2017 ኖቬምበር 29, ረቡዕ

ና....ተማር ልጄ

ና ተማር ልጄ !!!!!

ያኔ በለጋ እድሜዬ ጨቅላ ሳለው ከጥንቱ
በእጃቸው ልምጭን ይዘው ሲያስተምሩ ለህፃናቱ
እኔም ደግሞ እንድቀስም ከማያልቀው ጥኡም ዜማ
ጠርተውኝ ነበር የኔታ ወደ እውቀቱ ከተማ
ግዕዙን እንዳቀላጥፍ በንባብ ሆነ በዜማ
አዎ ጠርተውኝ ነበር
ሰላም እለኪን እንድደግም ቃለ እግዚአብሔር እንድማር
ና ብለውኝ ነበር ያኔ በአባቶች እግር እንድትካ
ውስጤ በቃሉ ታንፆ እንደ ፀደይ እንድፈካ
ጠርተውኝ ነበር ደጋግመው እውቀት ጥበብን ሊያወርሱኝ
ከአለም ዘፈን ዳንኪራ ጥኡም ዜማን ሊሰጡኝ
ታዲያ ልቤ ደንዳናው
ጨዋታን መርጦ የሄደው
አሁን የኔታን ናፈቀ ያንን ወርቃማ ጊዜ
አለምን አትኩሮ እያየ ተውጦ በዘን ትካዜ
ቁጭ ብሎ መማርን አሻ ከማያልቀው የእውቀት ማሳ
በየኔታ እግር ሊተካ በቅኔ ጌታን ሊያነሳ
አዎ ልቤ ፈለገ
ያኔ አሻፈረኝ ብሎ ሲለመን እንቢ እንዳላለ
አሁን ሁሉን ተመኘ ልቤ በሀሳብ ዋለለ
የኔታ እያለ ተጣራ ከፊቱ እርቀው ሄደው
ያ የልጅነት ጊዜ ደጉ ቀን እያናፈቀው
ና ተማር ልጄ ያሉት ድምፃቸው ትውስ እያለውsaramareyama.8900@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...