2018 ሴፕቴምበር 23, እሑድ

መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
@Teyakaenamels
@Teyakaenamels

1ኛ) አምሥቱ(5) አዕማደ ምስጢር የሚባሉት ምን ምን ናቸው?  መልስ፦  ሚስጥረ ሥላሴ
ሚስጥረ ስጋዌ
ሚስጥረ ጥምቀት
ሚስጥረ ቁርባን
ሚስጥረ ትንሳኤ ሙታን ናቸው።
2ኛ) ቤተ ክርስቲያን ስንት ባህሪ አሏት? መልስ፦ቤተ ክርስቲያን  4 ባህሪ አሏት እነሱም 1ኛ፦ በመጀመርያ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ነች።
2ኛ፦ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ነች።
3ኛ፦ቤተክርስቲያን ኩሉውይት ነች።
4ኛ፦ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ነች ማለት ነው።
3ኛ) እናታችን ቅድስት አርሴማ  ሰይፍ  ከአረፈባተ በኋላ ለስንት ስዓት ቆመች? የናታችን የአርሴማ ሃገርስ የት ነው? መልስ፦ እናታችን ቅድስት አርሴማ ሰይፍ ከአረፈባት በኋላ ለ3 ስዓት ቁማለች ሃገሯ ደግሞ አርመንያ ነው።
4ኛ)  የእመቤታችን በዓላት ስንት ናቸው? መልስ፦  33 ናቸው።
5ኛ) ማርያም ፊደል የሚለውን ቃል የተናገሩት አባት ማን ናቸው (ማን) ይባላሉ? መልስ፦ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ናቸው።
6ኛ) ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስትና የተመለሰው ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርገት በኋላ በስንተኛው አመት ነው?  መልስ፦በ8ኛ አመቱ ነው።
7ኛ) መጽሐፍ ነገስት በስንት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል? መልስ፦በ3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል።
8ኛ) ዜና መዋል ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦ የእለት ዜና ማለት ነው።
9ኛ) ምናሴ ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦  ማስረሻ ማለት ነው።
10ኛ)መስፍን ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦  ፈራጅ፤ አስተዳዳሪ ማለት ነው።
11ኛ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዘንዶ አፍ ያዳናት ልጅ ስማ ማን ትባላለች? መልስ፦ ብሩክታይት ትባላለች።
12ኛ) አኬልዳማ ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦  የደም መሬት ማለት ነው።
13ኛ) ፃዲቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ በስንት አመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ? መልስ፦  በ480 ዓ.ም ነው።
14ኛ ከነአን የምን ምሳሌ ናት?መልስ፦የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት።
15ኛ) ላንች የማይገዛ ህዝብና መንግስት ይጠፋል። ይህን ሃይለ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኛዋለን? ምዕራፍና ቁጥሩን? መልስ፦ኢ.ሳ 60፥12 ላይ ነው።
16ኛ)በጨረቃ በከዋክብት ላይ ስልጣን የተሰጠው መላክ ማን ነው? መልስ፦ ቅዱስ ሩፋኤል ነው።
17ኛ) ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦ በሱርስት ቋንቋ መባ፤ስጦታ ማለት ነው።
18ኛ) ደስታ በስንት ይከፈላል? መልስ፦ ደስታ በሁለት(2) ይከፈላል መንፈሳዊ ደስታ እና ሥጋዊ ደስታ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

20 አስተያየቶች:

  1. በውነት ቃለህይወት ያሰማልን ጸጋ እግዚአብሔር። ይብዛላችሁ ኦርቶዶክስ። በመሆኔ ኮራሁ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. ቃለ ህይወትን ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችሁ አሜን

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. ከልብ እናመሠግናለን ቀጥሉበት

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  4. ቃለ ህይወት ያሰማልን ግን ቁጥር 16 ቅዱስ ዑራኤል አይደለም እንዴ ቅዱስ ሩፋኤል የሰውና የእንስሳ ማኅፀን የሚፈታ አይደም እንዴ አብራሩልኝ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  5. አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት የስማልን

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  6. እግዚአብሔር ያክብርልን ቀጥሉበት

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  7. ቃለሒወት ይሰማልን ፀጋዉን እግዚአብሔርያድላችሁ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  8. በ 40 እና 50 ቀን ሀዋሪያቶች ምን ስያደርጉ ነበር

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  9. ቃል ሂወት ያሰማልን ፀጋዉን ያብዛላችሁ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...