2018 ጃንዋሪ 31, ረቡዕ

መንፈሳዊ የግጥም መድብል

እመቤቴ ማርያም የአምላክ እናት
እጅጉን ይደንቃል ያንችስ አሟሟት
በጥር 21 በክብር አርፈሽ
ስለ ኃጥዓን ስትይ ለመሞት ፈቀድሽ
አይሁድ በክፋት በአመጽ ተነስተው
እናቃጥላት አሉ ቅድስናሽን ስተው
ልጅሽ ይህን አይቶ መቼ ዝም አላቸው
መላእክትን ልኮ ተዓምር አሳያቸው
ክብርት ሥጋሽንም ነጠቁ ከእጃቸው
በክብር አኖርላሽ ከገነት አግብተው
የጌታ ቀን ደርሶ ትንሳኤሽን እስኪያዩ
ቅዱስን ሐዋርያትም በፆም ጸሎት ጸኑ
እግዚአብሔር ፈቅዶ እስክልሚደርስ ቀኑ
ያሟሟትሽን ነገር እጹብ እጹብ አሉ
እውነት ነው ይደንቃል የአምላክ እናት
እኛም እንድንድን ከሲዖል እሳት
እመ አምላክ አደራ ምልጃሽ አይለየን
እንደመናፍቃን እንደማያምኑ ሳይሆን
ሞትሽን በጥር ወር ነሐሴ መቃብር
ትንሳኤና እርገትሽን ሁሉን እናምናለን
ሐዋርያት አበውን አብነት አድርገን
እጹብ ድንቅ እያልን እናወድሳለን
እስከ ለዘለዓለም ብጽሒት እንላለን።

@ከ ወለተ ሥላሴ

♥♥♥♥♥♥♥♥

ጌታ ሆይ
አሁን በዚህ ስአት ፊትህ ተደፍቼ እንዲህ ምለምንህ ፣
አንድ ነገርን ነው ዛሬ ምጠይቅህ ፣
እንደ ትላንትናው እንዳለፈው ጊዚያት ፣
ለንዋይ አይደለም መምጣቴ ካንተ ፊት፣
ወይም ህይወት ግራ ሆና እጅግ  ከብዳኛለች ፣
ደስታ'ዬን ነጥቃ ሀዘን ሞልታኛለች ፣
በችግር በርሀብ ወዜ ተሟጠጠብርታቴን ተቀማው ፣
ያ ፀአዳ ፊቴን ማጣት አጠቆረው ፣
በማዲያት ተሞላ እንባዬ አሻከረው ፣
የተትረፈረፈው የሞላው ማጀቴ ፣
ዘይት ሆነ ዱቄት የለኝም ከቤቴ ፣
ሚቀመስ እንጀራ ጠፍቷል ከሌማቴ ፣
ምቀይረው የለም ከለበስኩት በቀር ፣
ማጥብበት እንኳን ጠፍቷል አንዳቺ ነገር ፣
ያው ተራቁቻለው ድህነት አጠቃኝ ፣
ምን ነው ዝም አልክ ታዲያ ምህረትህን ነፈከኝ ፣
ለሌላው ስትቸር ለእኔ ከለከልከኝ ፣
ይሄው የታደሉት እማ ....
4 አምስት ልጅ በቤታቸው ሞልቶደስታቸው ያስቀናል  ፣
የህፃናቱ ድምፅ ለመኖር ያጓጓል ፣
ልብን ተስፋ ሰጥቶ መንፈስን ያድሳል ፣
የእኔስ ወዴት አለ የማህፀኔ ክፋይ ዘሬን ምተካበት ፣
አይኔን በአይኔ አይቼ ምደሰትበት ፣
መውጣቴ መውረዴ ምክንያቴ ምልበት ፣
እኮወዴት አለዘሬን ምተካበት ?
አሁን ይሄን ሁሉ ልጠይቅ አይደለም ዛሬ መገኘቴ ፣
ያሁን ግን ይለያል ሌላ ነው ምኞቴ  ፣
በል ስማኝ ልንገርህ አድምጠኝ አባቴ፣
ስው ናፈቀኝ ብዬ ያነባውት እንባዛሬ ላይ ላልቅሰው ፣
በፀፀት ልታጠብ ሀጥያቴን ላስታውሰው፣
የዘላለም ቤቴ የሰጠኸኝን እርስት ገነትን ልናፍቀው ፣
መሪር እንባን ላውርድ ቃልህ ይመልሰኝ፣
የጴጥሮስን እንባ ለእኔም ዛሬ አድለኝ ፣
በደልሽን እመኚ ዶሮ ጮኃል በለኝ፣
ደግሞም አንዳንድ ጊዜ....
የስጋዬ አምሮት ጌደለብኝ ብዬ ምጉተመተመው ፣
በነጋ በጠባ እሮሮ እማሰማው ፣
እንዲያ ሲለኝ ደግሞ ...
እረሳኸኝ ብዬ ማነባውን እንባ ባክህ ዛሬ ስጠኝ ፣
ለበደሌ ይሁን በሀጥያት መኖር ይብቃኝ ፣
ይሄው.....
ዲያቆኑ በመቅደስ ተንስዑ እያለ ደውል ይደውላል ፣
በፀሎት እንድተጋ ወደ አንተ እንዳንጋጥጥ ቃሉን ይናገራል ፣
ስባኪውም ይላል ..?
ወደ ቤቱ ግቡ በንስሀ ውሀ በፍቅሩ ታጠቡ ፣
ስጋውንም ብሉ ክቡር ደሙን ጠጡ ፣
ከረከሰች ዓለም ቀጠሮ ሳትይዙ ዛሬውኑ ውጡ ፣
ሁሉም በእየፊናው መዳንን ይሰብካል ፣
መንግስትህን እንድወርስ ኑ ቅረቡ ይላል ፣
እባክህ አባቴ ሁሉም ነገር ቀርቶ ይህን አሳካልኝ ፣
የጴጥሮስን እንባ ለእኔ ልጅህ ስጠኝ ፣
አንተን ልፈልግህ አለም አድክሞኛል ፣
የጨበጥኩት ደስታ ወና ሆኖብኛል ፣
አለ ያልኩት ነገር የተማመንኩበት ባንድ ጊዜ ከድቶኛል፣
ደንዳናውን ልቤን በቃልህ ሰብረጀው ፣
ከአለም ምናምንቴ ቀራንዮን ልየው ፣
ጎልጎታን ልመልከት ፍቅርህን ላስበው ፣
አዎ መዳኒቴ

በህይወት ዘመኔ ያለቀስኩት ለቅሶ ፣
ለንስሀ ላንባው ይምጣ ተመልሶ።

@ከ ወለተ ብርሀንsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...