2018 ጃንዋሪ 2, ማክሰኞ

አታልቅስ

የአባታችን የመጨረሻ ቃል
♥♥♥♥♥♥♥
‹‹ልጆቼ! አታልቅሱ፤ ነገር ግን የሽማግሌውን የአባታችሁን ቃል ስሙ፡፡ መጀመሪያ
እምነታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ በዚህ ዓለም እንደተያዙ እንደ ዓለም ሰዎች
ስለ ልብስና ስለ ምግብ አሳብ አታብዙ፡፡ በየጊዜው ሁሉ መጸለይን አታቋርጡ፣ ለቤተ
ክርስቲያን ሌትና ቀን አገልግሉ፡፡ እግዚአብሔር በሚወደው ገንዘብ ንጽሐ ሥጋንና ጾምን
ውደዱ፡፡ ውዳሴ ከንቱም የሚቀረውንም የዚህን ዓለም ክብር አትውደዱት፤ እናንተስ
የቀደሙትን አባቶች በመከራና በድካም ብዛት ከዓለም የወጡትን በመጋደላቸውም
ክፉውን ሀሳብ ድል የነሡትን ምሰሏቸው፡፡ ፍለጋቸውንም ካልተከተላችሁ ልጆቻቸው
አትባሉምና፤ በመከራቸው ካልመሰላችኋቸው በደስታቸው አትመስሏቸውም፤
በድካማቸውም ካልተባበራችሁ ወደ ቤታቸው አትገቡም፡፡ የቀደሙትን ቅዱሳን
አባቶቻቸሁን መስላችሁ ኃጢአተኛ አባታችሁን እኔን ደግሞ ምሰሉ፤ ስለትኅርምቱም
በመብል በመጠጥ ልባችሁ እንዳይከብድ፣ ሥጋ ከመብላትና ጠጅ ከመጠጣት
ተጠበቁ፡፡ ለመመካትም በዓለማዊ ልብስ አታጊጡ፡፡ የመላእክት አስኬማ ከዓለማዊ
ሥራ ጋር አይስማማምና፤ ዓለምንም በዓለም ላይ ያለውን ሁሉ አትውደዱ፡፡ ዓለሙም
ፈቃዱም ሓላፊ ነውና፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፡፡
ልጆቼ ሆይ! ትሩፋትን ሁሉ በችኮላ ሠርታችሁ በጎይቱን ሃይማኖታችሁን አስከትሏት፡፡
ለነፍሳችሁ እንጂ ለሆዳችሁ አትገዙ፡፡ ሁላችሁ ወንድማማች ሁኑ፡፡ እርስ በርሳችሁም
ተፋቀሩ፤ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ፍቅር ኃጢአትን ያጠፋልና፤ የነፍስና የሥጋን ርኲሰት
ያነጻልና፡፡ ይህንንም ብትጠብቁ በእውነት ልጆቼ ናችሁ፡፡ የሕይወትንም ፍሬ የምታፈሩ
ትሆናላችሁ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ፊት በክብር ትደርሳላችሁ…ልጆቼ ሆይ! ሰላም ለእናንተ
ይሁን፡፡››saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...