2018 ጁላይ 18, ረቡዕ

የምዕራፍ አራት(፬)/የ36ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

✝የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ እና መልስ✝

🖊የምዕፍ(፬)የ36ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የቃልና የፁህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር
👏🏻👏🏻👏🏻👏🏻👏🏻👏🏻👏🏻

ማጠቃለያ መልስ እነሆ⤵️
1⃣ሐዋርያት ማለት ምን ማለት ነው??
ሀ.መምህርት
ለ. ተማሪ
ሐ.ተጓዥ
መ. ነቢይ

መልስ✅ሐ.

2⃣ጌታችን ርግብ ሻጮችንና ለዋጮችን ከቤተ መቅደስ በኃይል  ወቅት አይሁድ ተሰብስበው "ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየኛለህ;? በአስወጣበትብለው በጠየቁት ጊዜ ጌታችን ምን ብሎ መለሰላቸው??
ሀ. የቤትህ ቅናት ይበላኛል
ለ.ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሰዋለሁ
ሐ. አንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ
መ.ምንም አልመለሰላቸውም

መልስ✅ለ.

3⃣ሠላሳ ስምንት ዓመት በሽተኛ የነበረው ሰው የተፈወሰባት መጠመቂያ ቦታ ማን ትባላለች??
ሀ. እየሩሳሌም
ለ.የበጎች በር
ሐ.ቤተ ሳይዳ
መ.መልስ የለም

መልስ✅ሐ.

4⃣"እርሱ ሙሉ ሰው ነው እርሱ ስለራሱ ይናገራል" ያሉ እነማን ናቸው??
ሀ.አይሁድ ክርስቶስን በጲላጦስ ፊት በከሰሱት ጊዜ
ለ. አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን በከሰሱት ጊዜ
ሐ. ከሕፃንነቱ እውር ሆኖ የተወለደውንና ክርስቶስ የፈወሰውን ሰው ወላጆች አይሁድ ስለሁኔታው በጠየቋቸው ወቅት
መ. መልስ የለም

መልስ✅ሐ.

5⃣ከሚከተሉት ውስጥ ክርስቶስ በተሰቀለ ወቅት ታልተደረገ ተአምር የትኛው ነው???
ሀ.ዐለቶች ተሰነጣጠቁ
ለ.ሙታን ተነሱ
ሐ.ፀሐይ ጨለመች
መ.መልሱ አልተሰጠም

መልስ✅መ.

6⃣"አይሁድ ጌታችንን ብዙ ጥያቄ ጠይቀውታል፤አንዳንድ ጊዜም እርሱ ጥያቄአቸውን በጥያቄ ይመልስ ነበር። በአንድ ወቅት "የዮሐንስ ጥምቀት ከሰው ነው ወይስ ከእግዚአብሔር ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ ምን ብለው መለሱለት.?
ሀ.አናውቅም
ለ.ከእግዚአብሔር ነው
ሐ.ከሰው ነውል
መ.መልሱ አልተሰጠም

መልስ✅ሀ.

7⃣ጌታችን የወይን አትክልት ስለነበረው ሰው በተናገረበት አንቀጹ ላይ የወይኑ ባአለቤት ለንግድ ወደ ሌላ ቦታ እንደሄደና እርሻው የሚያፈራበት ወቅት ሲደርስ ባሮቹን እና ልጁን እንደ ላከ ነገር ግን ገበሬዎቹ ግማሹን እንደ ደበደቧቸው ልጁን ደግሞ እንደገደሉት ተናግሯል። አይሁድ ይህን ሲሰሙ ሊይዙት ፈልገው ነበር። ነገር ግን አልያዙትም ለምን??
ሀ. በመካከላቸድ አልፎ በመሔዱ
ለ.ሰንበት ስለነበረ
ሐ. ሕዝቡን በመፍራት
መ.ቢይዙት ምሳሌው ለእነርሱ እንደተናገረ መቀበል ስለሚያስመስልባቸው

መልስ✅ሐ. ሉቃ 20፥9-21

8⃣ክርስቶስ ከመስቀሉ በፊት በነበሩ ቀናት፣ ቀን ቀን በቤተመቅደስ እያስተማረ ይውል ነበር። ሌሊቱን የት ነበር የሚያሳልፈው??
ሀ. በቤቱ
ለ. በደብረ ዘይት ተራራ
ሐ.ከኒቆዲሞስ ጋር
መ. በባህረ ጌንሳሬጥ

መልስ✅ለ.

9⃣የርኅሩኁ ሳምራዊ ታሪክ በየትኛው ወንጌል ላይ ይገኛል???
ሀ. በማቴዎስ ወንጌል
ለ. በማርቆስ ወንጌል
ሐ. በሉቃስ ወንጌል
መ. በዮሐንስ ወንጌል

መልስ✅ሐ.

1⃣0⃣ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በመሆኑ ለስብከተ ወንጌል ይፋጠን የነበረው በርናባስ የየትኛው ወንጌላዊ አጎት ነው።?
ሀ. የቅዱስ ማቴዎስ
ለ.የቅዱስ ማርቅቆስ
ሐ. የቅዱስ ሉቃስ
መ. የቅዱስ ዮሐንስ

✅ለ.

1⃣1⃣ጎለጎታ ማለት ምን ማለት ነው..?
ሀ. ቀራንዮ
ለ.የመስቀያ ቦታ
ሐ. ራስ ቅል
መ.የወንበዴ መቅጫ

መልስ✅ሐ.

1⃣2⃣በሰሞነ ሕማማት የማይደረግ የቤተ ክርስቲያን ስርዓት የትኛው ነው..??
ሀ. ጸሎት
ለ.ስግደት
ሐ.ፍትሐት
መ.ምንባብ

መልስ✅ሐ.

1⃣3⃣ከሚከተሉት አንዱ ቅዱስ ጴጥሮስ በበዓለ ኃምሳ ከተናገራቸው ነጥቦች መካከል አይደለም??
ሀ.ክርስቶስ ያደረጋቸው ተአምራት ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ የተገለጠ መሆኑ
ለ.የክርስቶስ ልደት በመላእክት የተበሠረ መሆኑን
ሐ.ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ አስቀድሞ ነቢዩ ዳዊት እንደ ተነበየው
መ. አይሁድ በአመፀኞች እጅ ሰቅለው እንደገደሉት

መልስ✅ለ.

1⃣4⃣መልካም በተባለች ቦታ ተቀምጦ ሲለምን የነበረው ሰው ለዘጠኝ ሰዓት ጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጡ የፈወሱት እነ ማን ነበሩ??
ሀ. አሥራ አንዱ ሐዋርያት
ለ.ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ
ሐ.ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ
መ. አዲስ የተጠመቁ ክርስቲያኖች

መልስ✅ለ.

1⃣5⃣ደቀ መዛሙርቱ ለመጀመርያ ጊዜ ክርስቲያን የተባሉት በየት ከተማ ነው??
ሀ.በቁስጥንጥንያ
ለ.እስክንድርያ
ሐ.በአንጾኪያ
መ.በፊልጵስዩስ

መልስ✅ሐ.

1⃣6⃣ከሚከተሉት አንዱ ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል አይደለም..?
ሀ. እስጢፋኖስ
ለ.ፊልጶስ
ሐ.አርኬላዎስ
መ.ኒቆላዎስ

መልስ✅ሐ.

1⃣7⃣የካህኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ጎረቤቶች፤ የዘካርያስ ልጅ ስም ማን እንዲባል ፈለጉ.?
ሀ.ዘካርያስ
ለ.ዮሐንስ
ሐ.ኤልያስ
መ.መጥምቁ

መልስ✅ሀ.

1⃣8⃣ከሚከተሉት አንዱ በዮሐንስ ራእይ ከተገለጹት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አንዱ አይደልም??.
ሀ. ኤፌሶን
ለ.ጴርጋሞን
ሐ.ሎዶቅያ
መ.ሮም

መልስ✅መ.

1⃣9⃣የመንፈስ ቅዱስን ሀብት ከሐዋርያት በገንዘብ ለመግዛት የፈለገው ማነው??
ሀ. ይሁዳ
ለ.ሲሞን
ሐ. አናንያ
መ.ሰጴራ

መልስ✅ለ.

2⃣0⃣ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ያደረገው ሁለተኛው ተአምር ምንድን ነው??
ሀ. ውኃውን ወደ ወይነ ጠጅ ለወጠ
ለ.ለ5000 ሰው መመገብ
ሐ.የንጉሱን ሹም ልጅ መፈወሱ
መ.ለምፃሞችን ማንፃቱ

መልስ✅ሐ.ዮሐ 4፥46-

ማጠቃለያ መልስ ይህንን ይመስላል
ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyam.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...