2018 ኦገስት 4, ቅዳሜ

የምዕራፍ አራት(፬)የ38ኛዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፫

↪የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄና መልስ↩

➡ማጠቃለያ መልስ⤵

የምዕራፍ አራት(፬)/የ38ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር

@ምንጭ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ከቀረበው 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ⤵

➡1⃣ከሚከተሉት ውስጥ ከሐዋርያው  ቅዱስ ጳውሎ ጋር በጉዞ የተሳተፈው ማን ነው??
ሀ/ቲቶ
ለ/ ሉቃስ
ሐ/ጢሞቴዎስ
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

➡2⃣የመጥምቀ ቅዱስ ዮሐንስ አንገት እንድትቆረጥ ያደረገው ማን ነው??

ሀ/ጢባርዮስ ቄሳር
ለ/ፊልክስ
ሐ/ ሄሮድስ
መ/ፈርዖን

✅ሐ.

➡3⃣ከመጠራቱ አስቀድሞ ከሰዱቃውያን ወገን የሆነው ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/ ሉቃስ
ለ/ ሰምዖን
ሐ/ቶማስ
መ/ታዴዎስ

✅ሐ

➡4⃣ጴጥሮስ ለስምዖን፣ ማቴዎስ ለሌዌ፣ ቶማስ ፣ ታዴዎስ ለ___ ነው?

ሀ/ሳውል
ለ/ልብድዮስ
ሐ/ናትናኤል
መ/ለዲዲሞስመ/ስምዖን ቀነናዊ

✅ለ.

➡5⃣"ጌታችን የኢያአሮስን ልጅ ከሙታን በአስነሳ ጊዜ አብረውት የነበሩት ደቀ መዛሙት እነማን ነበሩ??

ሀ/ 12ቱ የሐዋርያት
ለ/ጴጥሮስ፣ እንድርያስ
ሐ/ ዮሐንስ፣ያዕቆብና ጴጥሮስ
መ/ያእቆብ፣ፊልጶስ፣እንድርያስ ያዕቆብ

✅ሐ.

➡6⃣"አብን አሳየንና ይበቃናል። ያለው ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/እንድሪያስ
ለ/ዮሐንስ
ሐ/ፊልጶስ
መ/ጴጥሮስ

✅ሐ.

➡7⃣ለአብ መርዓቱ ለወልድ ወላዲቱ፣ ወለመንፈስ ቅዱስ ___

ሀ/ታቦት
ለ/ ጽርሐ ቤቱ
ሐ/እናቱ
መ/ መልስ የለም

✅ለ.

➡8⃣ከዐራቱ ወንጌላውያን መካከል ሐኪምም ሠዓሊም የነበረው ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ቅዱስ ሉቃስ
መ/ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሐ.

➡9⃣ጌታችን ደጋግሞ እኔ ነኝ በማለት ያስተማረው ትምህርት በየትኛው የወንጌል ክፍል ላይ ይገኛል?

ሀ/በማቴዎስ ወንጌል
ለ/ በማርቆስ ወንጌል
ሐ/በሉቃስ ወንጌል
መ/ በዮሐንስ ወንጌል

✅መ.

➡🔟ጌታችን በአዛኙ ሳምራዊ ምሳሌ የመሰለው ምን በመጠየቁ ነው??

ሀ/ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው
ለ/የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ
ሐ/ ባልንጀራዬ ማን ነው?
መ/ለሌሎች እንዴት  መልካም እናድርግ

✅ሐ.

➡1⃣1⃣ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስንት መልእክታትን ጽፏል??

ሀ/12
ለ/14
ሐ/15
መ/7

✅ለ.

➡1⃣2⃣ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ያጠመቀው ማን ነው?

ሀ/ ቅዱስ እስጢፋኖስ
ለ/ ቅዱስ ፊሊጶስ
ሐ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ
መ/ ቅዱስ ቲቶ

✅ለ.

➡1⃣3⃣ክርስቶስ ሊሰቀል ወደ ጎለጎታ በሚሄድበት ወቅት መስቀሉን ይሸከም ዘንድ ግድ ያሉት ሰው ማን ነው?

ሀ/አሌክሳንድሮስ
ለ/ሩፎስ
ሐ/ የአርማትያሱ ዮሴፍ
መ/የቀሬናው ስምዖን

✅መ.

➡1⃣4⃣የቁም ተዝካሩን/ሀብቱን በመጽውቶ/በማውጣት ጌታን የተከተለው ወንጌላዊ ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ቅዱስ ሉቃስ
መ/ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሀ.

➡1⃣5⃣ትንሳዔ ሙታን የለም ይሉ የነበሩት እነማን ነበሩ??

ሀ/ፈሪሳውያን
ለ/ሰዱቃሰዱቃውያን
ሐ/ኤሴያውያን
መ/መለካውያን

✅ለ

➡1⃣6⃣ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር አይደለም?

ሀ/ ጢምቲዎስ
ለ/ቲቶ
ሐ/ሉቃስ
መ/አፍሮዲ
ሠ/ሲላስ
ረ/እስጢፋኖስ

✅ረ

➡1⃣7⃣ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ የአይሁድ ንጉሥ፣ የናዝሪቱ ኢየሱስ የሚለው ጽሑፍ በሦስት ቋንቋዎች ተጽፏል።ከሚከተሉት ውስጥ ያልተፃፈበት ቋንቋ የትኛው ነው??

ሀ/ሮማይስጥ
ለ/ሱርስት
ሐ/ግሪክ
መ/ዕብራይስጥ

✅ለ

➡1⃣8⃣መጽሐፍ ቅዱስ 66 ብቻ ሳይሆን 81 እንደሆነ ለማጠየቅ ከመጽሐፈ ሄኖክ የጠቀሰ ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ያዕቆብ
ለ/ቅዱስ ቶማስ
ሐ/ቅዱስ በርተሎሜዎስ
መ/ቅዱስ ይሁዳ

✅.መ.

➡1⃣9⃣ከሚከተሉት ውስጥ የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት እንደሚያደርግ የተጻፈለት ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ/ቅዱስ ዮሐንስ
ሐ/ቆርኔሌዎስ
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ.

➡2⃣0⃣ሐናንያና ሰጲራ መሬት ሽጠው ወደ ሐዋርያቱ እግር ሥር አምጥተው ነበር። ነገር ግን ሁለቱም በሞት ተቀስፈዋል፣ በምን ምክንያት.?

ሀ/ የሰው መሬት በመሸጣቸው
ለ/ከመሬቱ ሽያጭ አስቀርተው እኩሌተውን በመስጠታቸው
ሐ/በሐዋርያቱ ላይ በማጉረምረማቸው
መ/መልስ የለም

✅ለ.

🖊ማጠቃለያ መልስ ይህ ይመስላል ስተት ከአለ አርሙን.?

✝ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜንsaramareyama@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...