2017 ኖቬምበር 29, ረቡዕ

ያንቺን እኔ ልኑር

*ያንቺን እኔ ልኑር*
በሆድሽ አርግዘሽ አምጠሽ መውልደሽ፣
አፈረ ትቢያ ለብሰሽ እኔን ማሳደግሽ ፣
ለአንቺ ሳሰስች ለእኔ መብሰልሰልሽ፣
የመከራሽ ብዛት ሲገባሽ ስቃይሽ፣
ያንቺን ልኑር አልኩኝ ባልኖረው ኑረሽን፣
ፊትሽ ማዲያት ለብሶ ውበት መልክሽ ጠፍቶ፣
የነበረሽ ውበት አዲስ መልክ አውጥቶ፣
የሚያሳሳው መልክሽ ከአንቺ ሳይኖር ቀርቶ፣
ልጄ ልጄ ማለት ደግነትሽ በዝቶ፣
እኔን ውብ አረግሽኝ የአንቺ ውበት ጠፍቶ፣
የአለም ዳርቻ ልክሽን አይለካው ስፍር ቁጥር የለው ሚዛን አይመዝነው፣
እምዬ ፍቅርሽን ምን ቃላት ሊገልፀው፣
ልክ ያልተገኘለት ጥልቅ ውቃኖስ ነው፣
መቼ ኖርሽ እናቴ ከቶ ያንቺን ኑሮ፣
ልጄ ልጄ እያልሽ ከአምና ከዘንድሮ፣
ሁሌ እንደተጓዝሽ በሀዘን እንጉርጉሮ፣
እሞላለሁ ብለሽ  አንቺ የእኔን ጉሮሮ፣
መቼ ኑረሽ ታውቂያለሽ ከቶ ያንቺን ኑሮ፣
እስኪ ትንሽ እንኳን አረፍ በይ እማዬ፣
እኔ ያንቺን ልኑር ዛሬ በተራዬ፣
እንዳንቺ ባልሆንም አምጨ ባልወልድሽ፣
ከአፌ ነጥዬ ለአንቺ ባላጎርስሽ
እኔ እንዳንች ሁኔ ምን ባልኖርልሽ፣
እንደ ወለድ አንጀት አንጀቴ ባይሆንሽ፣
ለእኔ የኖርሽውም እሩብ  ባልኖርልሽ፣
አርፍ በይ እናቴ ትንሽም ላግዝች።
ተፃፈ የካቲት 21-2009 አም
.ምsaramareyama.8900Gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...