2018 ኦገስት 14, ማክሰኞ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የምዕራፍ አራት(፬) የ40 ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር

@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው  ከሚለው   መጽሐፍ የተወሰደ⤵

➡1⃣ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት ያለፉባት ከተማ ማን ትባላለች???
ሀ/ አንጾኪያ
ለ/ ሰማርያ
ሐ/ሮም
መ/ መቄዶንያ

✅ሐ

➡2⃣ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ በነበረበት ወቅት ከሰይጣን የቀረበለት ፈተና ምን ነበር??

ሀ/ የትዕቢት
ለ/ የስስት
ሐ/ የፍቅረ ነዋይ
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

➡3⃣ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ በላከው የመጀመርያ መልእክቱ ላይ በመጥፎ ምግባሩ ምክንያት አንድን ሰው ከመካከላቸው እንዲያስወግዱት ነግሮቸው ነበር። ሁለተኛ መልእክቱ ላይ ስለዚህ ሰው ምን አላቸው??

ሀ/ እስካሁ ባለማበረራቸው ተበሳጨ
ለ/ ይቅር እንዲሉት መከራቸው
ሐ/ ማንም ሰው እንዳያናግረው ፈረደበት
መ/ መልስ የለም

✅ለ. 1ኛ.ቆር,5፥4-5

➡4⃣ቅዱስ ጳውሎስ ከነዚህ እቃዎች መካከል ሰዎችን በምን መስሏቸዋል???

ሀ/ በሸክላ እቃ
ለ/ በጠርሙስ
ሐ/ በማንኪያ
መ/ በመጥረቢያ

✅ሀ

➡5⃣ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጴጥሮስን በአንጾኪያ ከተማ ፊት ለፊት የተቀዋወመው ለምን ነበር??

ሀ/ የስህተት ትምህርት በማስተማሩ
ለ/ ራሱን ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመለየቱ
ሐ/አይሁድን ሲያይ ከአሐዛብ ጋር የነበረውን ግንኙነት በማቋረጡ
መ/መልስ የለም

✅ሐ..
➡6⃣ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ መጀመርያ የታየው ለማን ነው??

ሀ/ ለሰሎሜ
ለ/ ለማርያም መግደላዊት
ሐ/ ለቅዱስ ጴጥሮስ
መ/ ለአርማትያሱ ዮሴፍ

✅ለ

➡7⃣በመጀመርያ ለአገልግሎት የተመረጡ ዲያቆናት ብዛት ስንት ነው?

ሀ/ 5
ለ/ 6
ሐ/ 7
መ/ 1

✅ሐ.

➡8⃣መልካም ዕድልን መረጠች ከእርሷም አይወሰድባትም ብሎ ክርስቶስ የተናገረላት ሴት ማን ናት???

ሀ/ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ለ/ ኤልሳቤጥ
ሐ/ ማርያም የአላዛር እኅት
መ/ ማርያም መግደላዊት

✅ሐ.

➡9⃣ስለ ጽድቅ የሚራቡ ብፁዓን ናቸው??

ሀ/መጽናናት ያገኛሉና
ለ/ ምድርን ይወርሳሉና
ሐ/ ይጠግባሉና
መ/ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና

✅ሐ.

➡1⃣0⃣በሌላ ስሙ "የቅዱስ ጴጥሮስ ወንጌል በመባል የሚታወቀው የወንጌል ክፍል የትኛው ነው?

ሀ/ የማቴዎስ ወንጌል
ለ/ የማርቆስ ወንጌል
ሐ/የሉቃስ ወንጌል
መ/ የዮሐንስ ወንጌል

✅ለ

➡1⃣1⃣የሕዝብ መምህር በመባል የሚታወቀው ሐዋርያ ማን ነው?

ሀ/ ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ ቅዱስ ጳውሎስ
ሐ/ ቅዱስ ታዴዎስ
መ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ

✅ለ

➡1⃣2⃣ከዐራቱ ወንጌላዊያን መካከል በንስር የሚመሰለው ማን ነው??

ሀ/ ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ ቅዱስ ሉቃስ
መ/ ቅዱስ ዮሐንስ

✅መ.

➡1⃣3⃣ከሚከተሉት ቋንቋዎች መካከል መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመርያ ያልተፃፈበት የትኛው ነው??

ሀ/ ፅርዕ/ግሪክ/
ለ/ ዕብራይስጥ
ሐ/ዐረብኛ
መ/ አረማይክ

✅ሐ

➡1⃣4⃣ከሚከተሉት ከተሞች መካከል ቅዱስ ጳውሎስ ያልጎበኘው የትኛው ነው??

ሀ/ አንጾኪያ
ለ/ አቴና
ሐ/ እስክንድርያ
መ/ ቤርያ

✅ሐ.

➡1⃣5⃣የጠፋው ልጅ ታሪክ በየትኛው የወንጌል ክፍል ይገኛል??

ሀ/ በማቴዎስ ወንጌል
ለ/በማርቆስ ወንጌል
ሐ/በሉቃስ ወንጌል
መ/ በዮሐንስ ወንጌል

✅ሐ.

➡1⃣6⃣የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የተቀበለው በማን አማካኝነት ነው??

ሀ/ በቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ በቅዱስ ጳውሎስ
ሐ/ በቅዱስ ዮሐንስ
መ/በቅዱስ ጢሞቴዎስ

✅ሀ

➡1⃣7⃣ክርስቶስ ሊሰቀል ባለበት ሰዓት የሚያስጨንቅ ሕልም ያየችውና ባሏ እንዲጠነቀቅ የመከረችው የማን ሚስት ነበረች??

ሀ/ የሊቀ ካህናት ሐና
ለ/የጲላጦስ
ሐ/የሄሮድስ
መ/የአግሪጳ

✅ለ

➡1⃣8⃣እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ዮሴፍና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ከስደት መልስ የኖሩበት ከተማ__ነው??

ሀ/ ናዝሬት
ለ/ ቤተልሄም
ሐ/ቅፍርናሆም
መ/ኢያሪኮ

✅ሀ

➡1⃣9⃣"ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም" ብሎ ጌታችን  ስለነማን ነው የተናገርው??

ሀ/ ቤተ ክርስቲያንና ሰይጣን
ለ/የራሳችን ፍላጎትና የእግዚአብሔር ፍላጎት
ሐ/እግዚአብሔርና ገንዘብ
መ/መልስ የለም

✅ሐ

➡2⃣0⃣የቅዱስ ጴጥሮስ አማት በሽታዋ ምን ነበር??

ሀ/ለምጽ
ለ/ፍርሃት
ሐ/ንዳድ
መ/ደም መፍሰስ

✅ሐ
🌹🌹🌹🌹🌹
ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ከስተታችን አርሙን.?
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜንsaramareyama.890Gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...