2018 ፌብሩዋሪ 27, ማክሰኞ

የእንቆቅልሽ/ህ መረሀ ግብር

⏩እንቆቅልሽ
     ✍🏾ምን አውቅልሽ❓
የጌታዬን ፊቱን በጨርቅ ባብስ
መልኩ ተስሎበት ያገኘሁት ወደ ቤቴ ስደርስ እኔ ማን ነኝ?

   *መልስ*✍🏾የጲላጦስ ሚስት  ቬሮኒካ ነሽ።

✍🏾 እንቆቅልሽ

     ⏩ምን አውቅልሽ❓
✍🏾ቢበሉት ቢጠቱን የማያልቅ
ቢለብሱት የማያረጅ ቢሸከሙት የማይከብድ
ከጨለማ ከዓለም የሚያላቅቅ
ከክፉ የሚያድን የሚጠብቅ ምንድነው ታውቂዋለሽ?

  *መልስ*⏩ ላመነ ለተቀበለ ለተረዳው
ልቡን ላስማረከ ላላቅማማው
ጠላትን መዋጊያ ጋሻ ጦር ወንጌል ነው

⏩እንቆቅልሽ
     ✍🏾ምን አውቅልሽ❓
⏩በፋሲካ ምሽት ጌታን አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ የጠየቀ
የወንጌሉ ቋንቋ ፅር የሆነ
በህይወቱ መጨረሻ በእስያ ሀገር በኤፌሶን ያስተማረ  ይሄ ቅዱስ ማን ነው

*መልስ*✍🏾ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

✍🏾 እንቆቅልሽ
     ⏩ምን አውቅልሽ❓

✍🏾የሰማዕታትን መከራ ተጋድሎቸውን አይታ
ለመኖር የወሰነች እንደእነርሱ ጸንታ
መኮንኑ ወብቷን አይቶ
አልፈልግም ስትለው እጅግ ቢያሰቃያት መከራን አብዝቶ ሥገዋን
 ተልትለው ዘቅዝቀው  ሲሰቅሏት
 መልሰው በፈላ ውሃ ሲከቷት
ከሰማያት አክሊል በነጭ እርግብ አምሳል
የወረደላት ያም ውሃ ጥምቀት የሆነላት
ይቺ ቅድስት እናት ማናት ታውቂያታለሽ❓

*መልስ*⏩የጣኦት አምላኪው የዳኪዎስ ልጅ
በአንፆኪያ ተወልዳ ያደገች
በዕስር ሆና ዘንዶ ውጦ የተፋት
ሴጣንን በፀጉሩ ይዛ የቀጠቀጠች
ጌታ ቃል ኪዳንን የገባላት
እናታችን ቅድስት መሪና ናት

⏩እንቆቅልሽ
     ✍🏾ምን አውቅልሽ❓

⏩አውሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ!
ባህር የተባለው ማነው?
አውሬውስ ማን ነው?

  *መልስ*✍🏾ይሄ አለም ሲሆን  ባህር የተባለው
አውሬው ደግሞ የሰው ልጅ ባህሪ ብሎም ሀሳዌ መሲህ ነው!!

✍🏾 እንቆቅልሽ
     ⏩ምን አውቅልሽ❓
✍🏾 ጌታ ሲጠራው 56 ዓመቱ
ከአለም ሲለይ ዕድሜው ሰማንያ ስምንት
መሰረተ ቤተክርስትያን የተባለ
በ66ኛው ክፍለ ዘመን  ሰማዕትነት የተቀበለ?

*መልስ*⏩እኔስ እንደ አምላኬ ሽቅብ አትስቀሉኝ
ስለማይገባኝ ከዕርሱ አታወዳድሩኝ
ባይሆን ስለ ፍቅሩ መሞቴ ካልቀረ
እራሴን ወደታች ዘቅዝቃችሁ ቸንክሩኝ
በማለት በሮም አደባባይ ህይወቱን የሰጠ
ፍቅሩን እስከመስቀል ይዞ የዘለቀ
አባታችን ቅዱስ ጴጥሮስ ነው

⏩ እንቆቅልሽ
     ✍🏾ምን አውቅልሽ❓
⏩እመቤታችን ፊደል ናት ምክንያቱም
ወንጌልን ስለወለደችልን
መባረክ የጀመርንባት
ወደቤተ መቅደስ መግባት ያስተማረችን
የእናት መጀመሪያዋ 
ትህትናን ያስተማረችን እርሷ ስለሆነች ያለው ቅዱስ ማን ነው❓

*መልስ* አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ

✅ @Teyakaenamels
✅ @Teyakaenamels
✅ @Teyakaenamelssaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...