2018 ጁን 13, ረቡዕ

አሻጋሪ ዎች

"አሻጋሪዎች"

ሰባኪው በ አንድ ቤተክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር
ያስተምራል። በየ እለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ። ከ እነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ የመሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው።

አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ፡
ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ቢኖራቹ ይህን ተራራ በገፋችሁት ሂድ እልፍ በል ባላችሁት ግዜ በሄደ። " የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ሃይለ ቃል ገልጾ በ እምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳ።
በሚዞረው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ።
ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዜብሔር አምናለው እግዜብሔርም ይህን ለ እኔ ማድረግ አይሳነውም" በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም ይሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ እቤቱ ግባ።
ሚስቱም በመደንገጥ " ቤተክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ" ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው ብላ በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" ብላ ባለቤቷን ተማጸነች።
በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ፡ ትምህርት ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄዶ፥ " ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው፡ እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ፡ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው።
በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን " ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ እናሻግራለን እንጂ አንሻገርም!" ሲል መለሰለት።
እኛስ በእውነቱ የምንናገረውን የምናስተምረውን የምንሰብከውን እየኖርን ነውን? መልሱን ለእናንተ ትቻለው።
(እኔም ያነበብኩትን እንዲህ አካፈልኳችሁ እናንተም ከተመቻችሁ ለሌሎች አድርሱትsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...