ማክሰኞ 27 ማርች 2018

መንፈሳዊ የውድድር ጥያቄና መልስ

https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን👇

✍በድንግል ማርያም የአስራትመልስ ልጆች ቻናል የቀረበ የውድድር መንፈሳዊ ጥያቄና  እንደሚከተለው ነው⤵

➡ጥ.ተራ ቁጥር 1⃣➡ሐዋርያት መቼ ተጠመቁ?

ሀ/ጌታችን ከአረገ በኋላ

ለ/ በጸሎተ ሐሙስ ማታ

ሐ/ በዕለተ ዓርብ


መ/መልስ የለም


//መልስ//↪ለ,

➡ጥ.ተራ.ቁ2⃣➡ከአራቱ(4) የሴት ነብያት መካከል የሆነችው ማናት??

ሀ/ የሙሴ እህት ማርያም

ለ/ዲቦራ

ሐ/ ሑልዳና

መ/ሀ እና ለ

ሠ/ ሁለም

//መልስ//↪ሠ,

➡ጥ.ተራ.ቁ3⃣➡በቅዱስ መጽሐፍ ያልተመዘገበ የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ የያዘ አዋሊድ መጽሐፍ ምን ይባላል???

ሀ/ ታምረ ማርያም

ለ/መጽሐፈ መነኩሳት

ሐ/ታምረ ኢየሱስ

መ/ መልስ የለም

//መልስ//↪ሐ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.4⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ አዕማደ(ሚስጢረ) ሐዋርያት ከሚባሉት መካከል የሆነ የትኛው ነው???

.ሀ/ ዮሐንስ

ለ/ ያዕቆብ

ሐ/ ጴጥሮስ

መ/ ሁሉም መልስ ነው

//መልስ//↪መ,,

➡ጥ.ተራ.ቁ.5⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ የኦሪት መሰዋት የሚሰዋባቸው አብያተ ክርስቲያናትን የትኞቹ ናቸው??

ሀ/ መርጦ ለማርያም

ለ/ ተድባባ ማርያም

ሐ/ብርብር ማርያም

መ/አክሱም ፅዮን

ሠ/ ለ እና ሐ

ረ/ ሁሉም

//መልስ//↪ረ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.6⃣➡ቤተ ክርስቲያን ስንት ክፍሎች አሏት

ሀ/ ሁለት

ለ/ ሦስት

ሐ/ 7

መ/ መልስ የለም

//መልስ//↪ለ,

➡ጥ ተራ ቁ7⃣➡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "በኩር" የሚባልበት ምክንያት  ምንድን ነው???

ሀ/የአብ አንድያ ልጁ ስለሆነ

ለ/ በእስራኤላውያን መጀመርያ ማኅፀን የሚከፍት ልጅ በኩር ስለሚባል

ሐ/ ሞት የማይገዛው ትንሣኤን ለመነሣት እርሱ የመጀመርያ ስለሆነ

መ/ ሁሉም መልስ ነው።

//መልስ//↪መ,

➡ጥ.ተራ.ቁ 8⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትቀበላቸው ጉባኤያት የትኞቹ ናቸው??

ሀ/ ኒቂያ ጉባኤ

ለ/ ኤፌሶን

ሐ/ ቁስጥንንጥንያ

መ/ ሁሉም

ሠ/ መልስ የለም

ረ/ ሀ እናለ

//መልስ//↪መ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.9⃣➡የሙሴን ሕግ በብዙ ጥንቃቄ እንተረጉማለን የሚሉና ሰውም ሕጉን እንዳይተላለፍ በማለት የራሳቸውን ትእዛዝና ሥርዓት ያወጡ በዘመነ ካህናት ጊዜ የነበሩ የቤተ  ክርስቲያን ጥላቶች ምን ተብለው ይጠራሉ??

ሀ/ ፈሪሳውያን

ለ/ ሰዲቃውያን

ሐ/ ኤሲያውያን

መ/ አይታወቁም

//መልስ//↪ሀ/

➡ጥ.ተራ.ቁ.🔟➡በሐዋርያት ጊዜ  የነበሩ የመጀመርያዎቹ  መናፍቃን ምን ተብለው ይጠራሉ??

ሀ/ ግንስቲኮች

ለ/ ቢጽ ሐሳውያን

/ አርዮሳውያን

መ/ ሁሉም

//መልስ//↪ለ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.1⃣1⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ የግዝት በዓላት የሚባሉት የትኞቹ ናቸው??

 ሀ/ የወልድ በዓል ወር በገባ በ29 ቀን

ለ/ ወር በገባ በ21 የእመቤታችን

ሐ/ወር በገባ በ30

መ/ወር በገባ በ7

ሠ/ ሀ እና ለ

ረ/ ሐ እና መ

//መልስ//↪ሠ,

➡ጥ.ተራ ቁ. 1⃣2⃣➡ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው መብቶች ውስጥ የትኞቹ ናቸው??_

ሀ) ቤተ ክርስቲያን ከግብር ነጻ ናት።

ለ) ከመንግሥት ገቢ ለቤተ ክርስቲያን የተወሰነ ድርሻ አላት።

ሐ) ዕለተ እሑድ /ሰንበት/ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ ሥራ እንዳይሠራበት አወጀ።

መ) ከክርስቲያን ወገን በሕይወቱም ሆነ በሞቱ ንብረቱን ለቤተ ክርስቲያን አወርሳለሁ የሚል ምእንመን   ቤተ ክርስቲያን ኑዛዜ የመቀበል መብት አላት

ሠ/ሁሉም

//መልስ//↪ሠ,

➡ጥ.ተራ.ቁ1⃣3⃣.➡ንጽሕት ድንግል በእውነት አምላክን የወለደች እንደሆነች እንናገራለን እግዚአብሔር ቃል ከእርሷ ሥጋን ተዋሕዷልና። በማለት ስለ እመቤታችን ክብር የመሰከረው አባት ማነው??_

ሀ/ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ

ለ/ ቅዱስ ሳዊሮስ  ዘአንጾኪያ

ሐ/ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘ...

መ/ ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራቅ

//መልስ//↪ሐ,

 ➡ጥ.ተራ ቁ. 1⃣4⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ የተቀደሱ ተራራዎች ከሚባሉት መካከል የሆነው የትኛው ነው??

 ሀ/ደብረ-ታቦር

ለ/ ደብረ ሲና

ሐ/ደበረ ዘይት

መ/ ቀራኒዮ

ሠ/መልስ የለም

ረ/ ሁሉም

//መልስ//↪ረ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.1⃣5⃣➡"አንቺ ሴት ከአንች ጋር ምን አለኝ"? በሚለው ኃይለ ቃል ውስጥ ሴት የሚለው ቃል....ነው??

ሀ/ በእስራኤላውያን የትሕትና አነጋገር ነው።

ለ/ የቁጣ አነጋገር ነው።

ሐ/ ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ ማለት ነው።

መ/ ሀ እና ሐ መልስ ነው።

ሠ/መልስ የለም

//መልስ//↪መ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.➡1⃣6⃣➡የአዳም ሰባተኛ ትውልድ  የትኛው ነው??

ሀ/ አብርሀም

 ለ/ ሄኖክ 

ሐ/ ሙሴ 

መ/ ያዕቄብ

//መልስ// ↪ለ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.1⃣7⃣  አንድ ሰው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሰላምታ ታቀርባለች በማለት መልእክት ቢያደርስ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ምንን ያመለክታል??

ሀ/  ሕንፃ ቤተክርስቲያንን

ለ/ እያንዳንዱ ክርስቲያንን

ሐ/የክርስቲያኖች አንድነትን

መ/ አይታወቅም።

//መልስ//↪ሐ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.1⃣8⃣የመጀመርያዋ  ቤተ ክርስቲያን የተሰራችው በማን ከተማ ነው??

ሀ)በፊልጵስዩስ

ለ) በደማስቆ

ሐ) በአንጾኪያ

መ) መልስ የለም

// መልስ//↪ሀ,

➡ጥ.ተራ.ቁ1⃣9⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከሚለው መጠርያ ስሟ ሌላ በየትኛው ትጠራ ነበር??

/ፉጥ

ለ/ ቶኔቶር

 ሐ/ የኩሽ ምድር

መ/የሳባ ምድር

ሠ/ ሐ/መ

ረ/ሁሉም መልስ ነው

// መልስ//↪ረ,

➡ ጥ ተራ (ቁ)2⃣0⃣ ➡በ186 ዓ.ም በፍቼ የተወለዱና ከኢትዮጵያ የመጀምርያ አራት ጳጳሳት አንዱና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት። በኋላም ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም በኢትዮያ ላይ የግፍ ጦርነት ባነሳ ጊዜ እምቢ ለሃገሬ ለሃይማኖቴ በማለታቸው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በፋሽስት ኢጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት ታላቅ አባት ማን ይባላሉ??

 ሀ/ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ለ/ አፄ ዘረ ያዕቆብ

ሐ/ አፄ ገብረ መስቀል

መ/ መልስ የለም

//መልስ//↪ሀ,

.➡ጥ.ተራ.ቁ2⃣1⃣➡ ጉባኤ ኒቅያ የተካሄደው በስንት ዓመተ ምሕረት ነው??  በማንስ ምክንያት ነው የተካሄደው??

ሀ/ በ335 ዓ.ም በሉተር ምክንያት

ለ/ በ 325 ዓ.ም. በአሪዮስ ምክንያት

ሐ/በ381 ዓ.ም በመቅድንዮስ ምክንያት

መ/ መልስ የለም

//መልስ//↪ለ,


➡ጥ.ተራ .ቁ.2⃣2⃣➡መለኮት �ሥጋን ዋጠው መጠጠው  ብሎ  በማስተማሩ በሊቀ ጳጳስ ፍላብያኖስ የተወገዘው ማነው?( ማን) ይባላል??

ሀ/አሪዮስ

ለ/አውጣኪ ይባላል።

ሐ/ንስጥሮስ

መ/መልስ አልተሰጠም

//መልስ//↪ለ,

➡ጥ.ተራ ቁ.2⃣3⃣➡ለመናፍቃን መልስ ከሰጡ ታላላቅ ቅዱሳን አባቶች መካከል የሆኑት የትኞቹ ናቸው??

ሀ/ አባ አትናቴዎስ

ለ/ ቅዱስ ቄርሎስ

ሐ/ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

መ/ሁሉም.

//መልስ//↪መ,

➡ጥ.ተራ ቁ..2⃣4⃣➡የመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ ጽ/ት ቤት የት ይገኛል??

ሀ/ ኢትዮጵያ

ለ/ ህንድ

ሐ/ ናይሮቢ

መ/ ግብፅ

//መልስ// ↪ሐ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.2⃣5⃣➡የዓለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ንቅናቄ ማኅበር መቼ ተመሰረተ???

ሀ/ በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን

ለ/ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን

ሐ/በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን

መ/መልስ አልተሰጠም

//መልስ//↪ለ,

➡ጥ.ተራ.ቁ.2⃣6⃣➡በብሉይ ኪዳን ዘመን የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ያልሆነው የትኛው ነው??

ሀ/ የኖህ መርከብ

ለ/ የአሳ ማጥመጃ መረብ

ሐ/ ደብረ ሲና

መ/ የሙሴ ደብተራ ድንኳን

//መልስ//↪ለ,

➡ጥ.ተራ ቁ.➡2⃣7⃣በኦሪት አይሁድ ሃምሳ ቀን ቆይተው የሚያከብሩት የምን በዓል ነው??

ሀ/ የመከር በዓል/በዓለ ሠዊት/

ለ/ የፋሲካ በዓል

ሐ/የገና በዓል

መ/ መልስ የለም

//መልስ//↪ሀ,

➡ጥ.ተራ.ቁ2⃣8⃣➡መየቅዱስ ያሬድ ድርሰት ምንጮች

 ናቸው??

ሀ/መጽሐፈ ሐዲስ

እነማንለ/ ብሉያት

ሐ/ ሊቃውንት

መ/ መነኮሳት

ሠ/አዋሊድ፣ ትውፊት

ረ/ሁሉም

//መልስ//↪ረ,

➡ጥ.ተራ.ቁ..2⃣9⃣➡የእመቤታችን አባት ኢያቄም  -ከነገደ----ሲሆን ቅድስት ሐና ደግሞ ከነገደ ------ናት???

ሀ/ ሌዊ&ይሁዳ

ለ/ ይሁዳ&ሌዊ

ሐ/ ሌዌ&ብንያም

መ/ መልስ የለም.

//መልስ// ↪ለ,

➡ጥ.ተራ.ቁ..3⃣0⃣➡እንቆቅልሽ/ህ👇
ፍየልና በግ በቀኝ በግራ ይቆማሉ በተራራ...👉የዚህ ትውፊታዊ እንቆቅልሽ/ህ ፍች ምንን ያመለክታል??

ሀ/ ዳግም ምጽዓትን

ለ/ የጌታችን ትንሳኤን

ሐ/ የጌታችን ስቅላቱን

መ/መልስ አልተሰጠም

//መልስ//↪
ሀ,
.
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
ሌሎች ጥያቄ መልሶችን ለማግኘት👆🏻

በድምፅ ለምትፈልጉ ወደ ይቱብ⤵
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

ከአዳም የተላከ ጦማር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ እምምላክ አሜን

ከአዳም የተላከ ጦማር

ይድረስ ዛሬም ዘወትርም ውድቀቴን ለምትመኝልኝ  ከይሲ /ዲያቢሎስ                          ሰላምታ የእግዚአብሄር ነዉና ሰላምታየ ይድረስህ እያልሁ ስልጣንህን ከተቀማህበት ቀን አንስቶ እንደምን አለህ እኔ እንዳተ ሳይሆን እንደእግዚአብሄር ቸርነት አለሁኝ ምንም እንኳን እግዚአብሄር እኔን አስዉቦና አሰማምሮ በሰራት በገነት ቢያኖረኝም ቅናት የጀመርከዉ ገና በፈጣሪህ ላይ ነዉና የእኔ በገነት መኖር አስቀንቶህ መልዕክተኛህን ልከህ መርዝን አበላሀኝ ጸጋየን አስገፈፍሀኝ ከአምላኬ አራቅሀኝ ሀፍረትን ላክብኝ ክብሬን አሳጣሀኝ ብሎም ወደመሬት አስመጣሀኝ  በስጋየም ካንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን : በላብህ በወዝህ ጥረህ ግረህ ብላ: እሾህና አሜካላ ይብቀልብህ : አፈር ነህና ወደአፈር ትመለሳለህ : የምድርን ቡቃያ ትበላለህ በሚል በአምስት መርገም አስረገምከኝ ከገነት አስወጣሀኝ በነፍሴም የማይጠፋ እሳት: የማያንቀላፋ ትል : የማይገፉት ጨለማ : የንስር ክንፍ በሮ የማይጨርሰዉ ጥልቅ ጉድጓድና ዘላለማዊ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት አስወረረወርሀኝ ::  እኔ እንዳንተ ንስሀን አልጠለሁምና ምንም አንኳን መርዙን አብልተህ ሀጢአት ብሰራም የፈጠረኝ አምላክ አንዲሁ አልተወኝም ቃልኪዳኑ ሲደርስ ከእናቴ ተወልዶ በመስቀል ላይ በአምስት ችንካር ተቸንክሮ በአንተ ምክንያት የመጣብኝን ችግር አስወገደልኝ የነበረኝ በሙሉ ተመለሰልኝ ሀይሉንና የአንተን ድል መንሻ መስቀሉን ሰጠኝ  አሁን አንተን ምን ዋጠህ ?የትአለህ? መዉጊያህስ የት አለ ?ብቻህን መኖሩን ትፈልገዋለህና ወዳንተ እንዳልመጣ እየማልሁ የብቸኝነት ንሮ ይመችህ እልሃለሁ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አንተ ጥንት ጠላቴ ተስፋ የማትቆርጥ
እኔን ለማሳሳት ስንት ግዜ ነው ምትሮጥ
ወይ አለማወቅህ የሰውን ልጅ ክብሩን
እስከ መስቀል ሞቶ ካሳ የሆነውን
ተው ለጥቂቱ እድሜህ አታውራ በከንቱ
እኔን እንደሁ ምሮኛል ተወልዶ ከሴቲቱ
በቃ ተፈጸመ ዓመተ ኩነኔ
በደሙ መለሰኝ ወደ ቀድሞ ክብሬ
ከድንግል ተወልዶ ኢየሱስ መድኅኔ
ሰልጥነህብኝ ነበር በዓመተ ኩነኔ
ዛሬ ተመለሰ ያ የቀድሞው ግብሬ
ስልጣን አሥመኝተህ ሲኦል አስወረድህኝ
እድሞት ፈለገህ ህገን አስፈረስህኝ
አተም አትገባት እኔም ወጣሁኝ ከገነት
ገነትም ተዘጋች ማንም አይገባባት
በእግዚአብሔር አርያ የተፈጠርሁ ነኝ
የምድነበተን አምላክ ተስፋ ሰጠኝ
እንኳን በፍጡሩ በጌታህ የአመፅህ ነህ
አምላክነት ሽተህ ከከብረህ የወረድህ
አመታትም በቆይ በሲኦል ታስሬ
ጌታ መልሶኛል ወደቀደመው ክብሬ
ከገነት ስባርር ነግሮኝ ነበር ጌታ
በ5 ቀናት ተኩል እስሬን እደ ሚፈታ
ከንግዲህ መን በጀህ እስሬም ተፈታልኝ
እኔ እዳልሞት ወዶ ዘርን አስቀረልኝ
ከዚያች ጣፋጭ ገነት አዝኘ ስወጣ
አተ መስሎህ ነበር ዳግም የማልመጣ
እኔ በአተ ምክኒያት ንስሃ ገብቸ ሱባኤ ሥቆጥር
ዳግም መጠህብኝ ተጣልሁ ወደ ምድር
እኔ በአተ ምክኒያት ከምድር ብወድቅም
ንስሃ መግባቴን መቸም አላቆምም
 ሀሳብህ ለጊዜው ምንም ቢሳካልህ
እኔን ላአተ ማድረግ ፍፁም አይሆንለህ
ከአምላኬ ለየኸኝ ክብሬን አስገፈፍኸኝ
ቦታህን ስለ ያዝሁ  ነው ለካን ማትለቀኝ
የተስፋ ጭላጭል አምላኬ ሰጦኛል
ከእናቴ ተወልዶ ይህው አድኖኛል
ከንግዲህ በሲኦል በቻህን ኑርበት
በአምላኬ ድኛለሁ በደሙ ቤዛነት
እናቴን አየኋት በመስቀሉ ግርጌ
ጌታም ቀደደልኝ የዳውን ደብዳቤ
አተ ክፉ ከእይሲ  ትቢት የሞላብህ
ደብዳቤህ ውድቅ ሆነ እኔም ነፃ ወጣሁ
===================
 ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

ሰኞ 26 ማርች 2018

የምዕራፍ ሦስት/የ28ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/QDqw3rGvjhc

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፍስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✝

እነሆ የምዕራፍ ሦስት/የ28ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር👇


🖊ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣ማራናታ ማለት ምን ማለት ነው?ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ???

//መልስ//፡- የአራማይክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም ጌታ ሆይ ቶሎ ና፡፡ 1ኛ ቆሮ.16÷22 ፣ ራዕ.


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪2⃣እግዚአብሔር አብርሃምን የጠራው ከምንድን ነው የተጠራውስ ከየትኛው ሃገር ነው???

//መልስ//፡- የተጠራው ከጣዖት አምልኮ ነው አገሩም ካራን/ ዑር/ ነው፡፡


🖊ጥ.ተራ ቁ3⃣↪ እግዚአብሔር ለሙሴ የተገለጠው በየት ነበር? ለቅዱስ ጳውሎስስ?

//መልስ///፡- ለሙሴ በሲና ፣ ለቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆና በአርዮስ ፋጎስ ነበር፡፡

.
 🖊ጥ..ተራ.ቁ.↪4⃣የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ተጽፈው ያለቁት እስከ ስንት ዓመተ ምህረት ድረስ ነው?

//መልስ//፡- የመጨረሻው የዮሐንስ ራእይ ሲሆን በ96 ዓ.ም.ተጽፎ እንዳለቀ ይነገራል፡፡

.🖊ጥ.ተራ.ቁጥር.↪5⃣ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ስህተት መተርጎም የሚችለው ማን ብቻ ነው?

//መልስ//፡- መንፈስ ቅዱስ እራሱ ብቻ ነው፡፡


🖊 ጥ.ተራ.ቁ.↪6⃣ከ1365-1395 ይኖሩ የነበሩ የጌታ ቀኝ እጅ ያረፈበትን ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ  ያመጡት ንጉሥ ማን ይባላሉ??

//መልስ//፡- ዐፄ ዳዊት ይባላ፡፡

🖊ጥ.ተራ.ቁ↪7⃣የቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዝሙር የነበረና የተሰሎንቄን ውበት አይቶ ወደ ኋላ የተመለሰው ሰው ማን ነው?

//መልስ//፦ ዴማስ

🖊ጥ.ተራ.ቁ ↪8⃣ከ 14ቱ የጳውሎስ መልዕክታት ውስጥ ለግለሰቦች/ በግለሰቦች በኩል/ የተላኩትን ለይተህ አሳይ/ተናገር፡፡

//መልስ//፡- ሶስት ናቸው፡፡ ጢሞቲዎስ ፣ ቲቶ እና ፊልሞና፡፡


🖊ጥ.ተራቁ ↪9⃣.. መጽሐፈ ሳሙኤል 1ኛ እና 2ኛ ስናነብ ልናስታውሳቸው የሚገቡን ዋና ዋና ነጥቦች ምንድን ናቸው?

//መልስ//፡- ስለ ነቢዩ ሳሙኤል፣ ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት መማረክ፣ ስለ ንጉሥ ሳኦል እና ስለ ንጉሥ ዳዊት መቀባት…ወ.ዘ.ተ.፡፡


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣0⃣ ነቢዩ ዳዊት መናገሻ ከተማውን ያደረገው በየት ነበር? ሰባት ዓመት የገዛውስ የትኛውን ነገድ ነው?

//መልስ//፡- ኬብሮን ስትሆን ለሰባትአምመት የገዛው የይሁዳን ነገድ ነው፡፡

🖊ጥ.ተራ.ቁ  ↪1⃣1⃣ነቢዩ ዳዊት ከእግዚአብሔር የተሰጡት ሀብታት ስንት ናቸው?ዝርዝራቸው?  መዝሙሮችንስ ስንት  ደርሷል? በስንት የዜማ መሳሪያስ አመስግኗል??

//መልስ//፡- ሰባት ናቸው፡፡ 1. ሀብተ በገና 2. ሀብተ ትንቢት 3. ሀብተ ፈውስ 4. ሀብተ መውዕ/ሀይል/ 5. ሀብተ መንግሥት 6. ሀብተ ክህነት 7. ሀብተ ዝማሬ/መዝሙር/ ሲሆኑ መዝሙሮቹ 50 ናቸው፡፡ መሳሪያዎቹ ከበሮ ፣ በገና፣ መዝ. 149 እና መዝ.150


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣2⃣ ለነቢዩ ናታን እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ እንደተቀመጠ እይ ያለው ሰው ማን ነው? ለስንት ዓመትስ ነግሷል?

//መልስ//፡- ንጉሥ ዳዊት ሲሆን ለ40 ዓመት ነግሷል፡፡ 2ኛ ሳሙ.7÷1-2

🖊ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣3⃣ነቢዩ ዳንኤል ለጣኦት ከሚሰዋው ምግብ በልተን እንዳንረክስ አሥር ቀን ብቻ በጥራጥሬ ፈትነን ያለው ማንን ነው?

//መልስ//፡- ሜልዳር ይባላል፡፡ ት.ዳን.1÷12


🖊ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣4⃣ እናንተ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በሰይፌ ትገደላላችሁ ይህን ጥቅስ የት እናገኘዋለን?

//መልስ//፡- ት.ሶፎ 2÷12


🖊ጥ.ተራ.ቁ 1⃣5⃣በዳዊት ዘመን የነበረው የመዘምራን አለቃ ስሙ ማን ነበር?

//መልስ//፡- አሳፍ፡፡ 1ኛ ዜና 16÷5
2.


.. 🖊ጥ.ተራ ቁ↪1⃣6⃣ የምታመልኩትን ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን ያለው ሰው ማን ነው?

//መልስ//፡- ኢየሱ፡፡ ኢያ.24÷15


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣7⃣120 ቤተሰቦች በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው?

መልስ፡- 12 ሐዋርያት ፣ 72 አርድዕት ፣ እና 36 ቅዱሳት አንስት፡፡

 🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣8⃣እሴይ ከነቢዩ ዳዊት ጋር ስንት ልጆች ነበሩት? ነቢዩ ሳሙኤል መጀመሪያ ሊቀባው የነበረውስ የትኛውን ልጅ ነው? ሁለተኛውስ?

መልስ፡- 8 ናቸው፡፡ ሁለቱ ኤልያብ እና አሚናዳብ ናቸው፡፡ 1ኛ ሳሙ.16÷6

 🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣9⃣ከሩት ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሉትን የዘር ሃረጎች ዘርዝር፡፡


መልስ፡- ሩትና ቦኤዝ፣ እሴይ፣ ዳዊት፣ሶሎሞን….ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ሩት 4÷21-22

🖊ጥ.ተራ ቁ ↪2⃣0⃣ነቢዩ ዳዊት የኦርዮን ሚስት ቤርሳቤን በመድፈሩ ከእግዚአብሔር ለተግሳጽ የተላከው ነቢይ ማን ነበር? ዳዊትስ ከዚያ በኋላ ምን አደረገ?

መልስ፡- ነቢዩ ናታን፡፡ሙሉ ታሪኩን 2ኛ ሳሙ.ምዕራፍ 11 እና 12 በሙሉ፡፡

.🖊ጥ.ተራ.ቁ↪2⃣1⃣ የነቢዩ ዳዊት ልጅ የአቤሴሎምን እህት የደፈረው ማን ነበር? አቤሴሎምስ የወሰደው እርምጃ ምን ነበር?


መልስ፡- አምኖን ሲሆን የተደፈረችው ትዕማር ትባላለች፡፡ አቤሴሎምም በንዴት አምኖንን ገድሎታል፡፡ 2ኛ ሰሙ.13÷1


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪2⃣2⃣ሐዋርያት ጌታን አጭር ፀሎት አስተምረን አሉት እሱም አስተማራቸው ፡፡ ያስተማራቸው ፀሎት ምን ነበር?

መልስ፡- እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ፡-" አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር…ማቴ.6÷9"


🖊ጥ.ተራ ቁ↪2⃣3⃣ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል ብሎ የጠየቀው ማን ነው? ማንን? መልስ ሰጪውስ ማን ነበር?

መልስ፡- ጌታችን ነው፡፡ የጠየቀው ሐዋርያትን ነው፡፡ መላሹ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ መልሱም ˝ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ˝ ማቴ. 16÷13


 🖊ጥ.ተራ.ቁ↪የቅዱስ ማቴዎስ አባትና እናት ስማቸው ማን ነው? ለሐዋርያትነት
የተጠራውስ ከምን ነበር?

መልስ፡- አባቱ ዲቁ እናቱ ክሩትያስ ሲሆኑ ሥራው ቀራጭነት ነበር፡፡

የ28ኛዙር ጥያቄና መልስ ይህን ይመስላልን። ሚኮ ዘ.ኢትዮጵያን/miko zE Ethiopian እናመሰግናለን።

ወስብኃት ለእግዚአብሔር


በፁህፍ ለምትፈልጉ ለቴሌ ግራም ተጠቃሚዎች👇
ቴሌ ግራም👉https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA

ይቱብ👉https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

እሑድ 25 ማርች 2018

የምዕራፍ ሦስት/27ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✝

↪ሰላመ እግዚአብሔርሦስት ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ?? እነሆ የምዕራፍ  (የ27ኛ) ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር እንዲህ ቀረበ⤵

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣✍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ሐናዎች ስንት? ናቸው?? ጥቀስ/ሽ፡፡

//መልስ//፡- ሐና እሙ ሳሙኤል፡፡ ነቢይቷ ሐና ሊቀ ካህኑ ሐና፡፡ 1ሳሙ.1÷1 ፣ ሉቃ.2÷36 ፣ ሉቃ.3፥2

🖊ጥ.ተራ.ቁ 2⃣✍. ግብፃውያን በእስራኤላውያን ላይ ግፍ በማድረሳቸው በእግዚአብሔር ቁጣ የደረሱባቸው መቅሰፍቶች ብዛት ስንት ናቸው?

//መልስ//፦አስር(ዘጸ 7፥12)

 🖊ጥ.ተራ ቁ.3⃣✍ጌታ የተቀበረበት መቃብር ለማን የተዘጋጀ መቃብር ነው?

//መልስ//፦ ቀሬናዊው ስምፆን(ማቴ 27፥32)

🖊ጥ.ተራ.ቁ.4⃣✍. ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና ሌሊት ከጾመ በኋላ ድል ያደረጋቸው ሶስቱ ታላላቅ ኃጢያቶች ምን ምን ናቸው?

//መልስ//፦ ስስት፣ትዕቢትና ገንዘብ መውደድ።

🖊ጥ.ተራ.ቁ 5⃣✍. ጌታ በተወለደበት ዘመን በጾምና በጸሎት ተወስና ትኖር የነበረችው የ 84 ዓመቷ የፋኑኤል ልጅ ማን ነች?

//መልስ//፡- ሐና /ነቢይት/ ሉቃስ 2÷37-38

🖊ጥ.ተራ.ቁ.6⃣✍ ከሐዋርያት መካከል አብን አሳየንና ይበቃናል ያለው ማን ነው?
//መልስ//፦ ፊልጶስ(ዮሐ.14፥8)

🖊ጥ.ተራ.ቁ.7⃣✍የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴ እና ቅዳሴ በተጨማሪም ሰዓታትን የደረሱት አባቶች እነማን ናቸው?

//መልስ//፡- አባ ኤፍሬም ሶርያዊ፣ አባ ሕርያቆስ ብህንሳ ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፡፡

🖊ጥ.ተራ.ቁ.8⃣✍ሁለቱ የኤማውስ መንገደኞች እያለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠራቸው ሰዎች ማንና ማን ናቸው?

//መልስ//፦ሉቃስና ቀለዮጳ።(ሉቃስ 24፥13-18)

🖊ጥ.ተራ.ቁ9⃣✍ሙሴ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያንን እየመራ ከነዓን ያደረሳቸው ሰው ማን ነው?


//መልስ//፦መስፍኑ ኢያሱ

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣0⃣✍ አባታችን አዳም እርቃኑን ከሆነ በኋላ ቅጠል እንዳገለደመ መጽሐፍ ቅዱስ ያስነብበናል፡፡ ከገነት ሲባረር ለብሶት የወጣው አዳምምንድን ነው?

//መልስ//፦ የቁርበት ልብስ (ዘፍ 3፥21)

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣1⃣✍ለአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ሐዋርያ ለብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነቢይ በመባል የሚታወቀው ሰው ማነው??

//መልስ//፦መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ(ት/ኢ.ሳ 40፥3፣ማቴ 3፥1)

🖊ጥ.ተራ.ቁ 1⃣2⃣✍ከ 12ቱ ነገደ እስራኤል ሁለቱ ከነዓን ያልገቡት ማንና ማን ናቸው? በእነሱ ምትክ የገቡት ሁለቱ ሰዎች እነማን ናቸው?


//መልስ//፦ዮሴፍና አሮን። ኤፍሬምንና ምናሴ ናቸው

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣3⃣✍የቅዱስ ያሬድን ዜማዎች በሙሉ እንደቅደም ተከተላቸው እና አገልግሎታቸው አስፍሮ መዝግቦ የሚገኘው መጽሐፍ ምን ይባላል?

//መልስ//፦ መጽሐፈ ድጓ


🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣4⃣✍ ስለ ንግስተ ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ለመመልከት ወደ እስራኤል መሄድ የሚተርኩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ጥቀስ??

//መልስ//፦1ኛ ነገ.10፥1(.10፥42)

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣5⃣✍. ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 7 ቁጥር 14 ሲያነብ ማመን ያልቻለና ይህን እስክታይ አትሞትም የተባለው ሰው ማን ነው?

//መልስ//፦አረጋዊው ስምፆን(ሉቃስ 2፥25)

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣6⃣✍ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲውል የታዩት ተአምራት ስንት ናቸው ምን ምን??

//መልስ//፦ሰባት ናቸው። በሰማይ ሦስት በምድር 4ት (ማቴ 27፥51-54)

🖊ጥ.ተራ.ቁ1⃣7⃣✍ በታቦር ተራራ ላይ ከብሔረ ሕያዋንና ከመቃብር የጌታን ክብር ለማየት የተጠሩት ሰዎች እነማን ናቸው?

//መልስ//፦ሙሴና ኤልያስ(ማቴ 17፥1)

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣8⃣✍በ400ኛው ክፍለ ዘመን በጣም ታዋቂ የነበሩ እነ አትናቲዎስ እና አርዮስ የተማሩበት ትምህርት ቤት ምንና ምን ናቸው?

//መልስ//፦አንጶኪያና አሌክሳንድርያ/ሶርያና ግብፅ

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣9⃣✍ ርእሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው የመጀመሪያው መነኩሴ ማን ነው? ሀገሩስ?

//መልስ//፦አባ እንጦስ ግብፃዊ

🖊ጥ.ተራ.ቁ.2⃣0⃣✍ሙሴን ከባህር ያገኘችው ሴት የማን ልጅ ነች? ስሟስ ማን ይባላል?

//መልስ//፦የፈርፆን ልጅ ተርሙት ናት።(ዘጸ.2፥1)


🖊ጥ.ተራ.ቁ✍2⃣1⃣እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመጸነሷ በፊት ፣ በጸነሰች ጊዜ ፣ ከጸነሰች በኋላ ፣ ከመውለዷ በፊት ፣ በወለደች ጊዜ ፣ ከወለደች በኋላ ድንግል መሆኗን የተነበየው ነቢይ ማን ነው?

//መልስ//፦ነቢዩ ሕዝቅኤል  ት/ሕዝ.44፥1፣ሉቃስ 1፥26

✍ምንጭ miko ZE Ethiopia ➡https://www.facebook.com/mikynice98

https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjAsaramareyama.890@gmail.com

ሰኞ 19 ማርች 2018

ገብር-ኄር አጭር መንፈሳዊ መነባንብ

💗 _*ገብርሔር*_ _*ገብርሔር*_

👨🏾‍🎓 ተነሱ ጓዶቼ ንጉሥ ይጠሩናል
ዛሬ ወደሆነ ቦታ ሊሄዱ ይመስለኛል

🙎🏾‍♂ ምን አይነት ጣጣ ነው
አሁን ብንተኛበት እስኪ ምን አለበት
ቆይ እኔ የምለው?.. አይሄዱ በኛ እግር
በትንሽ ትልቁ ጥርያ ባያበዙ

🙋🏾‍♂ተው እንጂ ወዳጄ እንዲህ አይባልም
ሲጠሩን አቤት ሲልኩን ወዴት ማለት የግድ ነው
ይልቁንስ ተነስ እንቅልፉ ይደርሳል

💗በሉ ልጆቼ እኔ የጠራኋችሁ
መክሊት ልሰጣችው ነው እንደ ያቅማችሁ
እስክመለስ ድረስ ቆዩኝ አትርፋችሁ

👨🏾‍🎓እሺ ጌታዬ ሰላም ይመልሶት
እኛንም ፈጣሪ ታማኞች ያድርገን
በተሰጠን ላይ እንድንገኝ
አትርፈን
ባሳባችን ሁሉ እርሱ ይቅደምልን

🙋🏾‍♂ጓዶች ደህና ሁኑ እንሰነባበት
ከዛሬ ጀምረን ለስራ እንፋጠን
ባላደራዎች ነን ባለብዙ መክሊት
እንገናኛለ ሲመለሱ ንጉሥ

🙎🏾‍♂ ወይ እዳ ምኑን አመጡብኝ
ጭረሽ ይባስ ብለው እጣጦስ ጣሉብኝ
ደሞ ንቀታቸው ለሌሎቹ ብዙ
ለኔ ግን አንድ ብቻ ሰጡኝ
ቆይ ባልሰራሎት አሁን ይጠብቁ
ቆፍሬ ቀብሬ ባልመልስሎት ሲመጡ

 *⚜ተራኪው* ሁሉም በየፊናው ተሰማራ
የተሰጠውን ይዞ መንገዱን አቀና
ከጊዜ በኋላ ሁሉም ተጠሩና
ጌቶች ተመልሰው ሆነው በዙፋኑ
የመረካከቢያ ደርሶ ኖሮ ቀኑ
እንደዚህ አሏቸው ወደ እነሱ እያዩ

💗 ያስረከብኳችሁን መልሱልኝ በሉ
ያተረፋችሁትን ይዛችሁ ቅረቡ
ልክፈላችሁ የድካማችሁን ዋጋ

👨🏾‍🎓 እሄው ጌታዬ ሆይ አመሰግናለሁ
ባምስት ፈንታ አስር አትርፌበታለሁ
በፊቶት ሞገስን ለማግኘት ችያለሁ
ነገር ግን ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው
ሀሳቤን አቅንቶ አምላክ እረድቶኝ ነው

🙋🏾‍♂ ሺ ዓመት ይንገሱ በዕውነት
ሁለት በዕጥፍ አድርጌ ቆያሆት
ለኔ ለደካማ አምነው የሰጡኝን
አሁን ከነ ትርፉ ይሄው ተረከቡኝ
በመልካም ጎዳና ስላሰማራኝ
ልቤን አነሳስቶ ህልሜን ላሳካልኝ
ለፍጥረታት ገዢ ክብር ለዕርሱ ይሁን

🙎🏾‍♂ ስንት ጊዜ ሙሉ እንቅልፌን ነፈጉኝ
ዛሬ ተመለሱ እንኳንም መጡልኝ
ይሄው ገንዘቦት በሉ ይረከቡኝ
አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዳይሆን ነገሩ
በጥንቃቄ ደብቄ ጠበኮት ይውሰዱ
ሳልቀንስ ሳለውጥ እራሱኑ እንኩ

💗 እውነት እውነት እላችኋለሁ
እናንተ ያባቴ ብሩካን ናችሁ
በጥቂት በብዙ ስለታመናችሁ
ከዛሬ ጀምሮ ከኔ ጋራ ናችሁ

አንተ ግን እልሃለው
ከዕነሱጋ ቦታ የለህም
በተሰጠህ መጠቀም አልቻልክም
ትዛዜን ተላልፈህ ህጌን አቃለሃል
አንተ ክፉ ባርያ ከፊቴ ወግድልኝ

⚜ *ተራኪው*
ገብርሔር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው
ጌታቸው ላንዱ 5 ላንዱ 2 ላንዱ ደሞ 1 መክሊት ሰተዋቸው ሄዱ ሲመለሱ ባለ አምስቱ 10 ባለ ሁለቱ 4 አርገው ሲቆዮዋቸው ባለ አንዱ ግን ቀብሮ ጠብቆ ያንኑ መለሰላቸው
አትርፈው የተገኙት በረከት ሲቀበሉ ቁጭ አርጎ የጥበቃቸው ጭርሱን ተባረረ
ታድያ እኛስ ከየትኞው ወገን ነን?
ሁላችንም የተለያየ ፀጋ ተሰቶናል
እየተጠቀምንበት ይሆን ወይስ እንደዛ ክፉ ባርያ መክሊታችንን ቀበርን?
ስላነሰ ስለበዛ ሳይሆን የሰው ልጅ የሚያተርፈው አምኖ በመቀበል ነው።
መቼም በያመቱ የሁዳዴ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ላይ እሄንን ትምህርት አባቶቻችን በስፋት ያስተምሩናል
እኛስ ሰምተን እየተጠቀምን ይሆንን?
ይሄንን ነገር ትኩረት ሰትን እንገንዘበው እያንዳንዳችን ገና ስንፈጠር የተሰጠን ትልቅ ነገር አለ እንደ ቀላል የምናየው
ነገ ያስጠይቀናል ያስቀጣናልና
ባለን እውቀት እየተጠቀምን በቅን ልቦና እናገልግ የሚል መልዕክቱን ያስተላልፍልናል ተዋህዶ እምነታችን ኪነ-ጥበብ ክፍል

አሜን ወስበሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.89@gmail.com

ጥያቄና መልስ

1. አዳም በምድር ላይ የኖረው የእድሜው ዘመን ስንት ነው?

መልስ፡- 930፡፡ ዘፍ.5÷1-5

2. የቅዱስ ጳውሎስን የሕይወት ታሪክ መዝግቦ የያዘ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የቱ ነው?

መልስ፡- የሐዋርያት ሥራ፡፡

3. ስለ ነቢያት በስፋት የሚተርከው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የቱ ነው?

መልስ፡- መጽሐፈ ነገሥት 1ኛ እና 2ኛ፡፡
4. ጌታ ሲወለድ የነበሩት የእስራኤልና የኢትዮጵያ ነገሥታት እነማን ነበሩ?

መልስ፡- ሄሮድስና ንጉሥ ባዚን፡፡ ማቴ.2÷1

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

1. የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አባት እና እናት ስማቸው ማን እና ማን ናቸው?

መልስ፡- አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ማርያም ስትሆን ከ 36 ቱ ቅዱሳን አንስት አንዷ ነች፡፡
2. ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሌላ ስንት መጠሪያ ስሞች አሉት ? ዘርዝሩ፡፡

መልስ፡- 7 ስሞች አሉት፡፡ ወልደ ዘብዴዎስ  ፣ ወልደ ነጎድጓድ / ቦአኔርጌስ/ ፣ ቁጽረ ገጽ ፣ ፍቁረ እግዚእ ፣ ነባቤ መለኮት/ ታዖሎጎስ/ ፣ አቡቀለምሲስ/ ባለራዕይ/ ፣ ወንጌላዊ/ ሐዋርያ/፡፡

3. ዮሐንስ ወንጌላዊ በአጠቃላይ ስንት መጻሕፍትን ጽፏል?ዝርዝሩ

መልስ፡- 5 ፡፡ የዮሐንስ ወንጌል ፣ 1ኛ የዮሐንስ መልዕክት ፣ 2ኛ ና 3ኛ የዮሐንስ መልዕክት  እና የዮሐንስ ራዕይ፡፡

4. በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ እኔ ነኝ ተብሎ የተጻፉ ሰባት ነገሮች አሉ ዘርዝራችሁ ጸፉ፡፡

መልስ፡- የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ፣ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ ፣ የበጎች በር እኔ ነኝ ፣ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ፣ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ ፣ መንገድ እውነትና  ሕይወትም እኔ ነኝ  እና እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፡፡

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨♥♥

1. ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ነገሮችን ያመለክታል ለመሆኑ እነዚህ 3 ነገሮች ምን ምን ናቸው?

መልስ፡- 1. ሕንጻው እራሱ ፣2. የክርስቲያኖች ህብረት፣ 3.አንድ አማኝ ብቻውን፡፡

2. ሳይወለድ የሞተው ወይም ወደመቃብር የወረደው ብቸኛው ሰው ማን ነው?

መልስ፡- አዳም፡፡ ተፈጠረ እንጂ አልተወለደም፡፡

3. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ እንደሌለባት የሚነገረ ጥቅስ ተናገሩ፡፡

መልስ፡- ኢሳ.1÷19

4. አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤልና ዳንኤል ከሌሎቹ የተለየ የነበራቸው የተለየ ነገር ምን ነበር?

መልስ፡- ጥበብ ፣ እውቀት፣ እና ማስተዋል ነበራቸው፡፡ ት.ዳን 1፥3


https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
ተጨማሪ ጥያቄና መልሶችን ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ሁኑ👆🏻

ዓርብ 9 ማርች 2018

የምዕራፍ ሦስት/የ26ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✝

✍ እነሆ፦ የምዕራፍ ሦስት/የ26ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ እንደሚከተለው ይቀርባል፦🖊
🖊ጥ.ተራ ቁ 1⃣✍አራቱ ባህርያተ ሥጋ እና ሦስቱ ባህርያት ነፍስ በመባል የሚጠሩትን አስረዳ??

//መልስ//🖊ነፋስ፣ እሳት፣  መሬት የሥጋ ባሕርያት ሲሆኑ ነባቢ/ተናጋሪ/የነፍስ ባሕርያት ናቸው።

ጥ.ተራ ቁ 2⃣✍የዐቢይ ፆም ሥንት ሳምንታት አሉት?? ውሃናየእያንዳንዳቸውን የስም ስያሜ ጥቀስ/ሽ???

//መልስ//በቤተክርስቲያናችን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፦
1,ዘወረደ   2,ቅድስት  3,ምኩራብ  4,መጻጉ
5,ደብረ ዘይት  6,ገብርኄር  7,ኒቆዲሞስ  8,ሆሳህና ናቸው።

✍ተጨማሪም፦፦(አስር )ሌሎች መጠሪያ ስያሜዎች

፩  , አቢይ ፆም

፪ , ፆመ ሁዳዴ

፫ ,የካሳ ፆም

፬ , የድል ፆም

፭  , የመሸጋገሪያ ፆም

፮ , ፆመ አስተምህሮ

፯ ,የቀድሶተ ገዳም ፆም

፰ ,የመዘጋጃ ፆም

፱ , የሥራ መጀመሪያ ፆም

፲  , ፆመ  አርብዓ ይባላሉ።

🖊ጥያቄ.ተራ.ቁ 3⃣✍ ወንድማችንን ብንገድል ምን ይጠቅመናል በጉድጓድ ውስጥ እንጣለው ያለው የዬሲፍ ወንድም ማን ነበር?

//መልስ//🖊 ሮቤል ነው። ዘፍ 37፥

✍ጥ.ተራ.ቁጥር✍4⃣ሰማዕት እና ጻድቅ የሚሉት  ቃላት  የምን ቃል ናቸው? ትርጓሜያቸውስ ምን ማለት ነው?

//መልስ//፡- ሁለቱም የግዕዝ ቃላት ሲሆኑ ሰማዕት ማለት ምስክር ሲሆን ጻድቅ ማለት እውነተኛ ማለት ነው፡፡

🖊ጥ.ተራ ቁ.5⃣✍ ኦሪት ዘጸአት ማለት ምን ማለት ነው? የመጽሐፉ ጸሐፊስ ማን ነው?

//መልስ//ዘጸዓት ማለት፦  የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መውጣህ ማለት ማለት ነው። ጸሐፊው ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ነው።

🖊ጥ.ተራ.ቁ.6⃣✍ከግራር እንጨት ታቦት የሰራው ሰው ማን ነው??(ማን ይባላል)
//መልስ//🖊ባስልኤል ይባላል(ዘጸዓት 37፥1)

🖊ጥ.ተራ ቁ.7⃣✍እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸው ሕጎች ብዛት ስንት ነበር? ዘርዝሩ፡፡

//መልስ//፡- 10.ቱ ትዕዛዛት፡፡ ዘፀ. 20 ÷ 1-18

 🖊ጥ.ተራ ቁ 8⃣✍በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስትናን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበሉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ማንና ማን ናቸው?

//መልስ//፡- አብርሃና አጽብሐ

🖊ጥ.ተራ ቁ.9⃣✍እውር እያመሰገኑየነበረውና በኢያሪኮ ተቀምጦ ይለምን የነበረው ሰው ማን ነበር? አባቱስ ማን ይባላል???
//መልስ//፦//መልስ//🖊፡- በርጠሜዎስ፡፡ ጢሜዎስ፡፡ ማቴ.20÷29-34

🖊ጥ.ተራ ቁጥር1⃣0⃣መጽሐፈ ሊቃውንት በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው?

//መልስ//፡- ሃይማኖተ አበው ፣ መጽሐፈ ቅዳሴ ፣ መጽሐፈ ቄርሎስ ፣ የዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳንና ተግሣፅ፡፡

🖊ጥ.ተራ.ቁ 1⃣1⃣✍እግዚአብሔር ለሙሴ አጋዥ እና አንደበት እንዲሆን የሰጠው ማንን ነበር???
//መልስ//፦🖊ወንድሙን አሮንን ነው፡፡ ዘፀ. 4÷10-15

🖊ጥ.ተራ.ቁ.1⃣2⃣✍.ቅዱስ ዮሐንስ ያስተማርበት አገር የትኛው ነው?
ሀ (A):አንፇኦኪያ
ለ (B):ሎዶቂያ
 (C): ምስራቅ
መ(D):አውስትራልያ
ሠ(E):ሀ(A)እና ለ(B)
ረ (F) : ሐ(C)እና መ(D)

ሐ//መልስ//🖊ሠ)ነው።

 🖊ጥ.ተራ.ቁ 1⃣3⃣✍አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው የጸለዩት ለስንት ዓመት ነው።

//መልስ//አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጽያን ማርልኝ እያሉ በባህር ውስጥ ወደ እግዚአብሔር የፀለይት ለመቶ ዓመት (100)ነው።

🖊ጥ.ተራ ቁ1⃣4⃣✍ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚፈጸሙ የትኞቹ ናቸው??
//መልስ//🖊 ምሥጢረ ክህነት ፣ ምሥጢረ ተክሊል ፡ ምክንያቱም ሁሉም ካህን አይሆኑም ሁሉም አያገቡም እና ነው፡፡

🖊ጥ.ተራ ቁ 1⃣5⃣✍ይዲድያ ወይም በእግዚአብሔር የተወደደ ብሎ ለሰሎሞን ስም ያወጣለት ማን ነው???

//መልስ///🖊፡- ነቢዩ ናታን፡፡ 2ሳሙ.12÷24

🖊ጥ.ተራ ቁ.1⃣6⃣✍ ከጥሩ ወርቅ ርዝመቱ-----ክንድ ወርዱም-------ክንድ የሆነ የስርየት መክደኛ ስራ! ክፍት ቦታውን ሙሉ?

//መልስ//፦🖊 ርዝመቱ ሁለት፦ ክንድ ተኩል
ወርዱ፦አንድ ክንድ ተኩል ኑው።(ዘጸአት 37፥6)

🖊ጥ.ተራ ቁ 1⃣7⃣✍ከትንሣኤ እስከ ጰራቅሊጦስ በቤተክርስቲያን የሚቀደሰው ቅዳሴ ምን ይባላል???

//መልስ//🖊፡- ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ/እምቅድመ ዓለም/፡፡

 🖊ጥ.ተራ ቁ.1⃣8⃣✍
. ስለ 666 ወይም ስለ ሐሳዊው መሲሕ የጻፈው ሐዋርያ ማን ነው? ምዕራፍና ቁጥሩስ?

//መልስ//፡- ራዕይ 3÷1

🖊ጥ.ተራ ቁ.1⃣9⃣✍ጰራቅልጦስ ማለት ምን ማለት ነው???.

//መልስ//፦🖊ጵራቅልጦስ ማለት አፅናኝ ማለት ነው።

. 🖊ጥ.ተራ.ቁ.2⃣0⃣✍የአራቱ አበይት ነቢያት የትንቢት መጽሐፍ ስንት ስንት ምዕራፎች አሉአቸው?

//መልስ//🖊፡-  ኢሳይያስ /66/ ፣ ኤርሚያስ/52/ ፣ ሕዝቅኤል/48/  እና ዳንኤል/12/፡፡

✍ውድ ተወጄጆች መልስና ጥያቄ ይህን ይመስካል ስዕተት አይጠፋም እና አርሙን እንልለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በፁህፍ ለምትፈልጉ ለቴሌ ግራም ተጠቃሚዎች👇
ቴሌ ግራም👉https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA

ይቱብ👉https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.89@gmail.com

መልእክቶቻችሁ መረሀ ግብር

/ስለ ፆም ቢሔለ አበው

☞ ኃይለኝ መድኃኒት መርዘኛ ፍጥረታትን ነቅሎ እንደሚወጣ ከጾም ጋር የተባበረ ጸሎትም ክ
ፍ ሐሳቦችን ነቅሎ ይጥላል ፡፡
           / ቅድስት ጠንቀሊጠቃ/

☞ ጾም ክብር ይግባውና ጌታችን በሠራልን በወንጌልና በኦሪት መካከል  የተሠራች ሕግ ናት ፡፡
     / ማር ይሰሕቅ /


☞ ሁል ጊዜ የምትጾም ከሆነ በቅፅበት  ራስህን ወደ ላይ አታውጣ ከዚህ  የተነሣ በራስህ  ከፍ አድርገህ  የምትመለከት ከሆነ ግን ሥጋ ብትበላ ይሻልሃል ፡፡   ለአንድ ሰው ራሱን ትዕቢት ከመንፋትና ራሱን ከማክበር  ሥጋ ቢበላ ይሻለዋል ፡፡
     / አባ ኤስድሮስ /

☞ ሀብት መልካም የሚሆነው  ባለቤቱ በቅንጦት በብርቱ መጠጥና ጉዳት በሚያስከትሉ ፈንጠዝያዎች ሲጠቀምበት ሳይሆኑ በመጠኑ ዘና በሎ በሚተርፈው የድሆችን ሆድ ለመሙላት  ሰያከፋፍለው ነው፡፡
        / ዮሐንስ አፈወርቅ /

የዓቢይ ፆም አራተኛ ሳምንት በመሆኑ ስለ መፃጉ ትንሽ እንበል👇
እኔ መፃጉ ነኝ

ለብዙ ዓመት በአልጋ ላይ የነበርኩ፣
በሥጋ በሽታ በህመም የደከምኩ፣
በአጭር ተቀጭቼ ሳላብብ የረገፍኩ፣
ፈውሴን የምናፍቅ ወገን ያልነበረኝ፣
ውሃው ሲነዋወጥ ጠልቆ የሚያወጣኝ፣
ከርታታ ባይተዋር ውዳቂ ነበርኩኝ፣
ከዕለታት አንድ ቀን በዚያ ሲያልፍ ጌታዬ፣
ሊፈውሰኝ ወዶ ገብቶ ከጎጆዬ፣
በቃሉ አድኖኝ ቆሜ ሄድኩኝ በዕግሬ፣
አይሁዳዊ እነቴ እንዳይቀር ዘሬን፣
ምስጋና ለማቅረብ ባይታደል ልቤ፣
ተንኮል በኔ ነግሶ ክፋትን  ደርቤ፣
ሰንበትን በመሻር የማረኝ ይሄ ነው በማለት፣
ብድሩን ስከፍለው ጥፊን መለስኩለት፣
የወዳጄ ጠላት እኔ መፃጉ ነኝ
በኩዳዴ ፆሙ ውስጥ የምታስታውሱኝ።saramareyama.89@gmail

በመንፈሳዊ ትውፊት የተዘጋጀ እንቆቅልሽ/ህ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝


       *እንቆቅልሽ/ህ*

1⃣🖊ከ12ቱ ደቀ መዛሙርት መካከል
አንዱ ገንዘብ ያዥ ነበር
ታድያ በልቡ ስስት ነግሶ
ጌተውን ሸጠ  ቃሉን አፍርሶ
አባትነቱን ክዶ
በእራሱ ላይ ጫነ የኃጢአት ነዶ
ይህ ካኃዲ ሰው ማነው?
ንገሪኝ ካወክሽው??

//መልስ// ፦  ይሁዳ ነው።
.
2⃣🖊ሸክሙን ብሸከም አዝኜ ህመሙን እኔ ብታመም
ምን ነው ልጄ ጨከነ ልቡን ወሰደው ዓለም
ጥፊን ለኔ መለሰ ያንን ውለታ እረስቶት
እስቲ ማን ይሆን ይህ ስው ስሙን ካወቃችሁት??

//መልስ//፦ መፃጉ ነው።


3⃣🖊እደልቤ ብሎ አምላክ የመርጠው
አንድ መቶ ሀምሳ መዝሙር የደርሰው
የእስራኤል መሪ ይኸ ንጉስ ማነው?


//መልስ//፦ቅዱስ ዳዊት


4⃣🖊ክርስቲያን ላሳድድ ጦር ይዠ ብወጣ
አታሳደኝ የሚል የአምላክ ድምጽ መጣ
በፍቅር ተናግሮ ልቤን አቀለጠው
 ተማረኬ መጣሁ ጦሬን እዛውትቸ
እስከመጨርሻው ተከተልኩት ፀንቸ

//መልስ// ፦ቅዱስ ጻውሎስ


5⃣🖊የአባቶቸን እርስት በፍጹም አለቅም
ከርስቴም አልወጣም አልነቃነቅም
የፈለከውንም በኔላይ ብትፈጽም
አክአብ እውነቴንነው እርስቴን አልሰጥም።

//መልስ//፦ ናቡቴ


6⃣🖊ወርቅና ብሩን በልዋጭ ሰጥቸህ
የአባቶችህን እርስት መጣሁኝ ልቀማህ
እንቢ ካልከኝ ግን በእምነትህ ከጸናህ
አንተን ገድዬ ለውሾች ነው እምሰጽህ ያለው ማነው

//መልስ//፦ አክአብ


7⃣🖊በንጹህ ልቦና አምላክን ቢያአመልከው
ሰይጣን ቀናበትና በቁስል አነደደው
ንብርቱን አጥፍቶ ባዶውን አስቀርው
እሱማ ሳይበገር እስከ መጨርሻው
በእምነቱ የጸናው
ይኽን ሁሉ አልፎ በክብር የቆመው
ካወቅሽው ንገሪኝ ይኸ ቅዱስ ማነው?

//መልስ//፦ እዮብ

8⃣🖊 ጣፋጭ የሆነ እንደማር
የማያስርብ የሚያጠግብ
በስደትም ስንቅ ነው
አምኖ ለሚጠራው

//መልስ//ቅዱስ ወንጌል/መጽሐፍ ቅዱስ


9⃣🖊ሰንሰለትን ለበሳ የተጋደለች
ለሃይማኖቷ ቆርጣ የታገለች
የሱስንዮስ ክኅደት ፍጹም ያላስፈራት
የእምነት አርበኛ ይህች ቅድስት እናት
በሉ እስኩ ንገሩኝ ማናት?

//መልስ//ቅድስት ወለተጴጥሮስ

1⃣0⃣🖊ሳይገባኝ የማልችለውን ነክቼ
ተጣብቃ ቀረች እጄ ሰለሉ ጣቶቼ
የምሕረትን እናት በክፋት ነክቼ
ኃጢአቴ የበዛ ማነኝ ወገኖቼ?

//መልስ//፦ታውፋንያ ነው  የእመቤታችን ክብርት ሥጋዋን .....ነክቶ...

1⃣1⃣🖊ለድንግል ማርያም በክብር የሸለማት
በሥጋ ወደሙ ባርኮ ያከበራት
የታቦተ ጽዮን የግዮን መገኛ
የታሪክ የሃይማኖት የእውቀት መመዘኛ
በቅዱስ መጽሐፍ ስሟ ተዘርዝሯል
ስለ ቅድስናዋ በስፋት ተጽፏል።

//መልስ// ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት።
..
የኢ/ኦ/ተ/ቤተ/ን  ጥያቄና መልሶች የሚተላለፉበት ቻናል

saramareyama.89@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...