2018 ፌብሩዋሪ 3, ቅዳሜ

መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ማኅበር የተዘጋጀ። መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር።👇✅

✍ጥ.ተራ ቁ✅ 1⃣አስተርዮ ማለት ምን ማለት ነው??

*//መልስ///* 👉መታየት መገለጥ ማለት ነው፡፡ ገሐድ የሚለው ቃልም በጾምነቱ ሌላ ትንታኔ ሲኖረውአስተርእዮ ቃሉ የግእዝ ትርጉሙ ያው መገለጥ ማለት ነው፡፡ በግሪክ ኤጲፋኒ ይሉታል፡፡ የኛም ሊቃውንት ቀጥታ በመውሰድ ኤጲፋኒያ እያሉ በዜማ መጻሕፍቶቻቸው ይጠሩታል፡፡ ትርጉሙም ከላይ ከጠቀስናቸው ጋር አንድ ነው፡፡

አስተርአየ የተባለው ግሥ ራሱን ችሎ ሳይለወጥ በአምስቱ አዕማድ የሚፈታ ብቸኛ ግሥ ነው፡፡ ይህም ማለት፡- አስተርአየ፤ ታየ፤ ተያየ፤ አሳየ፤ አስተያየ፤ አየ ተብሎ ይፈታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዘመነ አስተርእዮ ሲያጥር ከጥር 11 ቀን እስከ ጥር 30 ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት 20 ቀናት ይሆናሉ፡፡ ሲረዝም ደግሞ ከጥር 11 ቀን እስከ መጋቢት 3 ቀን ይሆናል፡፡ ይህም 53 ቀናት ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ጌታን ለሐዋርያት ህፅበተ እግር ያደረገበት ቀንም ከጸሎተ ሐሙስ እስከ ጰራቅሊጦስ ቢቆጠር 53 ቀናት ስለሚሆኑ የእነዚህ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ዮሐንስ በጥምቀት ዕለት ለልዕልና /ጌታ ሰውን ምን ያህል እንዳከበረው/ ለማሳየት እጁን ከጌታ ራስ በላይ ከፍ እንዳደረገ ጌታም ለትህትና እጁን ከሐዋርያት እግር በታች ዝቅ አድርጎ እግራቸውን አጥቧቸዋልና ነው፡፡ ጥምቀት የህጽበት አምሳል ሲሆን፤ /ህጽበት/ መታጠብ በንባብ አንድ ሆኖ ሁለት ምሥጢራት አሉት፡፡

አንደኛ፤- ምእመናን የእንግዳ እግር እንዲያጥቡ ትምህርት ማስተማሩ ሲሆን፤ ሁለተኛው ለሐዋርያት ጥምቀት ነው፡፡

በጸሎተ ሐሙስ ቢጠመቁም መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት የጰራቅሊጦስ ነውና ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፤ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያን ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት ጥምቀት እንደጠየቀውና ጥምቀታቸው ህጽበተ እግር መሆኑን እንደመለሰለት፡፡

በሌላ በኩል ከዘመነ ልደት እስከ ጥምቀት ተወልደ፤ ተሰገወ /ሰው ሆነ/ ይባላል እንጂ አስተርአየ አይባልም፡፡ ከጥምቀት በኋላ ግን አብሮ ተባብሮ ተጠምቀ፤ ተወለደ፤ ተሰገወ አስተርአየ ይባላል፡፡

✍ጥ.ተራ.ቁ.✅2⃣እመቤታችን በስንት አመቷ አረፈች?? የእረፍት በዓሏስ መቼ ነው የሚከበረው??

*//መልስ//*👉በ64 ዓመቷ አረፈች። በዓለ እረፍቷም ጥር 21 ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅3⃣⃣የነነዌን ፆም ለምን እንፆማለን??

*//መልስ//*👉እኛንም ይቅር እንዲለን እንፆማለን
👉🏻የዓብይ ፆም መዘጋጃ የንስሀ መግቢያ እንዲሆን አባቶቻችን እንድንፆመው ይህን ፆም ሰርተውልናል።

✍ጥ.ተራ.ቄ.✅4⃣ነቢያት በስንት ይከፈላሉ ?ምንና ምን በመባል?

መልስ፡- በሁለት ፡፡ ዐበይት ነቢያትና ደቂቀ ነቢያት፡፡ የጽህፍ ነቢያትና የቃል ነቢያት።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅5⃣ ቅዱስ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት በኋላ 3000 ሕዝብ ያሳመነው በስንት ሰዓት ነው?

*//መልስ//*፡- ከጠዋቱ በ 3 ሰዓት፡፡የሐዋ.2 ÷15

✍ጥ.ተራ ቁ✅ 6⃣መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ድንግል ማርያምን ደስ ይበልሽ ሲላት የመለሰችለት መልስ ምን ነበር?

*መልስ*፡- ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው፡፡ ሉቃ. 1 ÷29

✍ጥ.ተራ.ቁ✅7⃣ በሽተኛው መፃጉ ለመጠመቅ የሄደበት የመጠመቂያ / የፀበል/ ቦታ ምን ትባላለች ?ስንት መመላለሻዎች ነበሯት?

*መልስ*፡- ቤተሳይዳ ሲሆን አምስት መመላለሻ ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅.8⃣ ጾመ ነነዌ ወይም የ 3 ቀን ጾም በመባል የምትታወቀው ጾም የተሰየመችው በማን ነው??

*//መልስ//*👉በነነዌ ህዝቦች፡፡
" ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ  ትውልድ ምልክት ይሆናል።"
(የሉቃስ ወንጌል 11፡30)

✍ጥ.ተራ.ቁ✅የነብዩ ዮናስ እናትና አባቱ ማን ይባላሉ?

//መልስ//፦አባቱ አማቴ ሲባል እናቱ ደግሞ ሶና ይባላሉ።


✍ጥ.ተራ.ቁ✅🔟ነብዩ ዮናስ መቼ አረፈ በስንት  አረፍ??
//መልስ//፦👉በ170 ዓመቱ መስከረም "25" ቀን  አረፈ።

✍ጥ.ተራ ቁጥር✅1⃣1⃣ ዮናስ ማለት ምን ማለት  ነው??

//መልስ//፦👉ዮናስ ማለት፦ በዕብራይስጥ     ርግብ ማለት ነው።

✍ጥ.ተራ.ቁ✅1⃣2⃣ነብዩ ወደ ነነዌ አልሄድም ብሎ የኮበለለባት ተርሴስ አሁን የት ሀገር ውስጥ ትገኛለች??

//መልስ//👉በስፔን ትገኛለች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

6 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...