2018 ሜይ 13, እሑድ

መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ✍🖊
1 ቄሱ፡- ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ ማለት ምን ማለት ነው?
ሰማያዊ
ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ ማለት በልቡናችሁ  ቤታችሁን የምትወርሱበትን ሥራ አስቡ፤ አሳባችሁንም በሥራ ተርጉሙት ማለት ነው፡፡ ሕዝቡም ሰማያዊ ምስጢርን ካሰብን በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ ሲል ስለ ልቡናችህን ሀሳብ ርስተ መንግስተ ሰማያትን ማሰብ እንዳለብን ለመግለጽና አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡


ጥያቄ 2 ዲያቆኑ፡- የተቀመጣችሁ ተነሱ/ሁለተኛ ትርጓሜውን ስጥ?
የተቀመጣችሁ ተነሱ ሲል በቅዳሴ ጊዜ ከበሽተኛና ከአረጋውያን/ከሽማግሌዎች/ በቀር የሚቀመጥ ኖሮ አይደለም፡፡ ይህን ሲለን ከመዘንጋት አልጋ በንቃት፤ ከክፋት መኝታ አልጋ በቅንነትና በተመስጦ ከአምላካችሁ ጋር በጸሎት ተገኛኙ ማለቱ ነው፡፡ አንድም ክብሩንና የአምልኮቱ ዜና ሲነገር መቀመጥ አይቻልም ማለቱ ነው፡፡


ጥያቄ 3 ዱያቆኑ፡- ወደ ምስራቅ ተመልከቱ- ለምን?
ሀ. ምስራቅ ማህደረ እግዚአብሔር ፤ ምዕራብ ማህደረ ዲያቢሎስ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፤
ለ. ወንጌል የመጣችሁ በምስራቅ በኩል መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፤
ሐ. ምስራቃዊያን ሰባ ሰገል ባመኑበት ወንጌል እመኑ ሲል ነው፤
መ. የጌታን ነገረ ምፅዓቱን አስቡ ማለቱ ነው፤
ሠ. ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው፤ ምክንያቱም ጸሐይ በምስራቅ በኩል እንደሚወጣ ጸሐየ ጽድቅ     ኢየሱስ ክርስቶስም ከእመቤታችን መወለዱን ሲያስረዳ ነው፡፡ ማስረጃ ሚሊኪያስ 4÷2
ረ. ምስራቅ የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፡፡ ሕዝቄል 43÷2
ሰ. የክርስቶስ ዳግም ምጽዓቱም በምስራቅ በኩል መሆኑን ሲያስረዳ ነው፡፡ ማስረጃ ዘካሪያስ 14÷14


ጥያቄ 4 ዲያቆኑ እናስተውል /ምንን/?
-ያለንበትንና የቆምንበትን ሥፍራ የት እንደሆነ እንለይ /እናረጋግጥ/ ሲል ነው፤
-ከእግዚአብሔር ጋር ነን ወይስ ከስጋዊ ሃሳባችን ጋር ነን ሲለን ነው፤
-ከስጋውያን ዘመዶቻችን ጋር ነን ወይስ ከድንግል ማርያም፤ ከቅዱሳን መላዕክት ጋር፤ ከጻድቃን ሰማዕታት ጋር ነን ወይ ሲለን ነው፡፡


ጥየቄ 5 ልቡናችሁ በሰማይ ይኑር ማለት ምን ማለት ነው?
- ልቡናችሁ ሰማያዊ ነገርን በማሰብ በአንክሮ በተዘክሮ ጸንቶ ይኑር ማለቱ ነው፤
- የምድራዊ ኑሮአችን የኮንትራት ውላችንን እስክናበቃ ድረስ ብቻ መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፤
- ምድራዊያን ስንሆን ሰማያውያን መሆናችንን ልብ እንበል ማለቱ ነው፡፡
- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለፊሊጲዮስ ሰዎች በምዕራብ 3÷20 ሀገራችን በሰማይ ነው በማለት ሰማያውያን መሆናችንን መስክሯል፡፡
- ሕዝቡም እውነት ነው ልቡናችን ሰማያዊ ነገርን ያስብ ይበሉ ማለት ነው፡፡

ጥያቄ 6 አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ለምን እንላለን? ለምን ከአስራ ሁለት አልበለጠም? ከአስራ ሁለትስ ለምን አላነሰም? በጣትስ ለምን እንቆጥራለን?
አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ የምንለው የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ስም ፊደላት ሲቆጠሩ 12 መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ ሌላው በ12 ሐዋሪያት ምልጃ አድነን ይቅርም በለን ማለት ነው፡፡ ከ12 ያልበለጠበትና ያላነሰበት ምክንያት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም ፊደላት ከ12 አይበልጥም አያንስምም፡፡ ሌላው የሐዋርያት ቁጥር ብዛታቸው 12 መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው በራሱ ጥፋት በወጣበት በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ ሐዋሪያው ማትያስ በዕጣ መመረጡን ሐዋ.ሥ1÷23-26 ያስረዳል፡፡ ለዚህም ነው ከ12 ያልበለጠው ወይም ያላነሰው፡፡ ወደ ላይ ዕረገቱን ወደታች መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡
                                                     አዘጋጅ፡- መ/ስ/ቆ/አባ መዝሙር ሐዋዝ
.https://t.me/Teyakaenamels
https://t.me/Teyakaenamels
https://t.me/Teyakaenamels

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...