2018 ጁን 2, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬) የ31ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እያልን እነሆ የምዕራፍ አራት (፬) የ31ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር እንዲህ ይዘን ቀረብን የዚህ ጥያቄ ምንጭ፦ በማኅበረ ቅዱሳን 420 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ።👇
////////////////

✍ጥ.ተራ.ቁ1⃣ በኦሪት ዘዳግም ተዘግቦ እንደምናገኘው በሞዓብ ሸሎቆ የተቀበረው ማነው??

ሀ// ሙሴ
ለ// ኢያሱ
ሐ// አሮን
መ//ፈርፆን

//መልስ// ሀ) ሙሴ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ 2⃣ንጉሥ አቤሜሌክን ከመፍራታቸው የተነሳ ማንነታቸውን በተጠየቁ ጊዜ እኛ ወንድምና እህት ነን ያሉት ባልና ሚስት እነማን ናቸው??

ሀ/አዳምና ሔዋን
ለ/ያዕቆብና ራሔል
ሐ/ አብርሐምና ሳራ
መ/ዳዊትና ቤርሳቤህ

//መልስ// ሐ) አብርሃምና ሳራ

✍ጥ.ተራ ቁ3⃣ የመጀመርያውን የእስራኤል ንጉሥ ሳኦልን የገደለው ማን ነው??

ሀ/ ንጉሥ ዳዊት
ለ/ የዳዊት ልጅ አቤሴሎም
ሐ/ ራሱን በራሱ
መ/ መልስ የለም

//መልስ//መ) መልስ የለም።

✍ጥ.ተራ ቁጥር4⃣ከሚከተሉት ነገሥታት መካከል ሠለስቱ ደቂቅን /ሦስቱ/ ህፃናትን/ ወጣቶችን በእሳት ውስጥ እንዲጣሉ ያደረገው ማን ነው???

ሀ/አክዓብ
ለ/ ናቡከደነጾር
ሐ/ ዳርዮስ
መ/ኢዮሣፍጥ

//መልስ//፦ ለ) ናቡከደነጾር ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ5⃣ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ስንት ልጆች ነበሩት??

ሀ/ 11
ለ/ 12
ሐ/ 13
መ/14

//መልስ// ሐ/ 13 ናቸው።

✍ጥ.ተራ ቁጥር6⃣ ጥበብ ቤቷን ሠራች  ሰባቱንም ምሦሶዎችዋን አቆመች ያለው ማነው???

ሀ/ ንጉሥ ሳፆል
ለ/ ንጉሥ ዳዊት
ሐ/ ንጉሥ ሰሎሞን
መ/ ቅዱስ ጳውሎስ

//መልስ// ሐ) ንጉስ ሰሎሞን ነው።

✍ጥ.ተራ ቁ.7⃣እያሱና ሕዝበ እስራኤል በጩኸት ያፈረሱት የማነን ከተማ ቅጥር ነበር??

ሀ/ባቢሎን
ለ/ እስክንድርያ
ሐ/ ኢያሪኮ
መ/ አንፆኪያ

//መልስ//፦ሐ) ኢያሪኮ

✍ጥ.ተራ ቁጥር8⃣ከእስራኤል መሳፍንት ውስጥ የማይመደበው የትኛው ነው??

ሀ/ዲቦራ
ለ/ ዮፍታሔ
ሐ/ ሕዝቅያስ
መ/ ሶምሶን

//መልስ//፦ሐ) ሕዝቅያስ ነው።

✍ጥ.ተራ ቁጥር9⃣ንጉሥ ዳዊት ኦርዮንን በማስገደድ ሚስቱን እንደ ወሰደበት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይቺ የኦርዮን ሚስት ማን ትባላለች??

ሀ/ሩት
ለ/አስቴር
ሐ/ ቤርሳቤህ
መ/ ሜልኮል

//መልስ//፦ሐ) ቤርሳቤህ

✍ጥ.ተራ.ቁጥር🔟እስራኤል በሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ዘመን ለሁለት ተከፍለው ነበር፤ ስሜኑ እስራኤል የሚል ስም ወሰደ፤ የደቡቡ ስም ማን ይባል ነበር???
.ሀ/ ሰማርያ
ለ/  የሞዓብ ምድር
ሐ/ ከነዓን
መ/ ይሁዳ

//መልስ//፦መ) ይሁዳ

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣1⃣በአባቱ በንጉሥ ዳዊት ላይ ያመፀው ልጅ ማነው??

ሀ/ መቃቢስ
ለ/ ሰሎሞን
ሐ/ ይሁዳ
መ/አቤሴሎም

//መልስ//፦ መ) አቤሴሎም ነው።

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣2⃣ንጉሥ አክዓብ እስራኤልን የምትገለባበጥ አንተ ነህ ብሎ የተናገረው ማንነው??

ሀ/አብድዩ
ለ/ ኤልሳዕ
ሐ/ ኤልያስ
መ/መልስ የለም።

//መልስ//፦ ሐ) ኤልያስ

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣3⃣ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ መለከቱንም የሚነፉ መዘምራንም መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔር እያመሰገኑና እያከበሩ እግዚአብሔር ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ሲሉ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ከደመናው የተነሳ መቆምና ማገልገል አልቻሉም። ተብሎ የተ ፃፈው ለየትኛው በአል ነው??

ሀ/ ፍልስጤማውያን የመሸነፋቸው በዓል
ለ/ ለእግዚአብሔር ታቦት ቤተ መቅደስ ስለተሰራለት
ሐ/ ተማርካ የነበረችው ታቦተ ጽዮን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት በዓል

መ/ ኤልያስ የበኣልን ካህናት የማሸነፉ በዓላት

//መልስ//፦ ለ)

✍ጥ.ተራ.ቁጥር1⃣4⃣በመጽሐፍ ቅዱሳችን ጥራዝ፣ ከ2ኛ ዕዝራ በኋላ የሚመውጣ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማን ነው??

ሀ/ አስቴር
ለ/ ነህምያ
ሐ/ ዕዝራ ሱቱኤል
መ/ ጦቢት

//መልስ//፦ መ) መጽሐፈ ጦቢት

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣5⃣የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግስታት ሁሉ በይሁዳም ባላቸው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራበት ዘንድ አዞኛል፣ ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን። በማለት የተነገረው ማን ነው??

ሀ/ ንጉሥ ናቡከደነጾር
ለ/ ዕዝራ
ሐ/ የፋሪስ ንጉሥ ቄሮስ
መ/ ንጉሥ ኤዶምያስ

//መልስ//፦ ሐ) ዕዝ 1፥2

✍ጥ.ተራ ቁጥር 1⃣6⃣ወደላ ትባል የነበረችው የመርዶክዮስ እኅት ልጅ ማን ናት???

ሀ/ ርብቃ
ለ/ ራሔል
ሐ/ አስቴር
መ/ ሐና

//መልስ//፦ ሐ)አስቴር

✍ጥ.ተራ ቁጥር1⃣7⃣ከሚከተሉት ውስጥ የዳዊት ሀብት የሆነው የትኛው ነው??

ሀ/ ፈውስ መስጠት
ለ/ በገና መደርደር
ሐ/ ኃይል
መ/ መ ሁሉ መልስ ነው።

//መልስ//፦ መ) ሁሉም


✍ጥ.ተራ.ቁጥር1⃣8⃣ከሚከተሉት ምሥጉን የሚል ቅጽል የሚያሰጠው ሥራ የትኛው ነው??

ሀ/ በክፉዎች ምክር ያልሄዱ
ለ/ በኃጢአት መንገድ አለመሄድ
ሐ/ በዋዘኞች ወንድበር አለመቀመጡ
መ/ ሁሉም መልስ ነው

//መልስ//፦ መ) መዝ.1፥1-3

✍ጥ.ተራ. ቁጥር2⃣0⃣ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። የሚለውን ሃይለ ቃል የተናገረው ማን ነው??

ሀ/ ነቢዩ ዳንኤል
ለ/ ነቢዩ እንባቆም
ሐ/ነቢዩ ዳዊት
መ/ ነቢዩ ኤርሚያስ

//መልስ// መ/ ነቢዩ ኤርሚያስ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cwsaramareyama.890@gmail.com

4 አስተያየቶች:

  1. ጥሩ ነው በጣም ፍጣሪ ከዚ በላይ የምታገለግሉበትን እድሜና ጤና ይስጣቹ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
    ምላሾች
    1. በጣም ሃሪፍ ነው እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጣችሁ እኛንም ያነበብንውን በእዝነ ልቦና ያሳድርብን አሜን፫

      ሰርዝ
  2. መልሱን ስታስቀምጡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሚገኝበትን መልሱ ብትገልፁልን መልካም ነው እግዚአብሔር ይስጥልኝ በርቱ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. ፀጋውን ያብዛላቹ ብዙ እንማርበታለን ግን አንዳንድ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ከመልሱ ጋር አያይዛቹ ብታ ቀምጡልን መልካም ነው እናመሠግናለን

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...