2018 ኦክቶበር 27, ቅዳሜ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን!

↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️

1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር
  ሀ. ድጓ፣ጾመ-ድጓ እና መዋስዕት
  ለ. ቅኔ፣አቋቋም እና ዕጣነ-
  ሐ. ዋዜማ፣ስብሐተ-ነግህ እና አርያም
  መ.ግእዝ፣ዕዝል እና አራራይ


✅መ

2⃣ በሥርዓተ ክርስትና ወቅት፡በተጠማቂው ተገብቶ ጸሎተ ሃይማኖትን የሚያደርሰው ማን ነው?
  ሀ. ወላጅ አባት ወይም እናት
  ለ. ክርስትና አባት ወይም እናት
 ሐ. መምህረ-ንስሐ
 መ. በክርስትናው ጸሎት የተሰበሰበው ምዕመን

✅ለ

3⃣ «ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን/እሙታን» ለሚለው ሰላምታ ምላሽ የሚሆነው፡
  ሀ. አሠሮ ለሰይጣን
  ለ. በአማን
  ሐ. በዐብይ ኃይል ወሥልጣን
  መ. አግአዞ ለአዳም

✅ሐ

4⃣ የዐብይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ ምን በመባል ይታወቃል?
  ሀ.ቅድስት
  ለ. ብርሃን
  ሐ. ዘወረደ
  መ.ምኩራብ

✅ሐ

5⃣ በቤተክርስቲያን ሻማ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?
  ሀ. ለመንግስተ-ሰማያት ብርሃን
  ለ. ለእግዚአብሔር ብርሃን መሆን
  ሐ. ለቅዱሳን ሕይወት
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
.
✅መ

6⃣ ኢየሱስ የሚለው ስም ትርጓሜው ምንድን ነው?
  ሀ. መሲሕ
  ለ. ንጉሥ
  ሐ.ጌታ
  መ. መድኃኒት
.
✅መ

7⃣ ዐራቱ ወንጌላውያን ከአርባዕቱ (ዐራቱ) እንስሳት በተጨማሪ በዐራቱ ወቅቶች ይመሰላሉ።ከነዚህ መካከል በበጋ ወቅት የሚመሰለው ማን ነው?
  ሀ. ቅዱስ ማቴዎስ
  ለ. ቅዱስ ማርቆስ
  ሐ. ቅዱስ ሉቃስ
  መ. ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሀ መቅድመ ወንጌል

8⃣ ከሚከተሉት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ያልሆነው የትኛው ነው?
  ሀ. ርግብ
  ለ. ነፋስ
  ሐ. እሳት
  መ. በግ

✅መ

9⃣ ወንጌል የሚለው ቃል ሲተረጎም፡
  ሀ. ቃለ እግዚአብሔር ማለት ነው።
  ለ. የክርስቶስ ሕይወት ማለት ነው።
  ሐ. ግብረ ሐዋርያት ማለት ነው።
  መ. የምሥራች/መልካም ዜና ማለት ነው።

✅መ

1⃣0⃣ ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነት፡
  ሀ. የቅዱሳን ጸሎት መዓዛ ነው
  ለ. የእመቤታችን ምሳሌ ነው
  ሐ. የተስፋ መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ።

✅መ

1⃣1⃣ ኦርቶዶክሳዊ የቤተክርስቲያን ሕንፃ አሠራር የትኛውን ቅርጽ ሊይዝ ይችላል?
  ሀ. ክብ
  ለ. ሰቀላማ/መርከብ ቅርጽ
  ሐ. መስቀል
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ።

✅መ

1⃣2⃣ በግእዝ «መምህር« ካለ በዕብራይስጥ ----------------- ይላል።
  ሀ. ቦአኔርጌስ
  ለ. ረቢ
  ሐ. ጣቢታ
  መ. ኤፍታህ

✅ለ

1⃣3⃣ በቅዳሴ ሰዓት ንፍቅ ዲያቆኑ የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት ሲያነብ ፊቱን ወደየት አዙሮ ነው?
  ሀ. ወደ ምሥራቅ
  ለ. ወደ ምዕራብ
  ሐ. ወደ ሰሜን
  መ. ወደ ደቡብ

✅ሐ

1⃣4⃣ ቅዳሴውን ሲጀምር«ልቤ መልካም ነገር አፈለቀ»በማለት ከዳዊት መዝሙር የጠቀሰው ማን ነው?
  ሀ. ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ
  ለ. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
  ሐ. ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
  መ. አባ ሕርያቆስ

✅መ

1⃣5⃣ ጸሎተ ፍትሐት ሰው በሞተ በሦስተኛው ቀን የሚደረገው ለምንድን ነው?
  ሀ. የእግዚአብሔርን ሦስትነት ለማጠየቅ
  ለ. መጽሐፍ «ነገር በሦስት ይጸናል» ስለሚል
  ሐ. ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ መነሳቱን ለማጠየቅ
  መ. መልስ የለም

✅ሐ

1⃣6⃣ ርዕሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው አባት ማን ነው?
  ሀ. አባ መቃርዮስ
  ለ. አባ ጳውሊ
  ሐ. አባ እንጦንስ
  መ. አባ ጳኩሚስ

✅ሐ

1⃣7⃣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ድርሰቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ምን በማለት ጠርቷታል?
  ሀ. የመላዕክት እኅት
  ለ. የሰማዕታት እናት
  ሐ. የጻድቃን እመቤት
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣8⃣ የቤተክርስቲያን ዶግማ ስንል፡
  ሀ. የሚሻሻል የሚለወጥ ሥርዓት ማለት ነው።
  ለ. የማይሻሻል የማይለወጥ ትምህርተ ሃይማኖት ማለታችን ነው።
  ሐ. ቀኖና ማለታችን ነው።
  መ. ትውፊት ማለታችን ነው።

✅ለ

1⃣9⃣ ሰብአ ሰገል ( የጥበብ ሰዎች) ለጌታችን ካመጧቸው ስጦታዎች መካከል በፍቅር የሚመሰል የትኛው ነው?
  ሀ. ወርቅ
  ለ. ዕጣን
  ሐ. ከርቤ
  መ. መልስ የለም

✅ሐ

2⃣0⃣ በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ካህኑ የማቴዎስን ወንጌል ካነበበ በኋላ «ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም አለ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ» ይላል።የማርቆስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ የሚባለው የቱ ነው?
  ሀ. ኦሪት እና ነብያት ከተናገሩት አንዲት ከምታልፍ ሰማይ እና ምድር ቢያልፉ ይቀላል
  ለ. ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ
  ሐ. በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው
  መ. መልስ አልተሰጠም

✅ለ

🖊ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል💐
ቻናላችን ለመቀላቀል
saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...