2017 ዲሴምበር 24, እሑድ

ልዩ የግጥም መድብል

*አምላክን ሽንገላ*

ጾም የሚሏት ነገር የስጋ ፈተና
አስቸገረች በጣም ካቅም በላይ ሆና
የትሩፋት ስራ መሆኗ ተረስቶ
ሰው ፈጽሞ ጠላት ሸሸ ፊቱን ነስቶ
ወጣቱ አቃለላት ሻራት ቁርሱን በልቶ
ጌታ በቆሮንቶስ መጾሙን ዘንግቶ
"ኑሮ ራሱ ጾም ነው" ይላል አፉን ሞልቶ

ያልታደለ ትውልድ ሚሆነውን ያጣ
መረጠ ለያየው አካፈለው በዕጣ
👉ይሄ የጳጳስ ነው ያኛው🕺 የመነኩሴ
እንደት "ጹም" ይሉኛል ምን ነካወት ቄሴ!?
መጾም ከለከለኝ የጫት የሲጋራ የመጠጡ ሱሴ
እያለ መልሶ የአባን ግሳፄ

የሆነ ያልሆነ ምክንያቱን ደርድሮ
ጾሙን ይሽረዋል አንድ ስበብ ፈጥሮ

ከመልካሙ መንገድ ወተው ከመስመሩ
ያሻቸውን በልተው ካሻቸው ሊዳሩ
ያሻቸውን በልተው ጠጥተው ሊሰክሩ
ሄዱ ተጠራርተው ሊያድሩ ሲጨፍሩ

ወገኔ ተመለስ እባክህ ወድህ ና
ለጽድቅ የሚያበቃህ ምን ስራ አለህና
ደከመኝ ትላለህ ነፍስህ ባዶ ሆና
ጌታ ባለም ሲኖር መቸ ደላውና
"ኑሮ ጾም ነው"ምትል ሳይነካህ ፈተና

ወንድሜ ተመለስ ምልህን ስማ
እንድሆን ከፈለግክ ኑሮህ የተቃና
በገነት እንድትኖር ከቅዱሳን ጋራ
የስጋ ምኞትክን አሸንፈውና
አምላክን መሸንገል ማታለል ተውና
ነፍስህን አድናት ከሲኦል ፈተና
በጾም ጸሎት ትጋ በንጹህ ህሊና
ትዕዛዙን ጠብቅ በልብህ ጻፍና

✍ Written By Z

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

​አትውጡ ከመርከብ​
   ///////         //////

የአማኞች መኖሪያ የነፍሳት መዳኛ፤
ቤተክርስቲያ ናት መርከባችን ለኛ፤
ለሰማያት እየሩሳሌም ምሳሌ የሆነች፤
በክርስቶስ ደም ላይ የተመሰርተች፤
የሐዋርያት ስብከት ቤተክርስቲያን ነች፤
ወጀብ የማይገፋት ባለት የታነፀች፤
ሰባቱ ነፍሳትም ከጥፍት የዳኑት፤
ኖህን ተከትለው መርከቧበመግባት
በውስጥዋ ገብተው ፀንተ በመቆዬት፤
ዛሬም በመርከቧ ተነስቷል ማእበሉ ፤
አድነን እንበለው ፀጥ ይላል በቃሉ፤
መሰርቷ እሱነው ያለው በመቅደሷ ፤
ከመርከብ ሳንወጣ እጠብቅ በተስፋ፤
።።።።።.
ሐዋርያትም ከጌታ ጋር ሁነው በጉዞ ላይ ሳሉ፤
መርከብ ተናወጠች ተነሳ ማእበሉ
ወዳምላክም ጮሁ አድነን እያሉ
ስለመጥፍታችን እደት አይገድህም ብለው ተማጸኑ
ጌታም ተነስቶ ቃል ተናገራቸው
የታል እምነታችሁ ብሎ ገሰጻቸው
ጸተው እድቆሙ በአምልኮታቸው
ለደቀ መዛሙርቱ ትምህርት ሰጣቸው
እነሱም በርቱ ጸተው ተጋደሉ
እስከሞትም ድርስ ለቃሉ ታመኑ
አለምን በመዞር ወንጌል አስተማሩ
ሁሉን ንቀው ትተው እርሱን ተከተሉ
ከመርከብ ሳይወጡ ህዝቡን አስተማሩ
ከላይ ከአርያም ሀይልን ተቀበሉ


     ሙሉአለም // ወለተ ማሪያምsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...