2018 ኤፕሪል 15, እሑድ

ድንግል እመቤቴ

ድንግል እመቤቴ የአምላኬ እናት
የሰማእታት ክብር የአቤል ደግነት
የሲና ልምላሜ የያእቆብ መሰላል
የአሮን በትሩ ወላዲተ ልኡል
የሙሴ ፅላቱ የአዳም መዳን ተስፍ
የኤልሳ ማሰሮ የአይናችን ማረፊያ
አምባ መሸሸጊያ ከሞት ማምለጫችን
ስምሽ የሚያጠግብ ሲርበን ምግባችን
ሲከፍን መፅናኛ ፈጥነሽ ደራሻችን
በቃ ሁሉ ነገር የሆንሽ አለኝታችን
ዛሬ ግርም ቢለኝ መጣው ልጠይቅሽ
ያንን ክፍ ስደት እንዴት ስ እንደቻልሽ
የበረሀው ትልቀት
የአሸዋው ግለት
ድንግል እመቤቴ እንዴት ነበር ያኔ...??
የውሀ ጥም እንግልት
ደረሱብኝ ብለሽ ደግሞ ያሀ ጭንቀት
እንዴት ቻልሽው ከቶ ገና በለጋ እድሜሽ
የስደት መከራ እንዴት አለፈልሽ
ብጨንቀኝ እኮ ነው ...
ህይወት ግራ ሆና ሁሉ ቢጠምብኝ
ስድትን ቀምሸው መቋቋም ቢያቅተኝ
መቻል የሚባለው ውሉ ቢጠፋብኝ
ጠየኩሽ እናቴ.......
የስደትን ነገር  ጠንቅቀሽ ታውቂያለሽ
እስኪ መላ በይኝ ለኔ ከንቱ ልጅሽ
እባክሽ እመ አምላክ ......
የግብፅን በረሀ ሀሩር በሞላበት
ሁሉን እንደቻልሽው እንዳለፍሽ በትእግስት
እኔንም አበርቺኝ አደራ እመቤቴ
ተወሳስቦብኛል ተሳስሯል ህይወቴ
ተስፍዬ ተሟጧል
ልቤ ተረብሿል
ባዶነቴ በዝቶ ኑሮዬ ቅጥ አጥቷል
በቃ ምንበልሽ ..........
ብቻ በደፈናው እኔነቴ ሞቷል
እናም እመቤቴ ተመልከች ልጅሽን
በእጆችሽ ደባብሽኝ ደካማ ባሪያሽን
አበርችኝ እናቴ ትእግስት አድይኝ
ስደክም ምርኩዜ ብርታት ሀይሌ ሁኝኝ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...