2018 ጁላይ 23, ሰኞ

የምዕራፍ አራት(፬)/የ37ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

✍የምዕራፍ ፬የ37ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልሶች


1⃣➡ስለ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የተነበየ ነቢይ ማን ነው??

ሀ/ኢሳይያስ
ለ/ኤርምያስ
ሐ/ሕዝቅኤል
መ/ዘካርያስ

✅ሀ.

2⃣➡የነጎድጓድ ልጆች በመባል የሚታወቁት እነማን ናቸው??

ሀ/ዮሐንስና ጴጥሮስ
ለ/ ያዕቆብና ጤሞቴዎስ
ሐ/ ዮሐንስና ያዕቆብ
መ/ ማቴዎስና ስምፆን

✅ሐ.

3⃣➡የተራራው ስብከት በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል  ይገኛል??
ሀ/ በማቴዎስ ወንጌል
ለ/ በሉቃስ ወንጌል
ሐ/ በሐዋርያት ሥራ
መ/በመጽሐፈ ነገስት

✅ሀ.ማቴ 5፥1

4⃣➡ለስም አጠራሩ ክብር ይሁንና ጌታችን መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ "ቀበሮ" የሚል ቅፅል ስም የሰጠው ንጉሥ ማን ነው??
ሀ/አውግስጦስ ቄሳር
ለ/ሄሮድስ
ሐ/ ጴላጦስ
መ/አርኬላዎስ

✅ለ.

5⃣➡ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን አስቀድሞ የላከው ወደ የትኞቹ ነበር??

ሀ/ ወደ አሐዛብ
ለ/ ወደ ሰማርያ
ሐ/ወደ ጠፉት የእስራኤል ልጆች
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅ሐ. ማቴ 28፥19

6⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ማን ነው??
ሀ/ፊልጶስ
ለ/ስምዖን
ሐ/እንድሪያስ
መ/በርተሎሜዎስ

✅ሐ.ዮሐ.1፥41

7⃣➡"እውነት ምንድን ነው?? ብሎ ጌታችንን  የጠየቀው ማን ነው??

ሀ/ ቀያፋ
ለ/ጲላጦስ
ሐ/ሄሮድስ
መ/ኒቆዲሞ

✅ለ.ዮሐ.18፥38

8⃣➡በሐዋርያት ሥራ እንደተዘገበው የመጀመርያው የኢየሩሳሌም  ጳጳስ ማን ነው??

ሀ/ ቅዱስ ቶማስ
ለ/ቅዱስ ጳውሎስ
ሐ/ቅዱስ ታዴዎስ
መ/ቅዱስ ያዕቆብ

✅መ.

9⃣➡ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለራሱ  ለሐዋርያት በሚናገርበት ሰዓት ቅዱስ ጴጥሮስ "ይህስ አይሁንብህ; ሲለው ጌታችን ምን ብሎ መለሰለት?

ሀ/ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ
ለ/እኔም እልሀለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ
ሐ/ "ሒድ አንተ ሰይጣን
መ/ "ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ

✅ሐ..ማቴ 16፥23

1⃣0⃣➡"በነጋታው ሲፈረድበት፣ በእስር ላይ ሳለ የሰላም እንቅልፍ የተኛው ማን ነው??

ሀ/ ቅዱስ ጳውሎስ
ለ/ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ/ቅዱስ ሲላስ
መ/ቅዱስ ያዕቆብ

✅ለ.ሐዋ 12፥1-10

1⃣1⃣➡እመቤታችን ለዳዊት ልጅ ለሰሎሞን የታተመች ምንጭ፣ ለሕዝቅኤል የተዘጋጅ መቅደስ፣ ለኤልያስ_____ናት??

ሀ/ሠረገላ
ለ/ደመና
ሐ/ሽቶ
መ/ዮርዳኖስ

✅ለ.

1⃣2⃣➡በፊልጲሲዩስ ከተማ ለመጀመርያ ጊዜ ክርስቲያን የሆነው ማን ነው??

ሀ/ልድያ
ለ/የወኅኒው ጠባቂ
ሐ/ድሜጥሮስ
መ/ባርናባስ

✅ሀ.የሐዋርያት ሥራ 16፥11

1⃣3⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ የአርማትያሱ ዮሴፍን የሚገልጸው የትኛው ነው??
ሀ/ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ በመስቀል ሥር ተገኝቷል
ለ/በስውር የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነበር
ሐ/ክርስቶስን በአይሁድ ልማድ ገንዞታል
መ/ለ እና ሐ መልስ ይሆናሉ

✅መ.ዮሐ 19፥38-40

1⃣4⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ ተዋህዶን በተሻለ ሁኔታ የሚገልጸው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው ??

ሀ/1ኛ.ቆሮ 11፥1
ለ/ዮሐ.1፥16
ሐ/ሉቃ.23፥34
መ/ማር. 5፥34

✅ለ.ዮሐ.1፥16

1⃣5⃣➡የጌታችን ደቀ መዛሙርት በሰንበት ቀን ተርበው እሸት በቀጠፉ ጊዜ ፈሪሳውያን በጌታ ፊት ከሰዋቸው ነበር። ክርስቶስ ግን ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን አንድ ሰው በመጥቀስ ከካህናት በቀር በማንም መብላት የሌለበትን የመሥዋዕቱን ኅብስት መብላቱን ጠቅሶ ገሥጿቸዋል። ይህ የብሉይ ኪዳን ሰው ማን ነው??

ሀ/ ነቢዩ ኤልያስ
ለ/አብርሃም
ሐ/ቅዱስ ዳዊት
መ/ጠቢቡ ሰሎሞን

✅ሐ.ማቴ ም 12፥3

1⃣6⃣➡"እንግዲህ ከክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም" ያለው ሐዋርያ ማን ነው??

ሀ/ቅዱስ ጳውሎስ
ለ/ ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ
መ/ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሀ.

1⃣7⃣➡ከሚከተሉት ትዛዛት ውስጥ ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ሐዋርያትን የአዘዛቸው የትኛው ነው??
 ሀ/ ሂዱና አሐዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው
ለ/ህጌን አስተምሯአቸው
ሐ/ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው
መ/ በየኢየሱስ ስም አጥምቋቸው

✅ሀ.ማቴ 12፥3

1⃣8⃣➡"አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ,? የሚለው ቃል ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገረው ነው። ከብሉይ ኪዳን አባቶች መካከል ይህን ቃል በትንቢት የተናገረው ማን ነው??

ሀ/ ነቢዩ ኢሳይያስ
ለ/ነቢዩ ኤልያስ
ሐ/ነቢዩ ዕንባቆም
መ/ ንጉሥ ዳዊት

✅መ.

1⃣9⃣➡ክርስቶስ ሊሰቀል በአለበት ወቅት በመካከላቸው የነበረውን ጥል ትተው የታረቁ ሁለት ሐገረ ገዥዎች እነማን ነበሩ??

ሀ/ ሐናና ቀያፋ
ለ/ሄሮድስና ጲላጦስ
ሐ/አናሲሞስና ዲዲሞስ
መ/ጢባርዮስና አውግስጦስ

✅ለ.

2⃣0⃣➡ቴዎፍሎስ ለተባለው የግሪክ ባለ ሥልጣን የተጻፈው ወንጌል የትኛው ነው??

ሀ/የማቴዎስ ወንጌል
ለ/ የማርቆስ ወንጌል
ሐ/የሉቃስ ወንጌል
መ/የዮሐንስ ወንጌል

✅ሐ.
ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ስለሚኖር አርሙን⤴
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...