2018 ፌብሩዋሪ 19, ሰኞ

እርስቴን አልሰጥም

https://youtu.be/q-F5pOd2Cvg

🍁 ርስቴን አልሰጥም 🍁
🎤🎤ተራኪ  ፥ አንድ ደሃ ሰው ነበረ እግዚአብሔርን የሚፈራ
በአካአብ ቤት አጠገብ ያለው የወይን ስፍራ
አንድ ቀን ግን ንጉሱ በመስኮቱ ሲመለከት
ስፍራውን ወደደው መጣ ወደሱ ቤት
ንጉሱም አይቶ ስፍራውን ስለወደደው
ደሃውን ናቡቴን አግኝቶት እንዲህም አለው
🤴🏽አካአብ ፥ በጣም ደስ ይላል እጅግ የሚመስጥ
ቦታው ተስማምቶኛል ከሁሉ የሚበልጥ
ይህን የወይን ቦታ ለኔ ብትሰጠኝ
ክብርህ ከፍ ይላል ታገኛለህ ሲሳይ
ከፈለክ በገንዘብ ካሻህ ደሞ በቦታ
ጨምሬ ልስጥህ ፍጹም አታመንታ
🙎🏽‍♂ናቡቴን፥ የሰማዩስ አምልካ እኔን ምን ይለኛል
የአባቶቼን እርስት ብሰጥ ቅር ይሰኛል
አልፈልግም ገንዘብ ሀብትስ ለምኔ
እርስቴን አልሸጥም እስካለሁኝ እኔ
🎤🎤 ተራኪ፥ አክአብ ተናደደ ባጣምም ገረመው
ይህን ስላለው ብቻ ይበልጡን ወደደው
👸🏽ኤልዛቤል፥ ምን ሆነሃል ውዴ ምነው ተጨናነክ
ምግብ የማትበላው እንደዚህ የሆንክ
ንገረኝ እስኪ ምንድነው ችግሩ
መፍትሄ አይጠፋም ከተመካከሩ
🤴🏽አክአብ፥ ባክሽ ተይኚ ውዴ በጣሙን ጨንቆኛል
ውስጤን የሚረብሽ ነገርም ገጥሞኛል
ከኛ ቤት አጠገብ ያለውን እርሻ
ወድጄው ነበረ ልሰጠው መካሻ
አልፈልግም ብሎ ድርቅ አይል መሰለሽ
ያባቶቼን እርስት ምናምን ብሎ አልሰጥም አለልሽ
👸🏽ኤልዛቤል፥ ቱ ቱ ቱ እንደው ማን ይሙት አንተ አሁን ንጉስ ነህ
የእስራኤል መሪ ቆራጥ ትባላለህ
ለዚች ጥቂት ነገር እንደዚህ መሆንህ
ይገርመኛል እኔ እንዲህ መንጨርጨርህ
🤴🏽አከአብ፥ ምን ላድርግ ውዴ ምን አርግ ትይኛለሽ
አልፈልግም ካለ አላመጣ ከሳሽ
👸🏽ኤልዛቤል፥ ወይ አንተ ምን ያስፈልጋል ለዚህ ለደሃ ሰው
ከሳሽና ተከሳሽ የምታመላልሰው
ንጉሱ አንተ ነህ ሌያውም በከተማ
ስልጣንህን ተጠቀም ከወደድከውማ
አይ ይሄን አልሰራም የምትል ከሆነ
እኔው እራሴ አስልኬ እዛው ድረስ ጭፍሮቹን
ማን እንደሆንክ ያያል አሳየዋለው ልኩን
ደብዳቤ አጽፌ ቦታውን ቶሎ እንዲለቅ
ጨርቄን ማቄን ሳይል ከቦታው እንዲርቅ
🤴🏽አከአብ፥ ምን ልታደርጊ ነው ውዴ ምንስ አስበሻል
አንቺ እንደዚህ ስላልሽ ይሰጥሽ መስሎሻል
👸🏽ኤልዛቤል፥ አይ አንተ አታውቀኝም መሰለኝ እኔ ኮ ኤልዛቤል ነኝ
ምንም ነገር ፈልጌ ወዲያው እንደማገኝ
ይልቁንስ አሁን ሌላውን ነገር ትተህ
ማህተቡን ስጠኝ የጣት ቀለበትህ
የሀሰት ምስክር በሸንጎ አቁሜ
ማን እንደሆንኩ ያውቀዋል ይረዳው አቅሜ
ንጉስን ተሳድቧል ፈጣሪንም ደፍሯል
ይሄ ደሃ ምናምንቴ እጅግ ተገዳድሯል
ብዬ አስ ከስሼው የሀሰት ምስክር
ምን እንደሚሆን ያውቅ የለ ንጉስን መዳፈር
🎤🎤ተራኪ ፥ በሀሰት ምስክር ዳሃው ናቡቴንን
አስደብድበው ገደሎት እግጅ በሚያሳዝን
ይህንን አድርገው አሸከሮች ጭፍሮቹ
ወሬ ውን ለማድረስ ሮጡ ቀቅጥሮቹ
ይህንን ስትሰማ ኤልዛቤል ዘለለች
የደስታንም ሲቃ ለአከአብ ነገረች
👸🏽ኤልዛቤል፥ ደስ ይበልህ ውዴ ተሳካ ምኞትህ
ሂድና ውረሰው ይሁንልህ ሀብትህ
ደሃው ተገሏል በመንገድ ተጥሎ
በጸባይ ሲለመን አልታዘዝ ብሎ
🎤🎤ተራኪ ፥ እግዚአብሔርም አየ በጣምም ተቆጣ
እንዲህ የሚል ድምጽ ለነብዩ መጣ
💗💗በሰማሪያ በአትክልቱ ቦታ አክአብን አግኘው
እግዚአብሔር ይልሃል እንዲህ ብለህ ንገረው
ደሃውን በመግደል ርስቱን ወረስከው
መንገድ ላይ ጎትተህ ለውሻ ሰጠህው
አንተም እሱን ገለህ የትም እንደጣልከው
ውሻውን ለደም በጭካኔ እዳላስከው
ያንተንም ደም ውሾች ይልሱታል
ሚስትህን ኤልዛቤል ውሾች ይበሏታል

🎤🎤ተራኪ ፥ልብሱን ቀዳደደ አክአብ አለቀሰ
ይህንን ሲሰማ ማቅንም ለበሰ
ፈጣሪ እንዲምረው አዘነ በጣሙን
ከቁጣው መቅሰፍት እንዲያድነው እሱን
በመጸሃፍ ቅዱስ እንደሱ ያለ ከቶ አይገኝም
ሚስቱ የነዳችው ንጉስ አክአብን
እንግዲህ አስተውል ሁሉም ሰው ይህን ይወቅ
እርስትህን አትስጥ ትውፊትህን ጠብቅ
እርስት ማለት ሀገር ናት የነጻነትህ አርማ
የጀግኖች መፍለቂያ መገኛ አውድማ
ርስት ማለት ሀይማኖት ከአበው የወረስናት
እንጠብቅ እንያዛት ሌላ ሳይገባባት
ርስት ማለት ህብረት ነው የአንድነታችን ሚስጢር
ሳንከፋፈል የመቆየታችን ህብር
ርስት ማለት ርስት ማለት ርስት ማለት ሰላም ነው
የሰማዩ ጌታ የሚያከናውነውsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...