2018 ጃንዋሪ 15, ሰኞ

የጠፋው ልጄ ተገኘ መንፈሳዊ መነባንብ

*"*   *የጠፋው*  *ልጄ*   *ተገኘ*  *"*

🙎🏽‍♂ አባቴ ልንገርክ ኧኽ ብለክ ስማኝ
ንብረቴን እሻለሁ ለኔ የሚደርሰኝን አካፍልና ስጠኝ
ከህል ከከብት ከገንዘብም ቢሆን ሁሉን አስረክበኝ
ሆኖም አደራክን ዛሬ ነገ እንዳትል አሁኑኑ ይሰጠኝ
ሽማግሌዎች ጥራ ጉልማዬን ልወቅ ሸንሽነው ያካፍሉኝ
ድርሻዬን ለይተክ እንድታስረክበኝ እፈልጋለሁኝ

👴🏽 *በወላዲትዋ*!
ምንድነው የምትል የሆንከው አለ እንዴ?
እንዲህ ተበሳጭተክ የምታናግረኝ ምን ነክቶክ ነው ውዴ?
ማነው የስቀየመክ ክፉ የተናገረክ ወይስ ምን በደልኩክ
ገንዘብስ ለምንክ ምን ሊጠቅምህ ገና ልጅ አይደለክ?
ችግርም እንዳለ ንገረኝ አትፍራ አንተ በምን አቅምክ ትቋቋመዋለክ
እኔ እስካለሁ ድረስ አደራ እንዳይኖር ከቶ  የሚያስጨንቅክ

🙎🏽‍♂ እንደዚህ ስላልኩክ አይክፋክ አትናደድብኝ
ነገር ግን አሁን ደግሜ ዕልካለሁ ድርሻዬን አካፍለኝ
ያለኝን ስጥና ለኔ የሚደርሰኝ መርቅና ሸኘኝ
ተትረፍርፎ ሳለ አውድማ ጎተራው ለምን አሰሰተክ?
ብታካፍለኝም በእጥፍ ይገባል በወሰድኩት ምትክ
ይልቅ አባዬ ሳታመነታታ አሁኑኑ ስጠኝ ነው ደግሜ ምልክ


👴🏽 እሺ በቃ ልጄ እጅግ ከባሰብክ
እሰጥሀለሁኝ አትናደድ አሁን ውሰድ እሄው ድርሻክ
ሳልል ወደኋላ አስረክቤካለሁ ሁሉም ያልፋልና አትከፋ አይዞክ
ባገር ሽማግሌ ከንብረቴም ሁሉ አካፍዬካለሁ
ሰርተክ ጨምርበት አምላክ ይባርክልክ ብዬ መርቄሀለሁ

🙎🏽‍♂አመሰግናለሁ ደህና ሰንብቱልኝ
እንደዚህ ይሻላል በማያቁት ሀገር ዝና እላለሁኝ
መኖር እንዲህ እንጂ ቀብረር ፀዳ ብሎ
የት ነበርኩ እስካሁን እሄንን ለማየት ያልነቃሁት ቶሎ
በይ ነፍሴ ተደሰች ያሻሽን አድርጊ
ገንዘብ እንደው አለኝ በአንዳች አትስጊ
ብይ ጠጪ በቃ ሀሴት አድርጊ
ለስጋሽ እርካታ ለአይንሽም ደስታ ከቶም አትንፈጊ

💗 ከአባትህ ኮብልለህ ከፈሩ ወተሃል
አክብር የሚለውን ህጌንም ጥሰሃል
የልብህን ምኞት ስትፈፅም ኖረሃል
አላፊ ጠፊውን አለሙን መርጠሃል
መሰረት የሌለው ህወት ገንብተሀል
በዘፈን ጭፈራ በሱስይሁንህ ደንዝዘካል
ለሰራህው ስራ ደመወዝ ልክፈልህ
ተዘጋጅቻለው መማርያ

🙎🏽‍♂  ወይኔ ጉዴ ፈላ  ተራብኩኝ ተጠማው
ገንዘብ አለኝ እያልኩ ያኔ እንዳላቅራራው
 አለቀ ገንዘቤ  እሄው እጄ ባዶ ነው
የአባቴን ንብረት
ተድላን  የለመደው የቀድሞ ሕይውቴ
ጭራሽ ይባስ ብሎ ድንገት ተጎሳቁሎ ጠፋ ማንነቴ
ኪሴ ተራገፈ እጄ ባዶ ቀረ እኔም ሆንኩ ዋተቴ
ደስታ ሰላም ጠፋ  እራቀ  ከፊቴ
እርሀብ ፀናብኝ እጂግ ተንገላታሁ እስኪዝል ጉልበቴቤቴ
ከማር ከወተቱ የበላው  አንጀቴ
ትዝ ይለኝ  ጀመረ ፍቅሩ የአባቴ

ጥፋቴ ከባድ ነሁ አውቃለሁ ጠንቅቄ
ወደ አባቴ ልሂድ ልኑር በግ ጠብቄ
ይቅርታ ልጠይቅ እግሩ ላይ ወድቄ

💗 መመለስ አለብህ መልካም አስበሃል
ስህተት መስራትክ አሁን አስታውሰሃል
አባትክን ይቅርታ መጠየቅ ይገባሃል ስላንተ ያስባል ሁሌም ይወድሀል
ልጁን የሚጠላ አባት የት አይተሀል ?
ከልብህ ሁንና ጠይቀው ይቅርታ
ዳግም ለመበደል ልብህ አያመንታ

👴🏽 ገና ከሩቅ ሳይክ ሀሴት አገኘሁኝ
የጠፋውን ልጄን ጌታ ምልሶልኝ
ለብዙ ጊዜያት ደስታ ከኔ ርቆኝ
ሀዘን ሰፍኖ ቤቴ  ሰላምም  ሳላገኝ
ዛሬ መጣህልኝ ፍሪዳ ጣሉለት ጥሩ ዘመድአዝማድን
እጅግ ደስ ብሎና የጠፋው ልጃችን ስለተገኘልን
ለግሩ ጫማ አምጡ  ለዕጆቹም አንባር
ከጠፋበት ቦታ ስለተመለሰ አምላክ ተመስገን

🙍🏿‍♂ ምንድነው ይህ ሁሉ ትላንት ንቆን አይደል?
ዛሬ ተመልሶ ድርሻውን ሲጨርስ
ዳግም ደሞ መጣ ሌላውን ሊያፈርስ
እንዳሻው ሲቦርቅ ሲፈነጥዝ
ከርሞ የትም ሲልከሰከስ
ሲቸግረው መጣ የኛንም ሊካፈል ሳናስበው ድንገት
እንዴት ለዚህ ብኩን ለሆነብክ ሽፍታ
ንብረቱን አጥፍቶ ለመጣ ከርታታ
እንዴት ተቅበልከው በፍቅር በደስታ
 ለኔም አላሳየህኝ እሄንን ፈገግታ?
አገልጋይህ  ለሆንከህ ጠዋትና ማታ

👴🏽 ልጄ ተው እባክህ የስጋዬ ክፋይ
ላንተም  እንደዛው ነኝ ለያይቼም አላይ
የኔ ያልኩት ሁሉ ነው ግድ የለም ያንተ
ሳትለያዩበኝ አንድላይ ኑሩ እንጂ በፍቅር በሰላም
ወንድምክም አንተ
 ተገኘልን ከሞት ከጥፋት
ዛሬ
 ፀልይለት አንተም
ጥፋቱን እንዳይደግም
እናም እናመስግን ጌታን በዝማሬ


🙎🏽‍♂ ወይ አቤቴ ደጉ የቀዶሞ ስራዬን በደሌን ሳይቆጥር
ይልቁንም አባብሎ እሄው ተቀበለኝ በሰላም በፍቅር
ዕውነት ለውለታው ለታላቅ ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ
ስለቸርነቱ
 ስለዕርሕራሄው በሒወቴ ሁሉ አመሰግናለው
ዳግም ላልባድለው ገፍቼውም ላሌድ ቃል ገባለታለሁ።

   አሜን ወስበሀት ለእግዚአብሔር
ተፃፈ በእህተ ጊዮርጊስ
saramareyama.890gmail.com

8 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...