2018 ጃንዋሪ 9, ማክሰኞ

ልዩ የገና የግጥም መድብልን

ትህትናን አሳየህ
//////////////
ከነገስታት ሁሉ ንግስናህ የላቀ
ከሃያላን በላይ ሃይልህ የረቀቀ
የፍጥረታት ገዢ ሳለህ ታላቅ ጌታ
በግርግም ተወለድክ በተናቀው ቦታ
የምድር ነገሥታት አንተው የሾምካቸው
በወርቅ ያጌጠው ቤተ መንግስታቸው
ላንተ ቢያንስብህም ለክብርህ ባይመጥን
ሁሉ በእጅህ ሆኖ ያንን አላየህም
ከከብቶቹ በረት ራህን ዝቅ አርገህ
የትህትናን ጥግ ለዓለም አሳየህ


♥♥♥♥♥♥♥♥

#በልደትህ #ልወለድ

በልደትህ ልወለድ በመፈስህ አድሰኝ
በመንፈስ ቅዱስ ልመላ ሀጢያት መስራትን ይብቃኝ ከመስቀልህ
ደስታዬን በቤትህ ላክብር በተቀደሰው ዓላማ
በመልካሙ ነገር ልጎልብት  ዜማን ለበእልልታ ላሰማ
በመቅደስህ ልተከል  ሥር አኑረኝ
የሀጢያት ማቄን አስጥለህ ቅዱስ መንፈስን አልብሰኝ
ደካማነቴን ተመልከት በልደትህ ቀን ውለደኝ
የአለምን አሸንክታብ ተመልሼ እንዳላየው
ልቤን  በፍቅርህ አንጸው  በቃልህ መዶሻ አጥብቀው
አመት አመትን ጠብቄ ልደትህን ሳከብር
ተወለደ ብዬ በልልታ በታላቅ ደስታ ስዘምር
የኔን በሀጢያት መሞት ዘንግቼ ተቀምጫለው
አለው እያልኩ በሥጋ በመንገስ ግና ሞቻለው
ቅዱስ ስጋህን ሳልበላ ክቡር ደምህን ሳልጠጣ
አምና ያከበርኩት ልደትህ ይሄው ዛሬ ላይ መጣ
እናም እባክህ አባቴ
የታወረውን ልቤን በምህረትህ አብራልኝ
በቃሽ ተመለሽ ብለህ ከአለም ጎትተህ አውጣኝ
ለንሥሀ አትጋኝና በልደትህ ውለደኝ
♥♥♥♥♥♥

🌹እመጣለሁ 🌹
               .
            ...:...
               :
በአምሳልህ አክብረህ ፈጥረህኝ
ገነትን ያህል እርስት አውርሰህኝ
እንድኖር ፈቅደህልኝ ትዛዝን ጠብቄ
ውዳሴ ከንቱሲጥለኝ በምክረከይሲ ያኔ
ሲገፈፍ ፀጋዬ ስዋረድ ከክብሬ
ባዶ ስሆን ሲሟጠጥ ተስፋዬ
ሞት ተፈርዶብኝ ስኖር በጨለማ
ከውሃና ከመንፈስ ልትወልደኝ ዳግመኛ
በግርግም እንደ ህፃን ተወልደህ ልትሆነኝ አርያ
የፍቅርህን ጥግ ልታሳየኝ ልታደርገኝ የመስቀልክ ምርኮኛ
አንተ አባቴ ሆይ ሆነህ ሳለህ የዚህ አለም ፈጣሪ
በጭቃ አበጃጅተህ የሰውን ልጅ ሰሪ
በባህሪህ ቅዱስ የሆንክ ይቅር ባይ መሃሪ
ምድርን በአበባ ሰማያትን በከዋክብት የሸለምክ
መላእክት ሳይታክቱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሚያመሰግኑህ
አስበህኝ የጨለማውን አበጋዝ ልትሰብር
 ከክብር ዝቅ ብለህ እኔን ልታፈቅር
ሰገነት ልታቆመኝ የተናቀውን ቦታ መርጠህ
ከዘባነ ኪሩብ ከዙፋንህ ወርደህ
ከሲኦል እሳት ልታድነኝ ወደኔ ስትመጣ
ለበደል ለጥፋቴ አንተ ልትሆን ካሳ
የኔን ፅዋ አንተ ልትጠጣ
ልትሰቀል ልትገረፍ በኔ ፈታ
ህይወትን አሳልፈህ ሰተህ ልታለብሰኝ በፍታ
ስትከፍለኝ ይህን ሁሉ ዋጋ
        ፡
        ፡
ታዲያ እኔስ አለም ለምኔ
ይበቃኛል መዋኘቱ በሃፃት ኩነኔ
እናም አባቴ ሆይ እመጣለሁ ከቤትህ ይህን ሁሉ ትቼ
ከነግሳግሷ ቅራቅቦዋን አለምን ወደዚያ ገፍቼ
ስጦታ መባውን ይዜ
ባይሆንልኝ እንኳን እንደ ሰባ ሰገል እጣን ከርቤ
የንስሐ እንባ በጆቼ አቅፌ
እመጣለሁ ከመቅደስህ በልደትህ ልደቴ እንዲታደስ
እግሬ ብቻ  ሳይሆን ልቤ እዲመለስ
     ፡
አዎን እመጣለሁ
♥♥♥♥♥♥

ከጥቂቶች ተርታ

ከተመረጡት ከጥቂቶች ተርታ
ደምረኝ እባክህ እርዳኝ የኔ ጌታ
ድካሜን ሳታይ ሳትንቀኝ በግብሬ
ኃጢአትን አፍርቼ ባዝል መራራ ፍሬ
አንተ የመጣኸው ኃጥኣንን ልትጠራ
ልታወጣቸው ነው ከፍዳ መከራ
እንጅ ጻድቃንማ በስራቸው ጸድቀው
በመንግስትህ ቦታ እርስትን አግኝተው
ይኖሩ የለ እንዴ ጸጋን ተጎናጽፈው
እኔንም ደምረኝ ስለ ቅዱሳንህ
ባለቀው እድሜ ብመጣም ከወይንህ
ማልደው ከመጡት ጋር ክፈለኝ እባክህ
አምላኬ ሆይ እርዳኝ ከደጅ እንዳልጣል
እድል ፈንታ ስጠኝ ከመረጥካቸው ጋር
ስለቸርነትህ ስለቃልኪዳንህ
ምህረትህ ትድረሰኝ ስለቅዱሳንህ
ተጠርቼ እንዳልቀር ከሰርግ ከድግስህ
ከምርጦችህ ተርታ ቆሜ ላመስግንህ

♥♥♥♥♥♥
#የጌታ #ልደቱ

እሰይ ደስ ይበለን በዓሉ መጣልን
የጌታችን ልደት ቀኑ ደረሰልን

ለሀጢአታችን  ሲል ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ማርያም ከሄዋን ተወልዶ
መጣ ሊታደገን ስጋን ተዋህዶ

የኩነኔው ዘመን አልቋልና አመቱ
አድስ ጸሀይ ወጣ ደረሰ ሰዓቱ

ስሙ ተለወጠ በምህረት ተተካ
የጨለማው ዘመን በልደቱ ፈካ

የነቢያት ትንቢት የገብርኤል ብስራት
ይወለዳል ያሉት የአለም መድሃኒት
ተፈጸመ ቃሉ ተወለደ ጌታ በከብቶች በረት
መንገድን እያሳዩ ታዘዙ ከዋክብት

ለሰው ልጆች ብሎ ስጋን ተዋህዶ
ተንከራቶ ሊኖር ደጋ ቆላ ወርዶ
ሳይገባው መጣ እራሱን ዝቅ አርጎ

ፍቅሩ ገደብ አልባ አምሳያ የሌለው
በደልን ደምስሶ አለሙን ወደደው

ገና ሲደርስልን ሲመጣ ባመቱ
በዜማ ይደምቃል ቅኔ ማህሌቱ
ላንተ የተባለው ይቀርባል መስዋዕቱ
ይደምቃል በእኛ ዘንድ የጌታ ልደቱ


♥♥♥♥♥♥♥♥
.
እሷ ማለት ለእኔ

ምንሽ ነች ይሉኛል ምኔ ልበላቸው
የቱን ተናግሬ የቱንስ ልተወው

እሷ ማለት እኮ .....

በድንግዝግዝ ዓለም በጨለማው ቦታ
ብርሀን የወለደች እንዲያ ስንገላታ
ሰው አጣው ባልኩበት በችግሬ ስዓት
አለው የምትለኝ ፈጥኖ ደራሼ ናት

እሷ ማለት ለእኔ ......

ተስፋዬ ተሟጦ ሞቴን ስለምነው
ብቸኝነት ወሮኝ መኖሬን ስጠላው
እንባዬን አንብታ በተስፋ አለምማኝ
የምታነሳኝ ነች ድክመቴን ተረድታኝ
ከአይን ጥቅሻ ፈጥና ዘውትር ትመጣለች
የልቤን ስብራት በእናትነት ፍቅሯ ታክምልኛላች
እሷ ማለት .....በቃ!  ድንግል ማለት ለእኔ
በቃላት ማልገልጣት ልዩ ነች እናቴ
የአምላኬ ስጦታ ድንቅ ሽልማቴ

♥♥♥♥♥♥♥

*የጌታ ልደቱ*

እሰይ ደስ ይበለን በዓሉ መጣልን
የጌታችን ልደት ቀኑ ደረሰልን

ለኃጢአታችን  ሲል ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ማርያም ከሄዋን ተወልዶ
መጣ ሊታደገን ስጋን ተዋህዶ

የኩነኔው ዘመን አልቋልና አመቱ
አድስ ፅሐይ ወጣ ደረሰ ሰዓቱ

ስሙ ተለወጠ በምህረት ተተካ
የጨለማው ዘመን በልደቱ ፈካ

የነቢያት ትንቢት የገብርኤል ብስራት
ይወለዳል ያሉት የአለም መድኃኒት
ተፈጸመ ቃሉ ተወለደ ጌታ በከብቶች በረት
መንገድን እያሳዩ ታዘዙ ከዋክብት

ለሰው ልጆች ብሎ ሥጋን ተዋህዶ
ተንከራቶ ሊኖር ደጋ ቆላ ወርዶ
ሳይገባው መጣ እራሱን ዝቅ አርጎ

ፍቅሩ ገደብ አልባ አምሳያ የሌለው
በደልን ደምስሶ አለሙን ወደደው

ገና ሲደርስልን ሲመጣ በዓመቱ
በዜማ ይደምቃል ቅኔ ማህሌቱ
ላንተ የተባለው ይቀርባል መስዋዕቱ
ይደምቃል በእኛ ዘንድ የጌታ ልደቱ
♥♥♥♥♥♥♥♥
ወስብኃት ለእግዝአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን/saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...