ሰኞ 26 ማርች 2018

የምዕራፍ ሦስት/የ28ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/QDqw3rGvjhc

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፍስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✝

እነሆ የምዕራፍ ሦስት/የ28ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር👇


🖊ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣ማራናታ ማለት ምን ማለት ነው?ማስረጃ ከመጽሐፍ ቅዱስ???

//መልስ//፡- የአራማይክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም ጌታ ሆይ ቶሎ ና፡፡ 1ኛ ቆሮ.16÷22 ፣ ራዕ.


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪2⃣እግዚአብሔር አብርሃምን የጠራው ከምንድን ነው የተጠራውስ ከየትኛው ሃገር ነው???

//መልስ//፡- የተጠራው ከጣዖት አምልኮ ነው አገሩም ካራን/ ዑር/ ነው፡፡


🖊ጥ.ተራ ቁ3⃣↪ እግዚአብሔር ለሙሴ የተገለጠው በየት ነበር? ለቅዱስ ጳውሎስስ?

//መልስ///፡- ለሙሴ በሲና ፣ ለቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆና በአርዮስ ፋጎስ ነበር፡፡

.
 🖊ጥ..ተራ.ቁ.↪4⃣የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ተጽፈው ያለቁት እስከ ስንት ዓመተ ምህረት ድረስ ነው?

//መልስ//፡- የመጨረሻው የዮሐንስ ራእይ ሲሆን በ96 ዓ.ም.ተጽፎ እንዳለቀ ይነገራል፡፡

.🖊ጥ.ተራ.ቁጥር.↪5⃣ መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ስህተት መተርጎም የሚችለው ማን ብቻ ነው?

//መልስ//፡- መንፈስ ቅዱስ እራሱ ብቻ ነው፡፡


🖊 ጥ.ተራ.ቁ.↪6⃣ከ1365-1395 ይኖሩ የነበሩ የጌታ ቀኝ እጅ ያረፈበትን ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ  ያመጡት ንጉሥ ማን ይባላሉ??

//መልስ//፡- ዐፄ ዳዊት ይባላ፡፡

🖊ጥ.ተራ.ቁ↪7⃣የቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዝሙር የነበረና የተሰሎንቄን ውበት አይቶ ወደ ኋላ የተመለሰው ሰው ማን ነው?

//መልስ//፦ ዴማስ

🖊ጥ.ተራ.ቁ ↪8⃣ከ 14ቱ የጳውሎስ መልዕክታት ውስጥ ለግለሰቦች/ በግለሰቦች በኩል/ የተላኩትን ለይተህ አሳይ/ተናገር፡፡

//መልስ//፡- ሶስት ናቸው፡፡ ጢሞቲዎስ ፣ ቲቶ እና ፊልሞና፡፡


🖊ጥ.ተራቁ ↪9⃣.. መጽሐፈ ሳሙኤል 1ኛ እና 2ኛ ስናነብ ልናስታውሳቸው የሚገቡን ዋና ዋና ነጥቦች ምንድን ናቸው?

//መልስ//፡- ስለ ነቢዩ ሳሙኤል፣ ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት መማረክ፣ ስለ ንጉሥ ሳኦል እና ስለ ንጉሥ ዳዊት መቀባት…ወ.ዘ.ተ.፡፡


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣0⃣ ነቢዩ ዳዊት መናገሻ ከተማውን ያደረገው በየት ነበር? ሰባት ዓመት የገዛውስ የትኛውን ነገድ ነው?

//መልስ//፡- ኬብሮን ስትሆን ለሰባትአምመት የገዛው የይሁዳን ነገድ ነው፡፡

🖊ጥ.ተራ.ቁ  ↪1⃣1⃣ነቢዩ ዳዊት ከእግዚአብሔር የተሰጡት ሀብታት ስንት ናቸው?ዝርዝራቸው?  መዝሙሮችንስ ስንት  ደርሷል? በስንት የዜማ መሳሪያስ አመስግኗል??

//መልስ//፡- ሰባት ናቸው፡፡ 1. ሀብተ በገና 2. ሀብተ ትንቢት 3. ሀብተ ፈውስ 4. ሀብተ መውዕ/ሀይል/ 5. ሀብተ መንግሥት 6. ሀብተ ክህነት 7. ሀብተ ዝማሬ/መዝሙር/ ሲሆኑ መዝሙሮቹ 50 ናቸው፡፡ መሳሪያዎቹ ከበሮ ፣ በገና፣ መዝ. 149 እና መዝ.150


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣2⃣ ለነቢዩ ናታን እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ እንደተቀመጠ እይ ያለው ሰው ማን ነው? ለስንት ዓመትስ ነግሷል?

//መልስ//፡- ንጉሥ ዳዊት ሲሆን ለ40 ዓመት ነግሷል፡፡ 2ኛ ሳሙ.7÷1-2

🖊ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣3⃣ነቢዩ ዳንኤል ለጣኦት ከሚሰዋው ምግብ በልተን እንዳንረክስ አሥር ቀን ብቻ በጥራጥሬ ፈትነን ያለው ማንን ነው?

//መልስ//፡- ሜልዳር ይባላል፡፡ ት.ዳን.1÷12


🖊ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣4⃣ እናንተ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በሰይፌ ትገደላላችሁ ይህን ጥቅስ የት እናገኘዋለን?

//መልስ//፡- ት.ሶፎ 2÷12


🖊ጥ.ተራ.ቁ 1⃣5⃣በዳዊት ዘመን የነበረው የመዘምራን አለቃ ስሙ ማን ነበር?

//መልስ//፡- አሳፍ፡፡ 1ኛ ዜና 16÷5
2.


.. 🖊ጥ.ተራ ቁ↪1⃣6⃣ የምታመልኩትን ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን ያለው ሰው ማን ነው?

//መልስ//፡- ኢየሱ፡፡ ኢያ.24÷15


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣7⃣120 ቤተሰቦች በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው?

መልስ፡- 12 ሐዋርያት ፣ 72 አርድዕት ፣ እና 36 ቅዱሳት አንስት፡፡

 🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣8⃣እሴይ ከነቢዩ ዳዊት ጋር ስንት ልጆች ነበሩት? ነቢዩ ሳሙኤል መጀመሪያ ሊቀባው የነበረውስ የትኛውን ልጅ ነው? ሁለተኛውስ?

መልስ፡- 8 ናቸው፡፡ ሁለቱ ኤልያብ እና አሚናዳብ ናቸው፡፡ 1ኛ ሳሙ.16÷6

 🖊ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣9⃣ከሩት ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሉትን የዘር ሃረጎች ዘርዝር፡፡


መልስ፡- ሩትና ቦኤዝ፣ እሴይ፣ ዳዊት፣ሶሎሞን….ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ሩት 4÷21-22

🖊ጥ.ተራ ቁ ↪2⃣0⃣ነቢዩ ዳዊት የኦርዮን ሚስት ቤርሳቤን በመድፈሩ ከእግዚአብሔር ለተግሳጽ የተላከው ነቢይ ማን ነበር? ዳዊትስ ከዚያ በኋላ ምን አደረገ?

መልስ፡- ነቢዩ ናታን፡፡ሙሉ ታሪኩን 2ኛ ሳሙ.ምዕራፍ 11 እና 12 በሙሉ፡፡

.🖊ጥ.ተራ.ቁ↪2⃣1⃣ የነቢዩ ዳዊት ልጅ የአቤሴሎምን እህት የደፈረው ማን ነበር? አቤሴሎምስ የወሰደው እርምጃ ምን ነበር?


መልስ፡- አምኖን ሲሆን የተደፈረችው ትዕማር ትባላለች፡፡ አቤሴሎምም በንዴት አምኖንን ገድሎታል፡፡ 2ኛ ሰሙ.13÷1


🖊ጥ.ተራ.ቁ↪2⃣2⃣ሐዋርያት ጌታን አጭር ፀሎት አስተምረን አሉት እሱም አስተማራቸው ፡፡ ያስተማራቸው ፀሎት ምን ነበር?

መልስ፡- እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ፡-" አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር…ማቴ.6÷9"


🖊ጥ.ተራ ቁ↪2⃣3⃣ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል ብሎ የጠየቀው ማን ነው? ማንን? መልስ ሰጪውስ ማን ነበር?

መልስ፡- ጌታችን ነው፡፡ የጠየቀው ሐዋርያትን ነው፡፡ መላሹ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ መልሱም ˝ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ˝ ማቴ. 16÷13


 🖊ጥ.ተራ.ቁ↪የቅዱስ ማቴዎስ አባትና እናት ስማቸው ማን ነው? ለሐዋርያትነት
የተጠራውስ ከምን ነበር?

መልስ፡- አባቱ ዲቁ እናቱ ክሩትያስ ሲሆኑ ሥራው ቀራጭነት ነበር፡፡

የ28ኛዙር ጥያቄና መልስ ይህን ይመስላልን። ሚኮ ዘ.ኢትዮጵያን/miko zE Ethiopian እናመሰግናለን።

ወስብኃት ለእግዚአብሔር


በፁህፍ ለምትፈልጉ ለቴሌ ግራም ተጠቃሚዎች👇
ቴሌ ግራም👉https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA

ይቱብ👉https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...