2018 ኤፕሪል 3, ማክሰኞ

የሰሞነ ሕማማት ጥያቄና መልሶች

https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA
https:


https://youtu.be/lwfQaXDUk58
✝➡የሰሞነ ሕማማት ጥያቄና መልስ እንደ ሚከተለው ነው፦👇👇👇👇👇

✍ጥ.ተራ.ቁ.1⃣➡በዕለተ አርብ  ስግደት ከሰገድን በኋላ ለምንድ ነው ካህናቱ ጀርባችን በወይራ ዘንጣፌ ቸብ ቸብ የሚያደርጉት??

✝መልስ✝🖊 ወይራ በባህሪው  ጠንካራ  ነው 
እናተም ጠንካራ እሙን የሆነ ክርስቲያን ሁኑ ሲል አንድም  በኖህ ዘመን የጥፋት ውሃ ጎደለ ስትል እርግብ የወይራ ዝንጣፌ ይዛ መጥታለች  እኛም በወይራ ዘንጣፌ ጀርባችን መመታቱ የኃጢአት ቀንበር ተወገደላችሁ ሲል በእርሱ ቸብቸብ እንደረጋለን አንድም የሚወደኝ ቢኖር መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለው እኛም  በጀርባችን መስቀሉን ተሸክመናል ስንል አንድም መከራው በሚመስል መከራውን ከመሰልን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤውን እንመስላለን ስንል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.2⃣በሰሞነ ሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም አናማትብም ? ??


✝መልስ✝🖊የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀለ ከተሰቀለ በኋላ ነው በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልገሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ሕማማት በቤተክርስተያን ሥርዓት መሠረት መስቀል መሳለምም ሆነ የማማተብ ሥርዓት የለም።


✍ጥ.ተራ.ቁ 3⃣➡በሰሞነ ሕማማት ለምን አንንሳሳምም???


✝መልስ✝🖊

✍ይሁዳ በመሳም ጌታውን  አሳልፎ ሰጥቶአል እኛም እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችችንን ለማሰረዳት ከዚሀ በተጨማሪም ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰሞነ ሕማማት እሰከ ምሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሠላምታ የለም።

✍ጥ.ተራ.ቁ.4⃣➡ኪርያላይሶን ማለት ምን ማለት ነው ቃሉስ የምን ቃል ነው??


 ✝መልስ✝👇🖊ቃሉ የግሪክ(ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ  ኤሌይሶን"ቃሉዉ፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡


✍ጥ.ተራ.ቁ.5⃣➡አክፍሎት፡ ምንድን ነው?? እስኪ ስለ አክፍሎት አብራ/ሪ


✝መልስ✝🖊በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ / ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከአርብ እስከ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙዎች ያከፍላሉ፡፡ አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፤ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬኔዎስ፤ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፤ ሐዋርያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ  በቀር እንደማይመገቡ፤ ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉም ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ውኃ ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኸው ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ.6⃣➡ ስለ ጉልባን ትውፊት አስረዳ/ጅ??


 ✝መልስ✝🖊ጉልባን ከባቄላ ክክ፤ ከስንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታወሳል።

✍ጥ.ተራ.ቁ.7⃣➡ክብር ይግባውና ጌታችና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ በጸሎተ  ሐሙስ ምን ምን ነገሮችን  ያከናወነበት ዕለተ ነው?? 

✝መልስ✝👇🖊

በዚች ዕለት ጌታ በፍጹም ትሕትና የደቀመዛሙርቱን እግር ያጠበበት፤ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ሕይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው፡፡
አንድም ሕጽበተ እግር ጌታችን እናንተ ለወንድማችሁ እንዲህ አድርጉ በማለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና፤ እውነት እውነትኽ እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም፤ ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ 《  ዮሐ.13፡16-17 》በማለት ትሕትናውን አሳይቷል፡፡

✍ጥ.ተራ.ቁ8⃣➡ቄጤማ የምን ምሳሌ ነው?? በቀዳም ስዑርስ ለምን በግንባራችን ላይ እናስራለን??

✝መልስ✝👇🖊
✍በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል 《 ቃለ ዓዋዲ 》እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላም እንደሰጠን እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም ገጸ በረከት ያቀርባሉ፤ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው፤ ቃጭል ሲያቃጭሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሳኤውን ለሚናፍቁ ምእመናን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

6 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...