2018 ጃንዋሪ 19, ዓርብ

የምዕራፍ ሦስት/የ22ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ?? ሰላማችሁ ይብዛልኝ እያልኩ፦ እነሆ የምዕራፍ ሦስትን/ የ22ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ  ጥያቄና መልስ እንዲህ ተጀመረ።
//////////////////////////

✍ ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣አምስቱ እህት አብያተ ክርስቲያናት/Oriental Churches/ የሚባሉት ማን ማን ናቸው???

//መልስ//፦ ኢትዮጵያ፣ግብፅ፣ ህንድ፣ ሶርያ እና አርመን ናቸው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅2⃣በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የመጀመሪያዋ  ገዳምና ቤተ-ክርስቲያን የትኛዋ ነች??

//መልስ//፦  አክሱም ጽዮን ናት።

✍ ጥ.ተራ.ቁ.✅3⃣ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል አንዱ የሆኑት ባታችን አቡነ አረጋዊ ያረፉበት ገዳም ምን በመባል ይታወቃል?.

//መልስ//፦ትግራይ ውስጥ ደብረ ዳሞ ይባላል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅4⃣ወንጌል ማለት የስሙ ትርጉም ምን ማለት ነው??

//መልስ//፦ ዜና ሠናይ/ መልካም ዜና/ የምስራች ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅5⃣ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው??

//መልስ//ነብይ ማለት፦ኃላፍያን አልፎ የተሰወረውን ሚስጢር ገና ለወደፊት የሚሆነውን የሚያውቁ/ሀብተ ትንቢት  የተሰጣቸው ቅዱሳን አባቶች ቅዱሳት እናቶቻችን  ነብይ ተብለው ይጠራሉ።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅6⃣12ቱ ደቂቀ ነቢያት ከሚባሉት መካከል ቢያንስ 5ቱን ጥቀስ???

//መልስ//፦ደቂቀ ነብያት የሚባሉት
1ኛ ቅዱስ ሆሴዕ
2ኛ አሞፅ
3ኛ ሚክያስ
4ኛ ዮናስ
5ኛ. ናሆም
6ኛ አብድዩ
7ኛ ሶፎንያስ
8ኛ ሐጌ
9ኛ ኢዩኤል
10ኛ ዕንባቆም
11ኛ ዘካርያስ
12ኛ ሚልክያስ እነዚህ ናቸው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅7⃣ጌታችን የተጸነሰበትንና የተወለደበትን ወርና ቀን ጥቀስ??

//መልስ//መጋቢት 29 ተጸነሰ ታህሳስ 29 ተወለደ።


✍ጥ.ተራ.ቁ✅8⃣ አንድ ክርስቲያን ሥጋና ደሙን ከመቀበሉ  አስቀድሞ ስንት ሰዓት መፆም አለበት??

//መልስ//፦ ለ18 ሰዓት መፆም አለበት።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅9⃣ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን በመባል የምትታወቀዋ ድንቅ ቀን የቷ ነች?

//መልስ//መንፈስ ቅዱስ የወረደባት እለት/ቀን ነች። በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣0⃣ጥምቀት ማለት ምን ማለት ነው???

//መልስ//፦ ጥምቀት ማለት በውኃ መነከር መዘፈቅ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣1⃣ጥምቀትን አጥማቂው   ማን ተምማቂውስ ማን ነው???

//መልስ//፦አጥማቂዎች በሁለት የክህነት ደረጃዎች ብቻ ይፈጸማል። ይኸውም፦
በኤጲስ ቆጶስ በሚባለው ጳጳስ" እና በቄስ ብቻ ነው።
ተጠማቄዎች በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ
ዮሐ (8፥36)

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣2⃣ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ ወርዶ {ሄዶ)ለምን ተጠመቀ??

//መልስ//፦አንድም ለትህትና፤ ለፍቅር፤ ስርዓትን፣ ለማስተማር፤ ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢለው ኑሮ የዛሬ ምህመን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ካህናትን ባስቸገሩ
ነበር።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣3⃣ጌታችን ሲጠመቅ ባህር ሸሽች የመሸሹ ምሳሌ ምንድን ነው???

//መልስ// መሸሹ የኃጢአት ምሳሌ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣4⃣በዮርዳኖስ ወንዝ የሥላሴ ሚስጥር እንዴት ተገለጸ???

//መልስ//፦መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ተገለፀ
↪አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው ሲል በቃል ተገለፀ
↪ወልድ ስጋ ለብሶ በዮርዳኖስ መሀል ቁሞ ተገልፀዋል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣5⃣ዮርዳኖስ አንድ ወንዝ ሲሆን ዝቅ ብሎ ለስንት ተከፈለ ጌታችንስ ምኑ ላይ ነው የተጠመቀው???

//መልስ//፦ዮርዳኖስ አንድ ወንዝ መሆኑ አዳም አንድ ሁኖ መፈጠሩ ምሳሌ ነው ዝቅ ብሎ በ2 በዮር" እና በዳኖስ" ተከፍሎል ሁለቱም ዝቅ ብለው ተገናኝተዋል ከመገናኛው ላይም ጌታችን ተጠምቆል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣6⃣ጌታችን ለምን "በዮርዳኖስ" ወንዝ ተጠመቀ???

//መልስ//፦አንድም እዮብና ንእማን በዮርዳኖስ ተጠምቀው ከደዌ ሥጋ ድነዋል።
 ሚስጥሩ ግን አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በኋላ ዲያቢሎስ መከራ አፀናባቸው አዳም የዲያቢሎስ ወንድ አገልጋይ ሔዋን የሴት አገልጋይ ነን ብላችሁ ስማችሁን ጽፍችሁ ስጡኝ ብሎ ዲያቢሎስ አታሏቸው ነበርና ይሁንብን ይደረግብን ብለው አዳምና ሔዋን ቃል ሰተው ነበር። ያንን ቃላቸውን/የእዳ ደብዳቤ አድርጎ በ2 እምነ በረድ ቀርፆ አንዱን "በዮርዳኖስ" አንዱን "በሲዖል" ጥሎት ነበርና በዮርዳኖስ ያኖረውን የእዳ ደብዳቤ 'ጌታችን' በጥምቀቱ ጊዜ በዮርዳኖስ የተጣለውን እንደ ሰውነቱ እረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ደምስሶልናል።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣7⃣.በሀገራችን በኢትዮጵያ ጥምቀት ታቦት ወጥቶ መከበር የተጀመረው መቼ ነው???

//መልስ///፦ በ5ኛው ክ/ን በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣8⃣ባህር ሸሽች አንተ ዮርዳኖስስ ወደኋላ የተመለስከው ምን ሁነህ ነው። ይህን ቅዱስ  ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን ምዕራፍና ቁጥሩስ??

//መልስ//፦ መዝ (113፥3-5) ላይ እናገኘዋለን።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅1⃣9⃣የእግዚአብሔርን መኖር የምናውቅባቸው መንገዶች /ማስረጃዎቻችን/ የትኞቹ ናቸው??

 ሀ) በሥነ ፍጥረት መኖር

 ለ)የኅሊናችን ምስክርነት

 ሐ) የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት

መ) ሁሉም መልስ ነው

//መልስ//መ/ ሁሉም መልስ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅2⃣0⃣የጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ ምክንያት፡-

  ሀ) ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ

 ለ) የአዳምና የሔዋን የዕዳ ደብዳቤ በዚያ ተቀብሮ ስለነበረ

 ሐ)በብሉይ ኪዳን ለሥጋ ደዌ በዮርዳኖስ ይጠመቁ ስለነበረ ለነፍስ ድኅነት ይሆን ዘንድ።

 መ) ሁሉም መልስ ነው።

//መልስ//መ/ ሁሉም መልስ ነው።

የ22ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ይህን ይመስላል ከስተቴ አርሙኝ 👉ስል በትህትና እጠይቃለሁ።saramareyama.890@gmail.com

1 አስተያየት:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...