2018 ጁላይ 4, ረቡዕ

ቅኔ ሰምና ወርቁን ለዩ

saramareyama.890@gmail.com
#ቅኔ
ሰሙን ወርቁን በማውጣት ይሞክሩ፡፡

#ቅኔ
፩. ከዚያ ታች ያለችው ድውይ፤
ከቶ ምን ቀመሽ አልሻት ወይ
ኋላ ፀፀቱ ባንቺ ይሆናል
ተይ ሥጋ ብላሽ ይሆናል፡፡

#ቅኔ
፪.የቀድሞ ዘመን ስህተት
የፆም ቀን አሳ መብላት
የአሁን ዘመን ሰው አያውቅ መላ
በጦም ሽሮ ነው የሚበላ፡፡

✝ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንዴት ዋላችሁ እንዴትስ ቆያችሁ???

ለተሳተፋችሁ ሁሉ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ተስፋ ዕርሰተ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን አሜን፫


☞ የቅኔ ፩ መልስ

ሕብረ ቃሉ => ተይ ሥጋ ብላሽ
ሰሙ => #ሥጋው #ብላሽ (#የተበላሸ) ሊሆን ስለሚችል እንዳይፀፅትሽ ምንም አትበያት። ወይም ቅመሽው አትበያት ነው።
ወርቁ => 1ኛው ፍቺ #ሥጋ(የሰው ደካማው ሥጋ) ብላሽ መሆኑ አይቀርም። አፈር መግባቱ ወይም መበላሸቱ አይቀርም።

2ኛው የወርቁ ፍቺ ደግሞ => ነብስሽ ለሥጋሽ "ተይ ሥጋ" ብላሽ(ተናግራሽ)ይሆናልና፣ ይህን እያለችሽ(እንፁም )እያለችሽ) እንብላ(እንቅመስ) አትበያት። ኋላ እንዳይፀፅትሽ። ማለት ነው።


☞ የቅኔ ፪ መልስ

ሕብረ ቃሉ => በጦም ሽሮ
ሰሙ => የጦም ቀን ሽሮ የሚባል ወጥ ነው የሚበላው። ወይም የጦም ምግብ ነው የሚበላው።
ወርቁ => #ጦምን #ሽሮ ወይም #አፍርሶ ነው የሚበላው። የቀድሞዎቹ #በስህተት(#ባለማወቅ) ነበር የሚበሉት፣ የአሁኖቹ ግን #እያወቁ #ጦምን #ሽረው(#አፍርሰው) ነው አሳ የሚበሉት ማለት ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፫

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...