2018 ኤፕሪል 16, ሰኞ

ዘመነ ትንሳኤን አስመልክቶ የቀረቡ ጥያቄና መልሶች

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
@Teyakaenamels
ክርስቶስ ትንሳኤ እሙታን
በዐብይ ኃይል ወስልጣልን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ ፍስሀ ወሰላም
////    ;///
@Teyakaenamels
ጥያቄና መልስ👇

1ኛ✅✍ፋሲካ ማለት ምን ማለት ነው? ለእኛስ ፋሲካችን ማን ነው?  ማስረጃ ጥቀሱ?
መልስ፡- ፋሲካ ማለት ማለፍ ማለት ሲሆን ለእኛ ፋሲካችን ክርስቶስ ነው፡፡ ዘፀ.12÷1 ፣ 1ኛ ቆሮ.5÷8

2ኛ✅✍ የትንሣኤ ሁለተኛ ሣምንት ዳግም ትንሣኤ የሚባልበት ምክንያት ምንድን ነው?
መልስ፡- በተዘጋ ቤት ገብቶ ለሁሉም የተገለጠበት፡፡ ዮሐ.20÷19

3ኛ✅✍ከትንሳኤ በኋላ እስከ ዳግም ትንሳኤ ያሉ የዕለታትን ስያሜ ጥቀስ/ሽ??
መልስ፦👇
ሰኞ 👉ማዕዶት
ማክሰኞ 👉ቶማስ
ረቡዕ 👉አላዛር
ሐሙስ👉አዳም ሐሙስ
ዓርብ👉ቅድስት ቤተ ክርስቲያን

ቅዳሜ 👉ቅዱሳን አንስት

እሁድ👉 ዳግሚያ ትንሳኤ

4ኛ✅✍ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለመቅደላዊት ማርያም ስለምን አትንኪኝ አላት???

መልስ፦ስለ 3 ምክንያት አትንኪኝ ብሏታል።

1ኛ - "ሶስት መዓልት ሶስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሬ እነሳለው" ብሎ የተናገረውን ስለረሳች ስለ እምነቷ ማነስ ሊገስጻት ፈልጎ ነው ፡፡ ለመላእክት ስለምን ታለቅሺያለሽ ሲላት "ጌታዬን ወስደውታል" አለች እንጂ ‹‹እንደተናገረው ተነስቷል›› አላለችም ዮሐ 20፡11-13

2ኛ - በዛው ወደ ባህሪ አባቱ የሚያርግ መስሏት እግሩን ስማ ልትሰናበተው ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የማርግበት ጊዜ ገና ነውና ለመሰናበት ብለሽ አትንኪኝ ሲላት ነው

3ኛ -ሥርዓተ ክህነትን ሲመሰርት ሴቶች ካህን መሆን "ሥጋወ ደሙን መፈተት" እንደማይችሉ ሥርዓት ሲሰራልን ነው!

 ለዚህም ማረጋገጫ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን ግን እንዲዳስሰው የፈቀደለት ሲሆን መግደላዊት ማርያምን ግን አትንኪኝ ነው አላት፦
 " ቶማስን፣ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው አለው"ዮሐ 20፡27::

ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ÷ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ አርጋለሁ " ምን ማለት ነው?ክርስቶስ አምላኬ ያለው ስለምንድን ነው?

በመጀመሪያ ክርስቶስ በመለየት ወደ አባቴ እና ወደ አባታችሁ አለ እንጂ ወደ "አባታችን" አላለም እንዲሁም ወደ አምላኬና አምላካችሁ አለ እንጂ ወደ "አምላካችን" ብሎ ጠቅልሎ አልተናገረም!
 እንዲህም ለይቶ ማለቱየእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መባልናሕ የእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች መባል ፍጹም የተለያየ በመሆኑ ነው፡፡ እርሱ፥ «አባቴ» ቢል የባሕርይ ልጅ በመሆኑ
ነው፡፡ እነርሱ ግን የጸጋ ልጆች ናቸው፡፡ እርሱ፥ «አምላኬ» ቢል ስለተዋሐደው
ሥጋ ነው፡፡ የተዋሐደው የፈጠረውን ሥጋ ነውና ፡፡ እነርሱ ግን «አምላካችሁ»
ቢባሉ ፍጡራን ስለሆኑ ነው፡፡ በዚህም እርሱ ፈጣሪ እነርሱ

ፍጡራን መሆናቸውን አስረግጧል።

5ኛ✅✍የመጀመሪያው ፋሲካ በየት ተከበረ???

//መልስ//🖊 ግብጽ ውስጥ በችኮላ እንደተከበረ ከዘጸ 12, 1-20 እንረዳለን ነገር ግን ትክክለኛው ፋሲካ ወይም “ማለፍ” ወይ “መሻገረ” የሚለውን ትርጉም በሚያሳይ መልኩ የተከበረው ግን የግብጽን የባርነት ኑሮ አልፈው ከወጡ በኋላ እንደሆነ ከዘጸ 12, 43- 51 ላይ እንረዳለን ፡፡ በዘጸ 12, 21 በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ እንደተከበረ እንረዳለን ፦

6ኛ✅✍ከትንሳኤ እሁድ በኋላ የሚውሉ የዕለታትን ስም ስያሜ ትርጉም አስረዱ??

✍ሰኞ ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር ማለፍ ማለት ነው በዚህ
ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን
ከሞት ወደ ሕይወት ከሲኦል ወደ ገነት ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን
እናስባለን::

✍ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ጌታዬና
አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል ዮሐ. 20፡27-29::

✍ ረቡዕ አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ
ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን ክርስቶስ የሞትን ስልጣን
የሻረ የሕይወት ራስ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ
መሆኑን እንመሰክራለን::

✍ሐሙስ አዳም ሐሙስ ይባላል፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና
የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን::

✍አርብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን
በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ  ይሰበካል ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን
አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ጥቶ ስለመመስረቷእንዳከበራት
ይነገራል ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው ክርስቶስ
ለሕንፃ አልሞተምና::

✍ ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን
አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና
ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል::

✍ እሁድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ
ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል::

ወስብኃት ለእግዚአብሔር.
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjAsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...