2018 ኤፕሪል 1, እሑድ

ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው? ጥያቄና መልስ

sara mariyam:
https://youtu.be/yTY62za_Dww

sara mariyam:
https://youtu.be/yTY62za_Dww


✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች ሰላማችሁ ይብዛልን!!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🌿እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን እያልን፦ ዛሬ ስለ ሆሳዕና 8 ጥያቄዎችን እንጠያየቃለን...🌿🌿🌿🌿


1ኛ, 🌿ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው??

🌿መልስ🌿🌿✍ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

2ኛ, 🌿 በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው??

🌿መልስ🌿1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡

3ኛ,🌿 ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??

🌿መልስ🌿ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ " አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል። "
             (ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)
🌿በአህያ መቀመጡ፦
•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን  አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ፤.

4ኛ, 🌿ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው???

🌿መልስ🌿🌿✍ዝንባባ
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ  የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡


5ኛ,🌿 ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??

🌿መልስ🌿🌿🖊 ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡- ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡


6ኛ, 🌿 ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርንጭለዋስ???


🌿መልስ🌿🌿✍ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና

🌿✍ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡


7ኛ,🌿 አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል የሚለው ሃይለ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል???

🌿መልስ🌿🌿✍ት/ ዘካርያስ.ም 9፥9

8ኛ, 🌿 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ያልታሰሩ አህዮች እያሉ ለምን የታሰሩትን መረጠ???

🌿መልስ🌿🌿✍አህዮቹ የታሰሩት ሌባ ሰርቆ ነው ያሰራቸው፡፡ ወንበዴ ሰርቆ ነው ያሰራቸው አህዮቹ ለጌታ ውለታ ሰርተዋል፡፡ ጌታ ሲወለድ አሙቀውታልና  ለጌታ ውለታ ልንመልስ ያልቻልነው እኛ ሰዎች ብቻ ነን፡፡
        የታሰሩት እዲፈቱ የመረጠበት ሚስጥር፡-እኔ ከሃጥአታችሁ ልፈታችሁ የመጣሁ ነኝ ሲል ነው፡፡ወንበዴው አህዮቹን ሰርቆ በመንደር እንዳሰራቸው ዲያብሎስም ለሰው ልጅ በሃጥአት ሰንሰለት ከሲኦል መንደር አስሯቸው ነበርና፡፡
ሐዋርያቱ ሲልካቸው ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በልዋቸው አላቸው፡፡ የፈጠራቸው እሱ ነውና፡፡

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿መልካም የሆሳዕና በዓል ይሁንልን ወስብሐት እግዚአብሔር 🌿🌿🌿🌿🌿🌿saramareyama.890@gmail.com

1 አስተያየት:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...