2018 ኤፕሪል 2, ሰኞ

ከፊያታዊ/ጥጦስ/ የተላከ ጦማር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✝


ከፊያታዊ ዘይማን (ጥጦስ) የተላከ ጦማር
==========================
 ከሁሉ አስቀድሜ ታናሽነት ያልቀደመህ ታላቅ ዘመን የሌለህ ቀዳማዊ ድህነት የማይስማማህ  ባለጠጋ ለሆንከው ለንጽሀ ባህርይ ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ከባህርይ አባትህ ከአብ ከባህርይ ህይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ይሁን አሜን

ቀኑ ሽብር የነገሰበት ሙታን በሞት  የተዋጠ ዝምታቸዉን  ሰብረዉ የተናገሩበት አንዳንዶቹ የዘላለም ሞትን አንዳንዶቹ ደግሞ የዘላለም ህይወትን የወረሱበት እለት ነዉ። በእለቱ ብዙ እስረኞች አመለጡ ከእነዚያ መካከል በዉንብድና ወንጀሌ ተይዤ የሞት ፍርድ የተላለፈብኝ አንዱ ነበርኩ።
ታድያ፦ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ለሶስት ሰዓታት እኔ ከነብስ አባቴ ከክርስቶስ ጋር ተነጋግሬ ቀኖና ተሰጦኝ ስለሀጢአቴ የቀኖና ሰዓት እንጂ የቅጣት ሰዓት አልነበረችም ለሶስት ሰዓት የተሰጠኝን ቀኖና ጨርሼ የደም ማህተም ያረፈበት የነጻነት ደብዳቤ ከንጉሱ ተቀብየ በነፋሳት ጀርባ ተጭኜ እየበረርሁ የምስራቹን ለማዳረስ በምድር የተደረገዉን ድንቅ ነገር ገነትን ይጠብቁ ለነበሩ መላዕክት ለማድረስ ገሰገስሁ
እናም ከገነት ቅጥር  እስክደርስ ማንም  አልተናገረኝም  የእሳት  ባህሩ አላገደኝም  የሞት  ስልጣንም  አላገደኝም  የያዝሁት  ደብዳቤ  ከንጉሱ  ነበርና  ወደ  ገነት  እየተጠጋሁ  ስመጣ ግን አይኖቼ ያዩትን ማየት  ተሳናቸዉ።

ቁመቱ  ከምድር እስከ  ሰማይ  ይደርሳል  የክንፎቹ  ርዝመት  ሰዉ  አይመጥናቸዉም አይኖቹ  እንደ እሳት  ነበልባል  ይንቀለቀላሉ  የምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍን  በእጁ  ጨብጧል በዚያች  የመከራ  ቀን  በአዳም ፈንታ  ገነትን  ይጠብቅ ዘንድ  የተሰየመዉ  ኪሩብ መላዕክ ነበር።መካከል
በዚህ ጊዜ  ከፊት ለፊቴ  የቆመዉ መላዕክ  በመገረም  ተዋጠ   ። የሰዉ  ልጆች  ወደዚህ  ክልል መግባት  ካቆሙ 5534 ዘመናት  ተቆጥረዋል  በገነትና በሰዉ  ልጆች  የእሳት ባህር  ተዘርግቷል  በዚህም  ምክንያት  ተሻግሮ መምጣት  የቻለ  የሰዉ  ዘር እንዴት አልነበረም   እኔ  ግን ይህን  ባህር  ተሻግሬ  ከገነት በር  ስደርስ  ጠባቂዉ መለዓክ  መኑ  አንተ ማነህ  አንተ  የእሳቱንስ  ባህር   አለፍኸዉ  አለኝ።
ከዚች  ሶስት  ሰዓት  በቀር  በጎ  ስራ  ያልሰራሁ እኔ  የትኛዉ  ስራየን  ልንገረዉ   እጀን  በሰዉ  ደም ነክሬ  የምኖር  ወንበዴ    ወይስ  ነብሰ ገዳይ  ሌባና  ቀጣፊ ወይስ  መላ  ዘመኔን በሀጢዓት  የጨረስሁ ክፉ  ሰዉ  ነኝ  ልበል  የቱን  ስራየን  ልንገረዉ? መላዕኩም በመፅሀፍ  ስማቸዉ  በበጎ ስራቸዉ  የተፃፉ  ቅዱሳንን እያነሳ  መረመረኝ ጠየቀኝ እኔም  ዝም  አልሁ  ከብዙ ዝምታ  በሃላ   ትንሽም  ብትሆን  ያለችኝን ስራየን ነገርሁት  ዓለም  በጨለማ  ስትወረር  ደቀመዛሙርቱ  ርቀዉ ሲመለከቱ መላዕክቱም  ከፍርሃት  የተነሳ  ዝም  ሲሉ  አይሁድም  ልብሱን  ሲካፈሉ  አቤቱ  በመንግስትህ በመጣህ  ጊዜ  አስበኝ  ብየ  አምላክነቱን የመሰከርሁ ነኝ።
ታድያ  ጩኸቴን ሰምቶ  ዝም  አላለኝም  ብየ የተሰጠኝን የነፃነት ደብዳቤ  አሳየሁት  እሱም  በሁኔታው  በመገረም  ወደተላኩበት  ቦታ  አስገባኝ  አምላኬ  ሆይ ይህን  ያደርግህ  እኔ  ማን ነኝ  ዘመኔን  በሙሉ  በሀጢአት  ያሳለፍሁ  ከልጅ  እስከ  አዋቂ  ሳልል  ሁሉንም  የገደልሁ  ቀማኛና  ወንበዴ  አይደለሁምን? ታድያ  ከኔ  ሀጢአት  ያንተ ምህረት  በዝቶ  ለዚህ  አበቃኸኘ ስለሆነዉም እየሆነስላለዉም  ወደፊት ለሚሆነዉም  አመሰግንሀለሁ  ክብር  ምስጋና  ጌትነት ከባህርይ  አባትህ  ከአብ  ከባህርይ  ህይወትህ  ከመንፈስ  ቅዱስ  ጋር ይሁን  ዛሬም  ዘወትርም  ለዘላለሙ  አሜን ።

///////////////////////////
ፊያታዊ ዜይማ ወይንም ደግሞ ጢጦስ
የነበርሁ እኔ ነኝ የሰው ደም የማፈስ፣
ድሃን የምቀማ ደም ማፍሰስ የምሮጥ
እኔ ነበርሁ ጢጦስ ድሃን የማፋጥጥ፣
ወንበዴ የምባል ሐጢአተኛ እኔ ነኝ
በሙሉ ዘመኔ ስቀማ የኖርሁኝ
እኔ ዕብራዊ ነኝ ከቅዱሳን ወገን
 ግና አልታደልሁም እነርሱን ለመሆነ፣
ድሃን በመበደል ዘመኔም አለቀች
ጌታዋን በመፍራት ነፍሴም ተጨነቀች፣
በሀጢአቴ ምክኒያት በሰዎች እጅ ተያዝሁ
ፍርድን ፈርደውብኝ በመስቀል ተሰቀልሁ፣
በግራየ በኩል አየሁት አምላኬን
ስለ ሰው ልጅ ሀጢአት ሰማሁት ሲማፀን፣
እኔስ በስራየ እርሱ ምን አጠፋ
ብየ በልቤ አሰብሁ ወይ የእርሱ ሥራ፣
የእኔ ውንብድና በእርሱ ላይ ተጣለ
የቀድሞው ሐጢአቴ በእርሱ ተነቀለ፣
በመንግስትህ ጌታ አስበኝ በማለት
እርሱን ተማፀንሁት በመጨረሻው ስዓት፣
ወደኔ አየና አዲት ቃል ነገረኝ
ከነት ለመግባት እኔን አስቀደመኝ፣
በዘመኔ ስኖር መልካም ስራ የለኝ
ታዲያ እዴት ወዶኝ ነው እርስቱን የሰጠኝ፣
አዳምን የቀደምሁ ወነበዴው ጢጦ ነኝ
ወደ ገነት መግባት መጀመሪያው ሆንሁኝ፣

ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...