ማክሰኞ 27 ማርች 2018

ከአዳም የተላከ ጦማር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ እምምላክ አሜን

ከአዳም የተላከ ጦማር

ይድረስ ዛሬም ዘወትርም ውድቀቴን ለምትመኝልኝ  ከይሲ /ዲያቢሎስ                          ሰላምታ የእግዚአብሄር ነዉና ሰላምታየ ይድረስህ እያልሁ ስልጣንህን ከተቀማህበት ቀን አንስቶ እንደምን አለህ እኔ እንዳተ ሳይሆን እንደእግዚአብሄር ቸርነት አለሁኝ ምንም እንኳን እግዚአብሄር እኔን አስዉቦና አሰማምሮ በሰራት በገነት ቢያኖረኝም ቅናት የጀመርከዉ ገና በፈጣሪህ ላይ ነዉና የእኔ በገነት መኖር አስቀንቶህ መልዕክተኛህን ልከህ መርዝን አበላሀኝ ጸጋየን አስገፈፍሀኝ ከአምላኬ አራቅሀኝ ሀፍረትን ላክብኝ ክብሬን አሳጣሀኝ ብሎም ወደመሬት አስመጣሀኝ  በስጋየም ካንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን : በላብህ በወዝህ ጥረህ ግረህ ብላ: እሾህና አሜካላ ይብቀልብህ : አፈር ነህና ወደአፈር ትመለሳለህ : የምድርን ቡቃያ ትበላለህ በሚል በአምስት መርገም አስረገምከኝ ከገነት አስወጣሀኝ በነፍሴም የማይጠፋ እሳት: የማያንቀላፋ ትል : የማይገፉት ጨለማ : የንስር ክንፍ በሮ የማይጨርሰዉ ጥልቅ ጉድጓድና ዘላለማዊ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት አስወረረወርሀኝ ::  እኔ እንዳንተ ንስሀን አልጠለሁምና ምንም አንኳን መርዙን አብልተህ ሀጢአት ብሰራም የፈጠረኝ አምላክ አንዲሁ አልተወኝም ቃልኪዳኑ ሲደርስ ከእናቴ ተወልዶ በመስቀል ላይ በአምስት ችንካር ተቸንክሮ በአንተ ምክንያት የመጣብኝን ችግር አስወገደልኝ የነበረኝ በሙሉ ተመለሰልኝ ሀይሉንና የአንተን ድል መንሻ መስቀሉን ሰጠኝ  አሁን አንተን ምን ዋጠህ ?የትአለህ? መዉጊያህስ የት አለ ?ብቻህን መኖሩን ትፈልገዋለህና ወዳንተ እንዳልመጣ እየማልሁ የብቸኝነት ንሮ ይመችህ እልሃለሁ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አንተ ጥንት ጠላቴ ተስፋ የማትቆርጥ
እኔን ለማሳሳት ስንት ግዜ ነው ምትሮጥ
ወይ አለማወቅህ የሰውን ልጅ ክብሩን
እስከ መስቀል ሞቶ ካሳ የሆነውን
ተው ለጥቂቱ እድሜህ አታውራ በከንቱ
እኔን እንደሁ ምሮኛል ተወልዶ ከሴቲቱ
በቃ ተፈጸመ ዓመተ ኩነኔ
በደሙ መለሰኝ ወደ ቀድሞ ክብሬ
ከድንግል ተወልዶ ኢየሱስ መድኅኔ
ሰልጥነህብኝ ነበር በዓመተ ኩነኔ
ዛሬ ተመለሰ ያ የቀድሞው ግብሬ
ስልጣን አሥመኝተህ ሲኦል አስወረድህኝ
እድሞት ፈለገህ ህገን አስፈረስህኝ
አተም አትገባት እኔም ወጣሁኝ ከገነት
ገነትም ተዘጋች ማንም አይገባባት
በእግዚአብሔር አርያ የተፈጠርሁ ነኝ
የምድነበተን አምላክ ተስፋ ሰጠኝ
እንኳን በፍጡሩ በጌታህ የአመፅህ ነህ
አምላክነት ሽተህ ከከብረህ የወረድህ
አመታትም በቆይ በሲኦል ታስሬ
ጌታ መልሶኛል ወደቀደመው ክብሬ
ከገነት ስባርር ነግሮኝ ነበር ጌታ
በ5 ቀናት ተኩል እስሬን እደ ሚፈታ
ከንግዲህ መን በጀህ እስሬም ተፈታልኝ
እኔ እዳልሞት ወዶ ዘርን አስቀረልኝ
ከዚያች ጣፋጭ ገነት አዝኘ ስወጣ
አተ መስሎህ ነበር ዳግም የማልመጣ
እኔ በአተ ምክኒያት ንስሃ ገብቸ ሱባኤ ሥቆጥር
ዳግም መጠህብኝ ተጣልሁ ወደ ምድር
እኔ በአተ ምክኒያት ከምድር ብወድቅም
ንስሃ መግባቴን መቸም አላቆምም
 ሀሳብህ ለጊዜው ምንም ቢሳካልህ
እኔን ላአተ ማድረግ ፍፁም አይሆንለህ
ከአምላኬ ለየኸኝ ክብሬን አስገፈፍኸኝ
ቦታህን ስለ ያዝሁ  ነው ለካን ማትለቀኝ
የተስፋ ጭላጭል አምላኬ ሰጦኛል
ከእናቴ ተወልዶ ይህው አድኖኛል
ከንግዲህ በሲኦል በቻህን ኑርበት
በአምላኬ ድኛለሁ በደሙ ቤዛነት
እናቴን አየኋት በመስቀሉ ግርጌ
ጌታም ቀደደልኝ የዳውን ደብዳቤ
አተ ክፉ ከእይሲ  ትቢት የሞላብህ
ደብዳቤህ ውድቅ ሆነ እኔም ነፃ ወጣሁ
===================
 ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

1 አስተያየት:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...