2018 ሴፕቴምበር 9, እሑድ

እንኳን ለዐዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! የዐውድ ዓመት መዝሙሮች

​​🌼#የእንቁጣጣሽ #መዝሙር🌼
                  🌼🌼♥♥♥♥♥♥

እሰይ /ደስ ደስ ይበላችሁ/(፪)
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ
ደስ ደስ ይበላችሁ

      ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)ጌቶች አሉ ብለን
      ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን(፪)እሜቴ አሉ ብለን

አበባዮሽ 🌼 ለምለም   አበባዮሽ 🌼  ለምለም
እንቆቅልሽ   - -  ንግሥት   ልትፈትል ሄዳ - - ንግሥት
ንግስተ አዜብ - -  ንግሥት   እናት ማክዳ - - ንግሥት
በልቧ ያለውን -  ንግሥት   አጫወታቸው - -   ንግሥት
አሰቀምጣ አበባ🌼  ንግሥት  እያሳየችው - -    ንግሥት
መአዛው የሚሸት  - - ከሁለቱ የቱ ነው አለቸው - -  ለንጉሥ 

          ንግስት ሆይ ለጥያቄሽ ጥበብ አለሽ(፪)
      🌼የአገር አምባር የሚሆነው ከልብ ሽተሽ

እንቆቅልሹ -  -  የሳባ    ከበድም ቢለው -  -🌼 የሳባ
ጥበብ ሰላለው - - ንጉሡ  ሚሥጥሩን ሊያውቀው - - ንጉሡ
ክፈት መስኮቱን - -  ሰለሞን   ቢለው ለሎሌው  - -ሰለሞን
ገቡ ንቦቹ  - -  ሊቀስሙ🌼 ከአባባው አርፈው - - ሊቀስሙ
ብልህ ጠቢቡ  - -   መለሠ     ለተጠየቀው - -  በእውነት
ንጉስ ሰለሞን - -   አለ     አልተሠወረው      🌼     በእውነት

 🌼አደይ ቅድስት ሀገሬ እልል በይ (፪)
🌼 ኢትዩዮጲያ የዝና ስሟ በዓለም ተሠማ (፪)
🌼
ለፈጣሪዋ - - ንግሥት   ምስጋና አቅርባ - -   ንግሥት
ኢትዮጲያዊቷ - - ንግሥት   ንግስተ ሣባ   🌼   ንግሥት
ጥበቡን አይታ - -  ንግሥት   አደነቀችው  - -    ንግሥት
ወርቅ ሸቶውን - -  ንግሥት  ዕንቁ ሰጠችው - -   ንግሥት

      ንግስት ሆይ ምስክር ሆንሽ ለሀገርሽ (፪)🌼🌼
      የአምላክን የፈጣሪያችን ስሙን ጠርተሽ (፪)🌼🌼

የኢትዮጵያ ሠዎች  - -ለንግሥት   ቆሙ በተራ - -ለንግሥት
እደጅ ሆነው     🌼   ለንግሥት   ለዙፋን ክብሯ - - ለንግሥት
በመስከረም ወር - -  ለንግሥት   ሀገር ስትገባ - -  ለንግሥት
ይዘው ሥጦታ - -  ለንግሥት   የፈካ አበባ    🌼ለንግሥት

      🌼አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ (፪)🌼🌼
      🌼ኢትዮጲያ በታሪክሽ ጥንታዊት ነሽ (፪)🌼🌼

ኢየሩሳሌም - - ንግሥት   ደርሠሽ መጣሽ - -  ንግሥት
እንኳን በክብር - - ንግሥት   ለዚህ አበቃሽ - - ንግሥት
ከአምላክ በረከት - - ንግሥት  ፍሬ አግኝተሽ - - ንግሥት
የዘሽ ስጦታ - -  ንግሥት   ዕንቁ ለጣጣሽ - - ንግሥት

      🌼ንግስት ሆይ ለታሪክሽ ክብር አለሽ (፪)🌼🌼
      🌼ልጆችሽ አበባዮሽ እያልን እናስታውስሽ (፪)🌼🌼

🌼የአባቶች ተስፋ - -   ለፃድቃን   የነቢያት ትንቢት - - ለፅናት
የሙሴ ፅላት - -     ለፀሎት   የአሮን በትር  - -   ለፅናት
የዳዊት መንግስት - - ለፅናት    ይዘሸ የመጣሽ - -   ከጥንት
አምስቱን አውታር - - ለሠጠሽ   ለሀገር መሠረት -    በእውነት🌼🌼

 🌼 አደይ ቅድስት ኢትዮጵያ እልል በይ (፪)🌼🌼
      🌼ኢትዮጵያ በልጆችሽ ደስ ይበልሽ (፪)🌼🌼

በህገ ልቦና  - -   ህጉን     ፈጣሪን አውቀሽ - -  ህጉን
ህገ ነቢያትን - -  ከዓለም  ፈጥነሽ ተቀበልሽ - - ከዓለም
በብሉይ ኪዳን   🌼ለጌታ    መስዋዕት አቅርበሽ - -  ለጌታ
ተስፋ ካረጉት - - ከአይሁድ ከአስራኤል - - ከአይሁድ
ህገ ወንጌልን-  -በፊት    ይዘሽ ተገኘሽ    🌼    በፊት

      🌼ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ፀጋ አለሽ(፪)🌼🌼
      🌼ስለፈፀምሽ ሦስቱን ህግጋት ለፈጣሪሽ (፪)🌼🌼

ካለፈው ሰህተት - -  ሁላችን    እንድንመለስ - - ሁላችን
አዲሱ ዓመት  - -  ለሁሉም   መጣ ማቴዎስ- -ለሁሉም
ይህም ያልፍና - - በጊዜው    ይመጣል ማርቆስ - - በጊዜው
ሌላው ይተካል - -  በጊዜው    ዘመነ ሉቃስ - - በጊዜው
ወልደነጓድጓድ  - -  በጊዜው  🌼 ሲደርስ ዮሐንስ - - በጊዜው
በየአራት ዓመት -  -  በጊዜው   ለሁሉም ሲደርስ - - በጊዜው
በየዓመቱ  - -  መጥምቁ      ቅዱስ ዩሐንስ - - በጊዜው🌼🌼

      🌼አደይ የብርሃን ጮራ በዮሐንስ በራ(፪)🌼🌼
🌼 ኢትዮጵያ ባሕል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ (፪)🌼🌼

ልጅ አበባ ልጅ አበባዬ    🌼     አዬ ውዲቷ እናቴ
ልጅ አበባ 🌼እያለች እማማ      አዬ ውዲቷ እናቴ
ምክሯን ሁሌ እኔ እንድሰማ    አዬ ውዲቷ እናቴ
እያሻሸች እንድሆን ጤናማ     አዬ ውዲቷ እማማ
አዬ ውዲቷ እናቴ (፪)🌼

 🌼አበባ ለምለም 🌼 ቀጤማ ለምለም
    🌼ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም (፪)🌼

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ🌼
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰዎት ብዬ (፪)
🌼
ይሸታል ዶሮ ዶሮ (፪) ከማምዬ ጓሮ (፪)
ይሸታል የወይን ጠጅ (፪) ከጋሽዬ ደጅ (፪)

      ከበረው ይቆዩ ከብረው 🌼
       አመት አወደ አመት ደርሰው
      ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው
      ትሁት ሰው አክባሪ ሆነው
      የፍቅር ሸማን ለብሰው🌼
      ንስሐ ገብተው ቆርበው
  🌼ከብረው ይቆዩ ከብረው
         
               መዝሙር
      🌼በማህበረ ፊልጶስ🌼saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...