2018 ፌብሩዋሪ 27, ማክሰኞ

የምዕራፍ ሦስት/የ23ኛ/ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✝

🖊ይህ የምዕራፍ ሦስት የ23ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥቄቃና መልስ ውድድር እንዲህ ይቀርባል።

1⃣↪ ፆም  ማለት  ምን  ማለት  ነው⁉

2⃣↪ ኮዳዴ  ማለት  ምን  ማለት  ነው⁉

3⃣↪ ዐብይ ማለት  ምን  ማለት  ነው⁉


4⃣↪ የዐብይ ፆም ስንት ሳምንታት አሉት⁉

5⃣↪ ሰትጦሙም እንደ ግብዦች አትጠውልጉ:: ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና  እውነት እላችኇለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል:: አንተ ግን ስትጦም በስውር ላለው አባትህ እንጅ እንደጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ያስረክብሃል። ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል⁉

6⃣↪ፆምን ቀድሱ ፤ጉባኤውንም አውጁ፥ ሸማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ። ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል??

7⃣↪ ትንቢተ  ኢሳያት  58፥ 3,,,8  ያለው  ሀይለ  ቃል ምን ይላል⁉

8⃣↪የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤
ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ። ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል??


9⃣↪ ለሰዎች ኃጢአት ይቅር ብትሉ፤
የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፤
አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል??

🔟↪በዚህ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሒድ  አስቀምጠህም ከወንድምህ ታረቅ  ይህ ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል?? ⁉

1⃣1⃣↪ ልጄ ሆይ ሕጌን አትርሳ ልብህም ትእዛዜን ይጠብቅ ብዙ ዘመናትና ረጅም እድሜ ሰላምም ይጨምምሩልሃልና። ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል ⁉


1⃣2⃣↪ እግዚአብሔር  የፃድቁን ነብስ  አያስርብም  የኃጥአንን ምኞት ግን  ይገለበብጣል ይህን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል❗❓

1⃣3⃣↪ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለምን 40 ቀን እና ሌሊት ፆመ❗❓
ማጠቃለያ መልስ🖊👇

1⃣መተው መከልከል መታቀብ ማለት ነው።

2⃣ኩዳዴ ማለት ሰፊ እርሻ ማለት ነው።

3⃣ዓብይ ማለት ታላቅ ከፍ ያለ ማለት ነው።

4⃣8ት ናቸው። እነርሡም፦ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ምኩራብ፣ መጻጉ፣ደብረ ዘይት፣ ገብርሔር፣ኒቆዲሞስ፣ሆሳህና ናቸው።

5⃣ማቴዎስ 6፤16)📝 ስትጾሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጾመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

6⃣ ት.ኢዮኤል 1፥14))ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፤ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።

7⃣ት.ኢሳይያስ 58፤3_____8)📝
ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
 እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ይህ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
እኔስ የመረጥሁት ጾም  አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
 የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።

8⃣መ.መክብብ 12፤1-2)📝የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤
ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፤

9⃣ማቴዎስ 6፤14-15)📝 ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
 ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።

🔟 ማቴዎስ 5፥24)📝በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።

1⃣1⃣ ምሳሌ 3፤1))📝ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።

1⃣2⃣ ምሳሌ 10፤3))📝 እግዚአብሔር የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፤ የኅጥአንን ምኞት ግን ይገለብጣል።

1⃣3⃣📝/አብነት ሊሆነን
📝/ ጌታ የፆመው ስብከቱን ከመጀመሩ በፊት ነው እኛም ከሁሉ በፊት ፆም ፀሎትን እንድናስቀድም
📝/;ፆም ህግ እንደሆን ለማሳወቅ
📝/የዖሬት አባቶቻችን ነብያቶች የፆሙት አይሁዶችን ምክኒያት ስበብ ለማሳጣት
📝/ነቢዩ ሙሴ የዖሬትን ህግ ለመቀበል ፆሙዋል ጌታችን የአዲስ ኪዳን ህገ ወንጌል ለመስጠት
📝እስራኤላዊያን 40 ቀን እና ሌሊት ተጉዘው ነው ከተስፍይቱ ምድር የገቡት.
📝ነብሳትን ከሲዖል ሊያወጣ
አዳም በ40 ቀኑ ያገኘውን ልጅነት ዲያቢሎስ አጥቷል። ለአዳም የተሰጠውን ልጅነት ለማስመለስ ለካሳ እንደመጣ ለማሳወቅ 40 ሌሊት እና ቀን ፆመ።

ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ከስተታችን አርሙን።

ወስብሐት ለእግዝአብሔር

✅ @Teyakaenamels
✅ @Teyakaenamels
✅ @Teyakaenamels

2 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...