2018 ጁን 16, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬)/የ32ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን? ሰላማችሁ ይብዛልን እያልን እነሆ፦ የምዕራፍ ፬ የ32ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

@ምንጭ፦ 420 ጥያቄ እስከ መልሶቻቸው ከሚለው በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው መጽሐፍ የተወሰደ።

✍1⃣➡ከዐቢይት ነቢያት የማይመደበው  ነቢይ የትኛው ነው???

ሀ/ሚክያስ
ለ/ ኤርምያስ
ሐ/ኢሳያስ
መ/ዳንኤል

//መለስ//፦ሀ) ሚክያስ

✍2⃣➡ንጉሥ አክዓብ ጣዖት በማምለኩ ምክንያት የገሰጸው ነቢይ ማን ነው??

ሀ/ናታን
ለ/ ኢሳይያስ
ሐ/ ባሮክ
መ/ኤልያስ

//መልስ// ፦መ) ኤልያስ

✍3⃣➡የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ የነበረው ንዕማን ከለምጹ ለመፈወስ ስንት ጊዜ በዮርዳኖስ ወንዝ ብቅ ጥልም አለ፤

ሀ/ 1
ለ/ 3
ሐ/ 5
መ/ 7

//መልስ//፦ መ) 7ት ጊዜ

✍4⃣➡ከሚከተሉት ወንዞች መካከል ከኤደን በመውጣት ገነትን ያጠጣ የነበረው የትኛው ነው??

ሀ/ ዮርዳኖስ
ለ/ኤፌሶን
ሐ/ አባና
መ/ ፋርፋ

//መልስ//፦ለ) ኤፌሶን


✍5⃣➡ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች በባረከ ወቅት ቀኝ እጁን ያደረገው  ማን ራስ ላይ ነበር??።

ሀ/ ኤፍሬም
ለ/ ምናሴ
ሐ/የበኩር ልጁ
መ/መልስ የለም

//መልስ//፦ ለ) ምናሴ

✍6⃣➡ፈርፆን የዮሴፍን ሕልም የመፍታት ጸጋ ስላስደነቀው ለዮሴፍ ምን አደረገለት ??

ሀ/ ከእስር ቤት ፈተው

ለ/ በሀገሩ ላይ ሹም አደረገው
ሐ/ ገንዘብ ሰጠው
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ//፦መ) ሁሉም መልስ ነው።

✍7⃣➡እግዚአብሔር በግብፅ ካደረገው መቅሠፍት የማይመደበው የትኛው ነው??

ሀ/ ሀገሪቱ በበረዶ መመታት
ለ/የዝንብ ወረራ
ሐ/የውኃ ወደ ደም መለወጥ
መ/ የአዞ መንጋ

//መልስ//፦ መ) የአዞ መንጋ

✍8⃣➡በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያውን ሕልም ያለመው ማነው??

ሀ/ ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ ጻዲቁ ዘካርያስ
ሐ/ንጉሥ አቤሜሌክ
መ/አዳም

//መልስ//፦ ሐ) ንጉሥ አቤሜሌክ

✍9⃣➡ያዕቆብ ስለ ራሔል በአጎቱ ቤት ያገለግለው ለስንት ዓመት ነው??

ሀ/7
ለ/ 14
ሐ/ 21
መ/28

//መልስ//፦ለ) 14 ዓመት

✍1⃣0⃣➡በግብፅ ሐገር የወረደው የመጨረሻው መቅሰፍት ምን ነበር??
ሀ/በሰው ሁሉ ላይ ቁስል መውጣት
ለ/ሁሉም የከብት መንጋ ማለቅ
ሐ/ ምድሪቱ በጓጓንቸር መመታት
መ/በኩር የተባለ ሁሉ መሞት

//መልስ//፦መ) በኩር የተባለ ሁሉ መሞት

✍1⃣1⃣➡ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ ብሎ አገልጋዮን ያጽናና ነቢይ ማነው??

ሀ/ ኤልያስ
በማለትለ/ ኢሳይያስ
ሐ/ ዳንኤል
መ/ ኤልሳዕ

//መልስ//፦ መ) ኤልሳዕ

✍1⃣2⃣➡ከሚከተሉት መካከል የብሉይ ኪዳን ነቢይ የነበረ ማን ነው?

ሀ/ አብድዩ
ለ/ሐጌ
ሐ/ናሆም
መ/ሁሉም ናቸው

//መልስ//፦መ) ሁሉም

✍1⃣3⃣➡ ፈርዖን እስራኤላውያን አለቅም ባለ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ በመጀመርያ ያዘዘው መቅሰፍት ምንድን ነበር?

ሀ/ የዝንብ ምድሪቱን መውረር
ለ/ የወንዝ ወደ ደም መለወጥ
ሐ/ የአሮን በትር ወደ እባን መለወጥ
መ/ በሕዝቡ ላይ ቁስል መመታት

//መልስ//፦ ሐ)የአሮን በትር ወደ እባብነት መለወጥ

✍1⃣4⃣➡.የእስራኤላውያንን ከግብፅ የመውጣት የመጀመርያ ታሪክ የሚዘገበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው??
ሀ/ ኦሪት ዘፍጥረት
ለ/ ኦሪት ዘጽአት
ሐ/ ኦሪት ዘሌዋውያን
መ/ ኦሪት ዘኁልቁ

//መልስ//፦ለ)ኦሪት ዘጽአት

✍1⃣5⃣➡ከዳዊት መዝሙት ቀጥሎ ብዙ ምዕራፎች ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው??
ሀ/ ዘፍጥረት
ለ/ ኤርምያስ
ሐ/ ሐጌ
መ/ ኢሳይያስ

//መልስ//፦መ) ኢሳይያስ

✍1⃣6⃣➡ከጥፋት ዘመን በኋላ ኖኅ ከመርከብ መጥቶ በመጀመሪያ ያደረገው ምንድን ነው?

ሀ/የምሥጋና መዝሙር ዘመረ
ለ/እርሻ ማረስ
ሐ/ መስዋት ማቅረብ
መ/ የወይን ጠጅ መጠጥ

//መልስ//፦ ሐ)መሥዋት ማቅረብ

✍1⃣7⃣➡ለአብርሃም ትዕግስትን ለኢዮብ ጽናት፤ ለሰሎሞን ጥበብ፤ ለኤርሚያስ___ዳሽ ነው??
ሀ/ ትንቢት
ለ/ ሀብት
ሐ/ዕንባ
መ/ፈውስ

//መልስ//፦ ሀ) ትንቢት

✍1⃣8⃣➡ከሚከተሉት መካከል ካህኑ መልከ ጼዴቅን የሚገልፀው የትኛው ነው??

ሀ/ ትውልዱ ከአሕዛብ ወገን መሆኑ
ለ/ የሳሌም ንጉሥ መሆኑ
ሐ/ አብርሃም ከጦርነት ሲመለስ ዐሥራት ገብሮለታል
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

//መልስ//፦ መ/ ሁሉም

✍1⃣9⃣➡እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል ኪዳን ሲገባለት ልጆችህ እንደ___ይበዛሉ አለው.?

ሀ/ እንደ ሰማይ ከዋክብት
ለ/ እንደ ባህር አሸዋ
ሐ/ እንደ ምድር እንስሳት
መ/ መልስ የለም

//መልስ//፦ሀ) ዘፍጥረት 15፥1-21

✍2⃣0⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ በመጀመርያ የተፃፈው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ የትኛው ነው??

ሀ/ ኦሪት ዘፍጥረት
ለ/ መጽሐፈ ሄኖክ
ሐ/ 1ኛ ሳሙኤል
መ/ መጽሐፈ ጦቢት

//መልስ//፦ ለ) መጽሐፈ ሄኖክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyam.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...