2018 ጃንዋሪ 7, እሑድ

የመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ ሰብስብ መዝሙሮች

ዮሐንስኒ ሀሎ
♥♥♥♥
/ዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ ቁ.፪/
ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ/፪/ በሄኖን
ያጠምቅ በሄኖን
አዝ…
መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች እያለ
ዮሐንስ ሲያሰተምር ማነው ያስተዋለ
እንደ ተናገረ አዋጅ ነጋሪው
ተራራው ዝቅ ይበል ይሙላ ጎድጓዳው
አዝ…
እድገቱ ምናኔ ትምህርቱ ንስሐ
የጣዝማ ማር በልቶ ኖረ በበረሃ
መጓዝ እንዲያስችለን በሕይወት ጎዳና
ላይ ታቹ ይደልደል ጎባጣውም ይቅና
አዝ…
ሲኖር በምናኔ በሄኖን በረሃ
ያጠምቅ ነበረ ዮሐንስ በውሃ
በማየ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ
ጌታ ተጠመቀ ድኅነትን ሊያውጅ
አዝ…
ጌታውን አጥምቆ ለክብር የሚበቃ
ከእናቱ ማኅፀን ተገኘ ምርጥ ዕቃ
ኤልሳቤጥም ለክብር ሆና የታደለች
መልካም የነፍስ አባት መጥምቁን ወለደች
ዮሐንስኒ ሃሎ ያጠምቅ/፪/ በሄኖን/፫.

////////////////////////////////

♥♥የኤልሳቤጥ ልጅ♥♥
የኤልሳቤጥ ልጅ የዘካርያስ/2/
የእምነት ጀግና ቅዱስ ዮሐንስ /2/
አደገ በበረሃ ለጽድቅ ለይቶት/2/
መንገዱን ጠረገ ሆነ ሰማእት/2/
+~+~+ አዝ +~+~+~+~
ሲመሰክር ስለሚመጣው
ሲያገለግል በኄኖን ማጥመቂያው
ይመልሳል ህዝቡን በንስሀ
መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ፍስሀ
+++~+ አዝ ~+~+~+~+
እየጠጣ የቶራን ወተት
እየበላ የበረሃ ማር
ብትለይም እናቱ በስጋ
አድጓል ጸንቶ አንዳችም ሳይሰጋ
+~+~+~ አዝ +~+~+~+~
ይፈውሳል እምነትህ ጸበልህ
ለሚመጣ አምኖ ከደጅህ
ቃልኪዳኑ ለዘለአለም ነው
ከጌታ ዘንድ አንዴ የተሰጠው
+~+~+~አዝ +~+~+~+
አማላጄ ወዳጄ ብልህ
ድኜ እኮ ነው በቃልኪዳንህ
ፈዋሼ ነህ ዮሐንስ አባቴ
ይመሰክራል ይኸው አንደበቴ

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ


////////////////////////////////

እርሱ ፍፁም ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል
ከእኔ ይልቅ ጌታ እጅግ ይበርታል
እኔ ለንስሃ በውሃ አጠመቅኋችሁ
በእሳት ያጠምቃል ይመጣል ያልኳችሁ
++
ጫማውል ልሽከም ከቶ የማይገባኝ
እኔን አስቀድሞ ለ አገልግሎት ጠራኝ
ከሕዋላየ የመጠው ነበረ ከፊቴ
በስሙ ታምኑ ዘንድ እርሱ ነው ስብከቴ
++
በምድረ በዳ ላይ የጮኹለት ንጉስ
የሃያላን ሃያል ተግልጣል ኢየሱስ
ለሐጥያት ስርየት ይሰዋል ይሄ በግ
ለዐለም ሁሉ መዳን በቀራንዮ ሰርግ
++
ለንሰሃ የሚሆን ፍሬ ዛሬ ኣድርጉ
ለሰርጉ ሊጠራን መጥትዋል እና በጉ
ከሚመጣው ቁጣ በርሱ እንድታመልጡ
የእፉኝት ልጆች ከባቢሎን ውጡ
++
የኣብርሐም ልጆች ነን በማለት ላትድኑ
የመዳኑን ሰኣት ቀኑን ኣታባክኑ
ለ አብርሐም ልጆችን ከድንጋይ ያስነሳል
መንሹም በ እጁ ነው አውድማው ይጠራል
++
ጠማማው ልብ ይቅና ጥርጊያው ይስተካከል
ፍሬ የሌለው ዛፍ በቶን ሳይቃጠል
ምሳር በዛፎቹ ስር ዛሬም ተቀምጣል
ንሰሀ ግቡ ነው የመጨረሻው ቃል
///////////////////////////////
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ /2ጊዜ/

ወበህየ ዮሐንስ /2ጊዜ/ ፍጹመ ተፈሥሐ /2ጊዜ/

ትርጉም፡-

ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው /2×ጊዜ/

በዚህም ዮሐንስ /2×ጊዜ/ በፍጹም ደስ አለው /2×የጊዜን

ሊቀ መዘምራን ቴወድሮስ ዮሴፍ
//////////////////////////////////
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2
                     💟
                     💟
ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /2/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /2/
                 💟💟

በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/ /2/
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /2/
                  💟💟

ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም /2/
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /2/

                  💟💟
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማጸን ሳለህ /2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ /2

                      💟💟
ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...