እሑድ 31 ዲሴምበር 2017

አስተርአያ ዘገብርኤል

https://youtu.be/zvVnxNe_iaI
*© አስተርአያ ዘገብርኤል*

/ዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ ፩/

አስተርአያ ገብርኤል ግብተ/፪/
ወእንዘ ትፈትል/፬/ ወርቀ ወሜላተ

አዝ…

ከአዳም ልጅ መካከል ከእነዳዊት ዘር
መርጦ ተወለደ ከድንግል በክብር
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
አዳምን ሊያድነው ስላየው ተራቁቶ

አዝ…

ሐር እየፈተለች ቤተ መቅደስ ሆና
ገብርኤል ነገራት ሰማያዊ ዜና
ትፀንሲ እያለ በድንቅ ሰላምታ
በትኅትና ሆኖ ሲታጠቅ ሲፈታ

አዝ…

ከክቡር ዙፋኑ ከመንበሩ ወርዶ
አዳነን ከፍዳ ከማርያም ተወልዶ
የነገሥታት ንጉሥ ቤዛ ኩሉ ዓለም
ሥጋዋን ለበሰ መድኃኔ ዓለም

አዝ…

ንጉሥ መወለዱን ሰብአ ሰገል ሰምተው
አምኃ አቀረቡ ከሩቅ ምሥራቅ መጥተው
የዳዊት ትንቢቱ ተፈጸመለት
የሳባ ነገሥታት ወርቅ አመጡለት/፪/

አዝ…saramareyama.890@gmail.com

ቅዳሜ 30 ዲሴምበር 2017

አበሰራት ገብርኤል አበሰራት

#አበሰርት #ገብርአኤል
 #አበሰራት #ብርሀነ #መለኮት #ባችያድራል #አላት (፪)

ሐር ከወርቅጋር....  አበሰርት ገብርኤል
አስማምታ ስትፈትል። ።።።።።።
ሰላም ላንች ይሁን። ።።።።።።።
አላት ገብርኤል። ።።።።።፡
ይህ እንዴት  ያለ። ።።።።።
ሰላምታ  ነው አለች። ።።።።።
ንግግሩን ሰምታ። ።።።።።
ድግል ተደነቀች።  ።።።።።
         አዝ
በፍጹም ትህትና። ።።።።።።
በጽድቅ አደበት። ።።።
የሰማዩ ስራ። ።።።።
ሰላምታ ሰጣት።  ።።።
ከጌታ መላኩን።   ።።።።
ሲነግራት ብስራት።   ።።።
ድግልም በመፍራት።  ።።።
ሀሳብም ያዛት።  ።።።።

     አዝ
እንደ ቃልህ ይሁን።  ።።።
ብላ ተቀበለች።  ።።።።
እኔ ለእግዚአብሔር። ።።።።
ባርያው ነኝ እያለች።   ።።።
ይህው ክርስቶስን።።።።።
ለኛ ሰታናለች።።።።።።
ጽዮንን እዳናይ።።።።
ጌታን ወልዳዋለች።።።
      አዝ
ጌታችን ሲወለድ  አበሰራሲ ገብርኤል
በቤተልሔም።።።።።
ለረኞች ተነግሮ።።።።።
አዩት በግርግም።።።።
ሰውና መላእክት።።።።።
ባድነት ዘመሩ።።።።።
ስብኃት ለእግዚአብሔር።።።።
ይድርሰው እያሉ። 
አበሰራት ገብርኤል (፪)

እልልልልልልልልልልልልልልልልልsaramareyama.890@gmail.com

ዓርብ 29 ዲሴምበር 2017

የገና ኮሌክሽን መዝሙሮች

በኤፍራታ ምድር
/////////////////
በኤፍራታ ምድር (በቤተልሔም(2×)
ጌታ ተወለደ (ከድንግልኮከብ ማርያም(2×))
ብርሃናዊው  (ከሰማይ ዝቅ አለ(2×)
ፍጥረትም ዘመረ (ሀሌሉያ እያለ(2×)

              መንጋውን በሌሊት ሲጠብቁ እረኞች
              ከሰማይም ሰሙ ታላቅ የምስራች
              በመላዕክቱ ግርማ ምድር ስታበራ
              የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ
አዝ.....
ድንገት በሰማይ ሰራዊት ተገልጠው
በአንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋቤተልሔም
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሰላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሰው

አዝ.....
                ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሳለሙት
                 ከእናቱ ጋር ሆኖ በግርግም አገኙት
                የመላዕክትን ዜና እረኞች አወሩ
                በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ

አዝ......
ለህዝብ ሁሉ ሚሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈልጉት
እርሱ ነው ለሰዎች የድህነት ምልክት

በኤፍራታ ምድር (በቤተልሔም(2×)
ጌታ ተወለደ (ከድንግል ማርያም(2×))
ብርሃናዊው ኮከብ (ከሰማይ ዝቅ አለ(2×)
ፍጥረትም ዘመረ (ሀሌሉያ እያለ(2×)

//////////////////////////

በጎል በጎል ሰባ ሰገል (2)
     በጎል በጎል ሰባ ሰገል (2)
  በጎል ሰባ ሰገል ሰገዱ ሎቱ (2)

ፀሐይ ፀሐይ ፀሐይ ሰርቀ (2)
ፀሐይ ሰርቀ ክርስቶስ ተጠምቀ (2)
.
አ.ዝ....
አንቺ ዮርዳኖስ ምንኛ ታደልሽ (2)
የእግዚአብሔር መንፍስ ከላይ ውርዶብሽ(2)
የአለም መዳኚት ተጠመቀብሽ (2)

አ....ዝ....

ድንግል ማርያም የሰጠሽው ፍሬ (2)
ህዝቦቹን ለማዳን ተጠመቀ ዛሬ

አ..ዝ....

ድንግል ማርያም ንጽይት ቅድስት
የጌታዬ እናት ምስጋና ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ አንቺን መርጦሻል

አ....ዝ..

እልል እልል ደስ ይበለን (2)
ወንድ ልጅ ተዎልዶ ናጻ አወጣን (2)
ዮሐንስ አጥምቆ ድል አገኛን (2)

እልልልልል
///////////////////////

ተወለደ ጌታ ተወለደልጅ
ተወለደ አምላክ ተወለደ

አ..ዝ...

አንዲት ብላቴና የአሥራ አምስት ዓመት
ጌታን ወለደችው በመላዕክት አዋጅ
በፍጹም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ

አ..ዝ
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋህዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ

አ..ዝ...

ፍጹም ድንግልና ክብር የተሞላች
እንደምን አምላክን በማህጸን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ

አ...ዝ..

አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
ከምድር ተፈልጎ እንደ አንቺ አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንጹህ ስለሆነች
ለአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች

አ..ዝ..

ፍጹም ድንግልና ክብር የተሞላች
እንደምን አምላክን በማህጸን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ

///////////////////////

" በኤፍራታ
በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ------ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ------ሆ
በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ------ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ------ሆ
 
   /////////////////////////

#ተወልደናሆ እም ድንግል/4/
ሲነገር ነበረ በነብያት አፍ    ተወልደናሆ እም ድንግል
ባንዱ በእግዚአብሔር ባንዱ በመንፈስ    ,,,       ,,,
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሀይ እንዲወጣ       ,,,       ,,,
የናፈቅነው ንጉስ ስጋ ለብሶ መጣ            ,,,       ,,,

          #ተወልደናሆ እም ድንግል/2/
አብርሀም ያንን ቀን ለማየት ናፈቀ  ተወልደናሆ እም ድንግል
ዳዊት በኤፍራታ ልደቱን አወቀ               ,,,      ,,,
ኢሣያስ ከድንግል ሲወለድ አየና             ,,,      ,,,
ትንቢት ተናገረ ምልክት አለና                 ,,,      ,,,

        #ተወልደናሆ እም ድንግል/2/
ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል ሲባል   ተወልደናሆ እም ድንግል
ሠማይ ሆነችለት እናቱ ድንግል              ,,,      ,,,
በህዝቡ መካከል ሆኖ የሚያበራ           ,,,      ,,,
በርሱ ፈራረሠ የጨለማውድንግል ስራ             ,,,      ,,,

      #ተወልደናሆ እም ድንግል/2/
ከእረኞች ጋራ ቤተልሔም ግቡ  ተወልደናሆ እም
ከነገስታቱ ጋር አምሀን አቅርቡ             ,,,       ,,,
እንስገድ ለህፃኑ ይገባዋልና                ,,,        ,,,
አለቅነት ስልጣን በጫንቃው ነውና      ,,,        ,,,
         ======✞,,
//////////////////////////
ተወለደ ጌታ ተወለደ ጌታ
ይሁን ደስታ በበረት ተወለደ ጌታ
የአለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ
ሰላም ሰፈነልን በምድር ደስታ
      አ..ዝ..
            እስይ የምስራች ለእግዚአብሔር ክብር
           ለስው በጎ ፍቃድ ሰላም በምድር
           ነብያት የፃፉት ትንቢቱ ሊፍፅም
           ከድንግል ተወልዶ አገኘነው ግርግም
          የሰማይ መላእክት አመሰገኑት
          ስለተወለደ የአለም መዳሀኒት
ላዳም የገባውን ቃል ኪዳን አፀና
ቃሉን አከበረ አብ ልጁን ላከና
ሰማይ እና ምድር ባንድነት ተስማሙ
ሰውና መላእክት ለጌታ ዘመሩ
   
            ሰባት ስግድ መጡ በኮከብ ተመርተው
           ለጌታ ሊስግዱ ከምስራቅ ተነስተው
          ህፃኑን ከናቱ ከማርይም ጋር አዩት
           ወድቀው ስገዱለት ለአለም መድሀኒት

ለክብሩ ያመጡትን ሳጥኑን ከፈቱ
ላምላክ አቀረብ ወርቁን ለመንግስቱ
እጣኑን ለክህነት ከርቤን ሰለሞቱ

          መንጋቸውን ነጥቀው ሲጠብቁ ለሉት
        በዳዊት ከተማ ተውልዳል መኑኒት
        በብርሀን ሰሙና የመላኩን ብስራት
       መጡ ለምስጋና ልደቱን ለማየት
 
ምስጋና ይገባል ለጌታ ልደት
ታርቀዋልና ሰውና መላእክት
ቅዱሳን መላእክት ዘመሩለት
አድረው ቀደሱ ካህናት ለሌት
እኛም ቆመናል በቅዳሴው
የጌታን ልደት ልንዘክረው

      በኢትየጵያ ምድር ይሁን ስባት
      እልልልልልልልልልል እንበል ለጌታ ልደት
      እንበል የጌታ ፍቃድ ይሁን
     ደግም ላመቱ ሰላም ይድርሰን

እልልልልልልልልልልል

///////////////////////

ወስብኃት ለእግዚአብሔር

ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር
አሜን ይቆየን...saramareyama.890@gmail.com

ሐሙስ 28 ዲሴምበር 2017

የምዕራፍ ሁለት/የ20ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁልኝ??
......ሰላማችሁ ይብዛ እያልኩ እነሆ የምዕራፍ ሁለትን የ20ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ መረሀ ግብር እንዲህ ይቀርባል....
።።።።።።።።።።።።።።።።

✍✅ጥ ተራ ቁ.↪1⃣ ሰብአ ሰገል ማለት ምን ማለት ነው??? ሰባ ሰገል ወርቅ፤ ዕጣን፤ ከርቤ፤ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመገበራቸው ምስጢር ምንድነው??  አንደምታውን በዝርዝር አስረዳ???

//መልስ//👉ሰብአ ሰገል ማለት፦ በአጭሩ የጥበብ ሰዋች ማለት ነው።
👉ሰብአ ሰገል ወርቅ ዕጣን ከርቤ መገበራቸው #ወርቅ ለንግስናው አንድም በፊት ይህንን የምንገብርላቸው ቀድሞ ፍጡራን ኋላም ሀላፊያን ናቸው አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርክ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ አንድም ወርቅ ፅሩይ ነው አንተም ፅሩይ ባህሪ ነህ ሲሉ #ዕጣን ለዘላለማዊ ክህነቱ አንድም በፊት ይህንን  ቀድሞ ፍጡራን ኋላም ሀላፊያን ናቸው አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርክ ኋላም የማታልፍ ነህ ሲሉ አንድም ዕጣን ምዑዝ ነው የምንገብርላቸውአንተም ምዑዘ ባህሪ ነህ ሲሉ #ከርቤ ለሞቱ አንድም ምንም እንኳን ቀድሞም ያልተፈጠርክ ኋላም የማታልፍ ብትሆን በለበስከው ሥጋ  ሲሉ አንድም ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል የተለያየውን አንድ ያደርጋል አንተም ከመላእክት የተለየውን አዳምን አንድ ትሞታለህታደርጋለህ ሲሉ ገብረውለታል

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪2⃣ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የጌታችን ልደት የተረዳባቸው ምክንያቶች  ምን ምን ናቸው???

//መልስ//👉ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የጌታን ልደት ያወቀበት ወይም የተረዳበት ምልክቶች  (1ኛ)ፍርሀተ ኖሎት ወይም የእረኞች ፍርሀት (2ኛ)የመላእክትን ምስጋና በሰማ ጊዜ (3ኛ)የሰብአ ሰገል መምጣትና መገበር (4ኛ)ደማቅ ኮከብ መታየት (5ኛ)የጌትነቱ ወይም የአምላክነቱ ብርሃን ናቸው።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪3⃣ አስቀድሞ ካህን የነበረ ነገር ግን የሰማዕታትን መከራ በማየት የእምነታቸውን ጥናትና ጌታችንም እነርሱን ሲፈውሳቸው ተመልእክቶ ልቦናውን ወደቀናች እምነት መልሶ በጌታችን ያመነ በኋላም እንደ ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሰማዕትነትን የተቀበለ ቅዱስ አባት ማን ይባላል??

//መልስ//👉ሉኪያኖስ ይባላል።


✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪4⃣ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መላአኩ ስንት  ጊዜ አበሰራት ??

//መልስ//👉3 ጊዜ አበሰራት
👉ውሃ ስትቀዳ፤ ወደ ቤተ መቅደስ ስትገባ እና ወደ ዮሴፍ ቤት ስትገባ

👉አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ( ሉቃ ፩  ÷፳፮ _፴፰

👉 እግዚአብሔር ከአንችቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ( ማቴ ፩÷፲፰ _፳፭) 1÷18-25)

✍✅ጥ.ተራ.ቁ. ↪5⃣ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሥላሴ አንድነት የሚያስረዱን ምዕራፍና  ቁጥሮች ጥቀስ/ሽ??

//መልስ//👉እግዚአብሔር አለ፤ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር (ዘፍ 1፥26)

👉 አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ( ዘፍ 3፥23)

👉 ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚህ እንደባልቀው (ዘፍ 11፥7)

👉ዮሐንስ 10፥30 እኔና አብ አንድነንይልላል ሌሌችንም ጥቅሶች መትቀስ ይላልቻ።

✍✅ ጥ.ተራ.ቁ.↪6⃣አንደበታችን የድንግልን ስራ ያመሰግናል ያለው ቅዱስ አባት ማን ይባላል???

//መልስ//👉ቅዱስ ኤፍሬም ነው።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪7⃣እግዚአብሔር አምላክህን በፍፁም ልብህ በፍፁም ነፍስህ በፍፁም ኃይልህ ውደድ።
 ይህ ኃይለ ቃል በየትኛው  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል  ይገኛል ?  ምዕራፍና ቁጥሩስ??

//መልስ//👉ዘዳግም (6፥4-6)
👉ማር (12፥30)
👉ሉቃስ(10፥27)

✍✅ ጥ.ተራ.ቁ.↪8⃣ገድል ማለት ምን ማለት ነው ?


//መልስ//👉ገድል ማለት፦ ተጋደለ ከሚል የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ተጋደል፣ ተዋጋ ፣ታገለ፣ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ከዓለም ጋር በሥጋ ከዓለማውያን ነገስታት ጋር.. ከዲያብሎስ ጋር  መዋጋት ወዘ..ተ ማለት ነው ።

✍✅ጥ. ተራ.ቁ.↪9⃣የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማስረጃ ጥቀስ/ሽ???
//መልስ//👉ዮሐንስ (2 ፥3)
ሉቃስ (1፥28--1፥48)
መዝሙር (45፥9)
ኢሳያስ (62 ፣2)

ወ.ዘተ..

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣0⃣ እስራኤላውያን ከግብጽ ሲወጡ  በግብፅ ላይ  የተከሰተውን መቅሰፍትን  ዘርዝሩ ???

መልስ 👉ውሃው ወደ ደም ተለወጠ
👉እንቆራሪቶች
👉ቅማል
👉 የእንስሳት እልቂት
👉 በረዶ
👉 የአንበጣ መንጋ
👉 ጨለማ
👉በቁስል መመታት።
👉የግብፃውያ  የበኩር ልጆች እልቂት ወ.ዘተ የመሳሰሉት።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣1⃣በአዲስ ኪዳን ታቦትና ፅላት በማን ይመሰላል???

//መልስ// 👉 ታቦት፦ እመቤታችን ድንግል ማርያም የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማደርያ ሆናለችና  በታቦት እንመስላታለን።
ፅላት፣ በአምላካችን በመድኃኔታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰላል።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣2⃣ በዕለተ ምጽአት ሰዎች ለፍርድ በሚቆሙ ጊዜ ጻድቃን በምን ፣ ኃጥአን ደግሞ በምን ይመሰላሉ? ምዕራፍና ቁጥሩስ?

//መልስ//👉 ጻድቃን በበግ ኃጥአን በፍየል ይመሰላሉ፡፡ ማቲ(.27÷34)


✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣3⃣ በሥርዓተ ቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ ምስባክ ይሰብካል ለመሆኑ ምስባኩ ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው?

//መልስ//፡- ከመዝሙረ  ዳዊት ነው።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ↪1⃣4⃣አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በጸሎት ብዛት እግራቸው ተቆርጦ ሰባት ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው የጸለዩበት ቦታ የት ነው?

//መልስ//፡- ደብረ አስቦ/ ደብረ ሊባኖስ አካባቢ/

✍✅ጥ.ተራ.ቀ.↪1⃣5⃣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት እና የጸለየችበት ቦታ የት ነው??

//መልስ//፡-በጎለጎታ በጌታ መቃብር ላይ ነው፡፡ / የካቲት 16/

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣6⃣በ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መጽሐፈ ሶስናና ተረፈ ዳንኤል ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል  ጋር ቆጠራሉ?

//መልስ//👉ከትንቢተ ዳንኤል ጋር በአንድ ይቆጠራል።


✍✅ጥ.ተራቁ.↪1⃣7⃣ የሰው ልጅ ዕድሜ 70 ቢበዛ 80 ከዚያ ያለፈ ድካምና መከራ ነው ብሎ የተናገረው ማን ነው??

//መልስ//👉ነቢዩ ዳዊት/የሰውመዝሙረ 89፥9-10)


✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪1⃣8⃣ እግዚአብሔር ለአዳም ፣ ለአብርሃም ፣ ለኖህ የገባላቸው ቃል ኪዳን ምን ነበር??

//መልስ//፡- 👉ለአዳም፦ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው፡፡
👉ለአብርሃም፡- የሚባርኩህን እባርካለው ……
👉ለኖህ፦ ከአሁን በኋላ በንፍር ውሃ አላጠፋችሁም፡፡

✍✅ጥ.ተራ.ቁ..↪1⃣9⃣ኢየሱስ ፣ አማኑኤል ፣ ክርስቶስ እና መድኃኔዓለም የስማአቸውን ትርጉም አስረዳ/ጂ/.??

//መልስ//👉፦-

#ኢየሱስ፡- ኢየሱስ ማለት አዳኝ  ማለት ነው፡፡ ይህ ስሙ ቅድመ ዓለም በአብ ኅሊና ታስቦ ይኖር እንደነበር
መልክአ ኢየሱስ ይመሰክራል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መድኃኒትእመቤታችንን ሲያበሥራት “ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ”
ብሏታል፡፡ ሉቃ. 1÷"1፡፡ እመቤታችንና ዮሴፍ ጌታ በስምንት ቀኑ ወደ ቤተ ግዝረት ሲገባ በመልአኩ እንደ ተነገራቸው ኢየሱስ ብለው ጠሩት፡፡ ሉቃ. 2÷21፡፡ ከአምልኮ ጸሎት ፈውስና አገልግሎት የሚከናወነው በዚህ በስሙ ነው፡፡ ይህ ስም የባሕታዊያን የተመስጦ ማዕከል የማኅሌታዊያን የዜማቸው ጣዕም የሰባክያን የአትሮንሳቸው ግርማ ሞገስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከዚህ ስም ውጭ ውበት ደምግባት የላትም፡
 #ክርስቶስ፡- ክርስቶስ ማለት የተቀባ መሲህ ማለት ነው፡፡ አይሁድ የጠበቁት መሲህ ነቢያትና ጻድቃን ሊያዩት የናፈቁትጌታ የነፍስ ነጻ አውጪ ስለሆነ ክርስቶስ አሉት፡፡ ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ከእግዚአብሔር ተወልዷል፡፡ 1ዮሐ. 5÷1፡፡
 #አማኑኤል፡- አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ ኢሳ. 7÷14፡፡የተዋረደውን አዳምን ለማክበር ጌታ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጥቷል፡፡እርሱ አምላካችን የእኛን ሥጋና ደም ስለተካፈለ ከእኛ ጋራ ሆነ“አማኑኤል” ተብሏል፡፡ ማቴ. 1÷23፡፡
#መድኃኔአለም፡- መድኃኔዓለም ማለት የዓለም መድኃኒት ማለት ነው፡፡ አብ ልጁን የላከው የዓለም መድኃኒት እንዲሆንነው፡፡ 1ዮሐ. 4÷14፡፡ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን አዳነ፡፡ እኛም እንደ ሰማርያ ሰዎች መድኃኔዓለም አልነው የሁላችንም መድኃኒት ነውና፡፡ ዮሐ. 4÷42፡፡

 #የሰው_ልጅ፡- የሰውን ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች ለማድረግ ሰው ስለሆነ፡፡ ዮሐ. 6÷63፡፡
 #የእግዚአብሔር_ልጅ፡- የአብ የባሕርይ ልጅ ስለሆነ አባቱን በመልክ ስለሚመስልና በክብር ስለሚተካከል በዚህ ስምተጠራ፡፡ 1ዮሐ. 5÷5፡፡



✍✅ጥ.ተራ.ቁ.↪2⃣0⃣ሚከተሉትን የስም ትርጉሞችን አስረዳ/ጂ/?? ዘሩባቤል ፣ ቤቴል ፣ እና መሪባ፡፡??

//መልስ//መልስ፡- 👉ዘሩባቤል ማለት የባቢሎን ዘር ማለት ነው።
 👉ቤቴል ማለት የእግዚአክርክርብሔር ቤት ማለት ነው።
👉መሪባ ማለት፦ ክርክር፣ጥላቻ ማለት ነው፡፡1ኛ.ዜና 3÷16-19 ፣ ዘፍ.28÷19 ፣ ዘጸ.17÷1-7 እናገኘልለን።

የ20ኛው ዙር ጥቄና መልስ ይህን ይመስላል ከስተቴ ታርሙኝ ዘንድም በትህትና እጠይቃለሁ?..

ወስብሐት  ለእግዚአብሔርsaramareyama.890gmail.com

አፊያ ሁሴን ክፍል 10

#አፊያ #ሁሴን ክፍል 10

ፀሀፊ #ማርያማዊት ገብረ መድህን

አንባቢ #ገብረ ሚካኤል

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፲)

ከአንድ ሳምንት በኋላ ሁመይድ ደወለና አንድ ካፌ ውስጥ ቀጠረኝ፡፡ ሰርፕራይዝም አለሽ በማለት አጣደፈኝ፡፡ ብቻዬን እንድመጣም ለመነኝ፡፡ በቦታው ስደርስ ለብቻዬ እንድመጣ የወተወተኝ ብቻችንን ነፃ ሆነን ለማውራት እንዲመቸንና የያዘው ርዕስም ሌላ ሰው ማወቅ እንደማይገባው ስላመነ መሆኑን ሊያስረዳኝ ብዙ ጣረ፡፡ ሰርፕራይዝ ያለውና ሌላ ሰው እንዳይሰማው የፈለገው ነገር ባለፈው "እንድረዳሽ ፍቀጅልኝ" ብሎኝ የተስማማሁትንና አባቴ ቤተሰቤ ላይ እየፈጠረ ስላለው ችግር ነው፡፡ ፊት ለፊቴ ሆኖ አይን አይኔን እያየ "ከሐጂ ጋር በነገርሽኝ ነገር ላይ ተነጋግረን ነበር፡፡ እናም የቡና ላኪ ድርጅቱን ሃላፊነትና ውክልና ለፋይሰል ሊመልሱለት ተስማምተናል" አለኝ፡፡ በጣም ተደንቄ "እውነት...?!" አልኩት መዳፌን እየዘረጋሁለት፡፡ "really" አለ እኔ ባወጣሁት ዜማና መዳፌን በመሐላ መልክ እየመታ፡፡ በሰበቡም እጄን በእጆቹ ይዞ እያፍተለተለ ቆየ፡፡ "ያው ታውቂያለሽ ከሐጂ ጋር ቢዝነስ ፓርትነር ነን፡፡ ስለሆነም ቤት ያልተለመደ ፀባይ ማሳየታቸውንና የፋይሰልንም ሃላፊነት እንደነጠቁት ገልጬ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየኳቸው፡፡ እርሳቸውም መንስኤው አንቺ እንደሆንሽና ቤተሰቡ በጠቅላላ አድማ እንዳረጋችሁባቸው በከፍተኛ ንዴት ገለፁልኝ፡፡ እኔም ችግሮች በውይይት መፈታት እንዳለባቸውና በተለይ ነገሩን ከቢዝነስ አንፃር ስናየው ፋይሰል ብዙ ልምድ ካካበተበት ሥራው ማንሳት ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለው ቆይቶም ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ነገርኳቸው፡፡ ሥራን በእልህና በስሜት ለማስኬድ መሞከር በዘመናዊ የቢዝነስ አመራር ዘዴ ለውድቀት እንደሚዳርግ አስጠንቅቄ አሳሰብኳቸው፡፡ ያንቺንም ችግር በተመለከተ ከፈቀዱልኝ እኔም የመፍትሔው አካል በመሆን ላግዝ እንደምችል ገለፅኩላቸው፡፡ ከዚያ ትክክል እንደተናገርኩ አረጋግጠውልኝ የፋይሰልን ሥራና ሃላፊነት በቅርቡ እንደሚመልሱለት ቃል ገቡልኝ፡፡ አንቺንም የተሻለ ተግባቦት ካላችሁ እስቲ እባክህ ምከርልኝ ሲሉ አደራ ብለውኛል" አለና ፈገግ አለ፡፡

አባቴ እንዲህ በቀላሉና በፍጥነት ሃሳቡን የማለሳለሱ ነገር ከፍተኛ አግራሞት ፈጠረብኝ፡፡ በእርግጥ ለሁመይድ ትልቅ አክብሮት እንዳለው አጠያያቂ አይደለም፡፡ ቢሆንም ይህን ያህል በፍጥነት ውሳኔውን ይቀይራል ብዬ አልጠበኩም ነበር፡፡ ምናልባት የቡናው ንግድ አሳስቦቶ ይሆን? ስል አሰብኩ፡፡ ፋይሰል በዚህ ሥራ ላይ ብዙ ጊዜ በማሳለፉ ከፍተኛ ልምድ አካብቷል፡፡ ከሥራው ጋር የተያያዙና ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ሰዎችንም ያውቃል፡፡ የአባቴ ውሳኔ እልህ የወለደው እንደሆነ ገብቶት ነው ወይስ ሁመይድ ሲያናግረው ይሉኝታ ይዞት...? ለማንኛውም ለእኔ እጅግ በጣም ያሳሰበኝ የፋይሰል ሁኔታ ነበርና ይህንኑ ዜና ልነግረው ቸኩያለሁ፡፡ ይህን መሰሉን ነገር ፀጥ ብዬ እያብሰለሰልኩ እያለሁ ፊቴ የተቀመጠው ሁመይድ "ኤፊ ይህን ነገር ግን ለማንም አትንገሪ... ሐጂ በራሳቸው ተነሳሽነት ነገሩን እንዳስተካከሉት እንዲሰማቸው እፈልጋለሁ" አለኝ፡፡ ሃሳቡ ቢገባኝም እኔ ደግሞ ለፋይሰል የተፈጠረውን ችግር እንደማስተካክለው ቃሌ ገብቼለት ስለነበር ይህንኑ በስሱም ቢሆን ብነግረው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ስለሆነም ለሁመይድ ችግሩ ሁሉ የተፈጠረው በእኔ ምክንያት መሆኑን እየደጋገምኩና እያስረገጥኩ ከተናገርኩ በኋላ አያይዤም "ለፋይሰል ሁኔታዎችን እኔ ራሴ እንደማስተካክለው ቃል ገብቼለታለሁ" አልኩት፡፡ "so..?" አለኝ መቀመጫው ላይ እየተመቻቸ፡፡ "ስለዚህ የአባቴን ሃሳቡን የመቀየር ዜና ልነግረው እፈልግ ነበር...አንተን ቅር ካላለህ" አልኩት አተኩሬ እያየሁት፡፡ "እሺ..." አለ እየተኩመሸመሸ፡፡ ሁኔታውን ሳየው "ይህ ሰው በእርግጥ ከእኔ ፍቅር ይዞታል እንዴ?" ስል በሃሳቤ ራሴን ጠየኩ፡፡ አያይዞም "እሺ ኤፊ ነገሩ ምስጢር ቢሆን እመርጥ ነበር፣ አንቺ ካልሽ ግን ለሌላ ሰው እንዳያወራና ምንም እንዳላወቀ እንዲያስመስል አስጠንቅቀሽው ንገሪው፡፡ ሐጂ ከአንቺ ጋር ተነጋግሬ ጉዳዩን እንዳነሳሁባቸው ባያውቁ የተሻለ ነው" አለ፡፡ እኔም "ትክክል ነህ ሁመይድ... እኔም እንደዚያ ነው የማስበው" አልኩት፡፡

ሁመይድ ጥቂት በሃሳብ እንደመዋጥ ካረገው በኋላ "ኤፊ..እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?" አለ ፊቱ ላይ የሆነ የሥጋት ገፅታ እየታየበት፡፡ "ምን..?" አልኩት ቀልጠፍ ብዬ፡፡ በፍጥነት ፈገግታው ጠፍቶ መልኩ እንደ መወየብ ስላረገው በውስጤ እየገረመኝ ነበር፡፡ እንዳቀረቀረ "ለፋይሰል ችግሩን እንደምታስተካክዪው ቃል የገባሽለት በምን መንገድ ለማስተካከል አስበሽ ነው? ሌላ የማስተካከያ ዘዴ ነበረሽ?" ሲል ጠየቀኝ፡፡ ጥያቄውን እንደሰማሁ ሳቄ ተናነቀኝ፡፡ ምስኪን ሁመይድ የወንድሜንና የቤተሰቤን ችግር ከማይ የአባቴን ፈቃድ ፈፅሜ እርሱ ያመጣልኝን ባል ለማግባት የምስማማ መስሎታል፡፡ ወይም ደግሞ ሌላ የተለየ መንገድ ኖሮኝ የፎከርኩ መስሎት ነው ሥጋት በውስጡ የገባው፡፡ እንደምንም ያፈነኝን ሳቅ ተቆጣጥሬና ኮስተር ብዬ "የለኝም" አልኩት፡፡ ቀና ብሎ በጥርጣሬ ሲመለከተኝ "በእውነት ሌላ መንገድ አልነበረኝም፣ አንተን ተማምኜ ነው" አልኩት፡፡ ፊቱ ከደመና መሐል በምትወጣ ጸሐይ ምክንያት ብሩህነትን በቅጽበት እንደምትላበስ የምድር ገጽ እዚያው በዚያው ሲፈካ ሳየው ሳላስበው ፈገግ አልኩ፡፡ "really..? ትተማመኝብኛለሽ ኤፊ? በእኔ ትተማመኛለሽ?" አለ እንደመቆምም እንደመቀመጥም እያረገው፡፡ ያለ አንዳች ሃፍረት እየተፍለቀለቀ፣ እጄን እየሳመና እየተቁነጠነጠ የሚሆነውን ሲያሳጣው እኔ በሃፍረት ተሸማቅቄ ላልቅ ደረስኩ፡፡ የእርሱ ሁኔታ ካፌው ውስጥ ያሉትን ሰዎች ትኩረት በመሳቡ ወደ ግራ ወደ ቀኝ መዞር እንኳ አፈርኩ፡፡ ከሥንት መቁነጥነጥ በኋላ ተረጋጋና "ይህን ቃል ከአንቺ በመስማቴ የተሰማኝን ደስታ ልደብቅ አልችልም...ለምን ሌላ ቦታ ሄደን በቆንጆ ራት አናከብረውም?" አለኝ፡፡ ወደ ቤት ቶሎ መመለስ እንዳለብኝ ገልጬ የራት ግብዣው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍልኝ ጠየኩ፡፡ እርሱም "በእኔ ላይ ያለሽን እምነት እንድትጨምሪ እለምናለሁ፡፡ ከዚህም ለበለጠ ነገር ለመታመን ዝግጁ ነኝ" አለና ተያይዘን ወጣን፡፡ ወደ ቤት ከመግባቴ በፊት ስላደረገልኝ ነገር ልባዊ ምስጋናዬን አቅርቤ ተሰነባበትን፡፡

ነገሮች በዚህ ሁኔታ እያሉ ጥቂት ቀናት አለፉ፡፡ ለወንድሜ ፋይሰል ለሁመይድ ያለውን ችግር እንደነገርኩትና እርሱም አባቴን በማናገርና በመምከር የእርሱን ሥራና ሃላፊነት እንዲመልስለት እንዳሳመነው ነገርኩት፡፡ ይሁን እንጂ ወንድሜ በጸጥታ ካዳመጠኝ በኋላ ክፉም ደግም ሳይናገር ሄደ፡፡ አተኩረው ሲያዩኝ የነበሩ ዓይኖቹ ውስጥ በውስጡ የሚመላለሰውን ሃሳብ ለማግኘት አዕምሮዬን አስጨነኩት፡፡ ነገር ግን የተጨበጠና ወጥ የሆነ ሃሳብ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ታላቄ እንደመሆኑ መጠን የቤተሰቡን ችግር ለመፍታት ከአቅሜ በላይ የሆነ ሸክም ተሸክሜ መንገላታቴን አይቶ ያዘነልኝ መስሎ ተሰምቶኛል፡፡ በአባቴ በቀለኛ አካሄድ ያለልክ በመበሳጨቱ የነጠቀውን ሥራ መልሶ ቢሰጠውም ባይሰጠውም የማይበርደውም የማይሞቀውም የሚመስል ዓይነ ውሃም አይቼበታለሁ፡፡ በቤተሰብ ጉዳይ የሁመይድ ጣልቃ መግባትና የእርሱ እርዳታ ማስፈለጉም ከክብር አንፃር ምቾት ያልፈጠረለትም ይመስላል፡፡ ምናልባትም ይህን ችግር ለመፍታት ስል እኔ ይዤ የኖርኩትን ክብርና ኩራት እንዳላጣም ሰግቶ ይሆናል፡፡ ብቻ ምንም ይሁን አንዳች ሳይተነፍስ ሄደ፡፡ ዝምታው ትንሽ ቢያስጨንቀኝም እንዲህ ያለው የወንዶች እልህ ተፈጥሯዊ መሆኑን በማሰብ ራሴን አሳመንኩት ወይም ሸነገልኩት፡፡ ከሁመይድ ጋር ካወራን ከአንድ ሳምንት በኋላ አጠር ላለ የሥራ ጉዳይ ነው ብሎ ወደ እንግሊዝ ተጓዘ፡፡ እርሱ በሄደ በአሥረኛው ቀን አካባቢ አባቴ የቡናውን ንግድ ድርጅት ውክልና ሞልቶ መጥቶ እንዲፈርምና ሃላፊነቱንም እንዲረከብ ለፋይሰል ደውሎ ነገረው፡፡ ወንድሜ ክፉኛ አንገራግሮ የነበረ ቢሆንም በእኔና በእናቴ ግፊትና ልመና ጭምር ሄዶ ፈረመ፡፡ ሃላፊነቱንም መልሶ ተረከበ፡፡

ሁመይድ እንግሊዝ ሀገር ሳለ ሌላ ጊዜ አርጎት በማያውቀው ሁኔታ በየቀኑ ይደውልልኛል፡፡ የለንደንንና ሌሎች የእንግሊዝ ከተሞችን በወፍ በረር ያስቃኘኛል፡፡ እዚያ ስለሚገኙ ታሪካዊ ሥፍራዎች፣ ሙዚየሞች፣ አርት ጋለሪዎች፣ ሐውልቶች፣ ቤተ መጻሕፍቶችና ሌሎች መስህቦች ገለፃ ያደርግልኛል፡፡ አያይዞም እኔ ፈቃደኛ ከሆንኩ ምንም ዓይነት ምትክ ውለታ ሳይጠይቅ እንግሊዝንና ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮችን እንደሚያስጎበኘኝ እየደጋገመ ከመሐላ ጋር ይነግረኛል፡፡ በአንፃሩ አባቴ ደግሞ ለፋይሰል ሥራውን ከመለሰለት በኋላ በዚያው ኩርፊያው ቀጥሏል፡፡ ጥቂት የተሻሻለው ከፋይሰል ጋር የነበረው ግንኙነት ብቻ ነው፡፡ የሥራ ጉዳይ የግድ ስለሚያገናኛቸው በጥቂቱም ቢሆን ያወራሉ፡፡ እንደ ወትሮው ቤት የመምጣቱን ነገር ካቋረጠ በኋላ ይህን ነገር ሳያሻሽል መቆየቱ ሁልጊዜ ያሳስበኛል፡፡ በሳምንት አንዴ ብቅ ይልና እየተጎማለለ ግቢው ውስጥ ይዟዟራል፡፡ በትንሽ በትልቁ እናቴ ላይ ይጮሃል፡፡ በገዛ እጁ ከሚፈቀር አባት ወደሚፈራ ንጉሥ ራሱን ስለቀየረ የቤቱ ሰው ሁሉ በተቻለው መጠን ከእርሱ ለመራቅ ይጥራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በድፍረት ላናግረውና በእኔ ምክንያት ቤተሰቡን ሁሉ ማወክ እንደሌለበት ነግሬው ከፈለክ እኔን የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ ልለው አስባለሁ፡፡ ነገር ግን መልሼ ይህ ስሜታዊነት ነው ብዬ እተወዋለሁ፡፡ የጀመርኩትን ስልታዊ አካሄድም ማበላሸት መስሎ ይሰማኛል፡፡ ብቻ በአዕምሮዬ "ይህ ነገር ማብቂያው የት ይሆን?" እያልኩ ፍፃሜው ይናፍቀኛል፡፡ በዚህ ሁሉ የሃሳብ እንግልት ሰንብቼ ለጥቂት ቀናት ብሎ ወደ እንግሊዝ ሄዶ የነበረው ሁመይድ ከ40 ቀናት በኋላ ተመልሶ መጣ፡፡ ከአንድ ሳምንት የእንግሊዝ ቆይታው በኋላ ወደ ዱባይ ጎራ ብሎ በፍጥነት እንደሚመለስ በስልክ የነገረኝ ቢሆንም እዚያ ከወር በላይ መቆየቱ ትንሽ ግርታ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ እርሱ ግን እዚያም በርካታ ሥራዎች ስለቆዩት እንደዘገየ ነገረኝ፡፡ 

ከዚህ ሰው ጋር ያለኝ ግንኙነት ወደሆነ ምዕራፍ እየተሸጋገረ እንደሆነ በውስጤ ይታወቀኛል፡፡ በየቀኑ ማለት በሚቻል መልኩ አብረን ሻይ መጠጣት፣ ምሳ መብላትና አንዳንድ ሥፍራዎች መታየት አዘወተርን፡፡ እኔም የዚህን ሰው ሁኔታ ለማጥናት አስቤ ራሴን በመጠኑ ለቀቅ አደረኩት፡፡ በጣም የሚደንቀው አባቴ ወደ ውጭ ወጣ ወጣ ማለቴ መረጃ እንደሚኖረው የታወቀ ቢሆንም ምንም ያለማለቱ ነው፡፡ ሁመይድ ለአባቴ "ከፈቀዱልኝ የመፍትሄው አካል እሆናለሁ" ሲል እንደነገረው የነገረኝና እርሱም "ከሰማችህ እባክህ ምከርልኝ" ያለውን ተግባራዊ እያደረገው መስሎት ይሆን? ብዬ አሰብኩ፡፡ "ድንቄም ምክር እቴ" ስል ሁኔታው ላይ ለመዘባበት ሞከርኩ፡፡ ያም ሆኖ ከዚህ ክልስ ሰው ጋር የጀመርኩት ወጣ ገባ የት እንደሚያደርሰኝ ለመገመት እየጣርኩ ነበር፡፡ ከእማማ አፀደ ጋር በሁኔታው ልንፀልይበትና ልናስብበት የወሰድነው ጊዜ በራሳችን ግምት የተጠናቀቀ ሲመስል ቁጭ ብለን አውርተናል፡፡ እማማ አፀደም "እንግዲህ ልጄ በምንችለው አቅም ፀልየናል፣ ለእያንዳንዱ ነገር የራዕይ ወይም የሕልም ምሪት መጠበቅ የእምነት መጉደል ምልክት ነው፡፡ ምናልባት ወደ ስህተት የመምራት ዕድልም ይኖረዋል፡፡ በሕሊናሽ የተለየ መላ ካልተከሰተልሽ በያዝሽው መንገድ ወስኖ መቀጠሉ ተመራጭ ነው፡፡ እኔም ቢሆን የመውጫው መንገድ ይኸው ብቻ ነው መስሎ የተሰማኝ፡፡ ደግሞ አይዞሽ...አነሰም በዛም በነገሩ ላይ ፀለይንበት አይደል እንዴ? ጸሎት ማለት ራስንና ነገሮችን ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት ማለት ነው እኮ" ብለውኛል፡፡ ሁመይድ የገባልኝን የነፃነት ቃል በየጊዜው በብዙ እርግጠኝነት የሚደግመው ቢሆንም እንኳ በምስክር ፊት የሚያረጋግጥበትን አንድ የጋራ ሥልት ነደፍን፡፡ የእማማ አፀደ ሴት ልጅና የእኔም አብሮ አደግ የሆነችው ሄለንንም የስትራቴጂያችን አካል አደረግናት፡፡

ከሁመይድ ጋር ጊዜ ባሳለፍን ቁጥር እኔን በእጁ የማድረግ ፍላጎቱ ጣራ ነካ ማለቱ ይቀላል፡፡ የዘወትር ውትወታው እንድንጋባ ነው፡፡ ለሐጂም እኔ እሺ ሳልለው አንዳች ነገር እንደማይተነፍስ እየደጋገመ ይነግረኛል፡፡ ይህ አባባሉ ሁልጊዜ ትርጉም አልባ ቢሆንብኝም እንደ ዋዛ ግን እሰማው ነበር፡፡ ለተደጋጋሚው የጋብቻ ጥያቄው ከዚህ በፊት የነገርኩትን ወገብ የሚቆርጥ መልስ አሁን አልሰጠውም፡፡ ይልቁንም ለበርካታ ቀናት እሺም እምቢም ሳልል አብሬው እታይ ነበር፡፡ ወደ በኋላ ላይ "ወንዶች ስትባሉ ጠብ እርግፋችሁ የምትፈልጉትን በእጃችሁ እስክታስገቡ ድረስ ነው" እለው ጀመር፡፡ እንዲህ ስለው እሺ ለማለት ጫፍ የደረስኩ ነገር ግን በእርሱ ላይ እምነት የማጣቴ ነገር ትልቅ እንቅፋት የሆነ እየመሰለው ከብዙ መሃላ ጋር የቃል ኪዳን መዓት ይገባል፡፡ ከተደራረበብኝ ችግር በተጨማሪ በዋናነት ልቤን በከፊልም ቢሆን እንድከፍት ያደረገኝ እሰጥሻለሁ ያለኝ የሕሊና ነፃነት ነው፡፡ ይህንኑ ነገርም እያስረገጠ ይነግረኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ከእማማ አፀደና ከሄለን ጋር በተነጋገርነው መሰረት ከጓደኛዬ ጋር ላስተዋውቅህ ብዬ አንድ እሑድ ረፋድ ቀጠርኩት፡፡ ይህን ማድረጌ ለእርሱ የድል አጥቢያ እንደሆነ ስለተሰማው ያለልክ ፈነጠዘ፡፡ ብሥራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት በረንዳ ላይ ከሄለን ጋር ጠበቅነው፡፡ እርሱም በሰዓቱ ሲከንፍ መጣና ተቀላቅሎን ቁርስ እየበላን ስንጫወት ቆየን፡፡ ለሄለን እየሳቅሁና ነገሩን ለማዛት እየጣርኩ "ይኸውልሽ ጓደኛዬ ይህ ሰውዬ ካላገባሁሽ እያለ መቆሚያ መቀመጫ ነስቶኛል" አልኳት፡፡ እርሷም እኛ ቤት ሲመላለስና እኔ ጸበል ሳለሁ በተደጋጋሚ እንዳስተዋለችው ነገረችው፡፡ እርሱም ብድግ ብሎ በአክብሮት እጇን ከጨበጠ በኋላ ተቀመጠና ስለ ራሱ አንዳንድ ነገር ማውራት ቀጠለ፡፡ በመሐል ላይ ሄለን ወደ ውጭ ስታይ ቆየችና "እናቴ...እናቴ ያቻትና" ይቅርታ በመጠየቅ ደረጃውን ተንደርድራ ወርዳ ሄደች፡፡ ዓይናችን እርሷን ሲከተል እማማ አፀደ ከሁለት ሴቶች ጋር ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ ነበር፡፡ እኔም ከመቀመጫዬ እየተነሳሁ "እማማ አፀደ ናቸው፣ ታውቃቸዋለህ አይደል?... ያስታመሙኝ ሴቲዮ" አልኩት ለማስታወስ እንዲረዳው፡፡ "እህ...!" አለ አንገቱን በአዎንታ እየነቀነቀ፡፡ ወደርሳቸው መንገድ ስጀምር "ይዘሻቸው ነይ...ቁርስ ይብሉ" አለ፡፡ መንገዱ ዳር እንደቆሙ ተቀላቀልኳቸውና ጥቂት አውርተን እያመነቱና በግድ በሚመስል መልክ ከሰዎቹ ነጥለን ወሰድናቸው፡፡ ሁመይድ ብድግ ብሎ በአክብሮት ተቀበላቸው፡፡ በፍጥነትም ከበረንዳው ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብተን ተቀመጥን፡፡

እማማ አፀደ ከተላበሱት ግርማ ሞገስ በተጨማሪ ጨዋታ አዋቂም ናቸው፡፡ በራሳቸው ለዛና ዘይቤም ስለ እምነታቸው ሲመሰክሩ በጣም ያስገርማሉ፡፡ እርሱ በደንብ እንደሚያውቃቸው ሁሉ ለመስተንግዶ ተሽቆጠቆጠ፡፡ የቀረበላቸውን ቁርስ እንደነገሩ ቀማምሰው ሲያበቁ ስለ እኔ ከልጅነት ጊዜ አንስተው  የነበረኝን ቁጥብነት፣ አሁን በቤታችን የተፈጠረውን ችግር ከወጣነትና ዘመኑ ከፈጠረው ተፅዕኖ ጋር እያያያዙ አወጉ፡፡ እግረ መንገድም ከልጃቸው ከሄለን የማይለዩኝ ልጃቸው እንደሆንኩ አፅንኦት ሰጥተው ተናገሩ፡፡ እኔም በመሐል ለእማማ አፀደ ሁመይድ ካልተጋባን ብሎ ወጥሮ እንደያዘኝ ነገርኳቸው፡፡ እርሳቸው በእኔ ሕይወት ውስጥ ጉልህ ተፅዕኖ ካላቸው ጥቂት ሰዎች አንዷ ናቸው፡፡ በብዙ ነገር የሚተማመኑባቸው፣ ለእያንዳንዱ ችግር የሆነ መላ የማያጡ ዓይነትም ናቸው፡፡ የሁመይድን ጥያቄ ከነገርኳቸው በኋላ "እናንተ ወጣቶቹ እኛ አሮጊቶች ምንም የማናውቅና የማናስተውል ይመስላችኋል እንጂ በጥቂት እይታና በትንሽ መረጃ ወደ እውነታ የሚጠጋ ድምዳሜ ሰጭዎች ነን፡፡ ነገር ግን ይህን ብስለት እኛ ዕድሜ ላይ ሳትደርሱ በፍፁም አታውቁትም" ብለው እንቅስቃሴያችን ወደዚያ እንደሚያመራ ጠርጥረው እንደነበር ነገሩን፡፡ አያይዘውም ፈጣሪ ሃሳባችንን እንዲባርክልን ደጋግመው መረቁን፡፡ ከምርቃታቸው በኋላ በዘዴና በለዘብታ ቃል ጥያቄ አነሱ፡፡ "እሺ...ለቁም ነገር መብቃት ትልቅ ፀጋና ክብር ነው፡፡ ሆኖም በምን መልክ ነው ያሰባችሁት?? ከቤተሰብ ጋርስ ተማክራችኋል? ይቺ ልጅ ያሳለፈችውን መከራና በቤቷ ያለውንም ችግር ታውቃለህ አይደል?? በምን መልኩ ነው ጉዳያችሁን ልትፈፅሙ ያሰባችሁት??" አሉት ሁመይድን በሚመረምር አይኖቻቸው እያስተዋሉት፡፡

ሁመይድ የእማማ አፀደን ጥያቄ ለመመለስ ተርበተበተ፡፡ አይኖቻቸውን ሽሽትም እንደ ዓይናፋር ልጃገረድ አንዴ ወደ ሰማይ አንዴ ወደ ምድር ዓይኖቹን አቅበዘበዘ፡፡ ነገረ ሥራው ብሽቅ አደረገኝና በጠረጴዛው ሥር እግሬን ሰድጄ በጫማዬ ቅልጥሙ ላይ አቀመስኩት፡፡ እንደመባነን አለና ተንተባተበ፡፡ ሄለን ሁኔታው አስገርሟት ሳቋ ሊያመልጣት ሲል በዘዴ ጎንበስ ብላ እግሯን በማሸት ፊቷን ለመደበቅ ሞከረች፡፡ የእርሷን ሁኔታ አይቼ እኔም ሳቅ አፈነኝና ፈገግ እያልኩ "ሁመይድ የእማማ አፀደ ጥያቄ አልገባህም መሰለኝ" አልኩት፡፡ "አይ... አዎ... ምንድነው? መጀመሪያ እኮ እርሷ ገና ፈቃደኛ መሆኗን አልነገረችኝም እማማ" አለ እጁን ወደ እኔ እየጠቆመ፡፡ ሁኔታው ክስ የሚያቀርብ ከመምሰሉም በላይ በጭንቀት ፈገግ ለማለት ሲሞክር የውሸት ፈገግታው ፊቱ ላይ ደስ የማይል ገጽታ ይፈጥራል፡፡ እማማ አፀደ የሁመይድ ጭንቀት ስለገባቸው በዕድሜና በሕይወት ልምድ ያካባቱትን ጥበብ ተጠቅመው የተፈጠረውን ደስ የማይል ድባብ በፍጥነት ቀየሩት፡፡ እሳቸው ወጣት እያሉ የነበረውን የትዳር አመሰራረት፣ የሽምግልና አላላክ፣ የእጮኛ አመራረጥ እየተረኩ፣ የገጠሟቸውን አስቂኝ ገጠመኞች እያወሩ በሳቅ አፈረሱን፡፡ ሁመይድ በሁኔታው ፍፁም ተለወጠና ዘና አለ፡፡ ከዚያ በኋላ ማንም ሳይኮረኩረው እኔ እሺ ብዬ ላግባው እንጂ የሚያደርግልኝን ነገር፣ የሚወስደኝን ቦታ፣ የሚሰጠኝን ሥጦታ፣ የሚጠብቅልኝን የሃይማኖትና የህሊና ነፃነት እየማለና እየተገዘተ በዝርዝር ተናገረ፡፡ እንዲያውም እማማ አፀደን "እርስዎ እናቴ ነዎት፣ ትልቅ ሰውም ነዎት፣ በእርስዎ ፊት ያልኩትን ሁሉ ልፈፅም ቃል እገባለሁ" እስከማለት ደረሰ፡፡ የዚያን ዕለት ፕሮግራም ባቀድነው መልክ ከተጠናቀቀ በኋላ ሁመይድ እየፈነጠዘ በቅርብ ርቀት ወደሚገኘው ሰፈራችን አድርሶን ሄደ፡፡ እማማ አፀደ ቤት ገብተን ከሄለን ጋር በአንዳንድ ሁኔታዎች ስንሳሳቅ ቆየንና በመሐል ላይ ሄለን "ባልሽ ደስ የሚል ሰው ነው፣ በተለይ እንደ ሕጻን ልጅ ሲያፍር ያዝናናል... ከዚሁ ጋር ግን የአይኖቹን መቅበዝበዝ ሲያዩት ሌባ ያስመስለዋል" ብላ ከት ብላ ሳቀች፡፡ እኔም "አንቺ ባሌን እንዴት ነው የምትናገሪው?" ብዬ ለሳቅ ባጎነበሰችበት ጀርባዋን ደለቅኳት፡፡ እርሷ ግን ይባስ በሳቅ መንከትከት ጀመረች፡፡ ንግግሯን የሰሙት እማማ አፀደም "አንቺ ሹል አፍ ምኑን ነው የምትቀባጥሪው?" ብለው ሲጠጓት እየሳቀች ሮጣ አመለጠች፡፡ እማማ አፀደ እያቀፉኝ "ልጄ ሁሉን ፈፃሚው መድኃኔዓለም ነው፡፡ ለምናልባቱም ግን በእኛ ፊት ቃሉን መስጠቱ ደግ ነው" ብለው በብዙ ምርቃት አሰናበቱኝ፡፡

ከዚያ ቀን ጀምሮ ሁመይድ እርሱን ለማግባት እንደተስማማሁና የእሺታ ቃሌን እንደሰጠሁት ቆጠረ፡፡ እውነት ለመናገር እኔም ቀጣዮቹን የአካሄድና የቅደም ተከተል ጉዳዮች ማሰብ ጀምሬያለሁ፡፡ ስለሆነም መጀመሪያ ለፋይሰል ቀጥሎም ለእናቴ ለመንገር ወሰንኩኝ፡፡ ከአሁን በኋላ የነብር ጅራት እንደያዝኩ ዓይነት ራሴን አሳምኜ ቁርጠኛና የውሳኔ ሰው ለመሆን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ፋይሰልን ከቤት ውጭ አንድ ካፌ ቁጭ አድርጌ ያለውን ሁኔታና የደረስኩበትን ውሳኔ ነገርኩት፡፡ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ፀጥ ብሎ ሲሰማኝ ቆየና ምንም ሳይናገር ዝም አለ፡፡ "ወንድሜ አንድ ነገር አትለኝም እንዴ?" ብዬ ጠየኩት፡፡ በመስኮት ማዶ ማዶውን እያየ "ምን ልበልሽ? እኔ ያንቺን ውሳኔ አከብራለሁ፣ ደስተኛ እንድትሆኚ ብቻ ነው የምፈልገው" አለ፡፡ ገጽታው ላይና ዓይኖቹ ውስጥ ግን ግልፅ ቅሬታ ይነበብ ነበር፡፡ የተሸነፍኩ፣ የቤተሰቡን ሰላም ለመጠበቅና ከጥቃት ለመከላከል ስል ከአቋሜ የተንሸራተትኩ አድርጎ በማሰብ ያዘነልኝ ይመስላል፡፡ የወንድሜን አለኝታነትና አሁን ስለ እኔ ሲል ነፍሱን ማስጨነቁን አስቤ ድንገት ኤንባዬ ዝርግፍ አለብኝ፡፡ ማልቀሴን ሲመለከት አጠገቤ መጥቶ ሊያባብለኝ ብዙ ደከመ፡፡ እየደጋገመ "ደስተኛ እንድትሆኚ ብቻ ነው የምፈልገው" ይለኛል፡፡ የሚመለከቱን ሰዎች በአንዳች ነገር ያልተግባባን ፍቅረኛሞች እንጂ ወንድምና እህት አልመሰልናቸውም ነበር፡፡ ይህንኑ ነገር ለእናቴ ስነግራትም ተመሳሳይ ቅሬታ ተመልክቼ መደነቅ ጀመርሁ፡፡ ተስፋ በመቁረጥና አባቴን በማማረር ስሜት "እስቲ እንግዲህ አግቢላቸውና ይረፉት፣ ከዚያ ደግሞ በምን ሰበብ እንደሚነታረኩ እናያለን" አለች፡፡ ከሁሉ ያስገረመኝ ግን የሰዓዳ ነው፡፡ ግዴለሽ ከሚመስል ተፈጥሮዋና ለሁመይድ ካላት ቅርበት የተነሳ ዜናውን በደስታ ትቀበላዋለች ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ እያሳሳቅሁ "ሁመይድን እኮ ላገባው ነው" ስላት ዱብ ዕዳ የወረደባት ይመስል ክው ብላ ቀረች፡፡ ከመፍለቅለቅ ሙዷ ተስፈንጥራ ወጥታና ኮስተር ብላ "ምን..?" ብላ ስትጠይቀኝ በዕድሜዋ ላይ በአንድ ጊዜ 20 ዓመት ጨምራ ታየችኝ፡፡ "አንቺ ክርስቲያን አይደለሽ እንዴ? እንዴት ሙስሊም ታገቢያለሽ?"  አለችኝ፡፡ ረጋ ብዬና ደቂቃዎች ወስጄ ላስረዳት ብሞክር እንኳ በፍፁም ሊገባላት አልቻለም፡፡ "ያ ሁሉ ችግር ለዚሁ ነበር?" ብላ በሚታዘቡ የልጅነት ዓይኖቿ ስትመለከተኝ የምገባበት አሳጣችኝ፡፡ "እንጃ የምትዪው ነገር ምንም አልተዋጠልኝም" ብላ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች፡፡

ክፍሌ ገብቼ መራራ ለቅሶ አለቀስኩ፡፡ ባሳየሁት ጽናትና በፈፀምኩት ተጋድሎ በቤተሰቤ ዘንድ አትርፌው የነበረውን ሞገስ በአንድ ጊዜ ያጣሁት መስሎ ተሰማኝ፡፡ "የእኔ እንባ መቼ ይሆን የሚያቆመው?" እያልኩ ስነፈርቅ አመሸሁ፡፡ የደረስኩበትን ውሳኔ እንደገና ለመመርመር እስክከጅል ድረስ ውስጤ ተነዋወጠ፡፡ ሌሊቱን እንቅልፍ አጥቼ አድሬ ነጋ አልነጋ በማለት በማለዳ እማማ አፀደ ጋር ሄድኩ፡፡ ቤተክርስቲያን መሄዳቸውን ስሰማ ደፍሬ ብሥራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሄድኩ፡፡ እዚያው ስፀልይ ቆይቼ ሲወጡ ተገናኘንና መጠለያ ውስጥ ብዙ ደቂቃ ተቀመጥን፡፡ ከቤተሰቦቼ ያገኘሁትን ምላሽና የፈጠረብኝን አሉታዊ ስሜት እያለቀስኩ ነገርኳቸው፡፡ ውሳኔዬ ልክ መሆኑን መጠራጠር ሁሉ መጀመሬንም አልደበኳቸውም፡፡ እርሳቸው ግን ከእንዲህ ያለ ውሳኔ ጀርባ የተለያዩ ተግዳሮቶች መኖራቸው የተለመደ መሆኑን እየጠቀሱ ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ነገሩኝ፡፡ "በእርግጥ የሰው ልጅ ባህሪ ጀግና ወዳድና አድናቂ ከመሆኑም በላይ ያ ጀግና ጥራቱም ጽናቱም እንዳይቀንስ በብርቱ የሚመኝ ነው፡፡ ነገር ግን የእርሱን ጽዋ ለመቅመስ የሚፈልግ በባትሪም ተፈልጎ አይገኝ፡፡ አሁን አንድ ጊዜ ወስነሽ ከአፍሽ የወጣ ነገር ሆኗል፣ ወደ ኋላ መመለስ ደግ አይደለም፡፡ በዚያ ላይ ሁነኛ መፍትሄ ሳያመላክቱ ግፊ በርቺ ማለት ብቻውን የአንቺንም ሰብዐዊነት ግምት ውስጥ ያለመክተት ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ሁሉን ነገር ለመድኃኔዓለም ሰጥተናል፡፡ እርሱ እንደሚያበጀው በፍፁም ልብሽ እመኚ፡፡ ከብዙ ለቅሶ በኋላ ነው ሳቅና ደስታ የሚገኘው" ሲሉ መከሩኝ፡፡ እማማ አፀደ ሀኪሜ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ከእርሳቸው ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ እንደገና ሁሉን ነገር ለጌታ ሰጥቼ ወደፊት ብቻ መሄድ እንዳለብኝ ይሰማኝ ጀመር፡፡

ሁመይድ እንደገና ለጥቂት ቀናት ከሀገር ወጥቶ ቆየና ተመልሶ መጣ፡፡ ያን ጊዜ "ኤፊ አሁን ነገሩን ለሐጂ ብነግራቸው ምን ይመስልሻል?" ሲል እየተለማመጠ ጠየቀኝ፡፡ እኔም በአጭሩ "ንገረው" አልኩት፡፡ ያልሰማ ይመስል "እ..." አለኝ፡፡ "ንገረው..ከዚያ የሚልህን ትነግረኛለህ" አልኩት፡፡ የእርካታ ስሜት እየተነበበበት "አመሰግናለሁ ኤፊ" አለኝ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደ ሕጻን ልጅ አኩርፎ መጣና "ሐጂ እርሷ ካላረጋገጠችልኝ አላምንህም...እርሷ እንሆነ እኔን ያለማሳፈር ሥራ የላትም፡፡ ሽማግሌ ተልኮ ሲያበቃ ደግማ ታዋርደኝ እንዴ?" አሉኝ አለና ተከዘ፡፡ "ችግር የለውም...ሄጄ አረጋግጥለታለሁ" አልኩና ብድግ አልኩ፡፡ "የት ልትሄጂ ነው?" አለኝ በተቀመጠበት አሻቅቦ እያየኝ፡፡ "እርሱ ቢሮ እሄዳለሁ" አልኩት፡፡ "ቆይ ላድርስሽ" ሲል "በፍፁም በታክሲ ነው የምሄደው" ብዬ አዋክቤው ወጣንና ኮንትራት ታክሲ ይዤ ሱማሌ ተራ አካባቢ ወደሚገኘው ቢሮው አመራሁ፡፡ በከፍተኛ እልህና ወኔ ተሞልቼ ወደ አንድ ዓይነት ግጥሚያ የምሄድ ዓይነት ስሜት እየ ቢሮው ያሉት ሰራተኞችን ከሞላ ጎደል ያውቁኛል፡፡ ስለሆነም በቀጥታ ቢሮው ገባሁና ፊት ለፊቱ ቆምኩ፡፡ መነጽሩን ሰክቶ ከሚያየው ፋይል ቀና ብሎ ሲያየኝ ዓይኑን ማመን አቃተው መሰል መነጽሩን አውልቆ በግርምት አስተዋለኝ፡፡

                         (ይቀጥላል)

     ---------- ማርያማዊት ገብረመድኅን ----------saramareyama.890@gmail.com

አፊያ ሁሴን ክፍል ፱

#አፊያ ሁሴን ክፍል 9

#ፀሀፊ ማርያማዊት ገብረ መድህን

አፊያ ሁሴን (ክፍል ፱)
saramareyama.890@gmail.com
ሁመይድ የመላው ቤተሰብ ወዳጅና ቤተኛ ከሆነ ሰንበት ቢልም ከእኔ ጋር ለየት ያለ ቅርበት እንዳለው ሰራተኞቹ ሳይቀር ያስተዋሉ መሆናቸውን ከመልዕክቷ ተረዳን፡፡ ሆኖም መውጣት ስላልፈለኩ ፋይሰልን "ሂድ አጫውተው ራሷን አሟት ተኝታለች በለው" ብዬ ላኩት፡፡ መጀመሪያ ፋይሰል፣ ከዚያ ሰዓዳ ሄዱ፡፡ ከተኛሁ በኋላ ሰዓዳ መጥታ ከአንቺ ጋር ነው የምተኛው ብላ ምኑንም ምኑንም ስትለፈልፍ አመሸች፡፡ እንግዲህ በእርሷ ቤት እየጠበቀችኝ ነው ማለት ነው፡፡ ያን ሳምንት እንዲሁ ሲጠነቀቁኝና ሲፈሩኝ ሰነበቱ፡፡ እናቴ ወደ ሱቅ እንኳን ወጣ ለማለት በተነሳሁ ቁጥር "እባክሽ ልጄ ልጄ..እባክሽ የእኔ እናት.. እዚሁ ቁጭ በዪልኝ፣ የትም ቢሆን ሰራተኞቹን ላኪያቸው" እያለች ትለማመጠኛለች፡፡ እኔም የምችለው እርሷን ነውና "ሰው እኮ ነኝ፣ የቤቱ ውስጥ ዕቃ አረግሽኝ እንዴ? አየር ያስፈልገኛል፣ መንቀሳቀስ ያስፈልገኛል፣ ይሄ የእናንተ ቪላ ለእኔ መኖሪያ ቤቴ ነው ወይስ እስር ቤቴ ነው?" እያልኩ እጮህባታለሁ፡፡ የቱንም ያህል ብናገራት የእናቴን ልመና ረግጬ አልወጣም፡፡ እየተነጫነጭሁ መልሼ ቁጭ እላለሁ፡፡ ለአባቴ "ወይ ጥያችሁ እጠፋለሁ፣ አሊያ ራሴን አጠፋለሁ" ብላ በስንት ልመና በስንት ግልግል ነው የተረጋጋችው ተብሎ ተነግሮታል መሰለኝ ወደ ቤት በመጣ ቁጥር መኖሬን ጠይቆ ያረጋግጣል እንጂ ከእኔ ጋር መገናኘቱን አይፈልገውም ነበር፡፡ እኔም በርቀትም ቢሆን ባየሁትና ድምፁን በሰማሁ ቁጥር "ልጄ መሆኗን እጠራጠራለሁ" ያለው ነገር ትዝ እያለኝ እንደ አዲስ እናደዳለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ያሳየኝ የነበረው የአባትነት ፍቅር ሁሉ ለማስመሰል ያደረገው ሽንገላ እየመሰለኝ በክፉ ሃሳብ እናጣለሁ፡፡ ሽማግሌዎቹ የተቀጠሩበት ቀን እየቀረበ ሲመጣ አባቴ ሃሳቤን ቀይሬ እንደሆነና ረጋ ብለውም ሊያሳምኑኝ እንዲጥሩ እናቴ፣ እህቴና ፋይሰል ላይ ጫና ማድረጉን ተያያዘው፡፡ እነርሱ ደግሞ እኔን ከመናገር እርሱኑ መጋፈጥ የተሻለ እንደሆነ የቆጠሩበት ሳምንት ነበር፡፡ አንድ ቀን እንደውም ከፋይሰል ጋር ኃይለ ቃል እስከመነጋገር ደረሱ፡፡ ወንድሜ አባቴን ከዚህ በላይ ሊያስጨንቀኝ እንደማይገባ ሲነግረው በጄ ስላላለው "አንተ ብዙ ሴት ልጆች ስላሉህ የአንዷ መጨነቅ አልተሰማህ ይሆናል፡፡ እኔ ግን እህቴን እፈልጋታለሁ" ሲል አምርሮ ተናገረው፡፡ በዚህ የተበሳጨው አባቴ ልክ አድማ የተደረገበት ያህል መላ ቤተሰቡን አኮረፈ፡፡

ሽማግሌዎቹ እሑድ ሊመጡ ሐሙስ ከሰዐት ሾልኬ ወጣሁና ቤተክርስቲያን ቆይቼ ማምሻውን እህቴ ቤት ሄድኩኝ፡፡ ትንሽ ሲራበሹ ከቆዩ በኋላ እህቴ ደውላ እርሷ ጋር እንደሆነች ነገረቻቸው፡፡ እስከ እሑድ እዚያው እንደምቆይ ተናግሬ ይህንኑም ለእናቴ በስልክ አስረዳኋት፡፡ እርሷም "እሺ የእኔ ልጅ እንዲያውም እዚያ ብትሆኚ ይሻላል" አለችኝ፡፡ የእሑዱ ሽምግልና ቀዝቀዛ ድባብ እንደወረሰው መጠናቀቁን ሰማሁ፡፡ አባቴም "እነዚህ ሽማግሌዎች ምስክሮቼ ናቸው፣ በዱላም በምክርም በልመናም አልሸነፍም አለች፡፡ እንግዲህ ምን አድርግ ትሉኛላችሁ?...ልጄን አልገላት ነገር" በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሽምግልናው በአሉታ ከተደመደመ በኋላ ሽማግሌ የላከው መምህር "ድሮም ሐጂ ራሳቸው ልጄን ከካፊር ወጥመድ አድንልኝ፣ አግባትና እያስተማርክ ቀስ ብለህ ታቃናታለህ፡፡ እኔ ራሴ ድል አድርጌ ደግሼ እድራችኋለው ብለውኝ እንጂ በሃሳቤም አልነበረች" እያለ ማስወራቱ ተሰማ፡፡ ይህን የሰሙ ቤተሰቦቼ በአባቴ ተግባር አንጀታቸው ቢያርም ደፍሮ የተናገረው ግን አልነበረም፡፡ ለእኔ ግን "ልጄ መሆኗን እጠራጠራለሁ" ካለው ንግግሩ በተጨማሪ ይህን ድርጊቱን ስሰማ ይበልጥ እጠላውና እፈራው ጀመር፡፡ ፍላጎቱን ለመፈፀም አሁንም እንዳልተኛልኝና ማንኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለስ እንደ አዲስ ተገነዘብኩ፡፡

የሽምግልናው ዕለት ሁመይድ ሰዓዳን ይዟት መጣና ምሳ ካልጋበዝኳችሁ ብሎ ተያይዘን ወጣን፡፡ ስለ ሁሉ ነገር በቂ መረጃ የነበረው ሁመይድ "አንቺ ብትደብቂኝም ሁሉን ነገር ሰማሁት" ብሎ ወቀሳ መሳይ ነገር አቀረበ፡፡ "ይህ ምን ተብሎ ይነገራል?" አልኩና "ከየት ሰማህ? ሰዓዳ ናት የነገረችህ?" ብዬ ጠየኩት፡፡ እርሱ ግን "ምን ይሄ የተሰወረ ነገር ነው እንዴ? ሁሉ የሚያወራው አይደል...ዛሬ ራሱ ሽማግሌዎች ስምሽን በእምቢታ ሲያነሱ ብቻሽን ሆነሽ ስቅ ከሚልሽ እኔና ሰዓዳ እናዳብርሽ ብለን ነው የመጣነው" አለና "አይደል እንዴ ሰዓዳ..?" እያለ እርሷን መኮርኮርና አዎንታዋን መፈለግ ጀመረ፡፡ ሰዓዳም በኩርኮራው እየተቁነጠነጠች "አዎ ሃሳቡን እርሱ ነው ያቀረበው፣ እኔ ደግሞ አፀደቅሁት" ብላ መፍለቅለቅ ጀመረች፡፡ ሰዓዳ ባለችበት ቦታ ሁልጊዜም ቁዘማና ድብርት ቦታ አይኖራቸውም፡፡ ተፈጥሮዋ ሆኖ ነው መሰል ተረጋግታ መቀመጥም ሆነ ዝም ማለት አይሆንላትም፡፡ በዚያ ላይ የማታመጣው ወሬና ጨዋታ የለም፡፡ ኃይለኛ የመረጃ ሰውም ናት፡፡ ንግግሯ በፈሊጥ ከመሆኑም በላይ ጊዜውንና ሁኔታውን ያገናዘበ ቀልድ መፍጠር፣ አዋዝታም ማቅረብ ትችልበታለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ መንቀዥቀዧን ብታበዛውም በሰሚም ሆነ በተመልካች ዘንድ አትሰለችም፡፡ በተወሰነ መልኩም ቢሆን አደብ የማሲዛት እኔ ነኝ፡፡ ከአባቴ ጋር በፈጠርኩት ፀብና ቤታችን በገባው ያለመረጋጋት ይቺ ብልህና ተጫዋች እህቴ ቤታችን ውስጥ ባትኖር ኖሮ ሕይወት ለሁላችንም ከባድ በሆነ ነበር፡፡ አሁንም በዚሁ ጨዋታዋ እኔና ሁመይድን በሳቅ ስታፈርሰን ቆየች፡፡ በዚህ መሐል ሁመይድ ቁም ነገር መሳይ ጨዋታ ለማምጣት ደጋግሞ ቢሞክርም መሃላችን ሰዓዳ መኖሯን እየጠቆምኩ በዓይኔ ስገስፀውና ስከላከለው ቆየሁ፡፡ የዕለቱ ውሎአችን ሁመይድ እንዲሁ ከእኔ ጋር ለማውራት እንዳሰፈሰፈ እኔም እንደተከላከልሁ ተጠናቀቀ፡፡ በሁኔታዬ ስለተከፋም በታዛቢ ዓይኖቹ እየሸነቆጠኝ እታባ ቤት ካደረሱኝ በኋላ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡

የአባቴ ኩርፊያ በቶሎ እንደሚበርድ ተገምቶ ነበር፣ እናቴ ራሷ "አሁን ሳምንት ሳይሞላው ይረሱታል" እያለች ለወንድሜም ለእኔም ለቤቱ ሰው ሁሉ ትናገር ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አባቴ ወደ ቤት በመጣ ቁጥር በሆነው ባልሆነው እየተበሰጫጨ ቤተሰቡን ማመሱን ቀጠለበት፡፡ ለእኔ መልካም የሆነው ነገር "እዚህ ስመጣ ፊት ለፊቴ እንዳላያት በዚህ ከዘራ አናቷን ብዬ ነው የምገላግላት" ብሏል በመባሌ ከእርሱ ጋር መፋጠጤ መቅረቱ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ከቤት እንዳልወጣና እንደፈለገኝ እንዳልሆን በእጅ አዙር ጥብቅ ቁጥጥር ያደርግብኛል፡፡ ሽምግልና ሲላክ የአባቴ ስውር እጅ ሊኖርበት ይችላል የሚል ጥርጣሬ ነበረኝ፡፡ እንደገመትኩትም መጨረሻው እንደዚያው ሆኗል፡፡ ይህንኑ ነገር ደግሞ ሽማግሌ ላኪው የራሱን ሞራል ለመገንባት በሚመስል መልኩ ለጀማው በማውራቱ አባቴ ኃፍረትና ንዴት ክፉኛ ተሰምቶታል፡፡ በዚያ ላይ ወንድሜ ፋይሰል ግፊቱን ተቃውሞ በኃይለ ቃል ስለተናገረውና እናቴም በአቅሟ ዘወትር እኔን ስለምትከላከል የብስጭቱ ተጨማሪ ግብዐት ሆኖታል፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር የእኔ እንደ ልቡ አለመሆኔና የአባወራነት ሥልጣኑ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል መላ ማምጣት ያለመቻሉ ሳያብከነክነው አልቀረም፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ ተወዳጁ አባቴን አመል ነሳው፡፡ ለወትሮው ታስቀው የነበረችው ሰዓዳን እንኳን ፊት ነስቷት በቀልዷ መዝናናቱን እርግፍ አድርጎ ትቶታል፡፡ ሲለውም ከአጠገቡ ውሻ አርጎ ያባራታል፡፡ ከፋይሰል ጋር በጣም አስፈላጊ የቢዝነስ ጉዳይ ካልሆነ በቀር መነጋገር አቁመዋል ማለት ይቻላል፡፡ እናቴንማ እንዴት ቁም ስቅሏን እንደሚያሳያት አትጠይቂኝ፡፡ ለተፈጠረው ምስቅልቅል ሁሉ እርሷን ተጠያቂ በማድረግ በነገር ይጠብሳታል፣ ሁላችንም ላይ ይዝታል፡፡ የእናቴ ሥጋት እርሱ እንዲህ ሲበሳጭ ደም ግፊቱ ጨምሮ የባለፈው ዓይነት ወይም ከዚያ የባሰ ጉዳት እንዳይደርስበት ነው፡፡ እርሱ ግን የእርሷን ዝምታ ከንቀት፣ ለልጆቿ የምታሳየውንም ፍቅር ከአድማ በመቁጠር ይብስ ይንጨረጨራል፡፡ ነገሮች በዚህ ሁኔታ እየባሱና ይበልጥ እየተወሳሰቡ ሄዱ፡፡

አባቴ አዲስ ባመጣው ዓመልና ቤተሰቡ ላይ በፈጠረው ጫና እኔ ከፍተኛ የሕሊና ስቃይ አተረፍኩ፡፡ ይህ ሁሉ ነገር በእኔ ምክንያት እንደመጣ በመቁጠር የጥፋተኝነት ስሜት ያንገላታኝ ጀመር፡፡ እኔን በገዛ እጁ ቢሰቅለኝ እንኳ በፀጋ ለመቀበል ብርቱ ነበርኩ፡፡ የእናቴ ሥቃይ፣ የወንድሜ በአባቴ ችላ መባል፣ የቤተሰቡን ሥጋት ግን መቋቋም እየተሳነኝ መጣ፡፡ ጊዜው የአዲሱ ዓመት ሁለተኛ ወር ቢሆንም አባቴ በገባው ቃል መሰረት ትምህርት መጀመሪያዬ ጊዜ ነበር፡፡ ነገር ግን የአባቴ ሁኔታ ዶክሜንቶቼን እንዲሰጠኝና ትምህርት እንድቀጥል መጠየቅ ይቅርና ጭራሽ የሚታሰብም አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ እየተደማመረ ራሴን እንደ ቤተሰቡ እንከን የመቁጠር ሃሳብ በአዕምርዬ እየገባ ያስጨንቀኝ ጀመር፡፡ ይህን ክፉ ሃሳብ ለመጋፈጥ አቅም ባላጣም ይህንን ችግር በሰይጣናዊ መንገድ አንዳርም ውስጤን የሚመክር ክፉ ሃሳብ እየደጋገመ በጭንቅላቴ ያቃጭልብኛል፡፡ ከዚህ በፊት ለማስፈራራትና ጫና ለማሳደር እናገረው የነበረው ራስን የማጥፋት ሃሳብ ሞገዱን ፀጥ የሚያደርግ ሁነኛ መፍትሔ ሆኖ በአዕምሮዬ ይሳልብኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አባቴ ጭራሽ ቤታችን የሚመጣበትን ጊዜ እየቀነሰ መጣ፡፡ ይህ እናቴ ላይ የሚፈፀም ግልፅ መድልኦና ትልቅ በደል ቢሆንም እርሱ ግን "እዚያ ስሄድ የማተርፈው ብስጭት ነው" እያለ ለቀሩት ሚስቶቹና ልጆቹ በማውራት የእኛን ቤተሰብ ማጥላላት ተያያዘው፡፡ በዚሁ ከቀጠለ እናቴን ሊፈታት ሁሉ እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡ እነዚህ ነገሮች የጦርነት አውድማውን ከውጭ ወደ ውስጥ አዞሩብኝ፡፡ ከአባቴና የእርሱን ሃሳብ ደግፈው እኔን ከሚያጠቁ ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ የተሻለ ነበር፡፡ አሁን ግን በገዛ አዕምሮዬ ውስጥ ባለ አውደ ውጊያ ራሴ ከራሴ ጋር መፋለም ጀመርኩ፡፡ በጣም ሲጨንቀኝ ድንገት የዘነጋሁት ሃሳብ መጣልኝና ነጠቅ ብዬ ተነስቼ እማማ አፀደ ቤት ሄድኩ፡፡

የተቀጣጠርን ይመስል እማማ አፀደን ቤት ውስጥ ብቻቸውን ተቀምጠው አገኘኋቸው፡፡ የንባብ መነጽራቸውን ሰክተው የሆነ ደረሰኝ ነገር እየተመለከቱ ነበር፡፡ ሲያዩኝ ገና "ውይ አፊያ..ነይ ግቢ ልጄ" ብለው መነጽራቸው አውልቀው ከደረሰኙ ጋር ጠረጴዛ ላይ አኖሩትና አገላብጠው ሳሙኝ፡፡ አጠገባቸው ውሽቅ ብዬ ስቀመጥ እንደ ሕጻን ልጅ ራሴን ያሻሹኝ ጀመር፡፡ ይህን ሁኔታ መቋቋም የሚያስችል አቅም አልነበረኝምና ተንሰቅስቄ ማልቀሴን ቀጠልኩ፡፡ "እንኳን እናቴ ሞታብኝ እንዲሁም አልቅሽ አልቅሽ ይለኛል" እንደሚባለው ራሴን በእናትነት ወግ ሲደባብሱኝ ሆድ ባሰኝና መነፍረቄ በዛ፡፡ እማማ አፀደ የቅርብ ጎረቤትና የእናቴ ወዳጅ በመሆናቸው ብዙውን የቤታችንን ነገር ያውቁታል፡፡ ስለሆነም እኔ በውስጤ እየተሰማኝ ያለውን ክፉና አስጨናቂ ሃሳብ ስነግራቸው "ምነው ምነው ልጄ ምኑን አሰብሽው? ጠንካራም አልነበርሽ" ብለው አቅፈውና ራሴን ጭናቸው ላይ አስተኝተው አባበሉኝ፡፡ ለቅሶዬም እስኪወጣልኝ ጠበቁኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙ ነገር ስናወራ ቆየን፡፡ አባቴ በእልህና በጥላቻ ስሜት እኔን ብቻ ሳይሆን እናቴን፣ እህቴንና ወንድሜን በማጥቃት ላይ እንደሆነ፣ ቤት ቶሎ ቶሎ መምጣት እንደተወና ቀጥሎስ ምን እንደሚያደርግ እንደማይታወቅ በሥጋት ነገርኳቸው፡፡ አያይዤም "እኔ ላይ የፈለገውን ቢያደርግ ግድለየኝም፣ ነገር ግን በእኔ ምክንያት የገዛ ሚስቱና ልጆቹ ላይ የሚያደርገውን ነገር መቋቋም አልቻልኩም፡፡ ከፍተኛ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ነው፡፡ ይሄን ከማይ ... ብር ብዬ ብጠፋ እመርጣለሁ" አልኩና ሳጌን ለማቆም ታገልኩ፡፡

እማማ አፀደ ዝም ብለው ሲሰሙኝ ቆዩና ጉሮሮአቸውን አፅድተው ፀጉሬን እያሻሹ እንዲህ አሉኝ፡፡ "ይኸውልሽ ልጄ...ያንቺን ፍላጎት፣ የተጋፈጥሽውንም ፈተና፣ ያሳየሽውንም ተጋድሎ በደንብ ስከታተልና ሳደንቅ፣ በአቅሜም ስፀልይልሽ ቆይቻለሁ፡፡ ደግሞም እናትሽ ነኝ፡፡ እናም እስቲ የእናትነት ምክርና አስተያየት ልስጥሽ" አሉና ዓይኔን ፍለጋ ወደኔ ጎንበስና ዞር አሉ፡፡ እንባ ባቀረረው ዓይኔ እያየኋቸው "እኔም እኮ ሲጨንቀኝ ይህንኑ ፍለጋ ነው የመጣሁት" አልኳቸው፡፡ "አይዞሽ ልጄ" ብለው ይበልጥ ጥብቅ አርገው እያቀፉኝ ቀጠሉ፡፡ "ዝም ብዬ የአንቺን ነገር ሳስተውለው የፈተናሽ ብዛቱና ያንቺም ጽናት ከቅዱሳን አንስትና ከሰማዕታት ጋር ብዙው ነገር ይመሳሰልብኛል፡፡ ከቅድስት አርሴማ፣ ከቅድስት ኢየሉጣ፣ ከወለተ ጴጥሮስ፣ ከሌሎቹም ቅዱሳን ሴቶች ጋር፡፡ እኒህ ቅዱሳን የተጋፈጡት ፈተናና ያሳዩት ጽናት እጅግ ትልቅ ስለሆነ ለእንዲህ ያለው ደረጃና ክብር መመረጥም ያስፈልጋል፡፡ አንቺ ምንም እንኳ እስካሁን ያሳየሽው ተጋድሎ የዚህ ዘመን ሰማዕት ሊያሰኝሽ ቢችልም ቤታችሁ ካለው የገነገነ ችግር የተነሳ እንዳትሰበሪብኝ እሰጋለሁ፡፡ ይሄን ያሳሰበኝ ልጄ ስለሆንሽና ስለምሳሳልሽ ሊሆን ይችላል" አሉና ጥቂት ዝም አሉ፡፡ ቀና ብዬ እያየኋቸውና "ምን ሊሉኝ ነው?" የሚል ጉጉት እየናጠኝ "ታዲያ ምን አድርጊ እያሉኝ ነው?" ስል ጠየኳቸው፡፡ ረጋ ብለው ቀጠሉ "አንዳንድ ጊዜ እንደ ተራራ የገዘፈ ችግር ሲገጥመን ጽናታችን ብቻ፣ መጋፈጣችን ብቻ፣ ቁርጠኛነታችን ብቻ ለውጤት ላያበቃን ይችላል፡፡ በተጨማሪ ብልሃት ያስፈልገናል፡፡ አውሎ ነፋሱን ጎንበስ ብሎ የማሳለፍ ጥበብ፣ እንደ እሳት የሚነድ ቁጣን በለዘብታ ቃል የማብረድ ዘዴ፣ የሰይጣንን እብሪት በትሕትና ድል የመንሳት መላ ያስፈልጋል፡፡ መጽሐፉም "እንደ ርግብ የዋሕ እንደ እባብም ብልህ ሁኑ" ነው የሚለው፡፡ አሉና አሁንም ጥቂት ዝም አሉ፡፡ ዝም ባሉ ቁጥር የእኔን ስሜትና ግብረ መልስ እያጠኑ ነበሩ፡፡

የእምነትና የጽናት ተምሳሌቴ እኚህ ጎምቱ አዛውንት ዛሬ ምን እያሉኝ ነው? ስል አሰብኩና "ታዲያ ይህ የሚሉኝ ጥበብ ምንድነው?" አልኩ እንዳቀረቀርኩ፡፡ "በሆነ መንገድ ከአባትሽ ተፅዕኖ መላቀቅ አለብሽ" ሲሉኝ ክው አልኩ፡፡ "ይሄን ቃል የት ነበር የሰማሁት?" ቃሉን ከማስታወስ የእርሳቸውን ሃሳብ ማስጨረስ የተሻለ እንደሚሆን በቅጽበት አስቤና ወስኜ "እንዴት?" አልኳቸው፡፡ "ስፈልግ የኖርኩት ይህንኑ ነፃነት መሆኑ እንዴት ተሰወረባቸው?" ብዬ በማሰብ እየተደነቅሁ፡፡ እርሳቸው ግን "በሆነው መንገድ" አሉኝ፡፡ "በሆነው መንገድ...በጋብቻ ሊሆን ይችላል፣ የራስሽን ሥራ በመጀመር ሊሆን ይችላል፣ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ሊሆን ይችላል...ብቻ በሆነው መንገድ ይሁን፡፡ የሚፈለገው መንገዱ ሳይሆን ውጤቱ ነው" አሉ፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ያሉትን አማራጮች በውስጤ አውጠነጠንኳቸው፡፡ የራስን ሥራ መጀመር ያሉት በድፍረትና በኃይል ቤቱን ጥዬ መሄድን ተከትሎ የሚመጣ እንጂ በሰላምና በአባቴ ፈቃደኝነት የሚታሰብ አይደለም፡፡ እንኳን ሥራ ቀርቶ ትምህርት እንኳ እንዳልቀጥል በክፋትና በጥበብ ያስቀመጠውን የእንቅፋት ድንጋይ ቤተሰቤ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ ቤቱን ጥዬ ሄጄ ይህን አማራጭ ብሞክር እንኳ የሚገጥሙኝ ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው የቤተሰቤን ሰላም ከድጡ ወደ ማጡ የሚከት ነው፡፡ ወደ ውጭ ሀገር የመሄድን አማራጭም ከዚህ በፊት ለአባቴ አቅርቤለት አምርሮ የተቃወመው ሃሳብ ነው፡፡ ይህን ሃሳብ እርሱ የሚያየው ይበልጥ ካፊር ለመሆን መርቆ እንደ መሸኘት አድርጎ ነው፡፡ የጋብቻን አማራጭ ግን እማማ አፀደ እንዴት ሊያስቡት እንደቻሉ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ "ያዘጋጁልኝ ባል አለ እንዴ?" ስል አሰብኩና በራሴ ሃሳብ ፈገግታዬ አመለጠኝ፡፡ እንደገና መልሼ ደግሞ "ነው የጋብቻ ሽምግልናውን በአሉታ መመለሴን እየተቃወሙ ነው" ብዬ በማሰብ ተገረምኩ፡፡

ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ ወደ ውጭ ለመሄድ ለአባቴ ሃሳብ አቅርቤለት በምን አይነት ምሬት እንደተቃወመውና የራሴን ሥራ መጀመርም የሚፈጥረውን ሁከት በአጭሩ ካብራራሁላቸው በኋላ "ባል ማግባት የሚለውን አማራጭ ለምን እንዳቀረቡት ግን አልገባኝም፣ ክርስቲያን ባል አግቢ ማለቶት ነው ወይስ የአባትሽን ፈቃድ ፈፅሚ እያሉኝ ነው?" ስል በቀጥታ ጠየኳቸው፡፡ እርሳቸው ግን በዚያው እርግት ባለ አነጋገራቸው "ሁለቱንም ማለቴ አይደለም" አሉኝ፡፡ እኔም ወደርሳቸው ዞሬ ግራ ከተጋባ ገጽታዬ ጋር "እና ምን ማለቶት ነው?" በሚል አስተያየት አየኋቸው፡፡ ገልመጥ ብለው ገጽታዬን አዩና በፍጥነት እንደገባቸው ሁሉ "የትኛውንም አማራጭ አወዳድሮ የተሻለ ውጤት የሚያመጣውን መምረጥ ብልህነት ነው፡፡ ቢቻል አባትሽን ጨምሮ ሁሉንም ቤተሰብ የሚያስደስት የአንቺንም ዓላማና ፍላጎት የሚያሟላ፣ ካልሆነም ኪሳራውና የሚከፈለው ዋጋ አነስተኛ ሆኖ የአንቺን ፍላጎት የሚያሳካውን መምረጥ ይኖርብሻል" አሉኝ፡፡ በንግግራቸው ይበልጥ ዞሮብኝ እንደተደናገርኩ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ሆን ብለው ከእነ አዕምሮ ውዝግቤ የተዉኝ የሚያስመስልባቸው የዝምታ ጊዜ ሲያበቃ "እኔ የምልሽ አፊያ" ብለው ፈጠን ባለ እንቅስቃሴ ወደ እኔ ዞር አሉ፡፡ ድምፀታቸውም ከእስካሁኑ እርጋታ በመጠኑ ፈጠን ያለና ኃይል የተሞላ ነበረ፡፡ እኔም ባልረጋና ሥልት በሌለው አኳኋን ከሃሳብ ሃሳብ ሲዘል የነበረውን አዕምርዬን ሰብስቤ "አቤት እማማ አፀደ" አልኩ፡፡ ፊት ለፊቴ በሚመረምር ዓይኖቻቸው አተኩረው እያስተዋሉኝ "ይሄ ቤታችሁ የሚመላለሰው ክልስ ማነው?" ሲሉ ጠየቁኝ፡፡

ሜሪዬ..እንደዚያ ቀን ድንግጥ ያልኩባቸው ጊዜያት ቢቆጠሩ ከአንድ እጅ ጣቶች አያልፉም፡፡ ብቻ ክው ስል እርሳቸውም በደንብ አስተውለውኝ ነበረ፡፡ ከድንጋጤዬ ሌላ የሚያስደንቅ መገረምም በውስጤ ሲመላለስ ይታወቀኛል፡፡ በውስጤ "እኚህ ሴቲዮ የነቢያት ዘር አለባቸው እንዴ?" ስል ራሴን ደጋግሜ ጠየኩ፡፡ ሑመይድ ያቀረብልኝን ሃሳብ ለማንም አልተነፈስኩም፡፡ እርሱም ለሌላ ሰው ያወራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ በእርግጥ ቤታችን መመላለሱን ከቢዝነስ ጉዳዮች ሌላ እኔ ላይ ፍላጎት አሳድሮ በመሆኑ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጎረቤት በቀላሉ መገመት አያዳግተውም፡፡ እኔን በእጅጉ ያስደነቀኝ ሑመይድ ያቀረብልኝ ሃሳብ በእማማ አፀደ እንደ አማራጭ መፍትሄ ከመቅረቡም በላይ ስለ እርሱ ማንነት ጥያቄ ማንሳታቸው ነው፡፡ ከሁሉ ደግሞ  "ቢቻል አባትሽን ጨምሮ ሁሉንም ቤተሰብ የሚያስደስት የአንቺንም ዓላማና ፍላጎት የሚያሟላ.." ሲሉ ያቀረቡት ሃሳብ የሑመይድ ንግግር ኮፒ ፔስት መሆኑ ነው፡፡ ሑመይድ ያንን የጋብቻ ጥያቄ ሊያስገኝልኝ ከሚችለው ጥቅም ጋር አሰናስሎ ሲያቀርበው እጅግ ተጨንቄ እማማ አፀደን ለማማከር ወስኜ ነበር፡፡ ሆኖም በዝንጋታና በተለያዩ ያለመገጣጠሞች ሳላማክራቸው ቆይቼ በእንዲህ ያለ ሁኔታ የእርሱን ገለፃ የሚመስል ንግግር ከእርሳቸው ማድመጤን አጋጣሚ ነው ብሎ ማለፍ ከባድ ነበር፡፡ እኔ የውስጤን አግራሞት ሳዳምጥ እርሳቸው ፊቴ ላይ ያስተዋሉትን ድንጋጤ ታዝበው "ምነው ልጄ ደነገጥሽ? ጥያቄው ያስደነግጣል እንዴ?" አሉኝ አይናቸውን ከዓይኔ ሳይነቅሉ፡፡ ፈገግ እያልኩ "አይ ገርሞኝ ነው" አልኳቸው፡፡ "ምኑ ነው ያስገረመሽ?" አሉኝ ዜማ ባለው አነጋገር፡፡ እኔም ስለ ሑመይድ ማንነት፣ ስለሚከተለው የአኗኗር ዘይቤ፣ ስላቀረበልኝ የጋብቻ ጥያቄ፣ ስለገባልኝ ቃል፣ ያስገኘዋል ብሎ ስለሚያስበው ጥቅምና እኔ ስለሰጠሁት ምላሽ በዝርዝር ነገርኳቸው፡፡ ይህንኑ ነገር ከባለፈው ሽምግልና በፊትና ሑመይድ በነገረኝ ሰሞን ላማክራቸው አስቤ እንደነበርና በዝንጋታና በተለያየ ምክንያት እንደዘገየሁ ጨምሬ አስረዳሁ፡፡

እማማ አፀደ ሲያወጡ ሲያወርዱ ከቆዩ በኋላ "ለምክሩ እንኳን ብዙም አልዘገየሽ፣ ለሌላው ጊዜ ግን ወደ ልብሽ የመጣን ነገር አታሰንብቺው፡፡ ይህ ነገር እስከመቼ እንደዚህ ይቀጥላል? የሚለው ነገር ግን የእኔም የዘወትር ጭንቀት ነው፡፡ እንጃ...እስቲ ጸልዪበት ልጄ፡፡ እኔም ለማያልቅበት ጌታ ለመድኃኔዓለም እነግረዋለሁ" አሉ ሁለት እጃቸውን ዘርግተው በዓይኖቻቸው ሽቅብ እያንጋጠጡ፡፡ ቀጠሉናም "አየሽ...መድኃኔዓለም ያዘጋጀልሽ የዚህ ፈተና መውጫ ቀዳዳ ይሆን እንደሆን ማን ያውቃል? ብቻ አንድን ሃሳብ በቅጡ ሳያስቡበትና ሳይፀልዩበት በጥቁርም በነጭም መነጽር ማየት አይገባም፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ የሚበጀንን አናውቅም፡፡ ለውሳኔ የምንዘገይና የምንፈራ ስለሆንን ብዙ አጋጣሚዎችና መልካም ዕድሎች ያመልጡናል፡፡ በአላስፈላጊ ጥድፊያም ለበርካታ ወጥመዶች እንዳረጋለን፡፡ ስለዚህ ተረጋግቶ ብዙም ሳይዘገዩ፣ ተካልበውም ሳይጣደፉ ማሰብና አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይገባል፡፡ እስከዚያው ግን ይህን ሰው ሳትገፊውም ልብሽን ሳትሰጪውም በወዳጅነት አቆዪው፡፡ ይህ ነው የሚሻለው ልጄ" አሉና በብዙ የእናትነት ምክርና ምርቃት አሰናበቱኝ፡፡ ወደ ቤት ከገባሁ በኋላ አንድ ሰሞን አስጨንቆኝ የነበረው ይህ ሃሳብ አዲስ አጀንዳ ሆኖ አዕምሮዬን ያምሰው ጀመር፡፡ በሁኔታው ጊዜና ሥፍራ ሳልመርጥ እየደጋገምኩ በአጭሩም በረዥሙም እፀልያለሁ፡፡ የእማማ አፀደ ሃሳብ ይሁን፣ የጸሎቴ ውጤት ይሁን፣ ወይም ደግሞ ነፃ የመውጣት ጉጉቴ የፈጠረብኝ ተፅዕኖ ይሁን ባላውቅም የሑመይድ ሃሳብና ጥያቄ አዎንታዊ ጎኑ እየጎላብኝ ሲመጣ ይታወቀኝ ነበር፡፡

ከአራት ቀን በኋላ ታሪከኛው አባቴ በክፋቱ በመቀጠል ቤተሰቡን በሙሉ ያበሸቀ ሌላ ተጨማሪ ነገር አደረገ፡፡ አባቴ ያሉት ንብረቶችና የንግድ ሥራዎች ባልተፃፈ ሕግና በልማድ በሦሥቱ ቤተሰቦቹ ተከፋፍለው የተያዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በእኔ ስም የሚጠራ አንድ ባለ አራት ፎቅ ሕንጻ፣ ወንድሜ ፋይሰል የሚያስተዳድረው የቡና ላኪ ድርጅትና ሌሎች ሁለት ሱቆች በእኛ ቤተሰብ የሚተዳደሩ ናቸው፡፡ የቀሩትም ሁለት ቤተሰቦች እንዲሁ የሚቆጣጠሯቸው በቂ ቢዝነሶች አሏቸው፡፡ ታዲያ ሐጂ ሁሴን ሆዬ ቡና ኤክስፖርት ከሚያደርገው ድርጅቱ ለፋይሰል የሰጠውን ሙሉ ውክልና በማንሳት ሃላፊነቱንም ውክልናውንም ኢብራሒም ለሚባል ከሌላኛው ሚስቱ ለሚወለድ ልጅ ይሰጠዋል፡፡ ይህን የሰማው ወንድሜ እንዴት እንደተቃጠለ አትጠይቂኝ፡፡ በእርግጥም ፋይሰል ይህ ሥራ ብዙ ልምድ ያካበተበትና ትልቅ ደረጃ ያደረሰውም ነበር፡፡ በቂ ልምድና ችሎታ ለሌለው ሰው ሃላፊነቱን ማስተላለፉ የአባቴን በቀለኝነት ያመላከተ ነውረኛ አካሄድ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህን ሁሉም ቤተሰብ የተገነዘበው ሲሆን እኔ ደግሞ ይበልጥ ሃላፊነት በመውሰድ የተበሳጨ ወንድሜን አቅፌ አባበልኩት፡፡ "አይዞህ እኔ ሁሉንም አስተካክለዋለሁ" ስለው ከእቅፌ እየወጣ በመገረም ያየኝ ነበር፡፡ ይህን ጉዳይ ተሰብስበን በምናወራበት ምሽት ቤተኛው ሑመይድ "ጤና ይስጥልኝ...እንዴት አመሻችሁ?" እያለ ገባ፡፡ ከጥቂት የሰላምታ ግርግርና ጨዋታ በኋላ አንድ እያሉ ወጥተው እኔና እርሱ ብቻ ሳሎኑ ውስጥ ቀረን፡፡ "ምንድነው ኤፊ ችግር አለ? ሁላችሁ የሆነ ድብርት ውስጥ ትመስላላችሁ" አለ፡፡ በአጭሩ አባቴ ያደረገውንና ሰሞኑን እየሆነ ያለውን ነገርኩት፡፡ ጥቂት እንደ መተከዝ ብሎ ፈገግ አለና "ኤፊ ቆንጆ የመፍትሄ ሃሳብ አቅርቤልሽ ነበር...አንቺ ግን እምቢ አልሽ" አለ፡፡ ንግግሩ ከፈገግታው ጋር የፈጠረውን ሕብር ሳይ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ብሽቅ አረገኝ፡፡ ለአፍታም ቢሆን አስጠላኝ፡፡ ቀጠለናም "ኤፊ..ያን ጥያቄዬን ባትቀበዪውም እስቲ በሌላም መንገድ ቢሆን ችግርሽን እንድካፈል ፍቀጂልኝ" አለና እጁን ዘረጋልኝ፡፡ በጥርጣሬ ዓይን እያየሁትም ቢሆን እጄን ሰጠሁት፡፡ "አመሰግናለሁ ኤፊ" አለና ብድግ ብሎ እጄን ሳመና ተቀመጠ፡፡

                        (ይቀጥላል)

     --------- ማርያማዊት ገብረመድኅን ---------

እሑድ 24 ዲሴምበር 2017

ልዩ የግጥም መድብል

*አምላክን ሽንገላ*

ጾም የሚሏት ነገር የስጋ ፈተና
አስቸገረች በጣም ካቅም በላይ ሆና
የትሩፋት ስራ መሆኗ ተረስቶ
ሰው ፈጽሞ ጠላት ሸሸ ፊቱን ነስቶ
ወጣቱ አቃለላት ሻራት ቁርሱን በልቶ
ጌታ በቆሮንቶስ መጾሙን ዘንግቶ
"ኑሮ ራሱ ጾም ነው" ይላል አፉን ሞልቶ

ያልታደለ ትውልድ ሚሆነውን ያጣ
መረጠ ለያየው አካፈለው በዕጣ
👉ይሄ የጳጳስ ነው ያኛው🕺 የመነኩሴ
እንደት "ጹም" ይሉኛል ምን ነካወት ቄሴ!?
መጾም ከለከለኝ የጫት የሲጋራ የመጠጡ ሱሴ
እያለ መልሶ የአባን ግሳፄ

የሆነ ያልሆነ ምክንያቱን ደርድሮ
ጾሙን ይሽረዋል አንድ ስበብ ፈጥሮ

ከመልካሙ መንገድ ወተው ከመስመሩ
ያሻቸውን በልተው ካሻቸው ሊዳሩ
ያሻቸውን በልተው ጠጥተው ሊሰክሩ
ሄዱ ተጠራርተው ሊያድሩ ሲጨፍሩ

ወገኔ ተመለስ እባክህ ወድህ ና
ለጽድቅ የሚያበቃህ ምን ስራ አለህና
ደከመኝ ትላለህ ነፍስህ ባዶ ሆና
ጌታ ባለም ሲኖር መቸ ደላውና
"ኑሮ ጾም ነው"ምትል ሳይነካህ ፈተና

ወንድሜ ተመለስ ምልህን ስማ
እንድሆን ከፈለግክ ኑሮህ የተቃና
በገነት እንድትኖር ከቅዱሳን ጋራ
የስጋ ምኞትክን አሸንፈውና
አምላክን መሸንገል ማታለል ተውና
ነፍስህን አድናት ከሲኦል ፈተና
በጾም ጸሎት ትጋ በንጹህ ህሊና
ትዕዛዙን ጠብቅ በልብህ ጻፍና

✍ Written By Z

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

​አትውጡ ከመርከብ​
   ///////         //////

የአማኞች መኖሪያ የነፍሳት መዳኛ፤
ቤተክርስቲያ ናት መርከባችን ለኛ፤
ለሰማያት እየሩሳሌም ምሳሌ የሆነች፤
በክርስቶስ ደም ላይ የተመሰርተች፤
የሐዋርያት ስብከት ቤተክርስቲያን ነች፤
ወጀብ የማይገፋት ባለት የታነፀች፤
ሰባቱ ነፍሳትም ከጥፍት የዳኑት፤
ኖህን ተከትለው መርከቧበመግባት
በውስጥዋ ገብተው ፀንተ በመቆዬት፤
ዛሬም በመርከቧ ተነስቷል ማእበሉ ፤
አድነን እንበለው ፀጥ ይላል በቃሉ፤
መሰርቷ እሱነው ያለው በመቅደሷ ፤
ከመርከብ ሳንወጣ እጠብቅ በተስፋ፤
።።።።።.
ሐዋርያትም ከጌታ ጋር ሁነው በጉዞ ላይ ሳሉ፤
መርከብ ተናወጠች ተነሳ ማእበሉ
ወዳምላክም ጮሁ አድነን እያሉ
ስለመጥፍታችን እደት አይገድህም ብለው ተማጸኑ
ጌታም ተነስቶ ቃል ተናገራቸው
የታል እምነታችሁ ብሎ ገሰጻቸው
ጸተው እድቆሙ በአምልኮታቸው
ለደቀ መዛሙርቱ ትምህርት ሰጣቸው
እነሱም በርቱ ጸተው ተጋደሉ
እስከሞትም ድርስ ለቃሉ ታመኑ
አለምን በመዞር ወንጌል አስተማሩ
ሁሉን ንቀው ትተው እርሱን ተከተሉ
ከመርከብ ሳይወጡ ህዝቡን አስተማሩ
ከላይ ከአርያም ሀይልን ተቀበሉ


     ሙሉአለም // ወለተ ማሪያምsaramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...