2018 ሴፕቴምበር 23, እሑድ

የመስቀል መዝሙሮች !

ያሬዳዊ መዝሙሮች:
©✝መዝሙር በእንተ መስቀሉ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ©⤵️

©ይቤሎሙ ኢየሱስ

ይቤሎሙ ኢየሱስ/፪/ለአይሁድ/፪/
እመኑ ብየ ወእመኑ በአቡየ አበርህ በመስቀልየ ለእሊአ /፪/
#ወረብ


©ያሬድ ካህን
ያሬድ ካህን /፪/ ፀሐያ ለቤተክርስቲያን/፪/
አሰርገዋ ለኢትዮጵያ በስብሐት ወበሃሌ  ሉያ/፪/

#ዮምሰ
ዮምሰ ለእሊአየ /፪/
አበርህ በመስቀልየ/፬/

      #ወረብ

©ቤተ ክርስቲያን ርእየቶ

ቤተ ክርስቲያን ርእየቶ ቅንወ ለዘበጎልጎታ ደሙ ተክዕወ/፪/
ከመ እግረ ፀሐይ ሥኑ ኀተወ በዓለ መስቀል ዘዮም ትገብር ህልወ/፪/
ትርጉም:- በጎልጎታ ደሙ የፈሰሰውን አምላክ ቤተ ክርሲያን አየችው ደም ግባቱም እንደ ፀሐይ አውታር(ጮራ) አበራ የዛሬው የመስቀል በዓልም ለዘለዓለም ታበራለች

©መስቀሉሰ

መስቀሉሰ ለክርስቶሰ ብርሃን ነአምን ትብሌ ቤቴ ክርስቲያን/፪/
ዛህኑ ለባሕር ወመርሶ ለአሕማር ዝንቱ ውእቱ መስቀል/፪/
ትርጉም:-የክርስቶስ መስቀል ለመናምን ሰዎች ብርሃን ነው መስቀል የባሕር ፀጥታው የመርከቦች ወደብ ነው ትላለች ቤተ ክርስቲያን

©መርሕ ለፍኖት

ሃሌ ሉያ መርሕ ለፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን ሞገስ/2/
ዝንቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብኦ ውስተ ገነት/2/
ሃሌ ሉያ መሪ ነው በመንገድ ሞገሳቸው ለጻድቃን ሞገስ/2/
ይኸ መስቀል ነው አዳምን የመለሰው ወደ ገነት/2/

©ብከ ንወግዖሙ

ብከ ንወግዖሙ ለኵሎሙ ፀርነ/፪/ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት/፪/
በእንተ ዝንቱ  ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለ አብ /፪/

ትርጉም፡- ቅዱስ ዳዊት በትንቢት መንፈስ እንዲህ አለ፣ በአንተ
ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፤ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል/ኢየሱስ ክርስቶስ/ በተሰቀለበት፡፡
©ትቤሎ እሌኒ

ትቤሎ እሌኒ ለኪራኮስ ንግረኒ አፍጥን /፪/
ኀበ ሀሎ መስቀሉ ለኢየሱስ/፪/ ክርስቶስ /፬/

ትርጉም፡- ዕሌኒ ኪራኮስን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል
የት እንዳለ ፈጥነህ  ንገረኝ አለችው፡፡

©መስቀል አብርሃ

መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሰርገወ ኢትዮጵያ/፪/
እምኩሉሰ ፀሐየ አርአየ ዕፀ መስቀል/፪/

ትርጉም፡- መስቀል አበራ ኢትዮጵያንም  በከዋክብት ሸለመ
 ከሁሉ ይልቅ መስቀል እንደ ፀሐይ ደምቆ/በርቶ/ ታየ፡፡

©ለዕፀ መስቀል

ርእዩ ዕበዮ ለዕፀ መስቀል /፪/
ዘመጠነዝ/፪/ትርሢተ ክብር ትህትና ወፍቅር /፪/

ትርጉም፡-የዕፀ መስቀሉን ክብሩን ትህትናውን ፍቅሩን ሽልማቱን     
ምን ህል እንደሆነ እዩና አድንቁ ወይም ከፍ ከፍ አድርጉት፡፡

  ©ርእዩ ዕበዮ
ርእዩ ዕበዮ ለቅዱስ ዕፀ መስቀል /፪/
ዕውራን ይሬእዩ ወጽሙማን ይሰምዑ እለ ለምጽ 
ይነጽሑ እለ መጽኡ ኀቤሁ /፪/

ኑ እዩ የመስቀሉን ተአምራት /፪/
እውሮች ያያሉ ደንቆሮዎች
ይሰማሉ ለምጻሞችም           
ይነጻሉ ወደ እርሱ የመጡ ሁሉ /፪/

©ዮም መስቀል

ዮም መስቀል አስተርአየ እለ ማሰነ ፍጥረተ አሠነየ/፪/
ዮም መስቀል ተኬነወ ወዘተጼወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ/፪/

ትርጉም፡-ዛሬ መስቀል ተገለጠ የጠፉትን ሰዎች አዳነ ዛሬ
መስቀልብልሃተኛ ሆነ ምርኮኞች ወገኖቹንም
በክርስቶስ ደም አዳነ፡፡

©ወበእንተዝ

ወበእንተዝ አዘዙነ መምህራነ ቅዱስ ወንጌል/፪/
ንስግድ ለመስቀል ወለማርያም ድንግል/፬/

ትርጉም፡- ቅዱስ ወንጌልን የሚያስተምሩ መምህራን
ለመስቀልና  ለድንግል ማርያም እንድንሰግድ ያዝዙናል፡፡

©ሀብሩ ቃለ

ሀብሩ ቃለ ነቢያተ/፪/
ወይቤሉ መስቀል ብርሃን/፪/ ለኵሉ ዓለም /፪/

ትርጉም፡-ነቢያት መስቀል ለዓለም ሁሉ ብርሃን ነው
ብለው በአንድ ቃል  ሆነው  ተናገሩ፡፡

© ኀበ ቀራንዮ

ኅበ ቀራንዮ ደብረ መድኃኒት/2/
ቀራንዮ/2/ ኀበ ቀራንዮ/2/
የመስቀሉ ቃል ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው/4/
ለማያምኑት ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ሕይወት ነው/2/
እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ/4/
እንመነው አንካደው ፈጣሪያችን ቸር ነው/2/
እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት/2/
እንመሰክራለን ማርያም  አማላጅ ናት/4/
እንመናት አንካዳት የአምላክ እናት ናት/2/
ኅበ ጥበባት ኀበ ልሳናት/4/
ዮሐንስ/2/ ወንጌለ ስብከት/2/

#በመስቀሉ #ቤዘወነ

በመስቀሉ ቤዘወነ ወበደሙ ተሰሃለነ/2/
አምላከ ምሕረት ውእቱ መድኃኒነ
አምላከ ምሕረት ውእቱ
በመስቀሉ ቤዛ ሆነን ሞትን ሽሮ ከሞት አዳነን/2/
የምሕረት ጌታ ነውና ይቅር አለን
የምሕረት ጌታ ነውና

#ብርሃን ወጣ

ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ
የአምላክ እና የሰው ልጆች እውነተኛ እርቅ
ደስ ይበለን በመስቀሉ ብርሃን
እልል እንበል በአንድነት ሆነን
ተነሳልን መድኃኒታችን

ከፊት ለፊት በመሳሉ የመስቀሉ ነገር
የሚወደው ሐዋርያ የወንጌል መምህር
ዮሐንስም ስቅለቱን በማየቱ
ሲያዝን ኖረ በምድራዊ ሕይወቱ
ቢያሰቅቀው ሞቱ ግርፋቱ

ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው
በዓለም ጥበብ ለሚኖሩት እውነት ተሰኗቸው
ለጠቢብ ሰው በመንፈስ ለሚኖረው
የመዳን ቀን እውነተኛ ዓርማ ነው
ከገሀነም እሳት የሚያድን ነው

እስከመስቀል ላልተለየው ቅዱስ ሐዋርያ
ለዮሐንስ ለወንጌል ሰው የፍቅር ባለሞያ
ምስጋናችን በምድር ይድረሰው
እንድናለን በሰጠው ምሳሌው
ሰዎች ሁሉ

#ኧኸ #በመስቀልከ

ኧኸ በመስቀልከ ኧኸ ጽልመተ አብራህከ
ኧኸ በመስቀልከ ኧኸ ሙታነ  አንሣእከ/፪/
ኧኸ ወዘተዓጉለ ረዳእከ በመስቀልከ/፪/
ትርጉም:-በመስቀልህ ጨለማን አበራህ ሙታንንም አነሣህ የጠፋውንም በመስቀልህ ረዳኸው/አዳንኸው/።

#በኃይለ #መስቀሉ

 በኃይለ  መስቀሉ/2/ይዕቀበነ
በኃይለ መስቀሉ /3/  ይዕቀበነ/2/


      #©መስቀል #ብርሃነ
መስቀል ብርሃነ ለኲሉ ዓለም
መሠረተ ለቤተክርስቲያን/2/

ወሀቤ ሰላም መድኃኔዓለም መስቀል
መድኅን ለእለ ነአምን/2/

መስቀል ብርሃን ነው ለመላው  ዓለም
መሠረተ ነው ለቤተክርስቲያን/2/
ሰላምን ሰጪ ነው መድኃኔዓለም መስቀል
አዳኝ ነው ለኛ ለምናምን /2/

        #©አለው #ሞገስ
አለው አለው ሞገስ  ኧኸ  አለው ሞገስ
የመስቀል በአል ሲደርስ ኧኸ  አለው ሞገስ
አለው አለው አበባ  ኧኸ  አለው አበባ
የመስቀል በዓል ሲገባ  ኧኸ አለው አበባ
አለው አለው ደስታ  ኧኸ አለው ደስታ
መስቀል ሲከብር በእልልታ  ኧኸ አለው ደስታ
አለው አለው ሰላም ኧኸ አለዉ ሰላም
መስቀል ሲታይ በአለም  ኧኸ አለው ሰላም
አለው አለው አለኝታ  ኧኸ አለን አለኝታ
እፀመስቀል መከታ  ኧኧ አለን አለኝታ
እዩት እዩት ሲያበራ  ኧኸ እዪት ሲያምር
የመስቀል በዓል ደመራ  ኧኸ እዪት ሲያበራ
እዪት እዩት ሲያምር  ኧኸ እዩት ሲያም
መስቀል በዓለም ሲከብር  ኧኸ እዪት ሲያምር


   #©አየኸው #ደመራ
አየኸው ደመራ መስቀል ሲያበራ/2/
መስቀል አለ ወይ ቆሟል ወይ
አለእንጂ ለምጽ ያነጻል እንጂ
ያው ቆሟል ድውይ ይፈውሳል
      አምነዋለሁ የት አገኘዋለሁ
አለልሽ እሰሪው በአንገትሽ
ከልብሽ ተሳለሚው አምነሽ
      እኮራለሁ በእፀ መስቀል
ይፈውሳል ሙታንን ያስነሳል
ድል ያደርገል ድውይ ይፈውሳል


#©ዕሌኒ #ንግስት
እሌኒ ንግሥት ሐሠሠት መስቀሉ/2/ኧኸ
ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ክብሩ/4/
ትርጉም=ዕሌኒ ንግሰት መስቀሉን ፈለገች
ነቢይ እንባቆም የጌታችንን ሥራ አደነቀ።


    #©እንተ ተሐንፀት
እንተ ተሐንፀት በስሙ ወተቀደሰት
በደሙ ቤተክርስቲያን/2/
ወተአትበት/2/ በዕፀ መስቀሉ
እስመ ኃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ/2/
ትርጉም=በስሙ የታነፀች በደሙ የቀደሳት በዕፀ መስቀሉ የተባረከች ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ሀይል በላይዋ አለ።

  #©ከመትባርከነ
ከምትባርከነ በስቀልከ ክቡር/2/
ከመ ይኲን ቤዛ/2/ ለኩሉ አsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...