2018 ጁን 13, ረቡዕ

"ከእኔ አብ ይበልጣል"""

""'ከእኔ አብ ይበልጣል'"" ዮሐ14፥28
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን መናፍቃን ይህንን ጥቅስ በመጥቀስ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባህሪው ከአብ ያንሳል ብለው ይናገራሉ ዳሩ ግን ይህንን አባባል ጠለቅ ብለን ስናጤነው እንደአርዮሳውያን አባባል ወልድ በመለኮቱ ከአብ ያንሳል የሚለውን ትምህርት የሚደግፍ ሆኖ አናገኘውም እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን በመዋሐዱ መከራ የሚቀበልና ስለሰዎች ልጆች ድኀነት ሲልም በፈቃዱ እንደሚሞት ሲገልፅ ነው ሰውን ከወደቀበት የጉስቁልና ህይወት ለማንሳትና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ልዑለ ባህሪ አምላክ እራሱን አዋርዶ ሥጋን ተዋህዶ መከራን ተቀበለ ይህንንም ሲያደርግ ከእግዚአብሔርነቱ አልጎደለም ጳውሎስ በመልእክቱ እንደገለፀው ""ይኸውም የእግዚአብሔር መልኩ ነው ቀምቶ እግዚአብሔር የሆነ አይደለም እራሱን ዝቅ አድርጎ የአዳምን ባህሪ ባህሪ አደረገ እንጂ ሰውንም መሰለ""ፊል2፥6-7 እንግዲህ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ የሰው ፍቅር ስቦትና አስገድዶት ራሱን ዝቅ አድርጎ በሠራው የትህትና ሥራ እንኳን በባህሪ አንድ ከሆነው ከአብ ቀርቶ ከፈጠራቸው መላእክትም አንሶ እንደነበር መፅሀፍ ቅዱስ ይገልፅልናል ""ከመላእክት ይልቅ በጥቂቱ አሳነስከው ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስን...""ዕብ2፥7-9 እንግዲህ ይህንንም ጥቅስ ይዘው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክትም ያንሳል ብለው ሊናገሩ ይችላሉን? ጳውሎስ ጌታችን ስለ እኛ ሲል በተቀበለው መከራና ሞት መላእክትን እንኳን እንዳይሞቱ አድርጎ የፈጠረ እርሱ ስለሰው ልጅ ፍቅር ሲል ግን ሞተ ብሎ እግዚአብሔር ወልድ በለበሰው ሥጋ እንደ ሞተ ግልፅ አድርጎታል ስለዚህ ጌታም ከእኔ አብ ይበልጣል ማለቱ እራሱን ዝቅ አድርጎ ሥጋን ተዋሕዶ በምድር ላይ መንገላታቱን ሞትን በገዛ ፈቃዱ ሊቀበል መምጣቱን ሲገልፅ ሲሆን በትህትና የሚታይበትም ግዜ አጭር መሆኑን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ በልዕልና በክብሩ እንደሚኖር ሲገልፅ ""ወደ አብ በመሔዴ ደስ ይበላችሁ"" ብሏቸዋል በትህትና ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ አንሶ የታየው ጌታ የማዳኑን ሥራ ከፈፀመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሷልና በልዕልና ይታያልና የሐ ሥራ7፥55 ""'ኢየሱስን በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ አየዋለሁ""' ማለት በቀደመ ክብሩ በልዕልናው ሆኖ አየዋለሁ ማለቱ ነውና
ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...