2018 ፌብሩዋሪ 27, ማክሰኞ

የምዕራፍ ሦስት/የ24ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ?? እነሆ.... የምዕራፍ ሦስት/የ23ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል  መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር።

 ✅✍ጥ.ተራ ቁ👉1⃣ጌታ ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ዳርቻ ለወንጌል አገልግሎት ሲልካቸው ስንት ስንት አድርጎ ነው??

//መልስ//፡- ሁለት ሁለት አድርጎ ነው፡፡ ማቴ.10÷1

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉2⃣ነቢዩ ኤልያስ ፣ ፃድቁ ሄኖክ ፣ ዮሐንስ ወንጌላዊ እስከ ዕለተ ምጽአት የሚቆዩበት ቦታ ምን ይባላል?

///መልስ//፡- በብሔረ ሄዋን ነው፡፡

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉3⃣የጌታችንን ሥነ ስቅለት የሳለው ማን ነው ?የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምንስ?

//መልስ//፡- ወንጌላዊው ዮሐንስ እና ቅዱስ ሉቃስ ናቸው፡፡

 ✅✍4⃣አንድ ሰው ሱባኤ ገባ ሲባል ምን ማለት ነው? አንድ ሱባኤስ ስንት ቀን ነው?

//መልስ//፡- ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ከሰው ተለይቶ ቤቱን ዘጋ፣ጸለየ ማለት ሲሆን አንድ ሱባኤ ሰባት ቀን ነው።

 ✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉5⃣የመጀመሪያዋን የኢየሩሳሌምን ቤተመቅደስ  ሰው ማን ነበር? ያፈረሰውስ ማን ነው??

//መልስ//፡- ጠቢቡ የሠራውሰሎሞን ሲሆን ያፈረሰው የባቢሎኑ ንጉሥ ናቡከደነፆር ነው።

 ✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉6⃣ሩሐማ ማለት………ምን ማለት ነው??…. ሎሩሃማ ማለትስ………… እና ናታኒም ማለት …………. ምን ማለት ነው??

//መልስ//. ሩሐማ ማለት………….  ማለት………… እና ናታኒም ማለት …………. ነው፡፡
መልስ፡- ሩሐማ ማለት ምሕረት የሚገባት ሎሩሃማ፣ሎሩሃማ ማለት ምሕረት የማይገባት ሲሆን ናታኒም ደግሞ የቤተመቅደስ አጽጂ ማለት ነው፡፡


✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉7⃣የነቢዩ ዮናስ አባት አማቴ እንደሚባል በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጻል አማቴ ማለት በዕብራይስጥ ምን ማለት ነው??

//መልስ//👉አማቴ በዕብራይስትጥ እውነት ወይም እውነት ተናጋሪ ማለት ነው።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ.8⃣ነብዩ ዮናስ  ወደ ተርሴስ ሲኮበልል የተሳፈረበት  የኢዮጴ ወደብ ዛሬ የት ይገኛል ስሙስ ማን ይባላል???

//መልስ// ከጤግሮስ  ወንዝ በስተምስራቅ  በአዲሲቷ ሞስል ከተማ  በተቃራኒ ትገኛለች ነነዌ ማለት የዮናስ ከተማ ማለት ሲሆን እሱም ናምሩድ ነው።

.✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉9⃣ነብዩ ዮናስን የዋጠው  ዓሳ ነባሪ በየት በየት አድርጎ  ተጉዞ ነቢዩን ነነዌ ከተማ ዳር ተፋው??

//መልስ//👉ዮናስ ከኢዮጴ ወደብ ተሳፍሮ ወደ ተርሴስ/ስፔን/ ሲጓዝ
ወደ ባህር ተጥሎ በዓሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለሶስት ቀን
ቆይቶ ነነዌ ከተማ ጥግ ሊተፋ  የዋጠው ዓሳ
ነባሪ በሜድትራያንን ባህር አድርጎ…..በምዕራብ አፍሪካ
አድርጎ..በደቡብ አፍሪካ በኩል የቻለውዞሮ…ነው፡፡ ነነዌ/አሁን
ኢራቅ ውስጥ ነው የሚገኘው/ ከተማ ጥግ
የተተፋው….ለምን በቀይ ባህር  አያልፍም ቢሉ…
ሁለቱን አሀጉራት የሚያገናኘው ቦታ ያኔ ደረቅ ሲሆን
በዕርግጥ አሁን ተቆፍሮ የስዊዝ ካናል ተሰርቶበታል።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉🔟የጋብቻ ዋና ዓላማ ምንድን ነው??

//መልስ//👉የጋብቻ ዓላማ
የጋብቻ ዓላማዎች ሦስት ናቸው፡
1. የመጀመሪያው “የሚመቸውን  እንፍጠርለት” እንዲል ለመረዳዳት ነው። መረዳዳት ሲባልም በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስም ጭምር ነው። ለሥጋቸው በሥራ ሲረዳዱ ረዳትለነፍሳችው ደግሞ በጸሎት ይረዳዳሉ። ለምሳሌ ይስሐቅ ሚስቱ ርብቃ ለሃያ ዓመታት መክና ልጅ አልወለደችለትም ነበር። በዚህም ምክንያት ስለ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ተለመነው፤ ርብቃም መንታ ፀነሰች ይላል።  ፳፭፡ ፳፩።

2. ሁለተኛው ከፍትወተ ሥጋ ወይም ከዝሙት ለመጠበቅ። ፩ኛ ቆሮ ፯፡ ፰ - ፱፤ ፩ኛ ቆሮ ፭፡ ዘፍ፩፤ ምሳሌ ፮፡ ፴ - ፴፪።

3. ሦስተኛው ደግሞ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት” እንዲል ዘር ለመተካት ነው። ዘፍ ፩፡ ፳፰። እነዚህም እንደ ሦስት ጉልቻዎች የሚቆጠሩ ናቸው።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣1⃣ ሥላሴ ለቅዱሳን በፈለጉት መልክ የሚታዩት (የሚገለጡት)በየትኛው ሰማይ ሆነው ነው?


//መልስ//👉 መንበረ ስብሐት


 ✅✍ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣2⃣ለመናብርት አለቃ ሆኖ የተሰየመው መልአክ ማን ነው?

//መልስ//🖊ቅዱስ ሩፋኤል

✅✍ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣3⃣ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከመከተሉ በፊት ሥራው ምን ነበር??

//መልስ//👉ዶክተር/ሃኪም ነበር።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣4⃣እግዚአብሔር ከመልከ ጼዴቅ ጋር ያደረገው ኪዳን ምንድን ነው??

//መልስ//👉መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ  ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉስ ነው በ15 አመቱ መንኖ አጽመ አዳምን ይዞ በቀራንዮ በህብስትና በወይን. ያስታኩት ነበር. እግዚአብሔር የክርስቶስምለመልከ ጼዴቅ በሐድስ ኪዳን ለምትሰራው ክህነትና ምስጢር ቁርባን ምሳሌ. አድርጎ በቃል ኪዳን አትሞታል በዚሕም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ. ሞትን እስካሁን አልቀመሰም. ይህም ካሕኑ መልከ ጼዴቅ. ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት  ጊዜ ተገልጧል.  ዘፍ 14፡17 እና ዕብ 7፥1

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣5⃣ቅዱስ ሉቃስ ለምን ዘላህም/ላም እየተባለ ይጠራል??

//መልስ//👉 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበረት፣በላምና በአህያ መካከል መወለዱን አጉልቶ በመጻፉ።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣6⃣እግዚአብሔር በብሉይና በሐዲስ ኪዳን እኔነኝ ብሎ ከተናገራቸው መካከል ጥቀስ/ሽ

//መልስ//👉እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ። ዘፍ ፲፭፣፩
👉እኔ ኤልሻዳይ ነኝ።. ዘፍ ፲፯፣፩
👉የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ዘፍ ፵፮፣፫
👉ያለና የሚኖር እኔ ነኝ። ዘጸ ፫፣፲፬
👉እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ዘጸ ፮፣፫
👉ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ አኔ ነኝ። ዘጸ ፳፣፪
👉እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ።

👉በሐዲስ ኪዳንም ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ነኝ ብሏል

👉የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። ዮሐ ፮፣፴፭
👉እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ። ዮሐ ፰፣፲፪
  👉እኔ የበጎች በር ነኝ። ዮሐ ፲፣፯
👉መልካም እረኛ እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፣፲፩
 👉ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፩፣፳፭
   👉እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። ዮሐ ፲፬፣፮
👉እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ። ዮሐ ፲፭፣፩
👉እኔ…..እንዲህ… ነኝ ብሎ የተናገረና መናገር የሚችል አምላክ ብቻ ነው። ምክንያቱም፡-
፩. የማይለወጥ /የማይወሰን ስለሆነ፡
እንዲህ / እዚህ ነበርኩ። እንዲያ / እዚያ እሆናለሁ… አይልም። ቦታ ጊዜ ሁኔታ አይገድበውም።
እግዚአብሔር አይለወጥም፡ አይወሰንም።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም እስከለዘላለምም ያው ነው።… ዕብ ፲፫፣፰

፪. ሁሉ በእጁ / በእርሱ ስለሆነ፡
እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአል፣ ሁሉን ይመግባል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ ፲፩፣፴፮።
፫. ከእርሱ በላይ ማረጋገጫ ስለሌለ፡
አንድ ነገር. ነው አይደለም የሚል ልዩነት ቢፈጠር በሦስተኛ በበላይ አካል እንዲረጋገጥ ይደረጋል።
እግዚአብሔር ሌላ አስረጅ፣ ምስክር አያስፈልገውም። ከእርሱ በላይ የሚያረጋግጥ ስለሌለ።
፬. ነኝ ያለው የሆነውን ስለሆነ
ሁልጊዜ የነበረውን፣ የሆነውን፣ ወደፊትም የሚሆነውን ነኝ አለ።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉1⃣7⃣በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ካህናት ስማቸውን ማን ይባላል አባታቸውስ ማነው???

//መልስ//👉አፋኒን እና ፊንሐስ ናቸው። አባታቸውም፦ካህኑ ኤሊ ነው።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣8⃣ሰባ ሰገል ለጌታችን ያመጡለት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ ከየት የመጣ ታሪካዊ አመጣጡ ከየት ነው?? ??

//ልመስ//🖊ይህ ወርቅ እጣን ከርቤ አመጣጡ አዳም ከገነት ሲባረር
መለአከ ቅዱስ ሚካኤል፥ መለአከ ቅዱስ ገብረኤል ፥መለአከ
ቅዱስ እሩፋኤል አምጥተው ሰጡት እሱም ለሔዋን እደ ጥሎሽ
አበረከተላት <ሔዋን ለሴት <ከሴት ሲዋረድ < ከኖህ ደረሰ <
ኖህ ከመርከብ ከወጣ ቦሀላ < ለሴም ሰጠው <  ለመለከ
ፃድቅ ለአብረሀም
ከአብረሀም ሲወርድ ሲዋረድ ከዳዊት ና ከሰሎሞን ደረሰ።
ሴምበአከአዝ ዘመን ቴሌጌልፌልሰር ማርክ ወስዶ በቤተ
መንግስት አኑሮት ነበር።
የሰባ ሰገል አባታቸው #ዥረደሸት ይባላል።ፈላስፋ ነበር።
አንድ ቀን ከውሀ ዳር ሆኖ ሲፈላሰፍ በሰሌዳ ኮከብ ድንግል
ህፃን ታቅፋ አየ ያየውንም በሰሌዳ ቀርፆ አስቀመጠው።ሲሞት
ለልጅ ልጆቹ እድህ አለ ኮከብ ሲወጣ ባያችሁ ጊዜ ሰማያዊ
ንጉስ ይወለዳልና ይሄንን ወስዳችሁ እጅ ንሱ ብሎ ወርቅ፥ እጣን
፥ ከርቤውን ሰቷቸው አልፏል።

✍✅ጥ.ተራ.ቁ.👉1⃣9⃣ አስራ-ሦስቱ/13/ ሕምማተ መስልቀ የሚባሉት ማን ማን ነው???

//መልስ//🖊🖊13ቱ ህማማተ መስቀል
1 የሾክ አክልል መድፋቱ
2 ራሱን በዘንግ መመታት
3 በጥፍ መመታቱ
4 ምራቅ መተፋቱ
5 መራራ ኃሞት መጠጣቱ
6 ወደኋላ መታሰሩ
7 ጀርባን መገረፉ
8 ጎኑን በጦር መወጋቱ
9 ሳዶር
10 አላዶር
11 ዳናት
12 አዴራ
13 ሮዳስ
ከ 9_13 ያሉት አምስቱ ቅንዋቶች ናቸው።

✅✍ጥ.ተራ.ቁ👉2⃣0⃣ ስለ ጋብቻ ከተነገሩት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች መካከል ቢያንስ ሦስት ጥቀሱ/ሽ??....መልሱን ለእናንተ....?


ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...