2018 ኦገስት 27, ሰኞ

የምዕራፍ ፭ የ41ኛ ዙር መንፈሳዊ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡አሜን!
`````````````
የምዕራፍ (፭) 41ኛ ዙር

በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ ለተዘጋጀው ጥያቄ እና መልስ መርሐ-ግብር ከአዘጋጁ አካል የማጠቃለያ መልሱ እንደሚከተለው ይቀርባል።
   ✝✝✝


1.የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የትኛው ነው?
ሀ.አብርሃም
ለ.ሔኖክ
ሐ.ሙሴ
መ.ያዕቆብ

✔️ለ

2.ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ዘመን እስራኤላውያን በተለያዪ ቡድኖች ተክፍለው ነበር።እነርሱም፡
ሀ.ሰማርያና ሴኬም
ለ.ሮማዊያን እና እስራኤላውያን
ሐ.ፈሪሳውያን፣ሰዱቃውያን እና ኤሲያውያን
መ.ሰሜን እና ደቡብ እስራኤል

✔️ሐ

3. የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተ-ክርስቲያን የተሠራችው በየትኛዋ ከተማ ነበር?
ሀ.በፊሊጵስዩስ
ለ.በአንጾኪያ
ሐ.በደማስቆ
መ.መልሱ የለም

✔️ሀ

4.የሙሴን ሕግ በጥንቃቄ እንተረጉማለን ሚሉት የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ፈሪሳውያን
ለ.ኤሲያውያን
ሐ.ሰዱቃውያን
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️ሀ

5.ሊቀ-ሐዋርያት ተብሎ ሚታወቀው ማን ነበር?
ሀ.ቅዱስ ቶማስ
ለ.ቅዱስ ዮሐንስ
ሐ.ቅዱስ ታዴዎስ
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️መ

6.ከቅዱሳት አንስት ወገን ያልሆኑት የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ቅድስት ኤልሳቤጥ እና ቅድስት ሀና
ለ.ጤግላና ጲስ
ሐ.ጲላግያና መሪና
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️መ

7.ከምሥጢር ሐዋርያት መካከል ያልሆነ፡
ሀ.ዮሐንስ
ለ.ያዕቆብ-ወልደ ዘብዴዎስ
ሐ.ጴጥሮስ
መ.ያዕቆብ-ወልደ እልፍዮስ

✔️መ

8.«ይሁዳ»ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ.ፍቁረ-እግዚእ
ለ.ዓለት
ሐ.በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው.
መ.ጸጋ የበዛለት ማለት ነው።

✔️ሀ

9.የኒቂያ ጉባኤ ሰብሳቢ ማን ነበር?
ሀ.ቄርሎስ
ለ.እለስክንድሮስ
ሐ.ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ
መ.ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

✔️ለ

10.በቁስጥንጥንያው ጉባኤ ዋነኛው መናፍቅ ማን ነበር?
ሀ.ንስጥሮስ
ለ.መቅዶንዮስ
ሐ.አርዮስ
መ.አውጣቂ

✔️ለ

11.ከሚከተሉት የእስክንድርያ ሊቃነጳጳሳት መካከል«የቤተክርስቲያን ምሰሶ»ሚባለው ማን ነው?
ሀ.ቅዱስ እለስከንድሮስ
ለ.ቅዱስ ቄርሎስ ቀዳማዊ
ሐ.ቅዱስ አትናቴዎስ
መ.ቅዱስ ቄርሎስ 6ኛ

✔️ሐ

12.አቡነ ቄርርሎስ ቀዳማዊ ለእስክንድርያ ቤተ-ክርስቲያን በቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ስንተኛው ፓትርያርክ ነው?
ሀ.12
ለ.23
ሐ.24
መ.32

✔️ሐ

13.በነገረ ሥጋዌ ላይ የ«እውነተኛ ተዋህዶ-Real Unification»ሚልን ቀመር ያዘጋጀ ማን ነበር?
ሀ.ቅዱስ ቄሮሎስ ቀዳማዊ
ለ.ቅዱስ አትናቴዎስ
ሐ.ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ
መ.መልሱ አልተሰጠም

✔️ሀ

14.የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቡነ ባስልዮስ የምንኩስና(የቆብ) ስማቸው ማን ነበር?
ሀ.ንቡረእድ ገብረማርያም
ለ.እጨጌ ገብረጊዮርጊስ
ሐ.ፓትርያርክ ገብረእግዚአብሔር
መ.እጨጌ ተክለሃይማኖት

✔️ለ

15.ምንፍቅና የተጀመረው በማን ነበር?
ሀ.በሳጥናኤል
ለ.በይሁዳ
ሐ.በአርዮስ
መ.በዱዲያኖስ

✔️ሀ

16.በሐዋርያት ጊዜ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ መናፍቃን እነማን ናቸው?
ሀ.ግኖስቲኮች
ለ.አርዮሳውያን
ሐ.ቢጽሐሳውያን
መ.ሁሉም ነበሩ

✔️ሐ

17.ፍልስፍና፣ጥንቆላ እና ምትሐታዊ ሕይወት የነበራቸው የትኞቹ ናቸው?
ሀ.ግሪኮች
ለ.ቢጽ ሐሳውያን
ሐ.ይሁዳውያን
መ.ግኖስቲኮች

✔️መ

18.የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሲያን ቅጽል መጠሪያዋ ምንድን ነው?
ሀ.ጎርጎርዮሳዊት
ለ.ያዕቆባዊት
ሐ.እስጢፋኖሳዊት
መ.ማርቆሳዊት

✔️ለ

19.የመጀመሪያው የዓለም አብያተ-ክርስቲያናት ኅብረት ጉባኤ የተካሄደው የት ነበር?
ሀ.ኢቫንስተን-አሜሪካ
ለ.ናይሮቢ-ኪንያ
ሐ.ኤፕሳላ-ስዊድን
መ.አምስተርዳም-ሆላንድ

✔️መ

20.የመላው አፍሪካ አብያተ-ክርስቲያናት አንድነት ጽ/ቤቱ የት ይገኛል?
ሀ.አዲስአበባ-ኢትዮጵያ
ለ.ናይሮቢ-ኬንያ
ሐ.ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪካ
መ.አክራ-ጋና

✔️ለ

ማጠቃለያ መልሳችን ላይ ስህተት ካለ እርሙን።
saramareyama.890@gmail.com

2 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...