አሁን የያዝነው ዘመን ጨምሮ ያለው ነው።

↪ጥ.ተራ ቁ✍7⃣. ሙሴ ግብፃውያንን ገድሎ እስራኤላውያንን ነፃ አወጣ ወደ ክርስቶስ ታሪክ። ቀይሩ??

#መልስ#✍
➡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ።ዲያብሎስን ግድሎ እኛን ከዲያብሎስ ባርነት በደሙ ልጆቹን ነፃ አወጣን።

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍8⃣በብሉይ ኪዳን የሰመረ የአማረ ለእግዚአብሔር መስዋዕት ካቀረቡ አበው መካከል የ8 አባቶችን ስም ዘርዝሩ ??

#መልስ#

➡አዳም
➡አቤል
➡ሄኖክ
➡መልከ ፀዴቅ
➡አብረሀም
➡ይስሀቅ
➡ያዕቆብ
.
↪ጥ.ተራ.ቁ.✍9⃣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዬሐንስ በእስር ቤት እያለ ወደ ጌታ የላካቸው ደቀ መዛሙርቶች ስንት ነበሩ?  ጌታስ የላከለት መልስ ምን የሚል ነበር?

#መልስ#↪ሁለት ናቸው። ጌታ የላከለትም መልእክት ዕውሮች ያያሉ፣ አንኮች ይሄዳሉ፣ ለምፃሞች ይነፃሉ። (ማቴ 11፥26)

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍, ጌታ መስቀል ላይ እያለ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተቀዷል፡፡ ለመሆኑ ምስጢሩ ምንድን ነው??

#መልስ፡- በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለው የጠብ ግድግዳ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ ማቴ.27÷51።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣1⃣ አዲስ ኪዳን ማለት ምን ማለት ነው ?የተመሰረተው መቼ ነው? ዕለቱስ??

#መልስ፡-አዲስ ውል/ ስምምነት/ ማለት ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ እለት፡፡ ሉቃስ 22÷20. ኤር. 31÷31

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣2⃣. እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ሁለት  ጥንዶች ሲጋቡ የሚደረግላቸው ሥርዓት…………መጽሐፍም…….በመባል ይታወቃል??

#መልስ፦ ስርዓተ ተክሊልና መጽሐፈ ተክሊል።


↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣3⃣እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው በስንት ነገር ነው ?ምን ?ምን ናቸው?

#መልስ፦ በዝምታ፣ በመናገር፣ እና በተግባር ነው። ለምሳሌ፦ መላእክትን በዝምታ፣ ፀሐይና ጨረቃን በመናገር፣ሰውን በተግባር ።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣4⃣.እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ የስንት ዓመት እድሜ ነበሩ?

#መልስ፦ አዳም የ30 ሄዋን የ15 ዕድሜ ።

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣5⃣ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ፣ ሦስት ሲሆን አንድ ነው፡፡ ለመሆኑ አንድነቱ በምን በምን ነው? ሦስትነቱስ?

#መልስ፦ አንድነቱ በመለኮት፣በአገዛዝ፣በሥልጣን፣በፈቃድ።
ሦስትነቱ፦በስም፣በአካል፣በግብር ነው።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣6⃣ በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ላይ በተለይ በማቴዎስ ወንጌል ላይ የአብ ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም በግልጽ የተጠቀሰው በየትኛው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ነው?

#መልስ፦ በማቴዎስ ወንጌል ም.28፥19 ላይ ይገኛል።


↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣7⃣እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ የተባሉት ምን ምን ናቸው? ከሦስቱ የትኛው ይበልጣል? ምዕራፍና ቁጥሩስ?

#መልስ፦ እምነት፣ተስፋ ፍቅር ጸንተው ይኖራሉ ከሁሉም ፍቅር ይበልጣል። 1ኛ፦ቆሮ 13፥13

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣8⃣. ነቢዩ ኤርሚያስ ከትንቢተ ኤርሚያስ በኋላ የፃፋቸው 2 መጽሐፍት ምን እና ምን ናቸው ? ትርጓሜያቸውስ?

#መልስ፡- ሰቆቃው ኤርሚያስ / የኤርሚያስ ልቅሶ ወይም ሙሾ/ ማለት ነው፡፡ ተረፈ ኤርሚያስ / ከኤርሚያስ የተረፈ ማለት ነው/፡፡

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣9⃣ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ነገሮችን ያመለክታል ለመሆኑ እነዚህ 3 ነገሮች ምን ምን ናቸው?

#መልስ- 1. ሕንጻው እራሱ ፣2. የክርስቲያኖች ህብረት፣ 3.አንድ አማኝ ብቻውን፡፡

↪ጥ.ተራ.ቁ✍2⃣0⃣. ሳይወለድ የሞተው ወይም ወደመቃብር የወረደው ብቸኛው ሰው ማን ነው??

#መልስ፦ አዳም ነው። ተፈጠረ እንጅ አልተልለደም።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ/ን  ጥያቄና መልሶች የሚተላለፉበት ቻናል

 አስተያየት👇
@saramareyamesara mareyama.890@gmail.com
.
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA



የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...