2018 ጁን 25, ሰኞ

የምዕራፍ ፬/የ33ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ማኅበርተኞች!:
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁንልን እያልን እነሆ፦ የምዕራፍ አራት(፬) የ33ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር እንዲህ ተጀመረ
@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄ እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

✍1⃣➡እግዚአብሔር በቃየል ላይ ለምን ምልክት አደረገበት??

ሀ/ለመቅጣት
ለ/ ከአቤል ለመለየት
ሐ/ ከሚደርስበት መከራ ለመጠበቅ
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ// ሀ)

✍2⃣➡አብርሃም እግዚአብሔርን ስለ ሰዶም መዳን በማለደ ጊዜ እስከ ስንት ሰው ድረስ ቢገኝ እንዲምርለት ፈጣሪውን ተማጽኖት ነበር??
ሀ/ 5
ለ/ 10
ሐ/ 15
መ/ 50

// መልስ//ለ)

✍3⃣➡ያዕቆብ ይወዳቸው የነበሩት ከራሔል የተወለዱት ሁለት ልጆች ማን ናማን ናቸው??
ሀ/ ዮሴፍና ንፍታሌም
ለ/ ዛብሎንና ጋድ
ሐ/ ሮቤልና ይሁዳ
መ/ ዮሴፍና ብንያም

//መልስ//መ)

✍4⃣➡ከአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የመሬት ርስት ያልተሰጠው የትኛውው ነገድ ነው??

ሀ/ ነገደ ስምዖን
ለ/ ነገደ ዳን
ሐ/ ነገደ ይሳኮር
መ/ ነገደ ሌዊ

//መልስ// መ)

✍5⃣➡ሩት የማን ቅድመ አያት ናት??

ሀ/ የቦኤዝ
ለ/ የዳን
ሐ/የዳዊት
መ/ የሌዊ

//መልስ// ሐ)

✍6⃣➡እግዚአብሔር ለአብርሃም የማለለት ምድር  ተብሎ ይጠራል??

ሀ/ካራን
ለ/ቤቴል
ሐ/ ከነዓን
ምንመ/እስራኤል

//መልስ//ሐ)

✍7⃣➡ከሚከተሉት የአባቷን ጣዖት የደበቀችው ማናት??

ሀ/ ርብቃ
ለ/ ራሔል
ሐ/ሣራ
መ/ ልያ

//መልስ// ለ)

✍8⃣➡አባታችን ኖኅ ስንት ልጆች አሉት??

ሀ/ 2
ለ/ 3
ሐ/4
መ/8

//መልስ// ለ)

✍9⃣➡ደረቅ ሐዲስ ኪዳን በመባል የሚታወቀው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ የትኛው ነው??

ሀ/ ኦሪት ዘፍጥረት
ለ/መጽሐፈ ሩት
ሐ/ ትንቢተ ኢሳይያስ
መ/መጽሐፈ ጦቢት

//መልስ//ሐ)

✍1⃣0⃣➡የአምስቱ ብሔረ ኦሪት ጸሐፊ ማን ነው??

ሀ/ ሄኖክ
ለ/ ሰሎሞን
ሐ/ሙሴ
መ/አሮን

//መልስ// ሐ)

✍1⃣1⃣➡ዳዊት ፍልስጥኤማዊያውንን ጎልያድን የገደለበትን ታረክ በየትኛው መጽሐፍ ላይ ነው??

ሀ/ 1ኛ ነገሥት
ለ/1ኛ ሳሙኤል
ሐ/ 1ኛ ዜና መዋዕል
መ/2ኛ ዜና መዋዕል

//መልስ// ለ)

✍1⃣2⃣➡እኔ ከንፈር ቁልፍ ነኝ በማለት ራሱን ወደ እግዚአብሔር በትህትና ያቀረበው ማነው??

ሀ/ ቅዱስ ጳውሎስ
ለ/ ነቢዩ ዳዊት
ሐ/ሙሴ
መ/ ኤልሳዕ

//መልስ// ሐ)

✍1⃣3⃣➡እንደ በሬ ሣር በመጋጥ ሰባት ዓመት የተቀጣው ንጉስ ማነው??

ሀ/ ዳርዮስ
ለ/ ናቡከደነጾር
ሐ/ብልጣሶር
መ/ ኢዮርብዓም

//መልስ// ለ)

✍1⃣4⃣➡በመጽሐፍ ቅዱስ ርዝመቱ 300 ክንድ፣ ስፋቱ 50 ክንድ እና ከፍታው 30 ክንድ መጠነ ስፍር እንደሌለው የተገለፀው ለየትኛው ነው?

ሀ/ ታቦተ ጽዮን
ለ/ የኖህ መርከብ
ሐ/ ናቡከደነጾር ያቆመው ምስዕል
መ/ የዳዊት ቤተ መቅደስ

//መልስ// ለ)

✍1⃣5⃣➡ከሚከተሉት ሴቶች በመጽሐፈ መሳፍንት ታሪኳ የሠፈረው የእስራኤል ፈራጅ ማናት??
ሀ/ ሩት
ለ/አስቴር
ሐ/ዮዲት
መ/ ዲቦራ

//መልስ// መ)

✍1⃣6⃣➡"ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን የሚለው ሃይለ ቃል ከሚከተሉት ውስጥ በይበልጥ ማነን ይመለከታል??

ሀ/ አብርሃምን
ለ/ይስሐቅን
ሐ/ ያዕቆብ
መ/ ዮሴፍ

//መልስ// መ)

✍1⃣7⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ ክርስቶስን ይመስላል የሚባልለት ማነው??

ሀ/ ሎጥ
ለ/ ኤርምያስ
ሐ/ ሰሎሞን
መ/ ዮሴፍ

//መልስ//መ)

✍1⃣8⃣➡ከሚከተሉት ወንድም አማቾች ያልሆኑት እነማን ናቸው??

ሀ/ ሙሴና አሮን
ለ/ ያዕቆብና ዔሳው
ሐ/ ዳዊትና አቤሴሎም
መ/ አቤልና ቃየል

//መልስ// ሐ)

✍1⃣9⃣➡ዳዊት ንስሐ እንዲገባ በምሳሌ ያስተማረው ነቢይ ማነው??

ሀ/ናታን
ለ/ ነህምያ
ሐ/አሮን
መ/ዳንኤል

//መልስ//ሀ)

✍2⃣0⃣➡ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌሎች ይልቅ የተነበየው ነቢይ ማነው??አመሰግናለሁ

ሀ/ ኤልያስ
ለ/  ናሆም
ሐ/ ዮናስ
መ/ኢሳያስ

//መልስ// መ)


ወስብሀት ለእግዚአብሔር
. @Teyakaenamels
@Teyakaenamels

https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...